Back to Front Page

GAME OVER ያልኩት ገና ነው!

GAME OVER ያልኩት ገና ነው!

ኡስማን ሙሉዓለም፣ ከሓራ ገበያ

3-26-19

 

ክፍል አንድ

 

የሻዕብያ መንግስት መሪ ኢሳያስ እና ቡዱኑ ከአንድ ዓመት በፊት የወያኔ መንግስት አለቀለት (Weyane Game Over!) ብሎ ዳንኪራ ረግጦና አስረግጦ ነበር።ወዲ አፈይይህ አባባል አብይ አስመራ መጀመርያ በሄደበት ወቅትም አንፀባርቆት ነበር።

 

የኢሳያስ መንግስት የሰለላ መዋቅር ይሁን የለማ ቲም ዘግይቶም ቢሆን ጫወታው እንዳላበቀለት እየተገለፀላቸውና እየገባቸው መጥቷል።ሁኔታው አበቃለት የተባለው ጨዋታ የትግራይ ህዝብና ህወሓት የላላው በመወጠር አንድነታቸውበማጠናከር ላይ የበኩሉን ሚና መጫወቱን ከማወቅ አልፈውም የነበራቸው አያያዝም ስልታዊ ችግር እንደነበረው አምነዋል።

 

አሁን ያለው የህወሓት ጥንካሬ ምንጩ በትክክል ባይገባቸውም የጥንካሬውን ብቃት በማነፃፀር ሲገመግሙ ደርግ ሲወድቅ ከነበረው ዓቅም የበለጠ እንጂ ያነሰ እንዳልሆነ በመመዘን አስቀምጠውታል።በነሱ ትንተና የዚህ ብቃት ምንጭ የሻዕብያ መንግስት በተለይም የኢሳያስ ያልተገራ ልሳን አንድ ምንጭ መሆኑና ሞተ ሞተ ተብሎ የታሰበው ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት የተቻላቸውን ያህል የኢሳያስ አባባልና ምኞት ምን መሆኑ ደጋግመው ስለሰሩበትና ድርጅቱም ህዝቡም በንቃት ለህልውናቸው ሲሉ በአንድነት መሰለፍእንዳለባቸውስለተገነዘቡነው ይላሉ፡፡ ይሁንእንጂአሁንም ህወሓት ካለ ሰላም የለም እያሉ ናቸው።በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ህዝብና ብዙ የሻዕብያ አባላትና አመራሮችሳይቀሩ ይህን የኢሳያስ ቡድን አስተሳሰብ አይቀበሉትም።እንዳውም መለስ ኢትዮጰያን ቀይሮ ሞተ ኢሳያስ ግን ኤርትራን ገድሎ ሞትም እምቢ አለው እያሉ ናቸው።

Videos From Around The World

 

ሌላው የጥንካሬ ምንጭ የሚሉት የብአዴን/አዴፓ/ የተወላገደ አሰተሳሰብና ተግባር ነው፡፡ አዴፓ (ስሙ ምርጫ ቦርድ ባያፀድቀዉም) በትግራይ ህዝብ ላይ ግልፅ የጥላቻ ሰበካ በማካሄዱና በክልሉ ረዥም ዓመት የኖሩ የትግራይ ተወላጆችን የኢትዮጵያ ዜግነት መብታቸውን በካደ መንፈስ እንዲገለሉ፣ እንዲፈናቀሉ፣ እንዲባረሩና እንዲገደሉ አደረገ። የወልቃይትና የራያ የማንነት ጥያቄ ቀስቃሾቹ ፀረ ህዝቦች ናቸው እያለ በኢህአዴግ መድረክ ሲያወራ እንዳልከረመ በግላጭ የራሱም ጥያቄ መሆኑና እስከመጨረሻው እንደሚታገልለትና ወያኔ መሬት ወራሪ እንደሆነ ሰበከ።ወደ ትግራይ ምንም ነገር እንዳያልፍ መንገድ ዝጉ በማለት የሚያስተዳድረው ህዝብ ጎሮሮ እንዲዘጋ አደረገ። የጦርነት ዝግጅት ለማድረግ ወንጀለኞች ተብለው የተፈረደባቸው ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ፣ በሕግ ቁጥጥር የነበሩ ተጠርጣሪዎችንና በፍርድ ሂደት የነበሩትም ሂደቱ እንዲቋረጥ በማድረግ የጦር አበጋዝ አድርጎ በመሾም በየመድረኩ በትግራይ ህዝብና በመሪ ድርጅቱ ህወሓት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ሲያስታውኩ ህወሓቶች በሚገባ ይህን ስልት የጎደለው ንግግሮቻቸው በተከታታይ በመጠቀም ስላጋለጡ የህዝብ ድጋፋቸው ተጠናከረ ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ህዝብ በተለይ የገጠሩ ህዝብ ይህንንየአዴፓ አባባል አይቀበለውም። ህዝቡ እያለ ያለው እናንተ በአስተዳደራችሁ ስር ያለነውን የአማራ ህዝቦች በብቃት ሳታስተዳድሩ ሁሉንም ችግር ላላስተዳደሩንና ሩቅ ላሉት ህወሓቶች አታላክኩ ብሏቸዋል።

