Back to Front Page

የኢትዮጵያ ወጣቶች በተሰራ ቤት መግባት ሳይሆን ቤት መሰራት መቻል ይኖርባቸዋል።

ኢትዮጵያ ወጣቶች በተሰራ ቤት መግባት ሳይሆን ቤት መሰራት መቻል ይኖርባቸዋል።

በልኡል ገብረመድህን (ከአሜሪካ)

14 መጋቢት 2011..

የብሔር ጥላቻ መዘዙ ብዙ ነው።ከጎረቤት ወንድም የሩዋንዳ ህዝብ አሰቃቂ የሰው እልቂት ጥፋት መማር ካልተቻለ ከምን መማ ርእንደሚገባን መገመት ያዳግታል።ጥላቻ በወቅቱ ካልተፈወሰ መርዝ ነው።የጥላቻ ግጭትና እልቂት ለትውልድ የሚተርፍ በመሆኑ ጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት አለበት ። ዜጋ ዜጋውን ለምን ያፈናቅላል ? ። ለምን የህዝብ ጥላቻ ሥር ሰደደ ?። ሰው የብሔር ሐረጉ አፈር መሆኑ የተገነዘብነው አይመስልም ። በኢትዮጵያ እየታየ ያለ የጎሳ አክራሪነት /Tribal Nationalism / ጠቀሜታው በጥናትና ምርምር የተደገፈ ባለመሆኑ የሚያስከትለው ማህበራዊ ግጭት በአጭሩ መገመት አይቻልም ። ኢትዮጵያ በአለም ህዝብ በትልቁ የምትታወቀው በድህነት ነው ። ድህነት ማሸነፍ ያልተቻለው በዋናነት የአስተሳሰብ ድህነት ከሰው ሰራሽ ድህነት በልጦ በመገኘቱ ነው ። በኢትዮጵያ ስፋትና ጥልቀት ያላቸው የአስተሳሰብ ማህበራዊ ችግሮች አሉ ።የድህነት የመጀመሪያ መነሻ ችግር ራሱ ድህነት አይደለም ። ሰው ሲፈጠር ድሀ ሆኖ አልተፈጠረም ።ሆኖም ሰው በሒደት የአመለካከትና አሰተሳሰብ ምጥቀት ድክመት ማሳየቱ አንዱ ከሌላው የምርትና አማራች ተጠቃሚነት ላይ ልዩነት እየሰፋ መጥተዋል ። የአስተሳሰብ ችግር ፊደልካነበቡ፣ ቁጥር ከደረደሩ ሰዎች በስፋት ሲታይ ከባድ ሐዘን ነው ። ዘረኝነት እና አክራሪነት የለውጥ ማነቆ እንጂ የብልፅግና መሰረት አይሆንም ። ዘረኝነት ሆነ አክራሪነት አገር ያከስማል ፣ ህዝብ ያልተፈለገ ማህበራዊ ግጭት ውስጥ ያስገባል ፣ ድህነት ፣ መፈናቀልና ስደት ይስፋፋል ።

