Back to Front Page

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት፡ መጪዉ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ!

ብርሃኔ በርሄ ተስፋዬ

11-13-19

 • መልካም አጋጣሚ ነዉ! ቀድሞ ዉሽማ/ዉሽሚት የነበሩት ባል/ሚስት ስለሚሆኑ ፊዚካል ሜሬጅ ያበቃለታል! ሁሉም የልብ ፍቅረኛዉን ያገኛል!!!!
 • በተሳሳተ መንገድ የዉጭም የዉስጥም አሀዳዊያን ከተሳካላቸዉ የኢትዮጵያዊያን የአብሮነት ጉዞ ስለሚፈተን የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሂደት ለአደጋ ይጋለጣል

“……መንግስት ለመመስረት አብላጫ ድምፅ ለማግኘት ሲባል ቀደም ሲል በገዥ ፓርቲነትና በተቃዋሚነት የነበሩ የብሄር አደረጃጀት ፓርቲዎች ሳይቀሩ ወዳጅነት እና ቅንጅት እንዲፈጥሩ መልካም አጋጣሚ ይሆናል። ይህም የፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን እና የብሄር ብሄረሰቦችን መብትና ጥቅም በአግባቡ የሚያስጠብቅ እዉነተኛ ፌዴራሊዝምና እርቅ እንዲኖር ሲሰብኩ የነበሩትን ፍላጎት እዉን ያደርገዋል። በኢህአዴግ ዉስጥና ከኢህአዴግ ዉጭ በነበሩት የብሄር ፓርቲዎች መካከል የነበረዉ ያለመግባባት ቁስል እዉነተኛ ፈዉስ አግኝቶ እስከወዲያኛዉ ይድናል! በተቃራኒዉ ደግሞ ከልብ አምነዉበት ሳይሆን ስልጣን ለመያዝ ሲሉ ኢህአዴግን በግንባርነት በመመስረት ብሄርን መሰረት ላደረጉ ፓርቲዎች የጎን ዉጋት ሆነዉ የነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች በኢህአዴግ አሀዳዊነት ምክንያት ፍቺ በመመስረት ከቀድሞ አሀዳዊ ተቃዋሚዎቻቸዉ (የልብ ወዳጆቻቸዉ ከነበሩት) ጋር ዉህደት ስለሚመሰርቱ በተመሳሳይ ፓርቲዎች መካከል የነበረን ጥላቻ በማስወገድ ከእዉነተኛ ማንነታቸዉ ጋር ያገናኛቸዋል። ሁሉም አይነት የፖለቲካ አደረጃጀቶች እዉነተኛ ፍቅረኛቸዉን ስለሚያገኙ አንዱ በሌላዉ ዉስጥ ሆኖ ትዳር ለማፍረስና ከሚስት ወይንም ባል ይልቅ ለዉሽሚት ወይንም ዉሽማ ጋር የነበራቸዉን ታማኝነትና የብልግና ስራ ከመስራት የሚቆጠቡበት ትክክለኛ የፖለቲካ አሰላለፍ ይፈጠራል። ይህም በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ሀገራት በዓመታት ሂደት ለሀገሪቷ የማይበጅን የህገመንግስታዊና አስተዳደራዊ ስርአት አስተሳሰብ አራማጅ ፓርቲዎችን በማክሰም ለብሄር ብሄረሰቦች ህልዉና እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን ሲባል ሊኖሩ የሚገባቸዉን አዉራ ፓርቲዎች የመሪነት ሚና በማያወላዳ ሁኔታ ያረጋግጣል…”። ስለሆነም አሁን ያለዉ የኢህአዴግ መበጥበጥና መለያየት በበኩሌ በመልካም አጋጣሚነት እንጂ በመጥፎ አጋጣሚነት አይወሰድም። ሁሉም አዉነተኛ ፍቅረኛዉን ስለሚያገኝ የጣልቃ ገብነት ፖለቲካ ያከትምለታል። የተከበሩ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ሌሎች “….የእኛ ችግር ኢህአዴግ በዉስጣችን እየገባ ተለጣፊ ስለሚያበጅልን ነዉ …በማለት ይወቅሱ የነበረዉ ጉዳይ ያከትምለታል። ምክንየቱም በአሰላለፍ መስፈርት ሲመዘን አሁን ካለዉ ኢህአዴግ ዉስጥ በእርግጥም ለእርሳቸዉ ፓርቲ እዉነተኛ ወዳጅ የነበረዉን ስለሚያገኙ ሁሉም ከእዉነተኛ ወዳጁ ጋር ይገናኛል። ወዳጅን በአግባቡ የለየ እዉነተኛ እርቅ ማለት ደግሞ ይኸዉ ነዉ። የጣልቃ ገብነት ፖለቲካ ያበቃለታል!!! ሁላችሁም ወገኖች እንኳን ደስ አላችሁ። ቀድሞ ዉሽማ የነበሩት ከእንግዲህ ባል ወይንም ሚስት ስለሚሆኑ ሁሉም ከትክክለኛና እዉነተኛ ፍቅረኛዉ ጋር መኖር ይጀምራል!!!!”

የሙሉ ጊዜ ስራቸዉ በሆነዉ ምሁራን በሴናሪዮዉ ላይ ጠለቅ ያለ ትንታኔ የሚሰጥበት ቢሆንም የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሂደት ጉዳይ በአንፃሩ ለአደጋ ይጋለጣል። አሀዳዊያን ይሳካላቸዋል የሚል እምነት ባይኖረኝም ሁሉም የዉጭና የዉስጥ አሀዳዊያን ሀይሎች መዋሃዳቸዉ አይቀርም። እነዚህ ሀይሎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ደ/ር አብይን እየጠበቁ ያሉት የህገመንግስታዊና ፌዴራላዊ ስርአት አስቸጋሪ ጠበቃና ዘበኛ የነበረዉን ኢህአዴግን እስኪያፈርሱላቸዉ ድረስ ብቻ ነዉ። ከዚያ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ከአሀዳዊያን ሀይሎች ጋር መጋጨታቸዉ ስለማይቀር አይፈለጉም። የኤርትራ ነፃ አገርነትን በመቀበል ረገድ እስከአሁንም ያልተዋጠላቸዉ አሀዳዊያን ሀይሎች የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመደመር ፍልስፍና ጥለነዉ ወደመጣነዉ በሀይል ላይ የተመሰረተ መደመር ፍልስፍና በመለወጥ የኤርትራንም ጉዳይ ጥያቄ ዉስጥ ማስገባታቸዉ አይቀርም። በኢህአዴግ ዉስጥ ያሉትንም ይጨምራል። ተሳክቶላቸዉ የመንግስትነት ስልጣን ቢይዙ በዉስጣቸዉ የደበቁትን ኤርትራን ህልዉና የመፈታተን ጉዳይ ለጠረጴዛ ድርድር የማቅረባቸዉ ጉዳይ ሳይታለም የተፈታ ነዉ። ይቅርታ ይደረግልኝና የሰብአዊነት ተልእኮ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ታሪካዊ ጠላቶች እና የሀገሪቷ ታሪካዊና ተጨባጭ ሁኔታ በቅጡ ያልገባቸዉ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሀዳዊ ፓርቲነት ምስረታ ማግስት መሸኘታቸዉ አይቀርም። ተቀባዩ ደግሞ ክቡር ዶ/ር አብይ የጀመሩትን የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሂደት የሚቀለብስ አስተሳሰብ የተሸከመ ሀይል እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም። ኤርትራን የሚፈታተኑ ሀይሎች የተፅእኖ ፈጣሪነት ሚና ይኖራቸዋል። እነዚህ ሀይሎች ለምሳሌ አሰብንና መሰል የኢትዮጵያ ጥቅም የሚሏቸዉን ታሪካዊ ጥያቄዎች ካላገኙ ከኤርትራ ጋር የሚኖረዉን ጉዳይ በሀይል ወደመፍታት መሸጋገራቸዉ አይቀርም። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ አሀዳዊያን ሀይሎች እና በኤርትራ መካከል የሚፈጠረዉ ፍጥጫ በኢትዮጵያ የራስን እድል በራስ ለመወሰን መብት የሚታገሉት ብሄራዊ አደረጃጀቶች መካከል ግጭት ይፈጠራል። የኤርትራን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የሚፈታተን ዉስጣዊ ሀይል ለሀገር ዉስጦቹ ብሄርተኛ ፓርቲዎች ጤናማ ሁኔታን ስለማይፈጥር ከዉስጥ ትብብር ይልቅ ወደዉጭ መመልከትን ሊያስከትል ይችላል። ታሪክ ተደገመ ማለት ነዉ። ከደርግ ዉድቀት በፊት የዉስጥ ሀይሎች የዉስጥ ችግራቸዉን ለማስወገድ ከዉጫዊ ሀይሎች ጋር መተባበር የጀመሩበት መሰረታዊ ምክንያት ይኸዉ ነበር። የአሁኑ ግን ምናልባትም የዉስጥ አሀዳዊያን ፓርቲዎችን በማስወገድ የምንገላገለዉ አይሆንም። ከእንግዲህ ኢትዮጵያ አታስፈልገኝም የሚሉ ሀይሎች በሰሜን፣ በምእራብም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች እየጎለበቱ ስለሚመጡ የዋሁ ፖለቲከኛ ደ/ር አብይ የሚመኟት “ታላቋ ኢትዮጵያ” በመገንጠል ጥያቄዎች ጭምር ወደብዙ ትናንሾች ተመንዝራ እርማቸዉን ያወጣሉ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ቅን እሳቤ እንጂ የኢትዮጵያን ታሪካዊ አመጣጥ ያገናዘቡ ፖለቲከኛ አልመሰሉኝም። የብሄር ብሄረሰቦች ታሪካዊ ጠላቶች እስኪያሽቀነጥሯቸዉ ድረስ በየዋህነት ብቻ እየተጓዙ ያሉ ለሰብአዊነት ብቻ የሚመጥኑ ፖለቲከኛ ናቸዉ። ሌሎቹ አድፍጠዉ እየጠበቋቸዉ እንደሆነ የተገነዘቡ አልመሰለኝም- የኢትዮ- ኤርትራ ጉዳይንም ጨምሮ ማለቴ ነዉ!

