Back to Front Page

የኮነሬል አብይ የቅብዝብዝነትና የውሸት ሌጋሲ

የኮነሬል አብይ የቅብዝብዝነትና የውሸት ሌጋሲ

 

አልማዝ በዳኔ 8-7-19

ሰኔ 15/2011 በከፍተኛ የአገራችን የክልል መሪዎች ላይ ጥቃት ከተፈፀመ በኃላ ኮ/ል አብይ ፈጣን እንቅስቃሴዎች አድርገዋል።መጀመርያ ባልተጣራ ጉዳይ በዛ የሐዘን ወቅት ምን ለብሼ በቴሌቪዥን ልቅረብ ብለው፣ ተጨንቀው፣ህፃንነት እኩለ ሌሊት ላይ ዩኒፎርም ለብሰው መፈንቅለ መንግስት ተካሄደብኝ አሉ፡፡ ቀጥለውም የባህርዳሩና የአዲስ አበባ ሁለቱ ጥቃቶች ተያያዥነት አላቸው ብለውምመግለጫ ሰጡ።

 

አዴፓ በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ውስጥ የመረጠው አሳምነውን በነሱ አባባል በወያኔ ዘመን የግንቦት 7 አባል እንደነበረ፣ ጦር መሳርያ አከማችቶ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ የላከለትን የሳተላይት ስልክ ሲጠቀም እጅ ከፍንጅ ተይዞ፣ ብርሃኑ ነጋንና አንዳርጋቸውን ዱባይ አግኝቶ ሲሄድና ሲመለስ በክትትል ስር ቆይቶ በህግ ጥላ ስር የዋለውን ሰው ነፃ እንዲሆን ታግለን አስፈታን አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ገዳይም ተገዳይም ጅግና ናቸው በሚል ድርጅት ውስጥ ተጠርጣሪ ከመፈለግ ፈንታ አብንና ራሱን ባላደራ መንግስት ያለው የእስክንድር ነጋ አባላትን በመቶዎች ማሰር ተያያዙት።ይህን ድርጊት አማራን ለማዳከም ኮ/ል አብይ ያደረገው ዘመቻ ነው በሚል የለውጥ መሪ ሲባል የነበረው ሰውዬ ተቃውሞ ተነስቶበት በተለይም በውጭ ያሉት በዲሲ ዋሽንግቶን ሰልፍ ወጥተው በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሟቸውን ለመጀመርያ ጊዜ አሰሙ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከለውጡ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ ጮሁ።በሰብአዊነት ረገጣ ኮ/ል አብይን ለማጋለጥ አሁንም እየተንቀሳቀሱ ነው።ጉድ አደረገን! ስልጣኑ እስኪያደላድል ነው ኢትዮጵያዊነት ያለው እንጂ ውሸታምና አስመሳይ ሰው ነው አሉ።

Videos From Around The World

 

ይህ ሁሉ ሲሆንደግሞኮ/ል አብይ ሶሻል ሚድያው ዘጋግተዋል፡፡ ወያኔ አንዳንድ ጊዜ ሶሻል ሚድያው ሲዘጋ የነበረበት ሁኔታ ይወቅሱ እንዳልነበሩ፣ ኮነሬሉ ስልጣን በሶሻል ሚድያ እርካብነት እንዳልወጡ፣ አሁን ደግሞ ከስልጣናቸው እንዳያወርዳቸው ሶሻልሚድያውንክፉኛ ጠምደውታል።ኮ/ሉ በሚከፍሏቸው አርቲክል ፀሓፊዎቻቸው አማካይነት ሶሻልሚድያውን እንዲዘጋ እንዲለመኑ አስደርገው ጥርቅም አድርገው ዝግተው ሲያበቁ ጭራሽ ሰሙኑን በሰጡት መግለጫ ደግሞ ምንም ሳያፍሩ ውሃ አይደል አየር ጥርቅም አድርጌ እዘጋዋለሁአሉን።ፖለቲካ መድረኩን አሰፋለሁ ያሉት ከመቼ ረሱት?ነገር ግን ሾርት ሜሞሪ አለው ብለው የወቀሱትን የኢትዮጵያ ህዝብ ትተው ራሳቸውን ቢፈትሹ ሳይሻል አይቀርም።

 