Videos From Around The World

የአዲስ አበባ ጉዳይ የአንድ ወገን ተቃርኖ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ ቦታ ነው ። በኢትዮጵያ የኦሮሞ ህዝብ እንጂ የኦሮሞ ግዛት የሚባል ቦታ የለም ። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የፌደራል አወቃቀር ይፈቅዳል ። ይህ ሲባል ለአስተዳደር ያመች ዘንድ እንጂ ለግዞት ክፍፍል አይደለም ። የኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንደሚገባው የህግ ድጋፍ ቢኖረውም ልዩ ጥቅም የሚል አገላለጽ በዝርዝር የቀረበ አይደለም ። የሆነ ሆኖ የኦሮሞ አክራሪ ዘረኞች የሚያስተጋቡት ሰረወ ሓሳብ ወንዝ አያሻግርም ። በሚያራምዱት ሓሳብ የቅድሚያ ቅድሚያ ተጠቂዎች ያው ዘረኞች መሆናቸው የማይቀር ሐቅ ነው ። በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች የኑሮ ዘይቤያቸው ኦሮሞ መሆን ይኖርባቸዋል ሲሉ ፅንፍ የረገጡ የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኞች በተደጋጋሚ ይናገራሉ ። የኦሮምኛ ቋንቋ ማወቅ ጠቃሚ እንጂ ጉዳት የለውም ። ሁለም ቋንቋ መገልገያ እስከሆኑ ማወቁ ከማንም በላይ ለአዋቂው ይጠቅማል ። ሆኖም መከናወን ያለበት በፍቅርና በአብሮነት መንፈስ እንጂ በሐይልና አግላይነት መሆን አደጋ አለው ። በአንድ ውቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩ አንዲሁም በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ እስርቤት የረገጡ አቶ በቀል ገርባ በምን የትምህርት ዘርፍ ያሰተምሩ እንደነበሩ ባላውቅም አሁን አሁን ከሚሰጡት ውዳቂ ሓሳብ ተነስቼ መምህር በነበሩበት ጊዜ ምን አይነት ዜጋ ያፈሩ እንደነበር ለማወቅ የሚያዳግት አይሆንም ። በኦሮሚያ ክልል የሚኖር ህዝብ የኦሮምኛ ቋንቋ ሳይወድ በግድ ማወቅ አለበት አለዚያም በአስተርጓሚ ይኑር የሚል ፍትሀዊ ያልሆነ ሓሳብ በተደጋጋሚ ከአቶ በቀለ ገርባ ስሰማ እጅጉን አዘንኩኝ ። የኦሮሞ ህዝብ ሰብዓዊ ርህሬሔ እንዲሁም ሰብዓዊ መብት መከበር እና ማስከበር የሚያውቀው በአንቀጽ ሳይሆን በልቦናው ነው ። በኦሮሚያ ክልል ሆነ በአዲስ አበባ የመገበያያ ቋንቋ ኦሮምኞ መሆን አለበት የሚል የዘረኝነት ባህሪ መቆም አለበት ። በበኩሌ ሁለተኛ የኢትዮጵያ ቋንቋ ኦሮምኞ ቢሆን የሚያስጨንቀኝ አይሆንም ። ይህ ሲሆን ግን እንደ አቶ በቀለ ገርባ የወረደ አሰተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ከሆነ አይደለም ተጨማሪ ቋንቋ ሊሆን ቀርቶ የኦሮሞ ህዝብ ራሱ ኦሮምኞ ባይናገር ደስታዬ ነው ። ወንድሜ አቶ በቀለ ገርባ በመረጃ ልሞግተው፦ አቶ በቀለ ገርባ እንዲህ ይላሉ ፦ በኦሮሚያ እንዲሁም በፍንፍኔ ቦታዎች የመግባቢያ ቋንቋ በኦሮምኛ መሆን አለበት ። ግዢ ስትፈፅም ሜቃ ብለህ ጠይቅ ። ሜቃን ካልገባው ግብይት አትፈፅም። ነጋቲ ቡላ (ደህና ሰንብት ብለህ ሒድ) ። በሌላ ጊዜደግመህ ሜቃን ሰትጨይቀው ካላወቀ በሌላ ጊዜ ዳግም እንዳትሄድ ። ይህ የሐሳብ ልውውጥ የኦሮሞ ማህበረሰብ ባልሆ በንግድ ሰራ ላይ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና በኦሮሞ ማህበረሰብ መሀል ሊሆን የታሰበ መስተጋብር መሆኑ ነው ። ይህ አይነቱ ኋለቀር ዘረኛ አሰተሳሰብ ለማንም የማይበጅ በመሆኑ መሰበር አለበት ። በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች የመኖር መብታቸው ይከበር !። የአቶ በቀለ ገርባ እና መሰል እርባና የለሽ ሐሳቦች / Yaadota/ መወገዝ አለባቸው ። የአቶ በቀለ ገርባ ሀላፊነት / ltti gaafatamumma/ የጎደለው መርህ አልባ አሰተሳሰብና አመለካከት የኦሮሞ ወጣቶች ማውገዝ አለባቸው ። አቶ በቀለ ገርባ ንፁህ በዘረኝነት የጠበቡ ሰው እንደሆኑ በርካታ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል ።ጋብቻ በተመለከተም አቶ በቀል ገርባ የተሳሳተ እይታ እንዳላቸው ለመገንዘብ ችያለሁ ። የኦሮሞ ሰው ከኦሮሞ ማህበረሰብ ውጭ ጋብቻ መፈፀም የለበትም የሚል አመለካከት ያላቸው ጠባብ ሰው እንደሆኑ ለማወቅ አልተቸገርኩም ። ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸው ሥር የሰደደ ጥላቻና ንቀት ያሳያል ። የህዝብ ትስስር እና አንድነት የሚንድ አመለካከት በመሆኑ የአቶ በቀለ ገርባ ሰይጣናዊ አሰተሳሰብ መወገዝ እንዳለበት ይሰማኛል ። ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ መናቅ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እናቶች ክብር ያለመስጠት አመላካች ኢ ፍትሀዊ አመለካከት ነው ። Hadhaa fi bishaan hamaa hin qaban.