Videos From Around The World

ከዉስጠኛዉ ክፍል የተቀነጨበ ዋነኛዉ መልእክት ነዉ!

 

በአሁኑ ጊዜ የራሱን ህልዉና ማስከበር ያልቻለና በተግባርና በዓላማ አንድነት እጦት እየተሰቃየ ቢሆንም የኢህአዴግ ድርጅታዊ ቅርጽና ሰብእና እና የኢፌዴሪ ህገመንግስት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ። ኢህአዴግ የቆመባቸዉ የብሄራዊ ድርጅቶች የማእዘን ድንጋዮች(ምሰሶዎች) ከተነቀሉ ወይም ህልዉና ካጡ የህገመንግስቱን መሰረታዊ ምሰሶዎች /ድንጋጌዎች/ ለመናድ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረ ማለት ነዉ።

በኢህአዴግና በአሃዳዊ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የነበረዉ ልዩነት ህገመንግስትን ጨምሮ ያለዉን እያጠናከሩ በመሄድ የፖዘቲቭ ድምር ዉጤትና የነበረዉን አፈራርሶ ከዜሮ በመጀመር ላይ የተመሰረተ የዜሮ ድምር ዉጤት ጨዋታ ነዉ። ዛሬ ላይ ህልዉ ባይሆንም ኢህአዴግ ላለፉት ዓመታት በስልጣን የቆየበትና በዚህ ፖለቲካዊ መርሆ ቢቀጥል ኖሮ በአሻናፊነት ሊዘልቅ የሚችልበት ምስጢርም ይኸዉ ነዉ። ሙሉ በሙሉም ሆነ በተወሰኑ ፓርቲዎች ስምምነት ኢህአዴግ አሀዳዊ ፓርቲ ከመሰረተ በአሀዳዊነት ላይ የተመሰረቱ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ የአፍርሶ መገንባት አገዛዝ ስርአትን ለማስፈን ሲተጉበት ለቆዩት የቀዉስ መርሆ ተግባራዊነት በሩን ክፍት እንዳደረገ ይቆጠራል።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ሰንደቃላማ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎች

በአሀዳዊነት ላይ የተመሰረቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስልጣን በያዙ ማግስት አሁን ያለዉን የኢፌዴሪ ሰንደቅዓላማ እንደሚያሻሽሉት ደጋግመዉ ሲነግሩን ቆይተዋል። ዋነኛዉ ጠባቸዉ ደግሞ ከአርማዉና ከወከለዉ ፖለቲካዊና መብታዊ ትርጉም ጋር ነዉ። አርማዉ የብሄር ብሄረሰቦች፣የህዝቦችና የሀይማኖቶች እኩልነትንና ተፈቃቅዶ የመኖር ተምሳሌት እና ተልእኮ እንጂ ሌላ ክፉ ሃሳብ የለዉም። ይህን በጎ ተልእኮ የማደብዘዝ ወይም የማጥፋት ዓላማ ያለዉ ማንኛዉም አካል ደግሞ በኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዘንድ ከእንግዲህ ተቀባይነት የለዉም። የኢህአዴግ የትግል ዓላማና አፈጣጠርም ከዚህ ዓርማ ትርጓሜ ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸዉ። ከኢፌዴሪ የሰነደቅዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 ክፍል ሶስት ዉስጥ ከዚህ ጉዳይ ጋር ቀጥታ ተዛማጅነት ያላቸዉን ድንጋጌዎች በቅድሚያ እንመልከት። የአዋጁ አንቀፅ 5 የሰንደቃላማዉን ምንነት አስመልክቶ “…..የህዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት መግለጫ…መሆኑን ሲደነግግ በተመሳሳይ ሁኔታ ስለሰንደቅዓላማዉ አርማ የሚያስረዳዉ አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 23 እና 4 በቅደም ተከተል፦

 • “ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች የብሄሮች፣የብሄረሰቦችና የህዝቦች እንዲሁም የሀይማኖትን እኩልነት ያመለክታል”
 • “ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረዉ ኮከብ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ የመሰረቱትን አንድነት ያመለክታል”
 • “ቢጫ ጨረር በመፈቃቀድ አንድነት ለመሰረቱት ብሄር ብሄረሰቦች የፈነጠቀዉን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል”

የሚሉ ድንጋጌዎችን ይዟል። ከዚህ አኳያ ኢህአዴግ ሲጀመር በብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ላይ ተመስርቶ ከተዋቀረባቸዉ ዋነኛ ምክንያቶች ዉስጥ፦

 • ብሄራዊ ድርጅቶች የክልሎችና የብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትና ህልዉና ተምሳሌት ናቸዉ። ክልሎች በዉስጣቸዉ ያቀፏቸዉ ብሄሮችና ብሄረሰቦች እዉቅና ተጠብቆ የሚኖርባቸዉም ናቸዉ። ብሄራዊ ድርጅቶች ለፌዴራልና ለክልል ምክርቤቶች ዉክልና ሲወዳደሩ በየክልሉ ያሉትን ብሄሮችና ብሄረሰቦች በአግባቡ በመወከል ነዉ። አሁን ያለዉ የኢህአዴግ እና የተቃዋሚዎች ተፈጥሮ እንደዚሁም በህገመንግስቱ ላይ ያላቸዉ መሰረታዊ ልዩነት በዚህ ይገለጻል። ለፌዴራል እና ለየክልሉ ያለዉ የክልሎች ዉክልና ጉዳይ ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ እና ከድሬዳዋ ለፌዴራል እንደዚሁም ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ምክር ቤቶች ከሚያደርገዉ የዉክልና ዉድድር የተለየ ነዉ። የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ተጠሪነት ለፌዴራ
 • መንግስት በመሆኑ እና በአንድ ክልል በተሰየመ የብሄር ብሄረሰብ አስተዳደር ባለመዋቀራቸዉ የኢህአዴግ እጩዎች በቀጥታ ህወሓትን፣[ኦዲፓን]፣ደኢህዴንን ወይም [አዴፓን] እና እነርሱ የወከሏቸዉን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመወከል አይወዳደሩም። ኢህአዴግ በየክልሉ ሲወዳደር ግን የሚቀርቡት እጩዎች የክልሉን ብሄር ብሄረሰብ የሚወክሉት የብሄራዊ ድርጅቱ አባላት ናቸዉ። ኢህአዴግን የመሰረቱት የእነዚህ ብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ከጠፋ ግን ብሄር ብሄረሰቦች በአግባቡ የሚወከሉበት መሰረቱ ይናዳል። ብሄራዊ ድርጅቶቹ ከሌሉ በዚያ ክልል የሚኖረዉ የዉክልና ዉድድር አሃዳዊ የፖለቲካ ድርጅትን በሚወክሉ የአንድ ድርጅት አባላት ላይ እንዲመሰረት ሊያስገድድ ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ የብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መሰረታዊ መብት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተግባራዊ አይሆንም። የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ጽንሰሀሳብ የብሄር ብሄረሰቡን ቋንቋ ለስራ፣ለትምህርት፣ለፍትህና ለዳኝነት ተግባራት፤ የብሄር ብሄረሰቡን ባህልና ወግ የመጠቀምና የማሳደግ መብት፤ ከብሄር ብሄረሰቡ በወጡ ተወካዮችና አስተዳዳሪዎች የመተዳደር መብት፤የክልሉን ሀብት የመጠቀምና የማስተዳደር መብት ወዘተ ያጠቃልላል። ኢህአዴግ አሃዳዊ የፖለቲካ ድርጅት ከሆነ ግን ሁለት ፍላጎቶች መፋጠጣቸዉ አይቀርም። አንደኛዉ ፍላጎት የብሄር ብሄረሰቦች ደም ፈሶበትና አጥንት ተከስክሶበት ተግባራዊ በሆነዉ ህገመንግስት መሰረት በተዋቀሩት ክልሎች አማካኝነት የብሄር በሄረሰቦችን ሁለንተናዊ መብትና እኩልነት እያረጋገጡ ያሉት የአከላለልና የዉክልና ስርአቶች ተጠብቀዉ እንዲቀጥሉ

