ገር በዲሞክራሲ መርህ እንጂ በዘር ጣምራ መንግስት አይመራም።

ልኡል ገብረመድህን (አሜሪካ )

4.23.2019

አልፎ አልፎ ኦሮማራ የሚል ቃል አዳምጣለሁ።በተናጋሪዎች ሒሳብ የኦሮሞ እና የአማራ የዘር ተዋፅኦ አመራር አልያም የፖለቲካ መዋቅር ለማለት የከጀሉ ይመስለኛል።ሁኔታው እንደዚያ ከሆነ መሠረታዊ ስህተት ያለው አገላለጽ ወይም አባባል ነው።ከዛ ቀደም የለማ መገርሳ የለውጥ ቡድን እየተባለ ይገለፅ እንደነበር እሰማ ነበር።ይህ ስህተት ነበር። በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት የኦሮሞ ደም ደሜ ነው የሚሉ የጎንደ ርወጣቶች (ፋኖ) እንዲሁም ጣና ኬኛ የሚሉ የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ) የተቀጣጠለው ህዝባዊ አብዮት ለአመታት በመልካም አሰተዳደር እንዲሁም በውሰጠ ዲሞክራሲ እጦት ሲታመስ የቆየው የኢህአዴግ ሰርአት መሠረቱ እንዲነቃነቅ ተደርገዋል።በመሆኑም የለውጡ ባለቤት ህዝብ እንጂ የለማ አልያም የገዱ ለውጥ ነበር ለማለት የሚያስችል መረጃ የለም።በእርግጥ በድርጅታቸው የሀሳብ ልዩነት አሳርፎ ይሆን ይሆናል።ነገርግን ከዛ ቀደም ለምን በድርጅት ውሰጠ ትግል ለውጥ አላመጡም ለሚለው ጥየቄ በቂ መልስ የሚያቀርቡ አይመስለኝም። ለመገመት ያህል ስንታገል ነበርን የሚሉ ይመስለኛል።ያከሆነ ደግሞ በቂ መልስ አይሆንም።

Videos From Around The World

የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥን በዲሞክራሲያዊ መርህ የሚመራ ተቋማዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት ያለመኖር ኢትዮጵያ በድህነትና ኋላቀርነት ሰቆቃ ለመኖር ተገዳለች።የኢትዮጵያ ችግር የህዝብ ችግር ሳይሆን የጥቂት ጠባብ አሰተሳሰብ አመለካከት ያላቸው ሰነፍ ፖለቲከኞች ችግር ነው።እነዚህ ሰነፍ ፖለቲከኞች የአገርና የህዝብ ደህንነት ከቶ አያሳስባቸውም በዘር ጭቆና ሰም የሚነግዱ የፖለቲካ ነጋዴዎች ዘርን ከዘር የሚቃረንበት የታሪክ ቁርሾ እየመዘዙ ጎሳ ከጎሳ ጋር በማጋጨት የግል አልያም የቡድን የስልጣን አልያም የኢኮኖሚ ምዝበራ የሚፈፅሙ ናቸው።ፖለቲካ የህዝብ ፍላጎት ከማርካት ውጭ ሌላ ተልዕኮ የለውም ። በመሆኑም ፖለቲካ የአገርና ህዝብ ፍላጎት መርህ ላይ የተመሰረተ እንጂ በቡድን አልያም ጥቂት የለውጥ አራማጅ ሰዎች ላይ የተንጠለጠለ አይደለም ። ተቋማዊ ያልሆነ የፖለቲካ ሰርአት ጊዜያዊ እንዲሁም የሰላምና መረጋጋት ጠንቅ ነው ።

