Back to Front Page

ክቡር ጄነራል ሆይ ፥ በስዩም ተሾመ አይን እርስዎ ተጠርጣሪ ከሆኑ ፣ የትኛው ትግራዋይ ነው ንፁህ መሆን የሚችለው?።

ክቡር ጄነራል ሆይ ፥ በስዩም ተሾመ አይን እርስዎ ተጠርጣሪ ከሆኑ ፣ የትኛው ትግራይ ነው ንፁህ መሆን የሚችለው?።

 

Tsegazeab.K (MD,MPH)

August 5, 2019

 

መነሻ ሀሳብ - የዚህ ፅሁፍ መነሻ ሀሳብ የቀድሞ የኢትዮጽያ አየር ሀይል ዋና አዛዥና አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል አስተማሪ የሆኑት ሜ/ጄ አበበ ተክለሀይማኖት ፣ በለውጡ አዝመራ እንደ እምቧይ ከበቀሉት ሚድያዎች ውስጥ ከሆነው አንድ አፍታ ከተሰኘ የስዩም ተሾመና የኢዜማ የመረብ ላይ ቴሌቪዥን ያደረጉት ቃለመጠይቅ ነው።

ቃለ መጠይቁ ባልተለመደ መልኩ ይጀምራል። ተጠያቂው ፥ ጠያቂዉን በመጠየቅ ይጀምራሉ!። ተጠያቂው የጠየቀው ጥያቄ ቃል በቃል እንደሚከተለው ነው፦

አንዳንድ ሰዎች ወደ ስዩም ተሾመ ለኢንተርቪው እየሄድኩኝ ነው ስላቸው ፥ እሱኮ ፅንፈኛ ነው ፣ ፀረ ትግራይ ህዝብ ነው እንዴት እሱጋ ትሄዳለህ ብለው አሉኝ። አንተ ምን ታስባለህ? ብለው ይጠይቃሉ።

ጋዜጠኛ ስዩም ፥ አይደለሁም ፣ ልሆንም አልችልም ብሎ ይመልሳል።

ጄነራሉም (በመልሱ አለመርካታቸው በሚያሳብቅ መልኩ) Anyway, እኔ የመጣሁት ፅንፈኛ ቢሆን ፣ ፀረ ትግራይ ህዝብ አራማጅም ቢሆን እንዴት ፅንፈኛ ትሆናለህ ፣ እንዴት ፀረ ህዝብ ትሆናለህ ብዬ በሀስብ አስረዳዋሎህ። ከተሳካልኝ ጥሩ ፣ ካልሆነ የሚቻለኝን አድርጌሎህ ከሚል መነሻ እንደመጡ ያስረዳሉ።

እኔም ጄነራሉን ልጠይቃቸው። እናሳ ተሳካልዎት?

በግሌ አይመስለኝም። ለምን? ከጅምሩም ሊሳካ የማይችል (Mission Impossible) ስለሆነ።

Videos From Around The World

በእኔ እይታ ፥ በአጠቃላይ ከአክራሪ አሀዳውያንና ዜጋ ፖሌቴካ አራማጆች ጋር በሀሳብ ውይይት መግባባት ይቻላል ብሎ ማሰብ የሚቻል አይመስለኝም። ይህም የሚሆንበት ምክንያት የራሱ የሆነ የአስተሳሰብ ፣ የእምነትና የስነልቦና ስሪትና ውቅር ስላለው ነው ብዮ አምናሎህ። እነዚህ ሀይሎች ላለፉት 50ና 60 አመታት ሲያራምዱት ከነበረው የፖለቲአስተሳሰብና የፖለቲካ ግባቸውን ለማሳካት እንደ ዋና ታክቲክ ሲጠቀሙበት የነበረው አስተሳሰብ የመነጨ ነው። ይህ አስተሳሰብ በዋናነት ምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (instrumental irrationality) አስተሳሰብ ተብሎ መገለፅ ይችላል። ይህ ለረዥም ግዜ ያራመዱት አስተሳሰብ በሂደት ሁሉንም እምነቶቻቸውን ከመቅረፅ አልፎ ከስብእናቸው ጋር የተዋሀደ መገለጫ ባህሪያቸው ስለሆነ ነው። ምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (rational irrationality)የኢትዮጽያ ሊህቃን ፣ ጦማርያንን ኣንቂዎች መለያ ነው!።

