Back to Front Page

የመፈንቅለ መንግሰት ጉዳይ አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ

የመፈንቅለ መንግሰት ጉዳይ አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ

ሰመኘው አይቸው ከባህር ዳር 7-12-19

 

መግብያ

የባህርዳርና አዲስ አበባ የተከሰተው አሳዘኝና ታሰበት የተፈፀመ ድርጊት ህ/ሰቡ እሰከ አሁን የጠራ ስዕል አልያዘም ለወደፊትም የሚይዝ አይመስልም፡፡ መንግሰት ሁሉም ነገር በአሳምነውና ተራ የፀጥታ አባለትና ዜጎች ላይ ትኩረት አደርጎ ወደ ዋናው ጠንሳሾቹ ሳይገባ ዳር ዳር እያለ ይገኛል ፡፡ ፀሃፊው ከማችም ከገዳይም የተወሰነ ቅርበት የነበረኝ በመሆኔ ስለ አጠቃላይ ሁኔታ ለመፃፍ ሳመነታ ቆይቼ አሁን የማወቀውን ለመግለፅ ሞኩሬ አለሁ ፡፡ የሚገርመው የተፈጠረው አደጋ በጥልቀት ከማየት ይልቅ ሁሉም በየደረጃው ያለ አመራር በተለይ ከፍተኛው አመራሩ መከላከልና ነገሩን ማደባበስ ተያይዞታል ገመዱ ከተመዘዘ የት እንደሚደርስ ስለሚውቁ ፡፡

የስልጣን ሽምያና መፈንቅለ መንግሰቱ

Videos From Around The World

ዶ/ር አምባቸውና በደመቀ መካከል በነበረው ከፍተኛ የስልጣን ፍክክር ምክንያት ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ የወሎ ሰዎች ቁልፍ ቦታ ተቆጣጠሩ የሚል ወሬ ተስፋፋ ( ፀጥታ ክፍሉ በሙሉ፤ የድርጅቱ ሊ/መንበርና ም/ሊመንበር ወዘተ)፡፡ በተከፍተው ወሬው አና የደመቀ አቋም የለሽ ባህሪ ምክንያት በማህበራዊ ሚድያና ዲያስፖራ ፀረ ደመቀ ዘመቻ ተስፋፋ በምትኩ የዶ/ር አምባቸው ተቀባይነት ጣራ ነካ፡፡ በዚህ ምክንያትም ፀረ ደመቀ አስተሳሰብ የበላይነት በማግኘቱ ከደመቀና ገዱ ፍላጎት ውጪ በማዕከላይ ኮሚቴ ስብሰባ ደምቀ ከሊ/መንበር በሙሉ ድምፅ ከቦታው ሊውርድ ችለዋል ፡፡ ደመቀ ከሊ/መንበርነት ከወረደ ረጅም በመቆየት ሪከርድ የሰበረበት የም/ጠ/ሚስተርነት ስልጣን በዶ/ር አምባቸው መታካቱ አይቄሬ ሆነ፡፡ በዚህ ሂደት ወደ ድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ገዱና ደመቀ ከዶ/ር አብይ በመመሰጣር በዘረጉት ኔትዎርከ ተጥቅመው ባልተመደ ሁኔታ ጉባኤው ደመቀ ከሊ/መንበርነት መወረድ የለበትም ብሎ ወሰነ፡፡ ከዚህ ጌዜ ጀምሮ ደመቀና ገዱ ከዶ/ር አምባቸው ግንኝነት ሻከረ /የውሸት ሆነ/ ፡፡ በነ ደመቀ መልስ ምትም ዶ/ር አምባቸው ቦታ በማሳጣት በአማካሪ ስም በአዲስ አበባ ቁጭ አደረጉት ፡፡ በመጨረሻም ዶ/ር አምባቸው ከደመቀና ገዱ ባለመደመሩ ወደ ተዘጋጀለት ወጥመድ ወደ ባህር ዳር በመላክ የአሳምነው የጥቃት ሰለባ ሆናል፡፡ ምንም አውቀት የሌለው ገዱ ከክልል መጥቶ ውጭ ጉዳይ ሆነ ሆኖም ቦታው በሚልዮን እጥፍ ለዶ/ር አምባቸው ይገባ ነበር ፡፡ በዚህ ድራማ ደመቀና ገዱ ከዶ/ር አምባቸው የነበራቸው የስልጣን ሽኩቻ አበቃ ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ መጠላለፍና አሰላለፍ በማየት ላይ ነን፡፡