 

 

በቲም ለማ የሚታወቀውና ፈዴራል መንግስት የተቆጣጠረው የስልጣን ጥመኛም ቡዱን መጀመርያ የትግራይን ህዝብ ሞተር ነህ ብሎ የህዝቡ ድጋፍ ለመሸመት ጥረት አድርጓል፡፡የትግራይ ህዝብ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ አይደሉምተብላ ጣል የተደረገችው ንግግር ችሎ ድጋፉን ቢገልፅም፣ጠጉረ ልውጥየተባለውን ቢያስታውስምበለውጡ አገራችን ሰላም ሆና በ27 ዓመት የዕድገትና የብልፅግና ዓመታት ካጋጠሙን ዕንቅፋቶች ወጥተን ፈጣን ለውጥ ይመጣል በሚል ሆደ ሰፊነት በመጠባበቅ እያለ የጠበቀውን ሳይሆን ያልጠበቀውን የቀን ጅብ የሚል ኢንተርሃምያዊ ዱብ ዕዳ ወረደበት፡፡ሩዋንዳ ላይ ሰውን ያክል ፍጡር በነፍሳትስም በረሮ በማለት ሰይመው ሰውን አድኖ መግደል በረሮ እንጂ ሰው አልገደልኩም የሚል ስሜት እንዲፈጠር እንዳደረጉት ዓይነት በኢትዮጵያችንም ይህ የስልጣን ጥመኛ ቡዱን የቀን ጅቦችን መግደል፣ ማባረር፣ ማፈናቀል፣ ማሰር፣ መክሰስ፣ስም ማጥፋት፣ መስደብና ማዋረድ ቀላል እንዲመስልና እንዲሆን አድርጓል።ከቀን ጅብገለፃቸው በኃላ በትግራይ ተወላጆች ብቻ ያነጣጠረ በፊልም የታጀበ እስር ፈፀሙ፡፡ ለውጡንና የኔን ወደ ስልጣን መምጣት የማይቀበሉ በሚል የግል እይታ የአንድ ብሄር ሰዎች ብቻ ተለይተው ለእስርን እንግልት እንዲዳረጉ በቡዱኑ ተወሰነባቸው፡፡ በምን ምክንያት አሰርናቸው እንበል?ለሚል ደግሞ በሙስናና በስብአዊ መብት ጥሰት ይሁንላቸው ተባለ፡፡ ለዚህም እንዲረዳ በጠ/ሚኒስተር ቢሮ አማተርሽ ዳይረክተርነት ፎክመንተሪፊልም ተዘጋጅቶ ሰኞንማክሰኞ ቀደመው ዓይነት ፍርድቤት ሳይፈርድ ሚድያ ፍርድ ሰጠ።

 

በቀጣይነትም ይህ ቡዱን የኤርትራ ጉዳይ ህዝብ ሳያቀው ውስጥ ለውስጥ መፈራረም ሳይበቃ ሠራዊቱን ለማንሳት ያደረገው ሙከራ የትግራይን ህዝብ ከሠራዊቱ ለማጋጨት የተደረገ ሙከራ ቢሆንም በህዝቡና በሠራዊቱ ትዕግስትና ንቃት ከሽፏል።

 

በቅርቡ ደግሞ አብይ የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን ሰብስቦ ከህወሓት ጋር ትቀርቡና ወየላችሁ! አብዲ ኢሌን እንዳደረገነው ይፈፀምባቹሃል፣ ያፈነገጠው ክልል አራቱን በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በጀት ብዘጋው ተማሪው የሚበላው ሲያጣ ተንጫጭቶ ክልሉን ያፈርሰዋል እና በክልሉ የሚገኙ ባንኮች ትራንስአክሽን ብቆርጠው ገንዘብ ሲያጡ ድምብርብራቸውን ይወጣሉ በማለት እንደዛተ የአደባባይ ምስጥር ነው። እንዳያውም ጠቅላዩ በንዴት ይህ ሁሉ ሳያስፈልግም በቁጥጥሬ ያለውን ሠራዊት በአንድ መስመር ትዕዛዝ በማዘዝ ክልሉን መቆጣጠርም ይቻላል በማለቱ አገሩን እያስተዳደረ ያለ መሪ ሳይሆን ቁርጥ ቅኝ ገዥው ግራዝያኒ አስመሰለው።