 

የሚታገል ነዉ። ሌላኛዉና መጤ ፍላጎት ደግሞ ኢህአዴግ አሃዳዊ የፖለቲካ ድርጅት እስከሆነ ድረስ የክልሎች አስተዳደርም ሆነ የዉክልና ስርአት ብሄራዊ ዉክልናን እና ህልዉናን ገሸሽ የሚያደርግ ነዉ። ለክልሎች የብሄር ብሄረሰቦችን የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከመገንጠል መብት የሚያጎናጽፈዉን ክልላዊ የአስተዳደር ስርአት ለማጥፋት የሚተጋ ይሆናል። ማለትም የኢህአዴግ አባላት ባልተወለዱበት ክልልና አካባቢ እንደዚሁም በትዉልድ ለማይወክሉት ብሄር ብሄረሰብ የመወዳደር መብታቸዉ የተጠበቀ ይሆናል። ይህ መብታቸዉ እስከተጠበቀ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ በሚወዳደሩባቸዉ ክልልሎች (የየትኛዉም ብሄር የሆነ አባል የምርጫ ህጉን መስፈርት እስካሟላ ድረስ በሁሉም ክልሎች የመወዳደር መብት ይኖረዋል) የኢህአዴግ አባላትን በጋራ የሚያግባባ የስራ ቋንቋ ያስፈልጋቸዋል። አሃዳዊ ፓርቲ እስከሆነ ድረስ አባላቱ በሁሉም አካባቢ አንድ የጋራ ቋንቋ እንዲኖራቸዉ የመጠየቅ መብታቸዉ የተጠበቀ ነዉ።

በአሁኑ ጊዜ በክልልም ሆነ ከክልል በታች ያሉት የአስተዳደር መዋቅሮች የሚጠቀሙባቸዉ የአካባቢዉ ተወላጆች ቋነቋዎች ሁሉ ለአሃዳዊዉ የኢህአዴግ አባላት መብትና አመቺነት ሲባል በአንድ ቋንቋ የመተዳደራቸዉና የመዳኘታቸዉ ጉዳይ አስገዳጅ እየሆነ ይመጣል። ወላይትኛ፣ስልጢኛ፣ጉራጊኛ፣ ከምባትኛ፣ሃድይኛ፣ሲዳምኛ ፣ሶማሊኛ ወዘተ ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉት የአስተዳደር እርከኖች ቦታ አይኖራቸዉም። በአማርኛ ወይም በሌላ ቋንቋ የመተካታቸዉ ጉዳይ አይቀሬ ይሆናል።

ልክ በአዲስ አበባ ወይም ድሬዳዋ ተግባራዊ እንደሆነዉ ይህ ቋንቋ በክልሎችም ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባዊ በፖለቲካ አደረጃጀትም ሆነ በህግ አስተሳሰብ አሳማኝ የሆኑ አመክንዮዎች መቅረባቸዉ አይቀርም። ይህም አሁን ካለዉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ቅራኔ ዉስጥ መግባቱ የግድ ነዉ።ይህ ደግሞ በርካታ የመብት ጥሰትና በአስባቡም የተቃዎሞ ሰበቦችንና ግጭቶችን ማስከተሉ አይቀርም።

 

 • በዚህ መነሻነት አሁን ያለዉ የኢህአዴግ ድርጅታዊ አወቃቀርና ተልእኮ የአንቀፅ 8 አስተሳሰን ለመተግበር የወሰነ ነዉ።እኩል እዉቅና እና ስልጣን ያላቸዉ ኢህአዴግን የመሰረቱት ብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ….ለብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች… እኩልነት በተሰየሙት በሰንደቅዓላማዉ ቀጥታና እኩል መስመሮች ህልዉና የሚመሰል ነዉ።

የሰንደቅ ዓላማዉ አርማ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀድ የመሰረቱትን አንድነት እንደሚያመለክተዉ ሁሉ ብሄራዊ ድርጅቶችም በዚሁ እምነትና አስተሳሰብ ኢህአዴግን በግንባርነት የመሰረቱት ነዉ።

የአጼዉና የደርግ ዘመን አቀንቃኝ ሀይሎች ይህን አርማ ለማጥፋት እንደሚፎክሩት ሁሉ በኢህአዴግ አስተዳደር ዘመን ይህን አርማ ማጥፋት ማለት በብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ህልዉና ላይ የተመሰረተ አንድነት ለማስጠበቅ ይዞት የቀረበዉን ተልእኮ ማጥፋት ነዉ። በተነጻጻሪም የብሄራዊ ድርጅቶችን ህልዉና ያጠፋ በአሃዳዊነት ላይ የተመሰረተ አዲስ ኢህአዴግ መፍጠር የአርማዉን ዓላማና ተልእኮ ለማጥፋት በርን ወለል አድርጎ እንደመክፈት ይቆጠራል።

ብሄር ብሄረሰቦች ተፈቃቅደዉ በመሰረቱት አንድነት ምክንያት የፈነጠቀዉን ብሩህ ተስፋ ጨለማ እንደማልበስ ይቆጠራል።

ሌሎች አሃዳዊ አወቃቀር ያላቸዉ የፖለቲካ ድርጅቶች በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቀባይነት ይኖረናል ብለዉ እስካመኑ ድረስ አርማዉን በማጥፋት ላይ ያለመ ህገመንግስታዊ ይዘት ይቅርና እንደቀድሞአቸዉ “በኢትዮጵያ ዉስጥ ኦሮሞ፤ትግራይ፣ሶማሌ፣ ወላይታ፣ጉራጌ ወዘተ የሚባል ብሄረሰብ የለም …” የሚል ፖለቲካዊ አጀንዳ ይዘዉ መቅረብ ይችላሉ። ህገመንግስት ለግጭትና ለሁከት እንደዚሁም በህግ ለተከለከሉ ሌሎች የወንጀል ተግባራት የማያነሳሳ እሰካልሆነ ድረስ ሀሳብ ማቅረብን ይፈቅዳል። ብሄር ብሄረሰቦች ደግሞ ሀሳቡ ዘላቂ ሰላምና ልማት የሚያመጣላቸዉ ወይም የሚያርቅባቸዉ መሆኑን ገምግመዉ ይወስናሉ። ለግጭትና ለብጥብጥ ምክንያት እስካልሆነ ድረስ ሀሳብን ማራመድ አይከለከልም። ነገር ግን ያለ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ይሁንታ ስልጣን መያዝ የተከለከለ ነዉ። ምክንያቱም የሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ናቸዉ። ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ላለፉት 20 እና ከዚያ በላይ ዕመታት ስልጣን መያዝ ያልቻሉበት ምክንያትም ይዘዉ የቀረቧቸዉ ሀሳቦች በሉአላዊ የስልጣን ባለቤቶች ይሁንታ በማጣታቸዉና ቦታ የሌላቸዉ በመሆናቸዉ ነዉ። ስለሆነም የብሄራዊ ድርጅቶችን ህልዉና ደብዛ ያጠፋ አሀዳዊ ኢህአዴግ በአንቀጽ 8 ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ተልእኮ አንፃር ሲመዘን ብዙዎች የወደቁለትን ዓላማ ለማፈራረስ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር በራሳቸዉ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መዉደቁ አይቀርም። መምቻ ዱላዉን ቆርጦ እንደማቀበል ይቆጠራል። ኢህአዴግ ከግንባርነት ወደአሀዳዊ ፖለቲካ ድርጅትነት ቢሸጋገር ህገመንግስቱ የሚሸራረፍባቸዉን መሰረታዊ የመብት ጉዳዮች እያስመዘገብን ነዉ። አንድ በሉ።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 5