በሌላ በኩል ደግሞ የሲዳማ ህዝብ የራስ ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ በዲሞክራሲና በህገ መንግስት መመለስ ሲገባ ጦር አዘምተው የህዝብ የመጠየቅ መብትን በጭፍጨፋ ጨፈለቁ።ጩሆቱ እንዳይሰማ ሶሻል ሚድያ ዘጉ።ለማትሪክ መዘጋት የጀመረው ሶሻል ሚድያ እንደ ኤሌትሪክ ይመጣል። ይሄዳል።ኮ/ሉ በሚቆጣጠሩት ሚድያዎች ደግሞ ዘረፋ ተፈፀመ፣ ቸርች ተቃጠለ፣ ብሄር ተኮር ጥቃት ተፈፀመ፣ . . . ወዘተ እያሉበይፋ ያልታወጀ የአስቸካይ ጊዜ አሰራር በደቡብ ክልል ዘረጉ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፍርያት ደግሞ በክልሉ መንግስት መሰተዳድር ጣልቃ ገብተው የፌደራሉ ወታደራዊ መንግስት ክልሉን እንዲያስተዳድር ወሰኑ።ሰለዚህ የደቡብ ክልል በፌደራል ኮማንድ ፖስት ስር ወደቀ። ፓርቲና መንግስት አንቀላቅልም የተባለው የውሸት ለውጥ ተጋለጠ።

 

ኮ/ሉ ሕገመንግስቱ ተጠቅመው የአስቸካይ ግዜ አዋጅ ማወጅ እየቻሉ ከስልጣናቸው ውጭ በስመ ኮማንድ ፖስት በሉአላዊ ክልል ላይ ወታደራዊ ሃይል ጫኑ። ህጋዊነት በሌለው ኮማንድ ፖስት ሲዳማ ዞንና አከባቢው ጦር አዘመቱ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ክልል ጠርቶኝ ነው የሚለው አያስኬድም።በሕገ መንግስታዊ አካሄድ እንጂ ማንኛውም የክልል አስተዳዳሪ በሕገመንግስት የተሰጠውን ስልጣን አሳልፎ መስጠት አይችልም።ይሁንና ክልሉ ጠርቶኝ ነበር እንካን ቢሉ የክልሉ ፕሬዝደንትን ማገድ ታድያ ምን አመጣው? ፕሬዝደንቱ ጠርተው ከነበረ ብየ ነው፡፡

 

ቀጠሉና አስመራ ሳይጠሩ ሄዱ። ቃል አቀባያቸው የማነ ገ/መስቀል (ማንኪ) ደግሞ ኮ/ል አብይ አስመራ መሄድዎን ነገረን። የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችም ረስተው እንደሄዱም ሰማን። ወይስ በሚድያ በኩል ኢንተግረሽኑ ተጀመረ። ቀውስ እያለ እንዴት ያገር መሪ አስመራ ሄዶ በሰው አገር ሹፌር ሆኖ ለፎቶግራፍ ፍጆታ ድራማ ይሰራል?ሌሎች የአለም መሪዎች ከአገራቸው ውጭ ከነበሩና በአገራቸው እንካን የኛን ያክል ሁኔታ አጋጥማቸው ትንሽ ችግር ሲፈጠርምጉዛቸው ሰርዘው ይመለሳሉ።የኛው ግን ጭረው ስለሚሄዱናእሳት መፈጠሩ ቀድመው ስለሚያቁት ይሆን ዝም ብለው ጉብኝታቸውንና ሽርሽራቸውን ተረጋግተው ጨርሰው የሚመለሱት? ወይስ ደንዳና ልብ ስላላቸው ነው? በነገራችን ላይ ከአገር ሲወጡ ዛሬ ደግሞ ምን አደጋ ይገጥም ይሆን እንደሚባል እሳቸውም ሳያቁ ይቀራሉ ብዬ መገመት ያዳግተኛል።

 

ከአሰመራ መልስ ደግሞ በችግኝ ተከላ ሪከርድ መስበር አሉን። መቸም የሐሳብ አጀንዳ ማስቀየር ተክነውታል።አሁን አሁን ግን ይህችን ስልትም ሁሉም ነቅቶባታል።መደመር፣ ፍቅር፣ ይቅርታና ኢትዮጵያዊነት ብለው ከጫፍ እሰከ ጫፍ እኛንና ዓለም እንዳታለሉን አሁንም በድጋሚ ልሸውዳቸው ብለው በችግኝ ተከላ ተነሱ።ሚልዮኖች/ቢሊዮኖች ችግኝ እያሉ ሲያምታቱ ብዙም አጀንዳ ሳይሆን ሲቀር እንዲያውም መሳቅያ ሲሆኑ የውሸት ሌጋሲ ጥለው አለፉት።

 

እሳቸው ግን ቀጠሉና መነሻውና ዓለማው የማይታወቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ልስጥ ብለው አጀንዳ ለማስቀየስ ሞከሩ።አሁንም ምንም አዲስ ነገር የሌለው መግለጫ ነው ተባሉ።ኤክስፖርት አደገ የሚል አንድምታ ያለው የውጭ ምንዛሪ ከባለፈው ዓመት ጨመረ አሉ።ሰላም በታጣበት አገር የሞት፣ የመፈናቀልናየንብረት መውደም እድገት እንጂ ኢኮኖሚ ሲንቀሳቀስ አላየንም። ታድያ እንዴት ነው ነገሩ! ኤክስፖርት በነወጥ ነው እንዴ የሚያድገው፡፡