 

አሁን አሁን ጠቅላዩና ቡዱኑ ድጋፍ አለን ብለው በሚመኩበትና በህዝበኝነት የገነቡት ካብ እየፈረሰባቸው ነው፡፡ከህወሓት የተሻለ እኔን የሚመስሉ ሲኖሩም ሲሞቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው ብለው ያስገቡዋቸው የደርግ ርዥራዦች፣ ኢሣትና ግንቦት-ሰባቶች እኛ ካልነው ከወጣችሁ ለውጡ ተቀልብሷልበማለት የራስ ምታት ሁነውባቸዋል። መድረክ ሰፍቷል ሲባል የነበረው አሁን የተለየ መናገር ፀረ-ለውጥ የሚል ስም ያሰጣል። በስመ መድረክ ሰፍቷል ምን ያህል ሰዎች አሁን ንግግር ሲያደርጉ ግዴታ እስከሚመስል ለውጡ ያስገኘልን ምናምንቴ ሳይሉና ለውጡን ያጎናፀፉን ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሳይሉ መናገር የማይቻልበት የመደመር ፓስወርድ ተደርጎ ይቆጠራል። ከኢሣት በስተቀር የሚናገር የለም። ካሉም የንስሃ ግባ ዓይነት ፕሮግራም አቅራቢዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ማሳያ ሠራዊት ፍቅሬን ወደ ህወሓት 40ኛ ዓመት ለምን ሄድክ? ተብሎ በሚድያ በአደባባይ ሲወቀስና እንዲሸማቀቅ ሲደረግ ተስተውሏል፡፡ የተዘጉት ሚድያዎች በተመለከተ ሌላ ጊዜ ራሱን በቻለ አርእስት የምመጣበት ጉዳይይሆናል፡፡

 

እንደነ ዋልታ፣ ፋና፣ ጀይ፣ናሁ፣ኤል ቴለቪዥን ጣብያዎች ልክ እንደ ኢቲቪ በአንድ ማእከል የሚተዳደሩና ድጎማ የሚቸራቸዉ ሚዲያዎች መሆናቸዉ የአደባባይ ምስጥር ሁኗል።በምንም ዓይነት ተቃውሞ ያለውን ሰው ሲጋብዙና ዝግጅት ሲቀርቡ አይታዩም።ራሳቸውን የለውጡ ሐዋርያ ሰባኪ አድርገው በማየት የህዝቡ አጀንዳዎች ወደጎን ገፍተው ወደማያውቁት ጎዳና እየነጎዱ ናቸው።ቢያንስ ለውጡን ደግፎ እንዳይቀለበስ የሚል ቅኝት ያለው ተጋባዥ ብቻ ያስተናግዳሉ።በአንፃሩ ደግሞ ምንም ለውጥ የለም ትልቁ ለውጥስልጣን ላይ የመጣ ሰው መቀየሩ ብቻ ነው ፣በለውጥ ስም ሞት መፍናቀል ግጭቶች ተበራክቷል፣አገሪቱ ወዴት እየተጓዘች እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ አይታይም።የአብይ ለውጡ ሳይጀመር ለምን ወደቀ? ብሎ የጠየቀ ሚድያ ለናሙናም የለም። ይህንንተጨባጭ ሁኔታ እነዚህ ሰባኪ ሚድያዎች ደብቀውታል። በአገሪቱ ውስጥ የህዝቦች መፈናቀል፣ረሃብ፣ የፀጥታና የደሕንነትችግሮችእየተከሰቱ መሆኑን ዓለምአቀፍ ሚድያዎች ጭምር እስካሁን ደብቀውት ቆይተውገና አሁን ነው መዘገብ እየጀመሩት ያሉት።ምን ያደርጋል የአገርቤት ሚድያዎች ሙገሳ ቢሆን ያንጫጩት ነበር፡፡ ዳሰሳ! ወይም ሰበር ዜና! ብለው።

 

ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ህወሓት ፀረ ለውጥ፣ከኤርትራጋር የተደረገ የሰላም ሂደት ያለተቀበለ፣ ዘረኛ ፌደራሊዝም ያመጣ፣ሃያሰባት ዓመታት የትግራይ የበላይነት ያሰፈነ፣ ፈጣን ዕድገት እንዳይመጣ እንቅፋት ሆኖ የጨለማ ጊዜ ያኖረን፣የኢህአዴግ ስህተት በሙሉ የእንበሳውን ድርሻ ተጠያቂ፣ . . . ወዘተ እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ደግሞ የለየላቸው ጨፍጫፊ ደርጎችን ዋቢ አድርገው የአይጥ ምስክር ድምቢጥ እንዲሉ ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን ለማጠልሸት በተከታታይ ስራ ሰርተውበታል እየሰሩበትም ይገኛሉ፡፡ የትግራይ ህዝብ አኩሪ የትግል ታሪክና ከሁሉም የኢህአዴግ እህት ድርጅት በህዝባዊነት መለኪያ የተሻለውን ህወሓትን ስም ጥላሸት ለመቀባት የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል። እያደረጉም ናቸው፡፡ ተሳክቶላቸዋልም።

 

የነለማ ቲም ድግሞ እነዚህ የተንሸዋረሩ አመለካካቶችን ያልተገቡ ድርጊቶችን በመፈፀማችን ህወሓትንበትግራይ የህዝብ አለኝታ በማስገኘት ጠቅሟቷል እያሉ ናቸው። የበለጠ እንድትጠናከር አስችላታል ባዮች ናቸው። በመቀጠልም በትንተናቸው የትግራይ ህዝብ የሰራናቸው ስህተቶች እያየ ዝም ብሎ እንዲጠብቀን እንዴት እንገምታለን? ይህ የራሳችን የተዛባ እንቅስቃሴ ተጠቅሞ ህወሓትቢስራበትና ከትግራይ ህዝብ አንድነቱን ከመቼው ጊዜ በላይ ቢያጠናክር እንዴት እንገረማለን? በማለት በአሁኑ ወቅት የስልት ለውጥ እናድርግ ብለው ተወያይተው ወስነዋል፡፡ ስለዚህ ይህን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድነትና ጥንካሬ እንዴት እንሸርሽረው በሚል ስልቶች ነድፈው በአዲስ መልክስራ ጀምረናል! እያሉ ናቸው። ሰልቶቹ ደሞ የሚከተሉትን ናቸው፡፡

 

1) ህወሓትን መቀረብና ማለዘብ፡- እስካሁን የተደረጉ ነገሮች ከአንገት በላይ ይቅርታ በመጠየቅህወሓትና ህዝቡ እንዲዘናጉ ማድረግ፣የታሰሩትን እስከመፍታት መሄድና የዚህ አፈፃፀም በህወሓት አመራር ክፍፍል በሚፈጥር መንገድ ማስኬድ፣ደብረፅዮን ያለውን የድርጅትና የህዝብ ተቀባይነት እንዲሸረሸር ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ፣ድብቅ ያልታወጀ ድርድር ማጣጧፍያ ስልቶችን መጠቀም(ወደ ትግራይ የሚመላለሱ የአገር ውስጥና የውጭ ዜጎች መብዛት እየታየ ነው።ወደፊት ካልተገለፀ የምንገልፀው ይሆናል)፡፡

 

2) የትግራይን ህዝብ የሚከፋፈልበትአጀንዳ መፍጠር፡-የሃይማኖት ክፍፍል፣የመልካም አስተዳደር ችግሮን በአንድ ሌሊት ካልተፈቱ በሚል አንድነቱ እዲላላ ማድረግ፣የወልቃይትናየራያ የሚለውን ጉዳይ በሌላ መንገድ ማስኬድ/የአማራ ክልል ዝም ብሎ በስተጀርባ በከዱ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ማስጮህ/፡፡

 