የኦሮሞ ህዝብ እና የአማራ ህዝብ ድሮም ቢሆን የተለያዩ ህዝቦች አልነበሩም ። አዲስ ግንኙነትም መፍጠር አይቻልም ። የህዝብ አንድነት በፖለቲካ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ አይደለም ። በደምና በስጋ የተዋሐደ ህዝብ በምንም ምድራዊ ሐይል መነጠል አይቻልም ። አዲስ ታሪክና ባህል መፍጠር ሳይሆን የቆየ የህዝቦች መቀራረብና መረዳዳት ማዳበር የስልጣኔ ማሳያ ነው ። የፖለቲካ መርህ አልባ ፖለቲከኞች አዲሲቷ ኢትዮጵያ ፣ የህዝብ ለህዝብ አዲስ ግንኙነት ፣ አዲስ ታሪክ ፣ አዲስ ባህል ፣ አዲስ አሰተሳሰብና አመለካከት ፣ ወዘተረፈ የሚሉ አባባሎች ሲናገሩ መሰማት እጅጉን ያማል ። ኢትዮጵያ ምኗ ይታደሳል ? ። በአንድ አገር የሚኖር በደም የተጋመደ ህዝብ እንዴት አዲስ ግንኙነት ይመሠርታል ? ። ለዘመናት የቆየ የታሪክና ባህል ትስስር በምን የታሪክና የባህል ትስስር ይታደሳል ? ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች መነሻ ሆነ መድረሻ ግባቸው ሰልጣን በመሆኑ እርሰ በእርሳቸው እንደ ሐረግ ሲጠላለፊ አንድም ሰልጣን ላይ ሳይወጡ ምልዐተ አፈር ይወርዳሉ ። ለውጥ አሰፈላጊ ነው ። ግን የምን ለውጥ ? የማህበረሰብ የኑሮ ለውጥ ፣ የመንግሥት አሰተዳደር ለውጥ ፣ የሥራ አመራር ለውጥ ፣ የፍትህና ዲሞክራሲ ለውጥ ፣ የሰብአዊ መብት ለውጥ ፣ የአስተሳሰብና አመለካከት ለውጥ ወዘተረፈ ለውጥ ያሰፈልጋል ። በመሆኑም አዲስ የአስተዳደር ለውጥ ቢመጣ እንጂ ኢትዮጵያ ሁሌም አዲስ ናት ። አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚባል ፍልስፍና የለም ። አዲስ የኢኮኖሚ እድገት ለውጥ እንጂ አዲስ አገር አይኖርም ። አዲስ የለውጥ አሰተሳሰብ እንጂ አዲስ ህዝብ ሆነ አገር አይኖርም ።

አልፋና ኦሜጋ ሰገናኙ አገር ይቃናል ፣ ልማት ይፋጠናል ፣ ሰላምና ፀጥታ ይሰፍናል ፣ የዜጎች መብትና ጥቅም ይከበራል ፣ መከባበርና መተሳሰብ ይጠናከራል የሚሉ በርካቶች ቢሆኑም ዳሩ ግን ተቋማዊ የዲሞክራሲ ባህል ባልተጠናከረበት አገር የኦሮማራ የፖለቲካ አካሔድ ሰፊ አደጋ አለው ። ሰዎች ሲከፋፉሉን ነበር በሚል የመጣ የአንድነን ውህደት ዘላቂነት የለውም ።የጣምራ ዘር መንግስት የሚያስከትላቸው አገራዊ አደጋዎች ከወዲሁ በጥንቃቄ መፈተሽ ያስፈልገናል ።በጣምራ ዘር የመንግስት አሰተዳደር የኢኮኖሚ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት አይኖርም ። የመንግስት ተጠያቂነትም አይኖርም ።በጣምራ ዘር አሰተዳደር ተወዳዳሪ የዲሞክራሲ መድብለ ፖርቲ ስርአት አይኖርም ። አናሳ (Minority ) የዘር ጎሳ ያላቸው ህዝቦች ፍትሀዊ የአስተዳደር እንዲሁም የፍትህ ችግር ያጋጥማቸዋል ። የጣምራ ዘር አሰተዳደር የሁሉም ህዝቦች ተሳትፎ አያካትትም ። በመሆኑም የፖለቲካና ሆነ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውስብስብ ችግሮች ይኖራሉ ። በመሆኑም በዘር ላይ የተመሰረተ የመንግስት አሰተዳደር ለአገር እድገት ፣ ለህዝባች መቀራረብ ፣ ለሰላምና መረጋጋት ፣ እንዲሁም ለፍትህና የህዝብ መብት እንቅፋት በመሆኑ የዘር ጣምራ የመንግስት አሰተዳደር መቆም ይኖርበታል ።

የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብከማንም በላይ በጋብቻ የተዋሐደ ህዝብ ነው ። በተለይ የሸዋ ህዝብ ኦሮሞ ከአማራ ለመለየት የሚቻል አይሆንም ። የተዛመደ ፣ በደም የተዋሐደ አንድ ህዝብ ነው ። ነገር ግን የሁለቱ ህዝብ መቃቃርና ጥላቻ እንዲሰፍን በርካታ የተሳሳቱ የታሪክ ሴራዎች በተለያዩ የታሪክ አተላ ግለሰቦች ሲሸረብ ቆይተዋል። እንደ ተሰፋዬ ገብረአብ በመሰሉ የታሪክ ደላሎችና ሴረኛ ተላላኪዎች የቡርቃ ዝምታ የመሳሰሉ ውዳቂ መፅሐፍትበመፃፍ የአማራ ህዝብ እና የኦሮሞ ህዝብ ዝንተዓለም በቂም በቀል ጨለማ እንዲኖር ለማድረግ የተፈፀመ ሴራ በህግ ተጠያቂ ያደርጋል ። ሁለቱም ህዝቦች ባልፈፀሙት ታሪክ እንዲቃቃሩ ታሳቢ ያደረገ ሴራ ለማንም የሚበጅ አልነበረም ። ይልቁንም ለሰላም እጦት ምክንያት ሆኖ ዘልቀዋል ። ኦሮሞ ተገንጣይ ፣ አማራ ወራሪ እየተባለ ህዝቦች በመጠራጠር መንፈስ እንዲኖሩ ማድረግ ተገቢነት አልነበረውም ።የቡርቃ ዝምታ መፅሐፍ ደራሲ ተሰፋዬ ገብረአብ እድገት ከኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ቢሆንም የአማራ ህዝብ የኦሮማ ህዝብ ሲበደል እንደነበር በመረጃ አስደግፎ ማቅረብ የማይችል ነቀዝ እንዲሁም ንፉግ ሰው ነው ። ለበርካታ አመታት የአማራ ገዢ እየተባለ ስለአማራ ህዝብ ክፋትና ሴራ ማብዛት ላይ ሰፊ የሴራ ተግባራት ሲፈፀም ቆይተዋል። ይህ የተሳሳተ የታሪክ ትርክት የሚያራቡ የሴራ ፖለቲካ አራማጅ ግለሰቦች አገር አፍራሽ ሥራ ሲፈፅሙ ቆይተዋል። የአማራ ገዢ አልነበረም ። የአማራ ገዢ ጭቆናም አልነበረም ። ጨቋኝ ገዢዎች ዘር አልነበራቸውም ። የሁሉም ጎሳ ጨቋኝ መሪዎች ነበሩ ። በመሆኑም የአማራ ህዝብ ዘር ራሱ ተጨቋኝ እንጂ ጨቋኝና ገዳይ ህዝብ አልነበረም ። የአማራ ህዝብ በማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ያደረሰው የአስተዳደር ጭቆና አልነበረም ። የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ የዳበረ የመልካም ተግባር ተምሳሌት ያለው አቃፊ እንጂ አግላይ ህዝብ አይደለም ። ሆኖም አያውቅም ።