ስዩም ተሾመ በእኔ እምነት ይህ አስተሳሰብ ከተጠናወታቸው አሀዳውያን/ የዜጋ ፖለቲካ አራማጆች ቀንደኛውና እንደ ማሳያ ሊወሰድ የሚችል ነው። ጄነራሉ ከንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች በጠርጼዛ ዙርያ ተወያይተው እንዳሉት መግባብት ይቻል እንደ ሆነ ለመሞከር አስበው ከሆነ ፣ ምርጫቸውን ስዩም ተሾመ ማድረጋቸው ትክክል ነው።

የምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (rational irrationality) ባህሪ ፣ በነዚህ ሰዎች ላይ ምን ያክል የተዋሀዳቸውና ለመንቀል አስቸጋሪ መሆኑን ለመገንዘብ በዛው በቃለመጠይቁ ውስጥ የተነሱት ሀሳቦችን ማየት በቂ ነው። ስዩም ተሾመ ትግራዋይ ልዩ ተጠቃሚ ነበር የሚለውን እምነቱ ለማስረገጥ የሄደበት ርቀት አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ ፣ ለትግራይ ህዝብ ያለው ጥላቻ የደረሰበት ደረጃ ማሳያ ነው። በኢህአዴግ ቁ-1 የተበደሉ ፣ የተገፉና የተሳደዱ መሆናቸውን ሁሉም ኢትዮጽያዊ የሚያውቃቸውን ነራል የትግራይ ህዝብ ልዩ ተጠቃሚነትን ለማሳየት እንደ ማሳያ አድርጎ ሊጠቅምባቸው የሞከረበትን መንገድ እንይ። የጥያቄው ኣንኳር ሀሳብ ጄነራሉ ትግራዋይ በመሆናቸው በጃቸው እንጂ የሌላ ብሄር ተወላጅ ቢሆኑ ኑሮ አይደለም መታሰር በሂወትም መኖራቸው አጠራጣሪ ነው ፥ የሚል ነው። ለዚህም የሚቀጥሉትን መከራከርያዎች ያቀርባል፥-

1.   ስለ 1993 የህወሓት ክፍፍልና ተከትሎ የመጣውን ክስተትን ፥ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የበላይነትና ልዩ ተጠቃሚዎች እንደ ነበሩ ለማሳየት በማሰብ ስዩም ተሾም ይህን ጥያቄ ይጠይቃል ፦ ከክፍፍሉ በኋላ እርስዎና ጓደኞቻቸው አልታሰሩም። ምናልባት የኦህዴድ ወይም የብአዴን አባል ቢሆኑ ኖሮ ፣ እስክ አሁን በሂወት እኖራለሁ ብለው ያስባሉ? ብሎ ይጠይቃል።

ትግራዋይ ስለሆኑ ነው ጉዳት ያልደርሰቦትና ያልታሩት ነው ነገሩ። ከሌሎች ድርጅቶች በተመሳስይ መልኩ የተጠየቁ ሰዎች ግን ጭራሽ በሂወት የሉም ነው! ጥያቄው።

ጄነራሉ በእርጋታ ስነ አመክንያዊ አቋማቸውን ይዘው ለመመለስ ይሞክራሉ ፥- የነበረው ስርአት አምባገነን ነበር ብለን ከተስማማን በብሄሬ ምክንያት ሊተወኝ አይችለም ፣ ምክንያቱም አምባገነን እንኳን በብሄር ጥብቅና ሊቆም ቀርቶ በስልጣኑ የመጣበትን ወንድሙም ሆነ ልጁን እንኳ አይምርም። ስለዚህ አንዱን መምረጥ ነው። ወይ ስርአቱ አምባገነን አልነበረም በል ካልሆነ ግን አንድምታው አይሰራም። ይሁንና እነ አቶ ኩማ ደመቅሳ የመሰሉ ልዩነት ያሳዩ ሰዎችም ቢሆን አልታሰሩም ፥ ብለው ይመልሳሉ። [በተጨማሪም ግን ጄነራሉ እቶ ስየ አብራሃ ከነቤተሰቦቻቸው፣ አቶ ቢተው በላይ ወዘተ የመሳሰሉ ሁኔታውን ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ኦሮሞ ወይም አማራ እንዳልሆኑ አስረግጠው ማስረዳት ነበረባቸው]። ይሁነና ይህ ስነአመክንያዊ ማብራርያና ገለፃ ምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (rational irrationality) እምነትና ባህሪ ለተጠናወታቸው ሰዎች በቂ አስረጂ አልሆነም። ስለዚህ ወደ ሌላ ማሳያ ይሄዳል