 • ጉዳዩን ከኢፌዴሪ ህገምንግስት አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀፅ 3 ተልእኮ አንጻር እንመልከተዉ። ይህ አንቀጽ “….የፌዴሬሽኑ አባሎች የራሳቸዉን የስራ ቋንቋ በህግ ይወስናሉ…..” የሚል ድንጋጌ አስፍሯል። ሲጀመር ኢህአዴግ የብሄራዊ ድርጅቶችን ህልዉና ካጠፋ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን የራስን እድል በራስ ለመወሰን ስልጣን የሚሰጥ የአከላለ
 • ስርአት እንዳይኖር ተዘጋጅቷል ማለት ነዉ። ይህም የአሃዳዊ ድርጅቱ አባላት በሁሉም የመስተዳድር አካባቢዎች ያልምንም መስፈርት ሊወዳደሩና ሊያስተዳድሩ የሚችሉበት የአስተዳደር አወቃቀር ማስፈንን ግድ ይለዋል። ከዚህ ዉስጥ እንዱ የስራ ቋንቋ ነዉ። ስለሆነም አንድም በአሁኑ ጊዜ ያሉት የፌዴሬሽኑ አባሎች ለአሃዳዊዉ ኢህአዴግ በሚመጥኑ መልኩ እንደአዲስ መዋቀር ይኖርባቸዋል ሁለትም ብሄር ብሄረሰቦች እስከቀበሌ አስተዳደር መዋቅር ድረስ በመረጡት ቋንቋ የመተዳደር መብታቸዉን ለአሃዳዉዉ ኢህአዴግ ህልዉና እና ወጥ የሆነ አሰራር ሲባል መስዋእት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ አንቀጽ 5ም በራሱ በኢህአዴግ ተፈጥሮ ምክንያት ተሰረዘ ማለት ነዉ። ሁለት በሉ።ልብ በሉ የብሄር ብሄረሰቦች የትግል ዉጤቶች አንድ በአንድ እየተሸራረፉ ነዉ። መሸራረፋቸዉ ደግሞ የመገንጠል መብት ጥያቄን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 8/1 እና 3/

 • ሌላዉ የማይታለፈዉ ድንጋጌ በአንቀጽ 8 ንኡስ አንቀፅ 1 እና 3 በቅደም ተከተል የሰፈረዉ ነዉ። ድንጋጌዎቹ እንዲህ ይላሉ፦
 • “የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ስጣን ባለቤቶች ናቸዉ”
 • “ሉአላዊነታቸዉም የሚገለፀዉ በዚህ ህገመንግስት መሰረት በሚመርጧቸዉ ተወካዮቻቸዉና በቀጥታ በሚያደርጉት ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል”

በድርጅታዊ አወቃቀሩ የብሄራዊ ፓርቲዎችን ህልዉና ያላረጋገጠ ወይም እዉቅና ያልሰጠ የፖለቲካ ድርጅት የብሄር ብሄረሰቦችን ሉአላዊ ስልጣን ባለቤትነት ሊያረጋግጥ አይችልም። ብሄር ብሄረሰቦች የሉአላዊ ስልጣን ባለቤት መሆን ካለባቸዉ እነርሱን በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ በቀጥታ የሚወክሉ ተመራጮች መኖር አለባቸዉ። በአንጻሩ ግን እነርሱን የሚወክሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ህልዉ እንዳይሆኑ ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት በአንቀጽ 8 ንኡስ አንቀፅ 3 ስር ብሄር ብሄረሰቦች “…..በሚመርጧቸዉ ተወካዮቻቸዉ…አማካኝነት እንዲወከሉ፤ዲሞክራሲያዊ መብታቸዉ እነዲረጋገጥ በዋናነት ደግሞ በዉክልናቸዉ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑ የማድረግ ተፈጥሮም ዓላማም አይኖረዉም። እንዲህ አይነት አሃዳዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶቹን ለዉድድር የሚያቀርበዉ በብሄራዊ ዉክልና መስፈርት ሳይሆን በየትም ቦታ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲወዳደሩ በማድረግ ነዉ። አሁንም የብሄር ብሄረሰቦች መብቶች መሸራረፍ እንደቀጠሉ ነዉ። የህገመንግስቱ የመሰረት ድንጋይ የሆኑት ድንጋጌዎችም እንደዚሁ ተቀናንሰዉ ወይም ተሻሽለዉ እያለቁ እንደሆነ አስተዉሉ። ሊከተል የሚችለዉንም አደጋ ግምት ዉስጥ አስገቡ። ሰበቡ ይህ ከሆነ አሃዳዊ ኢህአዴግ ተቀባይነት ይኖረዋል? አይመስለኝም! ለህዝብ ሳይበቃ በዉስጥ ግጭት መፈራረሱ አይቀርም።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 39

 • ኢህአዴግ አሃዳዊ ፓርቲ ከሆነ በህገመንግስታችን ላይ የሚከተለዉ መዘዝ እንደቀጠለ ነዉ። አንቀጽ 39ን እንመልከት። የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦችን መብት ይመለከታል። በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 12 እና 3 በቅደም ተከተል፦

“…ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለዉ መብቱ በማንኛዉም [ሁኔታ] ያለገደብ የተጠበቀ ነዉ…”

“….ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ህዝብ በቋንቋዉ የመናገር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋዉን የማሳደግና ባህሉን የመግለፅ የማዳበርና የማስፋፋፋት እንዲሁም ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለዉ...”

“…ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለዉ…….በክልልና በፌዴራል አስተዳደሮች ዉስጥ ሚዛናዊ ዉክልና የማግኘት መብትን ያጠቃልላል” የሚሉ ድንጋጌዎች ሰፍረዋል።

 • የፌዴራሉ መንግስት የቆመዉ ከክልሎች ተቆርሶ በተሰጠዉ ስልጣን ነዉ። የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ስርአት bottom –up አካሄድን የተከተለ ነዉ። ፌዴሬሽኑ እንዲኖር ከተፈለገ የብሄር ብሄረሰቦችን የራስን እድል በራስ የማስተዳደርና ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት የሚያስጠብቅ ህገመንግስታዊ መሰረት እና ትግበራ መኖር አለበት። ይህ በሌለበት ሁኔታ ፌዴሬሽኑ አይኖርም። ምክንያቱም ክልሎቹ ለፌዴራል መንግስቱ ስልጣን አይሰጡትምና ነዉ። ህልዉናቸዉን ለማያስጠብቅ ማእከላዊ አካል የሚሆን በዉክልናም ሆነ በሌላ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተልእኮ ሚና የሚኖራቸዉን ተወካዮቻቸዉን አዋጥተዉ ለመላክ ፈቃደኛ አይሆኑም። ይህ ሊሆን የሚችለዉ ህገመንግስቱን አሻሽሎ አሁን ካለዉ የተለየ የአስተዳደር መዋቅር ማስፈን ሲቻል ነዉ። ቢሆንም ግን በዚህ የሚያበቃ አይደለም። የፌዴሬሽኑ አባላት ህገመንግስቱ በመሸራረፉ በአባልነት አንሳተፍበትም በመሆኑም የመገንጠል መብታችንን ተግባራዊ እናደርጋለን ሊሉ ይችላሉ።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 46

 • ከዚህ በላይ የቀረበዉን አመክንዮ ከህገመንግስቱ ድንጋጌ አንቀፅ 46 ጋር አቆራኝቶ ማየት ተገቢ ነዉ። በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 ስር የፌዴራሉ መንግስት በክልሎች የተዋቀረ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። በቅርቡ የሚካሄደዉን የሲዳማ ህዝብ ህዝበ ዉሳኔ፣በወላይታ፣ በጉራጌ እና በሀዲያና አካባቢዉ ህዝቦች ሲቀነቀን የነበረዉን ጨምሮ በህገመንግስቱ መሰረት የክልሎች ብዛት ሊጨምር የሚችሉበት እድልን ሳንዘነጋ ዘጠኝ ስለመሆናቸዉ ተጠቅሰዋል። ስያሜአቸዉ የትግራይ፣የአፋር፣የአማራ፣የኦሮሚያ ወዘተ በሚል ይገለፃል። ስለዚህ ሲጀመር የክልሎቹ ስያሜዎች የጠቀሷቸዉ ብሄር ብሄረሰቦች መኖር አለባቸዉ። ሲቀጥል የእነዚህ ክልሎች መኖር የብሄር ብሄረሰቦቹን የራስን እድል በራስ ለመወሰን መብት በሚያስጠብቅ አኳኋን ተጠብቀዉ መኖር አለባቸዉ። በሶስተኛ ደረጃ በዉስጣቸዉ ያሉትን ብሄር ብሄረሰቦች ሁለንተናዊ መብቶች የሚያስጠብቅ የፌዴራል መንግስት ፈቅደዉና አምነዉበት ማወቀር አለባቸዉ። ሲጠቃለል ፌዴሬሽኑ እንዲኖርም እንዳይኖርም የመወሰን ሉአላዊ ስልጣን በእጃቸዉ ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ አሃዳዊነት ቅርጽ ያለዉ ኢህአዴግ እነዚህን የክልሎች ስልጣናት ሊያሟላ አይችልም። አሃዳዊ ከሆነ ክልሎች በብሄራዊ ድርጅቶቻቸዉ መሪነት አይተዳደሩም። በግልባጩ የብሄር ብሄረሰቦችን ሉአላዊ ስልጣን የሚያስጠብቅ ፖለቲካዊ ሰብእና እና የአከላለል ስርአት አይኖርም። ይህን ጊዜ ከፌዴራል በመለስ ያሉት የመስተዳድር እርከኖች ስልጣን የሚያገኙት ከፌዴራል መንግስቱ ይሆናል። በመብት ሳይሆን በስጦታ መልክ ይንቆረቆርላቸዋል።