የድህንነቱ ሚና

የኢ/ያ ብሄራዊ ድህንነትም የመከላከያ መረጃ ክፍልም በሂወት መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ መረጃ ቢኖረውም የተደመረ ሀይል መፈንቅለ መንግሰት አያደርግም የሚል የመረጃ ፍልስፍና ይኖር ይሁን? ግጭት /ጦርነት / በግላጭ ማወጅ ፤ ህገ መንግሰቱንና ፈደራል ስርአቱ ለማፍረስ መንቀሳቀስ ለነዚህ ሀይሎች የመደመርና ፍቅር ትልቁ ምልክት መሆኑ ከታወቀ ቆይታል፡፡ ሰለሆነም ድህንነት መ/ቤቱ ስራው ስርአቱን ከሚያፈረሱ አካለት ተባብሮ መስራት የሚል ተልዕከ ተሰጥቶት ይሁን? ጀ/ል አደም በብሄራዊ ድህንነት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይሁን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ኢታማርዦ ሹም የተሾሙት ወይስ በብሄራዊ ድህንነት መ/ቤት የተሰጣቸው ድህንነትን የማፍረስ ግዳጅ በአግባቡ ተዋጥተው አሁን ደግሞ የኢ/ያ ህዘብ አለኝታ የሆነው የአገር መከላከያ ሚ/ር የድህንነቱ እጣ ፈንታ እንዲደርሰው ለማድረግ ይሁን? ፈደራል መንግሰት የጀመረው በሀይል የማሰፈራራት አበዜ ሁነኛ ሰው ሆኖ ይሆን? ወይስ እንደሚባለው ጠ/ሚ አብይ ቀጣይ ሊወስዱት ያሰቡት የሀይል እርመጃ ጄ/ል ሰአረ እንቅፋት ስለሚሆኑና መሆን ጀመረው ስለነበር አስወገድዋቸው የሚባለው እንመን? አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ሁለት መፈንቅለ መንግሰት ያስተናገደ የብሄራዊ ድህንነት ሃላፊ ከመጠየቅ አልፎ መልሶ ወደ ሌላ ከፍተኛ የድህንነት አና ፀጥታ ተቃም የሚሾም የት አገር ነው የታየው ? ጉድ ሳይሰማ መሰከረም አይጠባም ሆነ ነገሩ፡፡

 