በኢትዮጵያ የብሔር ግጭቶች ዋና መነሻ ምክንያቶች ድህነት ፣ ኋለቀርነትና ፣ የህዝቦች መብት በተግባር የሚያረጋግጥህዝባዊ መንግስት ያለመኖር ናቸው ። በአንድ አገር የሚኖሩ ዜጎች ህልውና የሚረጋገጠው የህዝብ ልዕልና ሲከበር ፣ የህግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ፣ እንዲሁም ህዝብ እና መንግስት በሐሳብ ልዕልና መናበብ ሲችሉ ነው ። በመርህ እና በህግ ልዕልና የሚመራ መንግስት ያለመኖር ለህግ መሸርሸር ፣ ለዜጐች መፈናቀል ፣ ለህገወጥ የሰዎች እና የመሣሪያ ዝውውር ምክንያት ይሆናል ። ህዝብ በሚኖሩበት ቦታ ያለምንም የፀጥታ ሆነ የሕይወት ስጋት ሳያድርበት የመኖር መብት እንዳለ የማያውቅ ህዝብ ባይኖርም ችግሩ ያለው ሰልጣን ላይ ባሉ ሀላፊዎች የሚፈፀም ደባ ነው ። ጎበዝ እንዴት በህዝብ ይቀልዳል ?። ህዝብ የሚያፈናቅል አስተዳዳሪ ኢትዮጵያ ላይ ካልሆነ አለም ላይ ያለ አይመስለኝም ። ሰዎች በመሰረተ ልማት ምክነያት ከነበሩበት ቦታ ከበቂ ካሳ ጋር ሊነሱ ይችሉ ይሆናል ግን ዜጋ ከቤቱ አውጥቶ መንገድ ላይ መወርወር አግባብነት የለውም ብቻ ሳይሆን ደረቅ ወንጀል ነው ። የጌዲኦ እና የጎጂ ጎሳዎች ግጭት ከሐምሳ ሺህ ህዝብ በላይ ለችግር ዳርገዋል። የኦሮሞ እና የኢትዮጵያ ሶማሊ ጎሳዊ ግጭት መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል ። የአርጎባ እና የከረዩ የጎሳ ትንኮሳ በማጋጋል ላይ ነው ። የሁሉም ጎሳዊ ግጭቶች መነሻ ባህሪ ተመሳሳይነት አላቸው ። የሁሉም የጎሳ ግጭቶች ከማንነት ጋር ያላቸው ተያያዥነት አነሰተኛ ሲሆን ዋናው የጎሳ ግጭቶች ምክንያት ጥላቻ አዘል የወሰን ግዛት እንዲሁም የመሬት አጠቃቀም እና የመሬት ባለቤትነት መረጋገጥ ጋር የተያያዙ መሆናቸው የሚያሳዩ የዳሰሳ መረጃዎች አሉ ። የኢትዮጵያ ከተሞች በወጉ እንዲሁም በፍጥነት የከተማ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ጥያቄዎች ያልተሰሩ በመሆናቸው በሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ መሬት ቦታ ህግ ባልተከተለ ሁኔታ ለመሥራት ፍላጎት እንደሚኖር እሙን ነው ። ከመኖሪያ ቤት ግንባታ ጀምሮ የሚከናወን ዜጎች የማፈናቀል አካሔድ ከጥላቻ እና ስሜታዊነት በነፃ መልኩ በቅድመ እንዲሁ ድህረ የማህበራዊ ጥናት ማድረግ ያሰፈልጋል ።መሬት የመንግስት ነው በሚል ሰልት መሬት የሚሸጡ የመንግስት ሀላፊዎች ላይ በቂ ህጋዊ እርምጃ ሳይወሰድ መንግስት ዜጎች ማፈናቀሉ አግባብነት የለውም ። የመሬት ባለቤትነት ይዞታ እና የመሬት አጠቃቀም ስሪት በአግባቡ ሥራ ላይ ባልዋለበት ሁኔታ እንዲሁም የመንግስት ሀላፊዎች ህገወጥ የመሬት ሺያጭ በተቆጣጠሩበት ሁኔታ ለምን ዜጎች ለችግር ይዳረጋሉ ?።

ሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች የአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አንጥሮ እና አበጥሮ መከታተል እንዲሁም መተንተን ይኖርባቸዋል ። ወጣቶች ከራሳቸው ፍላጎት ባሻገር የአገር አደራ ትረካ በመሆናቸው በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ምስቅልቅሎች በፍጥነት የማረም አገራዊ ግዴታ አለባቸው ። ወጣቶች በሰሜት ሳይሆን በአመክንዮ እና እውቀት ላይ የተመሠረተ አሰተሳሰብ እና አመለካከት ማበልጸግ ለአገር ግንባታ እና የተፋጠነ ልማት እገዛ ያደርጋል ። የኢትዮጵያ ወጣቶች የመጀመሪያ የቤት ሥራ ማድረግ ያለባቸው ጉዳይ ከዘረኝነት አሰና የጎሳ ጥላቻ መራቅ ሲሆን ችግሮች ለማረም የበኩላቸው ጥረት ማከናወን የግድ ይሆናል ። ያጋጠሙ ህዝብ የማፈናቀል ችግሮች መፍታት የሚቻለው በጉልበት እና አመፅ አይደለም ። ችግሮች በህግ ልዕልና አግባብ እልባት እንዲያገኙ በመንግሥት ላይ ተፅእኖ ከማድረግ ባሻገር የጎሳ ጥላቻ የሚያራምዱአካላት ላይ በጋራ የማውገዝ ሥራ መሰራት አለበት ። በኢትዮጵያ የመፈናቀል ችግር ያልደረሰበት ማህበረሰብ ውሰን ነው ። በማወቅ ይሁን በሌላ በማፈናቀል ተግባር ከመንግሥት ሀላፊዎች ቀጥሎ የወጣ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ነበረበት ። ይህ አሳዛኝ እና የሞራል ውድቀት ተግባር ነበር ። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ህዝብ እንዳይፈናቀል መከላከል ሲገባቸው ራሳቸው ሰብአዊነት በጎደለው አፀያፊ ተግባር መፈፀማቸው ከማሳዘን ያለፈ ነው ። የሆነ ሆኖ ያለፈው ስህተት ዳግም መታየት ያለበት አይመስለኝም ። በቅርቡ ክብርት የፌዴራል ፕረዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅዘውዴ ለወጣት ኢትዮጵያውያን ይህን መልዕክት አስተላልፎ ነበር የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ለውጥ በስሜት ሳይሆን በስሌት በጉልበት ሳይሆን በእውቀት መመራት አለበት ። ይህ የሚደነቅ አባባል ነው ። ከዛ ውጭም የተሻለ መፍትሔ አይኖርም ።ፕሬዚዳንቷ ለኢትዮጵያውያን ምሁራን ያስተላለፉት ታላቅ መልዕክት ነበር ። ያሉትም እንዲህ ነበር ኢትዮጵያውያን ምሁራኖች በአራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሥራት እንዳለባችሁ ይሰማኛል ። በአብረሆተ ሓሳብ / enlightenment / ፣ የሐሳብ ልዕልና ማሳደግ ፣ በሳል የውይይት ባህል እንዲጎለብት ሥር እንዲሰድ መጣር ፤እንዲሁም መንግሰታዊ ሆነ ማህበራዊ ሒሰን የማቅረብ ጥበብ ማፋጠን የሚሉ ምክረ ሓሳብ አስተላልፈዋል ። ይህም ድንቅ መልዕክት እንደሆነ በርካቶች የሚስማሙበት ይመስለኛል ።

ሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች አልፎ መሔድ እንጂ በማይረቡ አሰልቺ አመክንዮዎች ለመተብተብ ጊዜ የላቸውም ። ወጣቶች በጎሳ የጥላቻ መረብ መሳፈር አንፈልግም ፣ አያዋጣንም ፣ አያዛልቀንም ማለት መቻል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ማሳየት ይኖርባቸዋል ። ዘረኛ ሓሳብ መታገል ይኖርባቸዋል ። በሐሳብ ልዕልና እንጂ በገጀራ እና አጠና እንደ ጋማ እንሰሳት በወረ በላ የሚዲያ ወንበዴዎች መናጥ የለባቸውም ። ወጣቶች የኢትዮጵያ ህዝቦች የአገር ወርቆች መሆናቸው በሚገባ ጠንቅቆ መረዳት ይጠይቃል ። ከፋፋይ ፖለቲከኞች በሐሳብ መቅጣት ይኖርባቸዋል ። ወጣቶች ማንም በከፈተው ቀዳዳ ውስጥ መሸንቆር እና መሸምቀቅ የለባቸውም ። በሐሳብ ልዕልና መምራት እና መመራት ይኖርባቸዋል ። የሐሳብ ነፃነት ማክበር እና ማስከበር ይጠብቅባቸዋል ። ለሰብአዊ መብት መከበር መሥራት ይኖርባቸዋል ። ታዋቂው መጋቢ ሐዲሰ እሸቱ አለማየሁ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር ሰው ምንም መብት ከሌላው ባሪያ ነው ፣ ምንም ግዴታ ከሌላው ደግሞ የአዕምሮ በሽተኛ ነው ። ይህ ብዙ ጉዳዮች የሚያመላክት አብይት ምክረ ሓሳብ ነው ። ቃለ ሕይወት ያሰማልን ! ለፈረጃ ይሁነን !። የሰው መብት በማንም ሲጣስ በዝምታ የሚያልፍ ኢትዮጵያዊ ወጣት መኖር የለበትም። የትግራይ ህዝብ መፈናቀል ያመናል ፣ የሶማሌም ፣ የከረዩም ፣ የአማራም ፣ የአፋሩም፣ የሲዳማም ፣ የአርጎባም ፣ የቅማንትም ፣ የኦሮሞም ፣ የጉራጌም ፣ የሐረሪም ፤ የሐድያም ፤ የስዶም ፣ የጌዴኦም ፣ የጎርጅም ፣ የሺናሻም መፈናቀል ያመናል የሚል ኢትዮጵያዊ ወጣት መፈጠር አለበት ። የኢትዮጵያ ወጣቶች በጋራና በሐሳብ ልዕልና እንጂ በዘር ጥላቻና የጎሳ ግጭት የሚመጣ እርባና እንደሌለ በጥዋቱ መገንዘብ ያሰፈልጋል ። ወጣቶች ለአገር እድገትና ብልፅግና ይረዱ ዘንድ የአዋጭነት ሐሳቦች ማፍለቅና መተግበር እንጂ በዘር ሐረግ መቆራቆስ አይገባቸውም ። Extreme Ethnic Nationalism is absolutely viral to peace and development love people anywhere and everywhere . Therefore , the Ethiopian young generation must fight backwardness thinking like Ethnic divisiveness and hate mongers in Ethiopia for the sole purpose of National unity , peace, and development aspects .

ሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች ያለፈ ዘመን ታሪክ ግድፈቶች በመተው በጎውን በመልቀም በየትኛውም ቦታ የሚያጋጥሙ ማህበራዊ ችግሮች አልፎ መሔድ ካልቻሉ ተደራራቢ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል ። አንድ የምጣኔ ሀብት ችግር ሲሆን ሌላው የደህንነት ችግር ይሆናል ። በመሆኑም ማህበራዊ ክስተቶች በንቃተ ህሊና መከታተል እንደሚበጅ ምንም የሚያጠራጥር አይሆንም ። በዚህ አጋጣሚ ለቄሮ ወጣቶች ለመግለጽ የምፈልገው የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል ። በእውቀት እና በውይይት እንጂ በገጀራ መሳቂያና መሳለቂያ ከመሆን ውጭ የምታሳኩት አንዳች ነገር እንደማይኖር ማወቅ እንዳለባችሁ አትዘንጉ ። በተቋም የህግ የበላይነት እንጂ በግለሰብ መመራት ማቆም ያሰፈልጋል ። አይኑ ካፈጠጠ ድህነት በላይ ሌላ ጠላት እንደማይኖር መገንዘቡ ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ ። ሁኔታዎችን በሰክነት መመልከት እንዲሁም መፈጸም ተገቢነት አለው ። Harka abbaa tokktotin ibidda qabbaachuun nama hindhibu.አዲስ አበባ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች መኖሪያ ከተማ እንጂ የኦሮሞ ግዛት አይደለችም ። ከተማዋ በፍቅርና በመተሳሰብ ለሁሉም የጋራ ንብረት ማድረግ ተገቢ ይሆናል ። ፍንፍኔ ኬኛ የሚለው አመለካከት የደካሞች አመለካከት ከመሆኑም በላይ የኦሮሞ ህዝብ ከሌላ ማህበረሰብ በጋራ ለመኖር የሚያሳይ ነገር የለውም ። ወጣት ቄሮዎች ለልማት እንጂ ለጥፋት መሰለፍ የአስተሳሰብና የአመለካከት ችግር መሆኑ መረዳት ለሁሉም መልካም ይሆናል ። አዲስ አበባ ቀርቶ የተቀሩ የኦሮሚያ ከተሞች የኦሮሞ ህዝብ መሆናቸው ምድራዊ ማረጋገጫ የሚኖር አይመስለኝም ። የእኛ የሚል አሰተሳሰብ መስተካከል ይኖርበታል ። ወጣት ቄሮዎች የአመለካከት ለውጥ እንደሚያደርጉ አምናለሁ ። ከገጀራ የድንቁርና አሰተሳሰብ ወደ ሰለጠነ የውይይት መንፈስ ሽግግር እንደሚያደርጉ አምናለሁ ። በደመ ነብስ እንደ ጋማ ከብት የሚንዳቸው ቀልበ ቢሰ ጃዋር መሐመድ ወጥመድ በአጭር ጊዜ ነፃነታቸው እንደሚያውጁ አልጠራጠርም ። ወጣት ቄሮዎች በህልም ካልሆነ በጋህድ በገጀራ ፍላጎታቸው ማስፈፀም ከቶ የሚያስችል አቅም ሆነ ጥበብ በውል ያላቸው አይመስለኝም ። ቄሮዎች የሚያራምዱት ሓሳብ ሗላ ቀርነቱ ባያነጋግርም አሁን አለም ከደረሰበት የሐሳብ ልዕልና ጋር ሲመዘን የቄሮ የገጀራ ጉልበት በጋርዮሽ ሰርአት ውስጥ እንዳሉ መገመት የሚያስቸግር አይሆንም ። ህዝብ በሐሳብ ነፃነት እንጂ በገጀራ አይኖርም ። ገጀራና አጣና የደንቆሮዎች መሣሪያ ሲሆን የበሰለ በጋራ የመወያያ ነፃነት ደግሞ የአዋቂያን ጥበብ ማሳያ ፣ የሐሳብ ልዕልነት በረከት እንደሆነ አንዳች አጣራጣሪ ምክነያት የለውም ። በገጀራ ወንጀል እንጂ ልማት ማሳለጥ ከቶ አይቻልም ። Bad not to think in a rational way to enhance internal developments and National unity within one Nation. Knowledge base social demands are undeniably essential demands as far as the demands are legitimate and compel with the rule of law .There is no honest way not to be wiser when it comes to social interest in danger. People are dislocated forcefully by government officials in Ethiopia Nationwide due to lack of rule of law and positivity towards Ethnicity . Ethiopia has rich Ethnically but falls to accommodate such gifted phenomenon in shameful and disgrace ways . Ethnic conflict and hate towards Ethnicity are backward and primitive in nature and some scholars are still keep pushing Ethnic Nationalism sadly and extremely in this poor Nation Ethiopia . We all shall believe and govern in and by idea supremacy and rule of law for any and all social causes. All Ethnic categories in Ethiopia shall respect and reward it earthly honor for good reasons . Ethnic shall not be the root cause for social displeasure in Ethiopia rather shall be rewarded gracefully. Shame not to do so !.

ሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች ሓሳብ አፍላቂ እንጂ ሐሳብ ጠላፊ መሆን አይጠበቅም ። ለጎረቤት ኬንያ ወጣት ከምትሰጡት ክብር የበለጠ ለወገናችሁ ክብር ሰጡ ። ዘረኝነትን አስወግዱ ። በሐሳብ ነፃነትና ልዕልና ተማረኩ ፣ተመኩ። ከህገወጥ ተግባሮች ተቆጠቡ ። በምክንያታዊ ሓሳብ ተመሩ ። የነፃ ሓሳብ ሞጋች እና ተቆርቋሪ ሁኑ ። በዲሞክራሲ ጎደና ላይ ፈንድቁ። ለመብታችሁ ታገሉ። ሀብት ለማፍራት በእውቀት እና ጥበብ በመጠቀም ከተፈጥሮ ጋር ተገሉ። የበሰበሱ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ አትሁኑ ። መብታችሁ ለማስከበር በጋራ ሥሩ ። አትቁሙ ! አልፋችሁ ሒዱ ! ሰው በሠራው ቤት አትግቡ ። የራሳችሁ ቤት በጋራ ግንቡ ። በትላንት ታሪክ አትኑሩ ። ዛሬን ኑሩ ፣ ለነገ ደግሞ ተዘጋጁ ። መብታችሁ ለማንም ቀበኛ አሳልፋችሁ አትስጡ ።

ይኩነ ጥሩ ጊዜ ለኩሉ !

 

 

 

Back to Front Page