የመሬት ጥያቄ መሬት ላራሹ በሚለዉ ጠባብ ትርጉም ብቻ የሚታይ አይደለም

ኢህአዴግ በብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ላይ ካልተመሰረተ ስልጣን ተቆርሶ አልተሰጠዉም ማለት ነዉ። ይህ ሁኔታ በፌዴሬሽኑ ምስረታ ላይም በቀጥታ ተጽእኖ ይኖረዋል። በኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣን ደረጃም ሆነ በፌዴሬሽን ምስረታ ደረጃ ስልጣን ከታች ወደላይ ሳይሆን ከላይ ወደታች ይሆናል። ኢህአዴግ ይህን ሁሉ የህገመንግስት ድንጋጌ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ካጣ ምን ቀረዉ ሊባል ነዉ? ባዶዉን ቀረ እንጂ! የደርግ ወይም የንጉሳዊ አገዛዝ ስርአቶች ተመልሰዉ መጡ ማለት ነዉ። ከ27 ዓመታት በፊት የነበሩት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጥያቄዎች አገረሸባቸዉ ማለት ነዉ። ከ27 ዓመት በፊት የነበሩት ጥያቄዎች በመሰረቱ ሶስት ናቸዉ። የመሬት ፣ የዲሞክራሲና የብሄር ጥያቄዎች ናቸዉ። በበኩላችን የመሬት ጥያቄ መሬት ላራሹ በሚለዉ ጠባብ ትርጉም ብቻ የሚታይ አይደለም። ምክንያቱም የደርግ መንግስት የመሬት ላራሹን ጥያቄ ለስም ያህል ምላሽ ሰጥቶበታል። ቢሆንም ግን ከመሰረታዊ መብቶች መሰረተሃሳብ አንፃር ሲዳሰስ በተግባር አልተመለሰም። በመጀመሪያ ደረጃ አርሶ አደሩ ያመረተዉ ምርት በሙሉ ነፃነት ተጠቃሚ አልነበረም። በኮታና በተለያዩ ምክንያቶች የምርቱ ነፃ ተጠቃሚ አልነበረም። ማለትም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እና ከእርሱ ዉሳኔ ዉጭ በሆነ ተፅእኖ ምርቱን እንዲሸጥ ከተገደደና ከተወሰደበት የኢኮኖሚ መብት ነፃነቱን ሙሉ ለሙሉ ተነጥቆ ነበር። ዋነኛዉና መሰረታዊ ጭቆናዉ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸዉ ጉዳይ ላይ እራሳቸዉ እንዲወስኑ የሚያስችል ስልጣንም ሆነ መብት አልነበራቸዉም። ይህም ከመሬት ተጠቃሚነት ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ አለዉ። እራሱን በራሱ እና በሚያመቸዉ መንገድ የማስተዳደርና በሚመለከቱት ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን ያልተሰጠዉ ብሄር ብሄረሰብ በሀብቱ የመጠቀምና የመልማት መብቱን ተነፍጓል ማለት ነዉ። ሀብትና የመልማት መብት ሲባል ደግሞ መሬትንና መሬትን ተጠቅሞ የመልማት መብትን ያካትታል። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ መብትና ስልጣን በአሃዳዊዉ እና ለብሄር ብሄረሰቦች ህልዉና እዉቅና ባልሰጠዉ ደርግ ልኡካን እጅ እንጂ በብሄር ብሄረሰቦች እጅ አልነበረም። በመሆኑም የመሬት ላራሹ ጥያቄ ከብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በተለይ ደግሞ የራስን ሀብት ተጠቅሞ ከመልማትና በራስ አስተዳዳሪዎች ከመወሰን መብት አንጻር ሲታይ ምላሽ አላገኘም ነበር። የብሄራዊ ጭቆናዉም ጉዳይ ከዚሁ ጋር ተሳስሮ የሚታይ ነዉ። ስለዚህ ኢህአዴግ የደርግ ስርአተን ገርስሶ ይህን የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን መብት በተግባር የሚያረጋግጠዉን የአከላለል ስርአትና በክልሎች ሉአላዊ ስልጣንነት የተዋቀረዉን ፌዴሬሽን ማስቀጠል ከፈለገ መጀመሪያ በዉስጡ የብሄራዊ ድርጅቶችን ህልዉና ማስቀጠል ይጠበቅበታል። ለዚህ ሀሳብ እንዲያግዘን በኢፌዴሪ ህገመንግስት ደንጋጌዎች ይዘትና ተልእኮ ላይ የተሻለ እዉቀት ያላቸዉን የደ/ር መንበረፀሀይ ታደሰን አጭር ነገር ግን ሰፊ ሀሳብ የያዘ አገላለጽ እንጥቀስ። እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል።

/ር መንበረፀሀይ ታደሰ

“….ለብሄረሰቦች እዉቅና ከሰጠን እና ብሄር ብሄረሰቦች እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ህገመንግስታዊ መብት ከሰጠናቸዉ መልከአምድራዊ ፌዴራሊዝም ቦታ አይኖረዉም…ምክንያቱም እያንዳንዱ ብሄር ማንነቴ፣ ታሪኬ ፣ ቋንቋዬ [መከበር አለበት] ብሎ የሚያስብ ህብረተሰብ ራሱን የሚያስተዳድርበት የመንግስት አወቃቀር መፍጠር [ያስፈልገዋ

] ህገመንግስቱ ያደረገዉ ይህንን ነዉ…...”

የአሃዳዊ ኢህአዴግ ተፈጥሮ ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ደ/ር መንበረፀሀይ የገለጹትን አይነት የመንግስት አወቃቀር እንዲኖር ላያስገድድ ይችላል። በዚህ ህገመንግስታዊ መርህ ካልተገደደ ደግሞ በአጠቃላይ ለህገመንግስቱ ህልዉና እንደዚሁም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በህገመንግስቱ የተጎናጸፏቸዉን መብቶች እንዳይሸራረፉ ለ27 ዓመታት ዘብ የቆመዉ ኢህአዴግ አስተሳሰብ ተቸንፏል። ከተቸነፈ ደግሞ ለብሄር ብሄረሰቦች መብትና ማንነት መቸነፍና መጥፋት የሚሰራ የፖለቲካ ድርጅት ሆኗል። ይህ ከሆነ ዘንዳ ብሄር ብሄረሰቦች አሃዳዊ ኢህአዴግን በምርጫ ካርድ አይቀምሱትም። ብሄርን መሰረት አድርገዉ ለፖለቲካ ዉድድር የቀረቡ ድርጅቶችን ይመርጣሉ። መልካም አጋጣሚ ነዉ! ቀድሞ ዉሽማ/ዉሽሚት የነበሩት ባል/ሚስት ስለሚሆኑ ፊዚካል ሜሬጅ ያበቃለታል! ሁሉም የልብ ፍቅረኛዉን ያገኛል!!!!

“……መንግስት ለመመስረት አብላጫ ድምፅ ለማግኘት ሲባል ቀደም ሲል በገዥ ፓርቲነትና በተቃዋሚነት የነበሩ የብሄር አደረጃጀት ፓርቲዎች ሳይቀሩ ወዳጅነት እና ቅንጅት እንዲፈጥሩ መልካም አጋጣሚ ይሆናል። ይህም የፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን እና የብሄር ብሄረሰቦችን መብትና ጥቅም በአግባቡ የሚያስጠብቅ እዉነተኛ ፌዴራሊዝምና እርቅ እንዲኖር ሲሰብኩ የነበሩትን ፍላጎት እዉን ያደርገዋል። በኢህአዴግ ዉስጥና ከኢህአዴግ ዉጭ በነበሩት የብሄር ፓርቲዎች መካከል የነበረዉ ያለመግባባት ቁስል እዉነተኛ ፈዉስ አግኝቶ እስከወዲያኛዉ ይድናል! በተቃራኒዉ ደግሞ ከልብ አምነዉበት ሳይሆን ስልጣን ለመያዝ ሲሉ ኢህአዴግን በግንባርነት በመመስረት ብሄርን መሰረት ላደረጉ ፓርቲዎች የጎን ዉጋት ሆነዉ የነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች በኢህአዴግ አሀዳዊነት ምክንያት ፍቺ በመመስረት ከቀድሞ አሀዳዊ ተቃዋሚዎቻቸዉ (የልብ ወዳጆቻቸዉ ከነበሩት) ጋር ዉህደት ስለሚመሰርቱ በተመሳሳይ ፓርቲዎች መካከል የነበረን ጥላቻ በማስወገድ ከእዉነተኛ ማንነታቸዉ ጋር ያገናኛቸዋል። ሁሉም አይነት የፖለቲካ አደረጃጀቶች እዉነተኛ ፍቅረኛቸዉን ስለሚያገኙ አንዱ በሌላዉ ዉስጥ ሆኖ ትዳር ለማፍረስና ከሚስት ወይንም ባል ይልቅ ለዉሽሚት ወይንም ዉሽማ ጋር የነበራቸዉን ታማኝነትና የብልግና ስራ ከመስራት የሚቆጠቡበት ትክክለኛ የፖለቲካ አሰላለፍ ይፈጠራል። ይህም በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ሀገራት በዓመታት ሂደት ለሀገሪቷ የማይበጅን የህገመንግስታዊና አስተዳደራዊ ስርአት አስተሳሰብ አራማጅ ፓርቲዎችን በማክሰም ለብሄር ብሄረሰቦች ህልዉና እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን ሲባል ሊኖሩ የሚገባቸዉን አዉራ ፓርቲዎች የመሪነት ሚና በማያወላዳ ሁኔታ ያረጋግጣል…”። ስለሆነም አሁን ያለዉ የኢህአዴግ መበጥበጥና መለያየት በበኩሌ በመልካም አጋጣሚነት እንጂ በመጥፎ አጋጣሚነት አይወሰድም። ሁሉም አዉነተኛ ፍቅረኛዉን ስለሚያገኝ የጣልቃ ገብነት ፖለቲካ ያከትምለታል። የተከበሩ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ሌሎች “….የእኛ ችግር ኢህአዴግ በዉስጣችን እየገባ ተለጣፊ ስለሚያበጅልን ነዉ …በማለት ይወቅሱ የነበረዉ ጉዳይ ያከትምለታል። ምክንየቱም በአሰላለፍ መስፈርት ሲመዘን አሁን ካለዉ ኢህአዴግ ዉስጥ በእርግጥም ለእርሳቸዉ ፓርቲ እዉነተኛ ወዳጅ የነበረዉን ስለሚያገኙ ሁሉም ከእዉነተኛ ወዳጁ ጋር ይገናኛል። ወዳጅን በአግባቡ የለየ እዉነተኛ እርቅ ማለት ደግሞ ይኸዉ ነዉ። የጣልቃ ገብነት ፖለቲካ ያበቃለታል!!! ሁላችሁም ወገኖች እንኳን ደስ አላችሁ። ቀድሞ ዉሽማ የነበሩት ከእንግዲህ ባል ወይንም ሚስት ስለሚሆኑ ሁሉም ከትክክለኛና እዉነተኛ ፍቅረኛዉ ጋር መኖር ይጀምራል!!!!”