በመፈንቅለ መንግሰት ላይ መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች

አሳምነው ፅጌ አዳዲስ የልዩ ሃይል አባለት እሰከ ታች ቲም ወረዶ ገዳይ ቡዱን ሲመለምል፤ሲያደራጅ ፤ ሲቀሰቅስ ለምን ያለ አካል የለም ? በየደረጀው ካለ አመራር መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ ለምን አልተገኘም ወይስ የበላይ አመራሩ ሰምቶ ዝም ነው ያለው ? ዋናው ነገር ነውጠኛ እንዲሆን ያደረገው የተወሰኑ የአዴፓ አመራሮች ናቸው፡፡ ከአማራ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ስራ አስከያጅና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ የተደወለለት ከፍተኛ አመራር ስልኩ ለምን አላነሳም? ባለው ኔትዎረከ ቀድሞ መረጃ የደረሰው አመራር አገር ለምን ጥሎ ሄደ? አገር ቤት የነበረው አመራርም የአሳምነው ተግባር እየተመለከተ አስቀደሞ የሚከላከል ለምን ጠፋ? ከ20 አመታት በፊት በመንግስት አልባዋ ሶማሌ የነበረው ጄኔራል ፋራህ አይድድ አይነት ዘራፍ እያለ ሲያቅራራ መንግሰት ባለበት አገር ተው የሚል ለምን ጠፋ ? ብሄራዊ ድህንነትም የመፈንቅለ መንግሰት ሴራ ቢኖርም ለተደመረ ሰው ለጠ/ሚነስተሩ ኢ/ዊ ሙሴ ብሎ ያሞገሰ ሰወ አይከታተልም ማለት ነው ለምን ? ቢከታተልም ለጠ/ሚነስተሩ አያሳውቅም ነው ነገሩ? ወይስ እንደሚወራው ሪፖርት ደርሳቸው ይለይላቸው ብለዋል የሚባለው እንመን ? ለምን አሳምነው ከሁሉም በላይ አይነኬና እጅግ ተፈሪ ሊሆን ቻለ? ታድያ ህዘቡ ልዩ ሃይሉ የአሳምነው የግሉ ጦር ነው ቢል ምን ሀጥያት አለው ? በተጨባጭስ አልነበረም ወይ ? በክልሉ ውሰጥ የሚኖሩ ህዘቦች የቆሰቆሶው ግጭትስ ደፍሮ ማን አቁም አለው ? ይህ መልክ ለማስያዝ የሞኮሩ የክልሉ ባለስልጣናት የአሳምነው ፅጌ የግድያ ሰለባ ለምን ሆኑ? ለዘብተኛና በአደረባይነት አይዞህ ሲሉ የነበሩት ከሞት ተረፈው አሁን ለስልጣን በቅተዋል ፡፡ የገዱ አንዳረጋቸውና ደመቀ መኮንን ኦፊሻል ያልሆነ /ያልተቀደ ድንገተኛ የግል ጉብኝት ለምን ከመፈንቅለ መንግሰቱ ሙከራ ጋር ተገጣጠመ ? በአዲፓ የሚመራው የብሄራዊ ድህንነት ሹክ ስላላቸው አይመስላቹሁም ከአገር የወጡት ? ሁለቱ ቱባ ባለስልጣናት (ደመቀና ገዱ) የመፈንቅለ መንግሰት አድማስ እሰከ አዲስ አበባ የዘለቀ መሆኑ አስቀደመው ስላወቁ ይሁን የሽሽት አይነት ጉዞ ከአገር የወጡት ? ጠቅላይ ሚኒሰተሩስ ከብሄራዊ ድህንነት ስለ ጉዳዩ/አደጋው ዝግጅነት መረጃ አልደረሳቸውም ማለት ነው ወይስ ድህንነቱ ቁልፍ መረጃ ለአደፓ ነው የሚደርሰው ? ለዚህ ይሁን የድህንነት ሃላፊነት /ስልጣን /ከአዴፓ ወደ ኦዴፓ የተላለፈው?

 

አልፎ ተረፎም ከሞቱት አመራሮች አብረው አንድ ክፍል ውስጥ የነበሩት የክልሉ አመራሮች ሚድያ ቀርበው አሳምነው ፅጌ ልክ እንደ ዶ/ር አምባቸውና ባለደርቦቹ ለአገር የሞተ ጅግና አደረጉት፡፡ ደፍረውም ድርጊቱን ለመውቀስ አልቻሉም ፡፡ ይህ ለምን ሊሆን ቻለ ? ሳይገድላቸው ስለቀረ ውለታ መክፈላቸው ነው ? ውለታ መክፈል ከሆነስ የአሳምነው ድርጊት መውቀስ ቢያቅታቸው ዝም ማለትሰ አይቻልም ነበር? ወይስ የአላማ አና የእቀዱ አካል አንድነት ነበራቸው? ወይስ ገዳዮቹ ራሳቸው ናቸው? እጅግ ነውረኛ የሆነ ገዳይ ማሞገስ የማች ቤተሰብ ፤ የስራ ባለደርቦቹ፤ ጋደኞቹ አና ማንም ቅን ልቦና ያለው ዜጋ ህሊና አይጎዳም ወይ ? የአንድ አከባቢ የሆኑ አመራሮች ብቻ ለይቶ መግደሉስ ምን ማለት ነው ? የክልሉ ጠ/ አ/ህግ አቶ ግንባሩ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብቶ በደንብ ካገገመ እና መልዕክት በፅሁፍ ማሰተላለፈ ከጀመረ በኋላ በአንድ ስአት ልይነት ለምን ሞተ ተባለ? ወይስ ገዳዮቹ በነጭ ጋወን ጥቁር አምበሳ ገቡ? እንዲህ አይነት ወንጀል በግልፅ አለማወገዝ እና አድበስብሶ ማለፍ ምን አይነት የፖለቲካ ትርፍ እንዳለው አልገባኝም ? የክልሉ ህዝብስ ከዚህ የድብብቆሽ ፖለቲካ ምን ይጠቀማል?

