Back to Front Page

የፌደራሉ በሌሉበት ክስና አንደምታው

የፌደራሉ በሌሉበት ክስና አንደምታው

 

አልታይሽ አለኝ 5-16-19

ከልደታ

 

አገራችን መላቅጡ የጠፋበት ለውጥ ተብዬ ነውጥ ከጀመረች ጀምሮ ትላንት የተባለው ዛሬ አይደገምም። ይቀየራል። ለውጥ ይደረግበታል። ከለውጡ በኃላ የለውጡ መፈክር እስኪመስል ድረስ ስሙ የገነነው ጌታቸው አሰፋ በተመለከተ በሚድያ፣ በኢህአዴግ ስብሰባ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በካቢኔው፣ በዐቃቤ ህግ ወዘተ የምንሰማው የተለያየ መግለጫ ነው። የሚደንቀው ነገር የተለያዩ ሰዎች የተለያየ መግለጫ ቢያደርጉ ምንም አልነበረውም። የአንድ መንግሥት አካላት ድብልቅልቅ ያለ መግለጫ መስጠት የማይገባ ቢሆንም ግራ የሚያጋባው ደግሞ እያንዳንዱ ትላንት ያሉት ዛሬ ከሚሉት ራሱ የሚጣረስ መሆኑ ነው።

Videos From Around The World

ጠቅላዩ በስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጌታቸው እንዲታሰር አልፈልግም። ምንም የሚያሳስር ነገር የለውም። አሮጋንት መሆኑ ካልሆነ በስተቀር ንፁህ ሰው መሆኑ አውቃለሁ። ደብረፅዮን ይህን ያውቃል አውሮፕላን አዘጋጅቼ ውጭ ልልከው ነበር። በማለት (ሌሎች መያዝ አለበት፣ መከሰስ አለበት ብለው እንዳስቸገሯቸው ዓይነት አድርገው) በተደጋጋሚ ይናገራሉ። በቅርቡ ደግመው ይህንኑ ለኢህአዴግ ስብሰባ ለሄዱት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ለብቻቸው ሰብስበው እንደተናገሩ በእህት ድርጅቶቻቸውና በአጋሮቹ አከባቢ ይወራል።

 

ፓርላማ ላይ ደግሞ ከታስሩት በላይ ራሳቸውን ያሰሩት ነፃነት የላቸውም። ቢያዙም ባይያዙም ግድ አይስጠኝም አይነት ተናገሩ። በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚም በምክርቤትም ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ስም ሳይጠቀሱ ክልሎች በወንጀል የሚፈለጉ ደብቃችሁ አንሰጥም ብላቹሁ ዲሞክራሲያዊ ማእከልነትን እየጣሳቹህ ነው ብለው አምርረው ፅፈዋል። አራቱ ድርጅቶች ሲሰበሰቡና ጠቅላይ ሚኒስትሩና ህወሓት ብቻ ሲገናኙ ስለ ጌታቸው አሰፋ የሚሰጡዋቸው መግለጫዎችና አስተያየቶች ይለያያሉ።

 

ዐቃቤ ህጉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ጌታቸው አሰፋን ለመያዝ ብለን ተኩስ ከፍተን የሰው ህይወት እንዲጠፋ አንፈልግም አሉ። ትንሽ ሳይቆዩ ደግሞ ለፓርላማው ክልሉን ጠይቀናል ከክልሉ ጋር በመተባበር ይዘን ለፍርድ በቅርቡ እናቀርበዋልን ካሉንም ወራት አስቆጠረ። በሌላ ጊዜ ደግሞ የሚተባበረን ጠፋ ዓይነት ስሞታ አቀረቡ። የሰሙኑ ድራማ ግን የተለየ ነው።

 