የሙሉ ጊዜ ስራቸዉ በሆነዉ ምሁራን በሴናሪዮዉ ላይ ጠለቅ ያለ ትንታኔ የሚሰጥበት ቢሆንም የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሂደት ጉዳይ በአንፃሩ ለአደጋ ይጋለጣል። አሀዳዊያን ይሳካላቸዋል የሚል እምነት ባይኖረኝም ሁሉም የዉጭና የዉስጥ አሀዳዊያን ሀይሎች መዋሃዳቸዉ አይቀርም። እነዚህ ሀይሎች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ደ/ር አብይን እየጠበቁ ያሉት የህገመንግስታዊና ፌዴራላዊ ስርአት አስቸጋሪ ጠበቃና ዘበኛ የነበረዉን ኢህአዴግን እስኪያፈርሱላቸዉ ድረስ ብቻ ነዉ። ከዚያ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ ከአሀዳዊያን ሀይሎች ጋር መጋጨታቸዉ ስለማይቀር አይፈለጉም። የኤርትራ ነፃ አገርነትን በመቀበል ረገድ እስከአሁንም ያልተዋጠላቸዉ አሀዳዊያን ሀይሎች የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመደመር ፍልስፍና ጥለነዉ ወደመጣነዉ በሀይል ላይ የተመሰረተ መደመር ፍልስፍና በመለወጥ የኤርትራንም ጉዳይ ጥያቄ ዉስጥ ማስገባታቸዉ አይቀርም። በኢህአዴግ ዉስጥ ያሉትንም ይጨምራል። ተሳክቶላቸዉ የመንግስትነት ስልጣን ቢይዙ በዉስጣቸዉ የደበቁትን ኤርትራን ህልዉና የመፈታተን ጉዳይ ለጠረጴዛ ድርድር የማቅረባቸዉ ጉዳይ ሳይታለም የተፈታ ነዉ። ይቅርታ ይደረግልኝና የሰብአዊነት ተልእኮ እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ታሪካዊ ጠላቶች እና የሀገሪቷ ታሪካዊና ተጨባጭ ሁኔታ በቅጡ ያልገባቸዉ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሀዳዊ ፓርቲነት ምስረታ ማግስት መሸኘታቸዉ አይቀርም። ተቀባዩ ደግሞ ክቡር ዶ/ር አብይ የጀመሩትን የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ሂደት የሚቀለብስ አስተሳሰብ የተሸከመ ሀይል እንደሚሆን ምንም አያጠራጥርም። ኤርትራን የሚፈታተኑ ሀይሎች የተፅእኖ ፈጣሪነት ሚና ይኖራቸዋል። እነዚህ ሀይሎች ለምሳሌ አሰብንና መሰል የኢትዮጵያ ጥቅም የሚሏቸዉን ታሪካዊ ጥያቄዎች ካላገኙ ከኤርትራ ጋር የሚኖረዉን ጉዳይ በሀይል ወደመፍታት መሸጋገራቸዉ አይቀርም። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ አሀዳዊያን ሀይሎች እና በኤርትራ መካከል የሚፈጠረዉ ፍጥጫ በኢትዮጵያ የራስን እድል በራስ ለመወሰን መብት የሚታገሉት ብሄራዊ አደረጃጀቶች መካከል ግጭት ይፈጠራል። የኤርትራን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የሚፈታተን ዉስጣዊ ሀይል ለሀገር ዉስጦቹ ብሄርተኛ ፓርቲዎች ጤናማ ሁኔታን ስለማይፈጥር ከዉስጥ ትብብር ይልቅ ወደዉጭ መመልከትን ሊያስከትል ይችላል። ታሪክ ተደገመ ማለት ነዉ። ከደርግ ዉድቀት በፊት የዉስጥ ሀይሎች የዉስጥ ችግራቸዉን ለማስወገድ ከዉጫዊ ሀይሎች ጋር መተባበር የጀመሩበት መሰረታዊ ምክንያት ይኸዉ ነበር። የአሁኑ ግን ምናልባትም የዉስጥ አሀዳዊያን ፓርቲዎችን በማስወገድ የምንገላገለዉ አይሆንም። ከእንግዲህ ኢትዮጵያ አታስፈልገኝም የሚሉ ሀይሎች በሰሜን፣ በምእራብም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች እየጎለበቱ ስለሚመጡ የዋሁ ፖለቲከኛ ደ/ር አብይ የሚመኟት “ታላቋ ኢትዮጵያ” በመገንጠል ጥያቄዎች ጭምር ወደብዙ ትናንሾች ተመንዝራ እርማቸዉን ያወጣሉ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ቅን እሳቤ እንጂ የኢትዮጵያን ታሪካዊ አመጣጥ ያገናዘቡ ፖለቲከኛ አልመሰሉኝም። የብሄር ብሄረሰቦች ታሪካዊ ጠላቶች እስኪያሽቀነጥሯቸዉ ድረስ በየዋህነት ብቻ እየተጓዙ ያሉ ለሰብአዊነት ብቻ የሚመጥኑ ፖለቲከኛ ናቸዉ። ሌሎቹ አድፍጠዉ እየጠበቋቸዉ እንደሆነ የተገነዘቡ አልመሰለኝም- የኢትዮ- ኤርትራ ጉዳይንም ጨምሮ ማለቴ ነዉ!

በዚህ ጽሁፍ የተለያየ ክፍል ዉስጥ እንደተጠቀሰዉ አሀዳዊ ፖለቲካ አወቃቀር ያለዉ የፖለቲካ ድርጅት በአንቀጽ 46 ስር “ክልሎች የሚዋቀሩት በህዝብ አሰፋፈር፣ በቋንቋ ፣ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ…” ከሚለዉ ድንጋጌ ጋር ሊጣጣም አይችልም።በራሱ የፖለቲካ ድርጅት ዉስጥ ብሄር ብሄረሰቦችን መሰረተ ያደረገ የዉክልና ስርአት የማያስተናግድ የፖለቲካ ድርጅት በብሄር ብሄረሰብ አሰፋፈር ላይ የተመሰረተ የአከላለል ስርአት እንዲኖር በቅድመሁኔታነት የሚያስቀምጥ የፖለቲካ ርእዮተዓለም እንዲኖረዉ አይገደድም። የፖለቲካ ድርጅቱ የሚመሰረተዉ በሀገራችን በሊብራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ በግለሰብ መብት ላይ ብቻ ተመስርተዉ እንደተዋቀሩት የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ነዉ። የድርጅቱ አባል ለመሆን መስፈርቱ ግለሰብ መሆን እንጂ የብሄር ማህበራዊ መሰረት አይሆንም። ፓርቲዉ የሚዋቀረዉ በዚህ አስተሳሰብ ከሆነ የአከላለል ስርአቱም የእነዚህን ግለሰቦች ፖለቲካዊ መብት በየትም ቦታ ማስተናገድ የሚችል እንዲሆን ይጠበቃል። ይህ እንዲሟላ ደግሞ የቋንቋ ጉዳይ በማእከላዊዉ ፖለቲካ ድርጅት እና መንግስት እንጂ በብሄራዊ ፖለቲካ ድርጅት ወይም ከፌዴራል መንግስት በመለስ ባለ አስተዳደራዊ አካል የሚወሰንበት ስርአት የመኖሩ ጉዳይ እጅግ የጠበበ ነዉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ብሄር ብሄረሰቦች ማንነታቸዉን መሰረት አድርገዉ የመወሰን መብታቸዉ የጠበበ ይሆናል። ምክንያቱም የሚዋቀሩት አስተዳደራዊ ክልሎች በተማከለ የፖለቲካና የአሰተዳደር አስተሳሰብ ላይ ስለሚመሰረቱ ገዥዉ ጉዳይ የነባሩ ብሄረሰብ(indigenous) ማንነት፣ቋንቋ ወዘተ መብት ሳይሆን የግለሰብ መብት ጉዳይ ነዉ። በህገመንግስታችን ልዩ ትኩረት የተሠጠዉ የቡድን መብት በተማከለዉ አስተሳሰብ እና አሃዳዊ ስርአተመንግስት አስተሳሰብ ተጽእኖ ምክንያት ቦታ አይኖረዉም። ስለዚህ አንቀጽ 46 በተግባር የማይተረጎም ከሆነ ህልዉናዉ አደጋ ላይ ይወድቃል።

አሀዳዊነትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 47

የፌዴራል መንግስት አባላትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ያካተተዉ የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 47 ንኡስ አንቀጽ ሁለት በንኡስ አንቀፅ አንድ በተመለከቱት ዘጠኝ ክልሎችም ሁኑ ለወደፊቱ በሚጨመሩ ሌሎች ክልሎች ዉስጥ የተካተቱት ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በማንኛዉም ጊዜ የራሳቸዉን ክልል የማቋቋም መብት እንዳላቸዉ ያስረዳል። አሁን ያሉት ክልሎች የተመሰረቱት ይህን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ነዉ። በተመሳሳይ ሁኔታም በእያንዳንዱ ክልል ዉስጥ ያሉት ብሄሮች የራሳቸዉን እድል በራስ የመወሰን መብታቸዉን ተጠቅመዉ አካባቢያቸዉን የማስተዳደር፣ በመረጡት ቋንቋ የመጠቀም፤በመረጡት የአካባቢዉ ነዋሪ ተመራጭ መተዳደር፤ አስፈላጊ ነዉ ብለዉ ባመኑ ጊዜም ህገመንግስታዊ ስርአቱ በሚፈቅደዉ መሰረት የራሳቸዉን አካባቢያዊ ክልል የማቋቋም መብታቸዉ የተጠበቀ ነዉ። ከቅርብ ጊዜ ዲህ በተከበረዉ የሲዳማና ሌሎች ህዝቦች እየቀረበ ያለዉ ጥያቄም ይህን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ መሰረት ያደረገ ነዉ። በአንድ በኩል ነባሩንና እነዚህን መብቶች ለማስጠበቅ የታገለዉን የብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ፍጥረት የሆነዉን በሌላ በኩል ደግሞ የብሄራዊ ድርጅቶችን ህልዉና ያጠፋ አሀዳዊ ኢህአዴግን ከዚህ ድንጋጌ ጋር አስተሳስሮ ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል። አሃዳዊ የኢህአዴግ ፓርቲ ለብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና እዉቅና አይሰጥም። ለብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና እዉቅና የማይሰጥ የፖለቲካ ድርጅት በክልሎች ዉስጥ የሚኖሩ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸዉ ጉዳይ ላይ ሉአላዊ ስልጣን እንዲኖራቸዉ የማድረግ ድርጅታዊ ተፈጥሮ፤ተልእኮና የአባልነት መሰረት አይኖረዉም። የአባልነት መሰረቱ የግለሰብ መብት እንጂ ብሄራዊ ማንነት የወለዳቸዉ ብሄራዊ ድርጅቶች አይደሉም። ስለዚህም በአስተዳደራዊ መዋቅርና በህዝቦች ሉአላዊ ስልጣን ላይ የሚኖረዉ ጽንሰሀሳብ ብሄር ብሄረሰቦችን ሳይሆን ግለሰብን ብቻ ማእከል ያደረገ የአሀዳዊ ስርአተ መንግስት አስተሳሰብ ነዉ። ስለሆነም የአንቀጽ 47 ድንጋጌዎች ህልዉና በአሃዳዊዉ ኢህአዴግ ጥያቄ ዉስጥ መዉደቃቸዉ አይቀርም። ይህንን የብሄሮች፤ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት በአስተማማኝ ሁኔታ የማያስጠብቅ ፖለቲካ ድርጅት ወይም አስተሳሰብ ደግሞ ከማጥፋቱ በፊት መጥፋቱ አይቀርም። ይገባዋልም። የነባሩ ኢህአዴግ ተልእኮ ግን በብሄር ብሄረሰቦች ሉአላዊ ስልጣን ህልዉና ላይ የተመሰረቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ድምር ዉጤት የሆነዉን ዓላማ ማሳካት ነዉ። ብሄራዊ ድርጅቶቹ በቅድሚያ የሚወክሉትም በሚወክላቸዉ ክልልሎች ያሉትን ብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች ሉአላዊ ስልጣን ነዉ። ይህን ወደጎን የተወ ሀገራዊ ተልእኮና የፖለቲካ አወቃቀር የጋራ ጥቅምንና የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን ሉአላዊ ስልጣን ስለማያስጠብቅ ለአንቀጽ 47 ህልዉና እና ተግባራዊነት ይታገሉለታል። ስለዚህም አንቀጽ 47ም እንዲኖር እና በዉስጡ የያዛቸዉ ተልእኮዎች ተግባራዊነት እንዲቀጥሉ ከተፈለገ በብሄራዊ ድርጅቶች ህልዉና ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ስልጣን መያዝ የግድ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን።

ከአንድ አንበሳ ጋር የተደረገን ጥያቄና መልስ ተምሳሌታዊ መልእክት እንመልከት

ጥያቄ- “ስማ እንጂ አንበሳ ከትግራይነትህና ከአነበሳነትህ አንዱን ምረጥ ተብለህ ብትጠየቅ የቱን ትመርጣለህ

መልስጥያቄአችሁ የሚመለሰዉ በጥያቄ ነዉ። አንበሳነቴ ነዉ ትግራይ እንደሆን ያደረገኝ ወይስ ትግራይነቴ ነዉ አንበሳ እንድሆን ያደረገኝ