 

በዚህ አመት ጎልተው ከወጡት የኮ/ሉ መግለጫዎች ደግሞ ኢህአዴግ ይወሃዳል የሚለው ነው።ኢህአዴግ ቢወሃድ ለራሱ ይጠቅመዋል።ለኢትዮጵያም ይበጅ ይሆናል፡፡ እሰካአሁን መዋሃድ በግልፅ የሚቃወም አባል ድርጅት አልሰማንም።ነገር ግን ባለፈው የኢህአዴግ አመራሮች ሳይወያዩበት በራሳቸው ግለ ውሳኔ ይወሃዳል ብለው ያወጁ ሰውየ አሁን መያዣ የሌለውና ግልፅ ያልሆነ ነገር ለምን ተናገሩ? ምክንያቱ ግልፅ ነው።የሚወሃሃዱ ድርጅቶች መጀመርያ ህልውና ያላቸው መሆን አለባቸው።እውነት ግን ኮ/ል አብይ ድርጅቶቹ ህልውና የሌላቸው መሆኑን አያውቁም?።ወላሂ! ወይም ኢየሱስን! አላውቅም ብለው ይማሉ።ደህዴን እንደ ድርጅት አለ ብለው ያምናሉ? አሁን አዴፓ ድርጅት ነው?አመራሩ ተከፋፍሎ ገዳይን ጨካኝ ለማለት የሚፈራ ድርጅት ህልውና አለው ብለው ያምናሉ? ድርጅት ነው ካሉ ደግሞ በህገመንግስቱ፣ በፌደራል ስርዓቱና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ያምናል? ኦዴፓ ከስር አባላት አሉት ብለው ያምናሉ ወይ? ነው ጥያቄው፡፡ደሞ ለመዋሃሃድ ችግር የለበትም ይበሉን? እንኳን ኢህአዴግ ለስልጣን እርካብነት የተጠቀሙበት የቅርቡ ኦሮ-ማራ ድርጅትዎም ወላልቆና እንክትክቱ ወጥቶ ፈርሷል።ሰለዚህ ውህደቱ ውሸት ነው! እደግመዋለሁ የውሸት ውሸትነው!ስለሆነምስለ ፌክ-ኒውስ የሚያወሩት ኮነሬሉ ፌክ-መግለጫቸውን ቢያርሙ ይሻላል ባይ ነኝ! አምልጧቸው አገሪቱ ቀውስ ላይ መሆኗን እንደገለፁት የዚህ ሁሉ ቀውስ ምንጩ ደግሞ የሳቸው የአመራር ውድቀት መሆኑን ተቀብለው ስልጣናቸው በሰላማዊ መንገድ ቢያስረክቡ ይበጃል።

 

ስለሌላ አገር እንጂ ስለ ኢትዮጵያ የሚያወሩ የማይመስሉት ኮ/ል አብይ በለውጡ ምክንያት እኔ ይህን አገር መምራት ከጀመርኩኝ ጀምሮ በደህንነት፣በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መሰክ እጅግ በጣም የሚያስደንቁለውጦች ታይተዋል ብለዋል።ከዚህ በፊት አገሪቷ አይታው የማታቀውን ነገር አስገኘሁላት አሉን በድፍረት በመግለጫቸው ላይ።ምላሳቸው ቢደፍርም አካላዊ ገፅታቸው ሌላ ሲል ነበር፡፡ ይህንን ሲናገሩ ፊታቸው የሚያንፀባርቀው ግን ውሸት እየተናገሩ እንደሆነና ይህንንም ለመደበቅ ሲቸገሩ ያስታውቅባቸእንደነበር ነው። ካላመኑኝ የራስዎን መግለጫ ይወዱት ከነበረውና አሁን ከጠሉት ሶሻል ሚዲያይመልከቱት፡፡

 

ሌላው የሚያስቀው ባሌቤታቸው ወ/ሮ ዝናሽን ከእተጌ ጣይቱ አወዳድረው ልዩ ታሪክ የሰሩ አድርገው የካቧቸውን ንግግር ነው። ራሳቸው ወ/ሮ ዝናሽ እንኳን የሚቀበልዋቸው አይመስለኝም።

 