 

2.   እሺ እነ ኣሳምነው ፅጌና ተፈራ ታስረው እንዲሁም እነ ከማል ገልቹ ተገፍተው እንዲወጡ ተደርገው እርስዎ አልታሰሩም ይላል።

እነዚህ ሰዎች ክእስር ከወጡ በኋላና ከስደት ከተመለሱ በኋላ በተደረገላቸው የጀግና አቀባበል ሰክረው ለመርማሪ እንኳ ያልተናገሩትን ጨምረው ድርጊታቸውን ተናዝዘዋል። ሁለቱ ከእስር የተፈቱት ጄነራሎች አት ስለነበረው መፈንቅለ መንግስትና ከአዲስ አበባ እስክ ሮም ዱባይ ስለተዘረጋው እንቅስቃሴቸው በተለያየ ሚድያ ቀርበው በኩራት ተንትነዋል። እንዴት ንደከሸፈ ጭምር። ከማል ገልቹም ቢሆን በሚገርም ሁኔት የሰራዊቱ አባል ሆኖ የኦነግ ማ/ኮሚቴ አባል እንደነበረና በድርጅቱ ትእዛዝ የሰራዊት አባት ይዞ እንደወጣ እንዲሁ ኩራት የገለፀው ጉዳይ ነው። ስዩም ተሾመ ይህን ሉ መረጃ አለው። ለማንኛውም ጤነኛ አስተሳሰብ ላለው ሰው አንድን ድርጊት ፈፅምያሎህ ብሎ ያመነንና ግዜው ካለፈም በኋላ ምንም አልፈፀምኩም የሚልን ሰው በእኩል ደረጃ ለመፈረጅ ሲከጅል ከጭፍን ጥላቻ ውጪ በምንም ሊገለፅ አይችልም። ጄነራሉ ይህን ካስረዱት በኋላና ፤ እሳቸው በምንም አይነት ደረጃ ሊገለፅ የሚችል የህግ ጥሰት እንዳልፈፀሙና ድራማ ሊሰራባቸው ተፈልጎም ምናልባትም በቂ ስክሪፕት ስላልተገኘ ወይም እሳቸው በማያውቁት ሌላ ምክንያት እንደቀረ ከገለፁለት በኋላ እንኳ ጋዜጠኛው ማፈግፈግ አልፈለገም። ወይ የሚያውቀው የሰሩት ወንጀል ካለ አላቀረበ ወይ አምኖ አልተቀበለ እንዲሁ በሞትና በእድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈፅመናል ብለው ካመኑና ከተናዘዙ ሰዎች ጋር እያነፃፀር ፣ እሳቸው ያልታሰሩት ትግራዋይ ስለሆኑ ነው ብሎ ይከራከራል። አሁንም እጅ አልሰጠም ይቀጥላል፥-

3.   እሺ እኔና እርስዎ ሆርን አፈይርስ ላይ እንፅፍ ነበር። እንደውም የእርስዎ ፅሁፍ ከረር ያለ ነበር። ይሁንና እኔ ታስርኩ እርስዎ አልታሰሩም የሚል መከራከርያ ያቀርባል። ስለፃፍኩኝ ነው የታሰርኩት እያለ ነው። የጄነራሉ ፅሁፍ በሃስብ ላይ የተመሰረተ ትችትና ነውጥን የሚያወግዝ እንጂ ፣ በመከላካያ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ፣ የአመፅና የነውጥ ጥሪ የሚመስል እንኳ የለውም። እሳቸውም ብቻ አይደሉም ብዙ ሰዎች በተያየ አውድ ይፅፉ ነበር። እነሱም ቢሆኑ ፣ ፍንጭ ሳይገኝ ፃፍክ ተብሎ የሚታሰር ስላልነር አልታሰሩም። ፅሁፋቸው በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሁከት አመፅና ነውጥ ያበረታታል ተብለው የተጠረጠሩት ናቸው ሲታሰሩ የነበሩት። ልክ ነበር ስህተት ሌላ ነገር ሆኖ እንዲሁ የፃፍ ሁሉ ይታሰር ነበር ማለት ግን ስህተት ነው። እሳቸው እሱ በተጠረተርበትና በተከሰሰብት ጉዳይ ላይ ተመሳስይ ፅሁፍ አቅረበው ሳይታሰሩ ከቀሩ ማስረጃውን ጠቅሶ መከራከር ሲገባውእሱ ራሱ እንደ እውነት የተቀበለውና ከጥላቻ አስተሳሰብ የሚመጭ እምነቱን ለማስረገጥ ይዋትታል።