ቀደም ብለው ዐቃቤ ህጉ ትግራይ ውስጥ የተሸሸጉት በሌሉበት ልንከሳቸው ነው አሉ፡፡ አገር ቤት እያሉ እንደሌሉ ተቆጥሮ በሌሉበት ተብሎ በምን ህግ ነው ክስ የሚቀርብ ሲባል ደግሞ ጨዋታዉ ቀየሩት። ግንቦት 8 ተይዘው ይቅረቡ ተባለ። ለጥቆ ዐቃቤ ህግና ፌደራል ፖሊስ ክትትል አድርገን የት እንዳሉ ደርሰንበታልና ልንይዛቸው እየመጣን ነው ብለው ክልሉን እንደጠየቁ ተሰማ። ይህም ለሁሉም ግራ የገባ ነገር ሆነ፡፡ ጥያቄው ፍቃድ ነው? ወይስ ተቀበሉንና ሆቴል ያዙልን? ነው ተባሉ፡፡ ነገር ግን ዐቃቤ ህግና ፌደራል ፖሊስ ምን ያድርጉ! ከዚህ በፊትኮ ኮ/ል ደመቀን ለመያዝ ፌደራል መንግስት አማራ ክልልን አላስፈቀደም በሚል ህገወጥ አስተዳዳሪዎች ከወንጀለኛ ጋር ተሰልፈው የፌደራል ፖሊስን ከኃላ አስመትተው 11 የፖሊስ አባላትን አስገድለዋል። በዚህ የደነገጠው የሃይለማርያም መንግስት ከዚያ በኃላማ የመጀመሪው ጥያቄው ክልሎችን አስፈቀዳቹ? ሆነና እሱም ሌሎችም ይህንን መመርያ አደረጉት። የለውጡ ሀይል ስልጣን ከመያዙ በፊት ያለ አዋጅ የሃይለማርያም መንግስት ያወጣው መመርያ ሆነና አማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሊ ክልሎች በስራ ላይ ውሏል። በተራው አሁን ደግሞ ትግራይ ውስጥ በስራ ላይ ውሏል ማለት ነው። በነውጡ ግዜ እንኳን መመርያ ህገመንግስቱን ንደውት የለ! ሰለዚህ ህገመንግስት የናደ ፌደራል መንግስት በምንሞ ራሉ ነው ህግ አስከባሪ መስሎ ሊቀርብ የሚችለው ነው ጥያቄው።

የትግራይ ወጣት ግንቦት 8 የትግል ቀን እናደርጋታለን ብሎ መነሳሳት ሲጀምር ዐቃቤ ህጉ መግለጫዉ ቀየር አደረገና መያዣ ትዕዛዝ ልንሰጥ ነው ፍ/ቤቱ ያዘዘን ማለት ጀምሯል። ነገር ግን መጥርያ ትእዛዝ ለማን ነው የሚሰጡት? ለትግራይ ፖሊስ? ወይስ ለተከሰሱት? ለተከሰሱት ከሆነ የተከሰሱትን የት አግኝተው ሊሰጧቸው ነው? ወይስ ለወኪሎቻቸው? ግን ማነው ወኪላቸው? ወይስ ያደጉበት የወላጆቻቸው ቤት ትእዛዙን ሰጥተው አላቀረባቹሁትም በማለት ቤተሰቦቻቸውን ለማሰር! ለትግራይ ፖሊስ ከሆነ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። የትግራይ ፖሊስ እምቢ አለን አልተባበረንም ለማለት ካልሆነ ፋይዳ የለዉም፡፡ ታድያ አሁን ስርየስ ነን ለማለት ካልሆነ ምኑነው አዲስ ነገር? መጥርያ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ቀን ወይስ ፍ/ቤት የሚቀርቡበት ቀን ነው ግንቦት ስምንት ቀን? ዐቃቤ ህግና ፌደራል ፖሊስ የፍ/ቤትን ነፃነት የሚያከብሩ ከሆኑ ስንት ጊዜ ፍ/ቤት ፍቱት ያላቸውን ኢሳያስ ዳኛውን ለምን አልፈቱትም?

 

ሰለዚህ የሚሻለው ፖለቲካ ዓላማ ያለው ክሳቹሁን ተወት አድርጋችሁ ትላንት ለሀገራቸው ሰለቸን ሳይሉ ቀንና ሌሊት ያለ ዕረፍት ሰላም እንዲነግስ ላደረጉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ለሆኑት የድህንነትና መረጃ ሰራተኞችን ከእስር ቤት አውጥታቹሁ ይቅርታ ብትጠይቁ፣ ለማሰር ያልቻላችሆቸውንም ተወት አድርጋቹሁ ጉልበታቹሁን የቤሻንጉል ጆኖሳይድ፣ የቅማንት ጆኖሳይድ፣ የሶማሊ ጆኖሳይድንና የኦሮሞ ጆኖሳይድ ፈፃሚዎች ላይ ብትረባረቡ ነው ለአገራችን የሚበጀው። አለበለዝያ ግንቦት 8 ታልፋለች። ሌላ ድራማ አዘጋጁ።

 


Back to Front Page