 

የገዳዮቹ የእብደት ጀብደኝነት አጠቃላይ የአንድ አመት የተንኮል/ሴራ / ፖለቲካ የእርሰ በርስ መጣላለፍና የጎራ መደበላለቅ ውጤት እንጀ ግለሰባዊ ወንጀል አይደለም ፡፡ መፍትሄውም ከእብደት፤ ተንኮል፤መጠላለፍና ስሜት በመውጣት ሰከን ብሎ ስለ ክልሉ ህዘብና አገር ማሰብ ነው ፡፡

 

በተራ ወታደሮች የተሞከረ መፈንቅለ መንግሰት

በደሞዝ እና ጥቅማጥቅም ጥያቄ ለማቅረብ ከነ መሳርያቸው ቤተ መንግሰት የገቡት ወታደሮች (ከተራ ወታደር እሰከ አስር አልቃ ማእርግ ) ከፍተኛ ወንጀል /መፈንቅለ መንግሰት ሙኮራ/ ተብሎ እስከ 15 አመት በወ/ዊ ፍ/ቤት ተፈርዶባቸዋል ሆኖም ዋና የተንኮሉ ጠንሻሾች /master mind/ ምንም አልተባለም ፡፡ ከዚህ ጀርባ ማን መሆኑም አልተነገረንም? ወይስ ለመጀመርያ ጊዜ በአለም ታሪክ በተራ ወታደሮች የተሞከረ መፍንቅለ መንግሰት ብለን እንመን? ለምን ምርመራው በተራ ወታደሮቹ ተጀመሮ በነሱ አለቀ ? ከፍተኛ ወታደራዊና ሲቨል አመራሮቸ ወይም ሌሎች ሀይሎች የሉበትም ማለት ነው ? ይህ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው ወይም ወታደሮቹ እንዳሉት ቤተመንግሰት የሄዱት ቅን የሆነ የመብት ጥያቄ ነው ብለን እንውሰድ ወይሰ መፈንቅለ መንግስት የተባለው ለጊዛዊ ለፖለቲካ ጥቅም ነው?

 