 

ብዙ ተጨማሪ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል። በአጠቃላይ በለውጡ ሃይል የሚባለው ይህ ስተሳሰብ በጥልቅ የሰረፀ ከመሆኑ የተነሳ ወደ ባህሪነት ያደገ አስተሳሰብ ሆነዋል። አንዳንዱ አስተሳሰብም እምነት የሆነ ይመስላል።

 

እዚህ ጋር ምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (rational irrationality) አስተሳሰብና እምነትን ፣ ከማጭበርበር (doublethink) መለየት አለበን።

እነዚህ ሰዎች ሆን ለው ለማጨበርበር በማሰብ ውሸት መሆኑን እያውቁ መከራከርያቸውን መርጠው አይደለም እንዲህ አይነት አምነት የሚያራምዱት። ይልቁንስ ለፖሌቴካ ፍጆታ ብለው ስያራሙዱት የነበርው አቋም ቀስ በቀስ እየተዋሃዳቸው ይሄድና አላማቸውን ካሳኩ በኋል ወደ እምነት ያደገውን አስተሳሰባቸው ለማስተካከል ቀስቃሽ ህሊና ስለምያጡ ነው። ይህም የሚሆነው ምንም የሚያስከፍላቸው ዋጋ ስለማይኖርና ስለማይጨነቁበት ነው። ትግራዋይንና የትግራይን ህዝብ መወንጀል ምንም የሚያሰከፍለው ነገር ስለሌለ ፣ በዚህ ዙርያ የያዙትን አም ለስተካከልና ለመመርምር አይጨነቁም። ምንም የሚመጣባቸው ነገር የለም!። ስዩም ተሾመ ለታክቲካል የፖለቴካ ትርፍ ሲል ስያራምደው የነበረውን ትግራዋይ ልዩ ተጠቃሚ ነው የሚለውን እምነቱን ለመከለስ የሚያበቃ ምክንያት የለዉም። ምክንያቱም ይህን ኣቋምና እምነት በመያዙና በማራመዱ ፣ ከዚህ ተነስቶ የግለሰቦችና የህዝብ ክብርና ስሜት ወደ መንካት ቢያመራ ፣ ምናልባት ይሸለምበት እንደሆነ እንጂ ሞራላዊ ፣ አስተዳደራዊና ህግዊ ተጥያቂነት የሚያስከትልበት እድል የለም። ይህ በሁሉም ሚድያዎች ሊባል በሚችል ሁኔታ እየታየ ያለ ባህሪ ነው። ዝም ብለው ይለቁታል ፣ ምንም የሚያስከትልባቸው ነገር የለም።

 

አንድ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ፥ ሞራላዊ ፣ አስተዳደራዊና ህግዊ ተጥያቂነት ማስከተል የሚችሉ እምነቻቸውና አቋማቸውን ግን ፈትሸው አስተካክለዋል። ለምሳሌ ፥ ኦህድና ብአዴን ላይ ይዘውት የነበረው እምነት ቀይረዋል። እነዚህን ድርጅቶች በተላልኪነት ፣ በአቅመ ቢስነት እንዲሁም በሎሌነት ሲከሷቸው ነበር። አምነውበት ስለነበርም ለማስረዳት አይቻልም ነበር። አሁን ግን የሆነ መውጫ ቀዳዳ አበጅተው ፣ ክሶችን አቋርጠው ወደ ውዳሴ ዞረዋል። ድርጅቶቹ ያው ናቸው። ለምን? ዋጋ ስለምያስከፍላቸው!።