በአጠቃላይ ሰውዬው አገሪትዋን ቀውስ ውስጥ ከተው ራሳቸውም ቀውስ ውስጥ ወድቀዋል።የጭንቀት መድሃኒት ከመውሰድ አልፈው ሲጋራም ሌላም ጭንቀት የሚያስረሳና የሚያደነዝዝ ነገር መውሰድ እንደጀመሩ እልፍኝ አገልጋዮቻቸውና የጓዳ አዋቂዎች በሽኩሽኩታ እያወሩ ነው። ሽኩሽኩታም እንደ ማህበራዊ ገፅ ይዘጋ ወይም ህግ ይውጣለት እንዳይባል እንጂ ሽኩሽኩታዎች በዝተዋል፡፡

 

የህወሓት መግለጫ ለአዴፓ ብቻ እንደወጣ ተደርጎ ሆን ተብሎ በሚድያዎች እንዲቃኝ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ኮነሬሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ይህንን ጉዳይ የሁለቱ ክልሎች ጉዳይ እንዴት ይፈታል ይላሉ? ተብሎ ቀረቧል፡፡ ጠያቂ ጋዜጠኛ ታጣ እንጂ የህወሓት መግለጫ በግልፅ የኮ/ል አብይ መንግስትን ይጠይቃል።ቢያንስ ሁለት ነገሮችን አንስቷል።አንደኛ ኦሮ-ማራ የተባለ ከመርህ ውጭ የተባደነ ቡዱን በኢህአዴግ ውስጥ መፈጠሩና ይህን ቡዱን ፀረ-ህወሓት ዘመቻ ከፍቶ መቆየቱንና በባህርዳርና በአዲስ አበባ ለተፈፀመው ግድያም ምክንያት መሆኑን፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የግድያው ምርመራና የማጣራቱ ስራ የሚመራ ነፃና ገለልተኛ አካል እንዲቋቋም ይጠይቃል።ስለዚህ የህወሓት መግለጫ በቀጥታ የፌደራል መንግስቱና የአዴፓ አመራርን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ መግለጫ እያለ በሁለቱ ክልል መካከል እየተባለ ለምን ተምታትቶ እንደሚቀርብ አይገባኝም። ጉዳዩ ሲመረመርና ሲጣራ እርሶ ኮ/ል አብይንም ጭምር አካቶ በሰፊው የሚያጣራና የሚመረምር አካል ይደራጅ ይላል፡፡ ግልፅ ጥያቄ ነው።ለምን ኮ/ል አብይ በውይይት የፈታል አሉ፡፡ በቅርቡ መድረክ ፈጥረን እናየዋለንስ ምን አመጣው? ነገሩ በውይይት መፍታት ስላልተቻለ አይደለም እንዴ የክልል አስተዳዳሪናየካብኔ አባለቶቻቸው በግላጭ በቢሯቸው የተገደሉት?ሁኔታውን በህግ ለማጥራት ሲከታተሉ የነበሩት ጀነራል የተገደሉት?ኮ/ል አብይ እርሶንም አናምንም እኮነው የሚለው መግለጫው!ሚሊየኖም አደራሽ ስለአለቀሱ ንፁህ ኖት ማለት አይቻልም። በኢንጂነር ስመኘው አሟሟት የእርስዎ ስምም እየተነሳ ምርመራው ለህዝብ ይፍ ያልሆነበት ምክንያት ይገባናል፡፡ ሰለዚህ መግለጫው ገለልተኛ መርማሪና አጣሪ ያላጣራው የምርመራ ውጤት ማንም አምኖ አይቀበለውም።ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የሚሳተፉበት አጣሪና መርማሪ ቡዱን አሁኑኑ ይደራጅ ነው የሚለዉ እንጂ በሁለቱ ክልሎች ብቻ የታጠረ አይደለም።

 

በመጨረሻ በመግለጫቸው ላይ ከአንድ ዓመት በፊት ዘፋኝ ለአድናቂው መዝፈን አይችልም ነበር አሉን።ይህ ውሸት ነው፡፡ ይችል ነበር፡፡ ከወዳጃቸውና አብሮአደጋቸው ጀምሮ አንድ በአንድ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ዘፋኙ ከማያደንቁትና ከሚሰድባቸው ወገኖች ተቃውሞ ይገጥመው ነበር። ኮ/ል አብይግን ከአንድ ዓመት በፊት የነበረውን ከሚያስታውሱን አሁን በህዝብ ተወዳጅ የሆነውን ምን ልታዘዝ ድራማ እንዳይቀርብ በጥበብ ማን እንደከለከለው ቢነግሩን አይሻልም? አያልቅበት፣ደግሰው፣የባንክ ቤቶቹ ...ሌሎቹም ናፈቁን።የአሁኑን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዴት ያቀርቡት ነበር? የሾርት ሞሞሪ ችግር ላለባቸው ፍቱን መድሃኒት ነበር ምን ልታዘዝ ድራማ።

 

ቸር እንሰንብት።

 

Back to Front Page