በወቅቱ ከወታደሮቹ ቤተ መንግሰት ከነመሳርያቸው መግባት ተከትሎ በሰራዊት መካከለኛ አና ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች በተደረገው ውይይት ጄ/ብረሃኑ አና ሌሎች አመራሮች ከነበረው ሁኔታ ተነስተው በተራ ወታደር ብቻ መፈንቅለ መንግሰት አይደረግም በማለት ተጨማሪ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ዋናው አካል ( master mind) ይጣራ ፡፡ በመከላከያ መርማሪዎች የምርመራ ውጤቱ ለመከካለኛ ከፍተኛ አመራሮች ሲቀርብም ካለን ውሰን አቅም፤ ልምድና ችሎታ ተነሰተን ከድርጊቱ ተያያዥነት ያለው ሌላ አካል /ቡዱን አላገኝንም ብለዋል፡፡ መንግሰት ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ ይችላል ብለዋል፡፡ አሁንም ጄ/ ብርሃኑና ሌሎች አመራሮች መንግሰት ጉዳዩ ይቀጥልበት ወታደሮች ብቻ መጠየቅ የዋህነት ነው ብለዋል ፡፡ ይህ የአመራሮቹ አባባልም አብዛኛው ተሰብሳቢ ልብ ውሰጥ የነበረ መሆኑን ሁኔታው ያጨወተኝ ሰው ገልፀልኛል ፡፡ ሆኖም መንግሰት / ጠ/ሚ አብይ በወቅቱ ሌላ መዘዝ ያመጣል ወይም ስልጣናቸው ይነቃነቃል ብለው በመስጋት አድበስብሰው አልፈዋል፡፡ አሁን በም/ቤት ሪፖርት ሲቀርቡ የአሁኑ መፈንቅለ መንግሰት የተሳተፉት የከዚህ በፈት የተሳተፉት ወታደሮች አሉበት ብለዋል ስለሆነም እኛ አገር ወታደሩ እና ስሙ ያልተገለፀ ሀይል በመፈንቅለ መንግሰት ልምድ እየያዘ ነው ፡፡ በወቅቱ ወ/ዊ መረጃስ ምን ይሰራ ነበር የሚልም ጥያቄ ጭረዋል? በየደረጃው ያለ አመራረስ ወታደሮቹ እንዴት ከጨዋታ ውጪ አደረግዋቸው ? ስለሆነም በጠ/ሚኒስተሩ ማስረጃ መሰረት የሁለቱም መፈንቅለ መንግሰት ጠንሳሽና ፈፃሚዎች አንድ ቡዱን ነው፡፡ መቸስ የፈረደበት ዋናው ጠንሳሽ አሳምነው/ጌታቸው አሰፋ እንደማይሉን ተሰፋ አደርጋለህ፡፡ የመጀመርያው መፈንቅለ መንግሰት በዚህ መልኩ ተድበስብሶ ስለሄደ ይሄው ሁለተኛ መፈንቅለ መንግሰት ተሞከረ የሚል ዜና እየሰማን ነው፡፡

 

የአሳምነው መፈንቅለ መንግሰት

የአሁኑ መፈንቅለ መንግስትም እርምጃ አወሳሰዱ ተመሳሳይ ነው ፡፡ ቀጥታ ድርጊቱ ፈፃሚዎችና የቅርብ አመራሮቻው ከማሳደድ ወጪ የተንኮሉ ጠንሻሾች /master mind/ እስከ አሁን ምንም የተባለ የለም ፡፡ የአሁኑ መፈንቅለ መንግሰት አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ወደውም ይሁን ሳይወዱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረተሩ ተራ ዜጎች ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አባለት፤ የአሳመነው ፅጌ ሚሰት አና ወንድም ወዘተ በማሰር ሁሉም መነሻ እና መድረሻ በሂወት የሌለው አሳምነው ፅጌ ላይ በመደፍደፍ ዋናው የተንኮሉ ጠንሻሾች /master mind / በፈደራልና በክልል እነማን መሆናችው መንግሰት ለምን እንደማይገለፅ እንቆቅልሽ ነው፡፡ የአሁኑ ማድበስበስ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሌላ ጠጨማሪ እዳ ይዞ እንደሚመጣ ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡

 

ፅሁፌን ለማጠቃል ያክል አሁን ባለው አካሄድ /trend /ጠ/ሚ አብየ ጊዜ ደርሶ ከስልጣን ሲወረዱ /ሲቀየሩ/ አዲሱ ጠ/ሚ በመፈንቅለ መንግሰት ለታሰሩት ወታደሮች ጀግኖች ብሎ ቤተ መንግሰት ምሳ ጋብዞ ሹሞት ሊሰጣቸው ይጠበቃል፡፡ የአሀኑ የአማራ/ፌደራል መፈ ንቅለ መንግሰት ሙከራ የተሳተፉትም የሚታሰሩት ጠ/ሚ አብየ አህመድ ስልጣን ላይ እሰካሉ ብቻ ነው፡፡ ሌላ ጠ/ሚ ሲመጣ የአብየ አምባገነን መንግሰት ሲታገሉ መስዋዕት የሆኑ የታሰሩና የተገረፉ ጀግኖች ተብለው በክልልና በፈደራል ከፍተኛ ስልጣን ይጠብቃቸዋል ማለት ነው፡፡ ተወደደም ተጠላም እየሄድንበት ያለው መንገድ ይህ ነው ፡፡


Back to Front Page