በአጠቃላይ በትግራይ ህዝብና በትግራዋይ ላይ እንዲሁም በህወሓት ዙርያ ፣ እንዚህን ሰዎች ተከራክሮ እምነቶቻቸውን ለማስቀየር መሞከር ከንቱ ልፋት ነው። ይህን ለማድረግ በመጀመርያ ተጠያቂነት መስፈን አለበት። ማነቃቅያ ያስፈልጋቸዋል። በመንግስት ሚድያዎች ሳይቀር ህዝብን የሚያንቋሽሹ ዘገባዎች ቀርበው ተጠያቂነት ማስከተላቸው ቀርቶ ፣ እንደ አንድ የብቃት መመዘኛ ተቆጥሮ የሚያሸለምና የሚያሳድግ እስከሆነ ድረስ ወይ ፍንክች ያባቢላዋ ልጅ ከማለት ውጭ ፈጣሪን እንደምስክር ቆጥረህ ብትከራከራቸው እንኳ እምነቶቻቸውን ይቀይራሉ ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ክቡር ጄነራል ሆይ ፥ የስዩም ተሾመንና መሰሎቹን እምነትና አስተሳሰብ የመለውጥ ወይም የመቀየር ፍላጎት ካት ፣ ስነ አመክንያዊ ሙጉትና አስተሳሰብ በማራመድ ብቻ የመሳካት እድሉ ዝቅተኛ ስለሆነ ፣ ከነዚህ ሰዎች ጋር ጉንጭ አልፋ ሙግት ውስጥ ከመግባት ይልቅ ፣ የፈጠራ ፣ የማጠልሸት ፣ የተሳሳቱና ያልተረጋገጡ ትርክቶችን ማሰራጨት የሞራል ፣ የአስተዳደርና ህግዊ ተያቂነት የሚያስከትሉበት ስርአት በመፍጠር ላይ ቢሰሩ የተሻለ ውጤት የሚያግኙበት ይመስለኛል። ያኔ ፥ ስዩም ተሾመ ብ93 ክፍፍል ወቅት እነማን ታሰሩ እነማን አልታሰሩም ፣ እነ አሳምነውና ተፈራ ለምን ታሰሩ እርሰዎ ለምን አልታሰሩም ፣ በአንድ ድረገፅ ላይ የፃፋቹሁት ፅሁፍ ስዩምን ለእስር ሲዳርግ ለምን እርስዎ አልታሰሩም የሚለውን አጣርቶ መጥቶ ይጠይቆታል። ይህ አስከሚሆን ድረስ ግን ትግራዋይ ስለሆኑ ነው ያልታሰሩት የሚለው እምነቱን ለምን ይቀይራል?። በሱ ቤት እኮ ፥ የሚያራምደውና የሚያምንበት ኢምክንያታዊ አስተሳሰብ ምክንያታዊ ነው።

ለዚህም ነው ምክንያታዊ - ኢምክንያታዊነት (rational irrationality) እምነትና ባህሪ ከሚያራምዱት አሀዳውያንና የዜጋ ፖለቲካ አራማጆች እና በመጃና ማስረጃ የተደገፈ ምክንያታዊነት (Epistemic rationality) ከምያራምዱት የፌደራሊስት ሀይሎች መካከል ክርክር እንጂ ውይይት ማድረግ የማይቻለው። በኢህአዴግ ውስጥ የጎራ መቀላቀል አለ ሲባልም አንዱ ማሳያ ይህ ነው። የባህሪና የአስተሳሰብ ዋቅራቸው ጥግና ጥግ የሆኑን ሰዎች መቶ ግዜ ብትሰበሰባቸውም ጠብ የሚል ወደ ተግባር መቀየር የሚችል የሚረባ ነገር መውጣት አይችልም። መፍትሄው የሚመስለኝ ሁሉም አስተሳሰቡን ይዞ ጎን ለጎን ሁሉም ወደ ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንዲራድ የሚስችል ስራ እየሰሩ ህዝቡ እንዲፈርድ ለምርጫ መቅረብ ነው።

 

እንግዲህ የስዩም ተሾመን የትግራይ ህዝብ የጥላቻ ልክ ከራሱ መአድ ቀርበው ያረጋገጡ ይመስለኛል። በስዩም ተሾመ አይን እርስዎ ተጠርጣሪ ከሆኑ ፣ የትኛው ትግራይ ነው ንፁህ መሆን የሚችለው?።

 

 


Back to Front Page