“ግንባር ወይስ አሃዳዊ ፓርቲየሚል ጥያቄ ይዘን የቀረብነዉም በዚህ አስተሳሰብ ነዉ። በዚህች አገር ረጅም ዓመታትና ስፍር ቁጥር የሌላቸዉን የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን መስዋእት ያደረገዉ ትግል አንዱ ምክንያት “ ….አንተነትህ አንተነትህን ሳይሆን እኔነቴን ብቻ እያሰተጋባና ስለኔ ህልዉና ብቻ እየገለጸ ሊኖር ይገባል….ያንተ ማንነት እራስህን ሳይሆን እኔን ብቻ ዲፋይን እያደረገ ሊኖር ይገባል። ይህ እንዲሆን ደግሞ ታሪክህ፤ቋንቋህ፤ባህልህና ማህበራዊ መሰረትህ በአጠቃላይም ይህን ሁለንተናዊ መብትህን የሚያስጠብቅ ሉአላዊ ስልጣን ሊኖርህ አይገባም …የሚለዉን አስተሳሰብ በመገርሰስ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር የሆነች አዲስ ኢትዮጵያን ለመመስረት ነዉ። ስለዚህም በኢትዮጵያዊነታችን የምንኮራዉና በፍቅር የምንኖረዉ ትግራይ፣ኦሮሞ፣ወላይታ፣አማራ፣ሱማሌ፣ጋምቤላ ወዘተ የመሆናችንን ተፈጥሮአዊ መብታችንን የምታስጠብቅልን ኢትዮጵያ እና ስርአተ መንግስት ሲኖር ብቻ ነዉ። ፍርጥርጥ አድርጎ መነጋገር የማይወዱ እንዳሉ ብንገነዘብም በትግሉ ወቅት የተነገረን አንድ አባባል እንጠቀም። አንድ ታዋቂ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለ የህወሓት ታጋይ በትግሉ ወቅት ከኢትዮጵያ ዉጭ ሆኖ(ካልተሳሳትኩ ለንደን የነበረ መሰለኝ) ባደረገዉ ክርክር “…ለትግራይ ህዝብ ያልሆነች ኢትዮጵያ ትበጣጠስ…” ያለዉን ልብ ይሏል። እዉቁ ታጋይ ይህን ያለዉ እየታገለላት በነበረዉ ኢትዮጵያና ብሄር ብሄረሰቦቿ ላይ ክፉ ምኞትና ተልእኮ ስለነበረዉ አይደለም። ኢትዮጵያ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ብቻ መኖር አለባት ለማለት ፈልጎም አልነበረም።ለብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ህይወቱን ለመስጠት የወሰነ ታጋይ ስለትግራይና ስለህዝቧ ጥቅም ብቻ ያስባል የሚል ካለ እርሱ የፖለቲካ እዉቀት የሌለዉ ነዉ። የህወሓትና የአጋሮቹ የትግል ዉጤት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ እዉን እንዲሆን ያደረገዉም የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነትና የጋራ ተጠቃሚነት ነዉ። ስለሆነም በወቅቱ ይህን አባባል መሰረት አድርጎ የቀረበዉ ትችት ፍጹም ስህተትና በተግባር የተረጋገጠዉን የህወሓትን የትግል ዓላማ በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነበር። የአባባሉ መልእክት “…ሁላችንም በእኩልነት የማንታይባት ኢትዮጵያ ሰላም አይኖራትም። የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት እኩል እዉቅና እና መብት ያልተጠበቀባት ኢትዮጵያ ይህን መብት ለማስጠበቅ ሲባል ከሚደረግ ጦርነት ያለፈ ታሪክ አይኖራትም።…..….።ስለዚህ ኢትዮጵያን እንድንወዳትና እንድናፈቅራት ከተፈለገ የፖለቲካ ስርአቷ የእያንዳችንን ህልዉና ሊወድና ሊያፈቅር ይገባል…ከሚል መሰረታዊ ጭብጥ የመነጨ ነዉ። ስለዚህም ትግራይ እንድሆን ያደረገኝ አንበሳነቴ(ኢትዮጵያዊነቴ) አይደለም። ትግራይነቴ ስለተከበረልኝ ነዉ አንበሳነቴን(ኢትዮጵያዊነቴን) እንድወድ ያደረገኝ። መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዉስጥ የተገኘሁት ትግራይ ከሚባል ህብረተሰብ እና ወላጆች ተፈጥሬ ነዉ። ምንጬ እና ታሪኬ ባልተጠበቀበት ሁኔታ በሌሎች ምንጭና ታሪክ ልኮራም ልደሰትም አልችልም። ኢትዮጵያዊነቴ የሚያኮራኝ በሌሎች ታሪክና ማንነት ጥገኛ ሆኜ ሳይሆን በራሴ ማንነት ላይ ተመስርቼ ነዉ። ይህን አመክንዮ በመንተራስም ኢህአዴግ እንድንሆን ያደረገኝን የትግራይ ብሄር ብሄረሰቦችን ማንነት የሚያስጠብቀዉ የህወሓት መኖር ነዉ። ኢህአዴግ እንድንሆን የሚያደርገን ህወሓትነታችን ነዉ። መጀመሪያ ኢህአዴግ ከሆንን ህወሓት የሚባል የፖለቲካ ድርጅት አይኖርም። ህወሓት በሌለበት ሁኔታ ደግሞ የትግል ዉጤት እና ለብሄር ብሄረሰቦች መብቶች መከበር የመሰረት ድንጋይ የሆኑት የኢፌዴሪ ህገመንግስት ድንጋጌዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል ማለት ነዉ። ይህ አመክንዮም ለሌሎቹ ብሄራዊ ድርጅቶች ይሰራል። ስለዚህ መጀመሪያ ኢህአዴግ የመሆናችን ጉዳይ ትግራይነታችንን ጥያቄ ዉስጥ ያስገባዋል። ስለሆነም ኢህአዴግ እንድንሆን ከተፈለገ ህወሓት የመሆን መብታች ይጠበቅልን። መነሻዉ ከሌለ መድረሻዉ አይኖርም። በዚህ አስተሳሰብ ለመታገል የሚፈራ ካለ ለሁላችንም መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! በአሰላለፍ ስህተት ምክንያት በተቃራኒዉ ጎራ የነበሩና ሚስት ወይንም ባል መሆን ሲገባቸዉ ዉሽማ ሆነዉ ከቆዩት ጋር በእዉነተኛ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ጋብቻ መስርተን በኢትዮጵያ ዉስጥ እዉነተኛ የልዩነት ፖለቲካ እናራምድ!

የብሄር አደረጃጀትና የኢፌዴሪ ህገመንግስት መግቢያ

“….እኛ የኢትዮጵ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች…

ከኢፌዴሪ ህገመንግስት አንፃር “….እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች…ማለት፦

 • ሉኣላዊ ስልጣን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ነዉ ማለት ነዉ፤
 • ህገመንግስታችን እንደግለሰብ መብት ሁሉ ለቡድን እና ለብሄሮች መብትም እኩል እዉቅና ሰጥቷል ማለት ነዉ፤
 • አሃዳዊ የመንግስት አወቃቀር እና በግለሰብ መብት ላይ ብቻ መሰረት ያደረገ ህገመንግስትና የፖለቲካ አስተሳሰብ ለብሄሮች እና ለቡድኖች የማይሰጣቸዉን መብቶች በአንፃሩ ያጎናፀፈ መሆኑን የሚያስረዳ መሪ ቃል ነዉ፤
 • በጥቅሉ ብሄር ብሄረሰቦች ህልዉናቸዉ የታወጀበት እና ይህን ህልዉና ሊፈታተን የሚችል ፖለቲካዊ፣ ህገመንግስታዊና አስተዳደራዊ ስርአትና አወቃቀር ቦታ የሌለዉ መሆኑን ከወዲሁ የሚያስገነዝብ ነዉ።

እነዚህ ጽንሰሃሳቦች ሲረጋገጡ ሌሎቹ በዚህ ህገመንግስት መግቢያ ላይ የተካከቱት መሰረታዊ ጉዳዮች ይከተላሉ። የብሄር ብሄረሰቦች መብትና ህልዉና ሲረጋገጥ፦

 • በጋራና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት እየተጠናከረ ይሄዳል፤
 • የመብት ረገጣ ጥያቄዎች እንደ ቡድን ወይም እንደ ብሄር ወይም ብሄረሰብ ጥያቄ የሚቀርብባቸዉ ጉዳዮች አይሆኑም። ስለማይሆኑም በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለዉ ዲሞክራሲ እየተጠናከረ ይሄዳል፤
 • ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለዉ ዲሞክራሲ የተጎናፀፈች ኢትዮጵያን ማረጋገጥ ከቻልን ታሪካችን ማንነትንና ሌሎች መብቶችን ለማረጋገጥ ሲባል በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ሳቢያ የኋሊት የምንሄድበት ሳይሆን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታችን የሚፋጠንበት ታሪክ ይሆናል፤
 • የመልማት መብታችንን እና በየአካባቢያችን ያለዉን ሀብት ተጠቅመን በሁሉም አካባቢዎች ተመጣጣኝ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ማለት ነዉ፤
 • እነዚህና ሌሎች የብሄር ብሄረሰቦች መሰረታዊ መብቶች የተረጋገጡባት ኢትዮጵያ ስትፈጠር በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ይገነባል፤
 • ይህን የሚያሰፍነዉ ደግሞ በብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ላይ የተመሰረተ ህገምንግስታዊና አስተዳደራዊ ስርአት ለማስፈን የማያስችልን በአሃዳዊ አወቃቀር እና በግለሰብ መብት ቅኝት(ብቻ) የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን በብሄራዊ የፖለቲካ ድርጅትች ህልዉና እና ምሰሶ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ነዉ
 • ስለዚህም “….እኛ የኢትዮጵ ብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች…በኩራት፣በመፈቃቀድና በፍቅር ላይ ተመስርተን በአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ የምንመሰርተዉ ህልዉናችንን የሚያረጋግጥልን ህገመንግስታዊ፣ርእዮተዓለማዊ እና አስተዳደራዊ የፖለቲካ አስተሳሰብና አደረጃጀት ያለዉ ፓርቲ ሲመራን ነዉ። እንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ ማለት ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦች በህገመንግስቱ የተደነገጉላቸዉ ሁለንተናዊ መብቶችና ነፃነጾች በእኩልነት መረጋገጡ ሲረጋገጥ ነዉ። ምክንያቱም ይህ መብት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ መንገዳችን ወደአብሮነት ሳይሆነ ወደመለያየት እንዲያመራ ግድ የሚሉ ጭቆናዎች ስለሚከተሉ ነዉ

እናስ? እናማ አሃዳዊ ኢህአዴግን ማሰብ የብሄር ብሄረሰቦች የትግል ዉጤት በሆነዉ በአሁኑ ኢህአዴግ መቃብር ሳቢያ ሊከሰት የሚችለዉን የመጪዉ ዘመን የቀዉስ ታሪክ ለመስተናገድ የቆረጥን እለት ነዉ። ዳግም በኢትዮጵያ ምድር ይህን ታሪክ ሊያስከትል የሚችል የፖለቲካ ድርጅት እንኳንስ አባል

ንሆንለት እንዲያስተዳድረንም ድምጽ መስጠት የለብንም። ሰላም!

 

Back to Front Page