የድንበር
ጨዋታ
አየሁሽ አላየሁሽ
ከፍትኩልሽ ዘጋሁብሽ
አታለልኩሽ አሞኘሁሽ
ቅንነት የጠፋበት
ቆራጥነት የጎደለበት
ሌብነት የተመረጠበት
ፎቶ መነሳት
የተለመደበት
ሕዝብ የተናቀበት
የድንበር ሽኩቻ
መስካሪው ሕዝብ ብቻ
ማን አሸነፈ
ማን አጎበደደ
ማንስ ተሰበረ
ማንስ ከበረ
ማንስ ከሰረ
ሕዝብ ግን ተናገረ...
በድንበር ጨዋታ
ሽኩቻው ስለታ
በዚህም ወገን ሆነ
በዛም ማዶ ሆነ
አንሰበርም
አንሸነፍም
አንረታም አለ
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
1-8-19