3) የትግራይ ክልላዊ መንግስትን እያደረገው ያለውን ዝግጅት ለማክሸፍ የተለላዩ ስልቶችን መቀየስ፡- በዚህ መሰረት የፈደራል ፖሊስ ልዩ ሃይል ብቻ ተጠናክሮ በክልሉያሉ ሁሉም ልዩ ሓይሎች የፈዴራል አካል እንዲሆኑ ማድረግ፣በክልሉ ፖሊስ የሚታጠቀው መሣርያ ቀላል ጠበንጃና ሽጉጥ ብቻ እንዲሆን ማድረግ፣በክልሉ የነበሩ መትረየስ፣ አርቪጂ፣ ስናይፐር ለፈደራል መንግስት እንዲያስረክቡም የሚል ረቂቅ እየተዘጋጀ ነው። ከፈደራል መንግስት ተቃውሞ አሰምተው የመጡ የመከላከያ ጀነራሎችና ኮኔረሎች፣የፈዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣የድህንነት አመራሮችና ከፍተኛ ሞያ ያላቸውን ኦፊሰሮች በተላየየ መንገድ እንዲበተኑ ማድረግ፡፡ በዚህ ዙርያለምሳሌበጄነራል ሳሞራና በአብይ ይሁንታ የጄነራል ብርሃነ ነጋሽ (ወዲመድህን) ክስ እንዲቋረጥበማድረግ ለማባበል እየሞኮሩ መሆኑን እየታየ ነው።ሌሎችንም አብይ ይፈልጋችሀል ኑ እየተባለ ሎቢ ተጀምራል።የፈደራል ፖሊስ አመራርም ተቋርጦ የነበረየአምስት ወር ዶሞዛችሁ ሳይቀር ይከፈላችሃል ተብሎ ተነገሯቸዋል።የድህንነት አባላትም በተመሳሳይ ቆሞ የነበረ ደሞዛቸው እንደሚላክላቸዉና አዲስ አበባ ለምን አትመጡም? እየተባሉ እተጉተጎቱ ናቸው።ይህ ክልሉ አቅመ-ቢስ ለማድረግ የታቀደ ሴራ መሆኑን በቀለሉ መገንዘብ ይቸላል።

 

4) በዋናው ሚድያና በሶሻል ሚድያ የትግራይ ህዝብ ትግሉ እንዲቀንስ ማድረግ፡- እነሱ ግን በነዚህ ሚዲዎች የኛ አይደለም እያሉ እየማሉ የትግራይ ህዝብና የህወሓት አንድነት ለመሸርሸር ስልቱን ቀይረው ለማጧጧፍ ታጥቀው ተነስተዋል።ብዙ ሺ ገንዘብ ለማፍሰስም ተዘጋጅተዋል።ዋናው ሚድያ ነገሮችን ለማቀዝቀዝ እየሞከረ ነው፡፡ እስካሁን የነበሩ ችግሮች ዝም ብለችሁ ስላልገለፃችሁትነው በሚል ስልት የራሰቸውን ችግር ሊያጋሩን ሊሞክሩ ናቸዉ።ጀምረውታልም።የእኛ ሚድያ አይነአፋር አድርገው እነሱ ምሽጉጋ ገብተን እናተርምሳቸው ብለው የታጠቁት ጥያቄ እየተኮሱ ያጡትን አጀንዳ ቀያሽነት ለማስመለስ ሊጥሩ አቅደዋል።

 

5) የኢሳያስ ቡድን ቀድሞ የነበርቱን ተቃዋሚዎች ውስጥ ለውስጥ ስልጠና መስጠትና መረጃ በመሰብሰብ ክልሉን የማተረመስ የቆየውን ስትራተጂ በትግራይ መቀጠል፡- ትግራይ ሰላም እንደማትፈልግ በመስበክየኢሳያስ ቡዱን ከፍተኛ አስገዳጅ ምልመላ በማድረግ ሠራዊቱን እያጠናከረ ይገኛል።የኢትዮጵያ ሰራዊት ደግሞ ሰራዊት ቀስ በቀስ እየቀነሰ ነው።ይህ ዝግጅት ድንገተኛ ወረራ በመፈፀም በፍ/ቤት የተወሰነልኝን መሬት አስመለስኩኝ በማለት የትግራይ መንግስት በህዝቡ ተቃውሞ እንዲገጥመው የተወጠነ ሴራ ነው።በሚስጥር ምን እንደወሰነ አስካሁን ለመግለፅ ፍቃደኛ ያልሆነው አብይም ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለት ባይችልምአንዴ ሆኗል ድሮም ልናስረክባቸው አልነበር! ይውሰዱት! ሊል ይችላል።

 

6) ህወሓትን መነጠል፡-ከህወሓት ጋር ሊያብሩ ይችላሉ የሚባሉትን ክልሎችና ድርጅቶችን በግልፅ የማስፈራራትና የመደለል ስራ መስራት፡፡

 

የለማ ቲም እነዚህንና ሌሎች ለግዜው መጥቀስ የማልፈልጋቸው ስልቶች በማጠቃለል ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ያዳክምልኛል የሚሉዋቸው ስልቶችን ለመጠቀም አቅደዋል። አረ! አንዳንደቹም የሙከራ ስራዎች ለመስራት እየተንሳቀሱ ናቸው፡፡

 

Back to Front Page