በህዝብ ሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪነት ሰም ማህበራዊ መገናኛ ዘርግቶ የራሳቸው ገቢ የሚያሰባስቡ ግለሰቦች ለአገር ግንባታ ፣ለህዝቦች መቀራረብ ፣ ለመልካም አሰተዳደር ፣ ለፍትህ መጠንከር ፣ ለህግ በላይነት ፣ ለተቋማዊ ዲሞክራሲ ከመቆርቆር ይልቅ የግል እርባና በሌላው የግል ጠባብ ፍላጎት ተኮር አገር አፍራሽ ፣ ህዝብ በታኝ ተግባራት ላይ መረባረባቸው አሳዛኝ ነው ። የኦሮሚያ ማህበራዊ መገናኛ ( Oromia Media Network ) ባለቤት ኦቦ ጃዋር መሐመድ በታሪክ ፈጠራ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ እንዲሰፋ የሚጥር ፣ የሚሰራ አውደልዳይ ሰው ነው ። ይህ ሰው መጠኑ የማይታወቅ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጅ ካልሆኑ የአረብ አገሮች በሚሰጠው ድጋፍ እየታገዘ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም እንዳይኖር የዘረኝነት ጥላቻ የሚዘራ ሴረኛ ሰው ። ኦቦ ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ህዝብ ሰም የሚነግድ አትራፊ ነጋዴ ነው ።ኦቦ ጃዋር መሐመድ በኦሮሞ ህዝብ የሚሰበሰበው ገንዘብ ወጪና ገቢ የሚቆጣጠረው ራሱ በመሆኑ ከፍተኛ የገንዘብ ሰርቆት እንደሚፈፀም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ያሰረዳሉ ። ኦቦ ጃዋር መሐመድ ራሱ ሌባ ሆኖ ሳለ የመንግሰት አመራሮች በሌብነት የመፈረጅ ብቃት እንደሌለው ይነገራል። አይጥ ባጠፋው ዳዋተመታ እንደሚባለው ጃዋር መሐመድ በሚዘራው የዘር ግጭት ሴራ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሰተዳደር የህዝብ ወቀሳ ይደርስበታል ። ኦቦ ጃዋር መሐመድ በሚያሰራጨው የዘር ጥላቻ ዜና ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል ። ይህ ሰው የዘር ጥላቻ መርዝ መርጨቱን መገታት አለበት ።

በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን መንግስትና ህዝብ መደማመጥ ይኖርባቸዋል ። የሰላም መደፍረስ አንዱ ምክንያት የፖለቲካ አሰተዳደር አካሔድ ነው ። በሁለት ዘር የሚመራ የፖለቲካ አሰተዳደር በኢትዮጵያ ሰላም ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፍን አያደርግም ። በመሆኑም የኦሮማራ የፖለቲካ አሰተዳደርና አካሔድ በአጭር ጊዜ አገራዊና ተቋማዊ መሆን የግድ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ ። ካልሆነ ግን የሰላም መደፍረስ በተጋነነ መጠን በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የመከሰቱ ጉዳይ የማይቀር ይሆናል ።ይህ የኦሮማራ የዘር ጥምረት ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ውስጣዊ መረጋጋት አብይ እንቅፋት በመሆኑ ከዘር መሥመር ተላቆ አገራዊ ይዘትና ቅርፅ እንዲኖረው ማድረጉ በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታ እንዲያብብ ያደርጋል ። ተቋማዊ የፖለቲካ ቅርፅ የሌለው አገር ሁሉ ጊዜ የውስጥ ሰላም እጦት ተጋላጭ ይሆናል ። በኢትዮጵያ እያጋጠመ ያለ የውስጥ ችግር መነሻው በህግና መርህ ላይ የቆመ ተቋማዊ የፖለቲካ አሰተዳደር ያለመኖሩ ነው ። አሁንም በህጋዊ የዲሞክራሲ ተቋማዊ መተዳደር ካልተቻለ የህግ የበላይነት ሆነ ፍትሀዊ ፍትህ በኢትዮጵያ ሊያቆጠቁጥ የሚችልበት ሁኔታ የለም ።

የኢትዮጵያ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት ለማሰፈን ከዚህ ቀደም የተፈናቀሉ ዜጎች ሙሉ የሞራልና የንብረት ካሳ ተከፍሏቸው ወደነበሩበት ሥፍራ ሲመልሱ ፣ መንግስት የህግ በላይነት በብቃት ሲወጣ ፣ ዜጎች እንዳይፈናቀሉ የሚያግድ ህገ ደንብ ሲደነግግ ፣ የሴራ ፖለቲካ ሲያከትም ፣ የመንግስት ግልፅነትና ተጠያቂነት ሲኖር ፣ የዲሞክራሲ ተቋማዊ በገለልተኛ ምሁራን ሲመራ ፣ የህግ ተቋማት ከመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ ሲሆኑ ፣ ህዝብ በነፃ ሀሳቡ መግለጽ ሲችል ፣ ያለ ህጋዊ መሠረት የዜጎች እስራት ሲያበቃ ይሆናል ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሰተዳደር በነፃ ፕሬስ መስክ የወሰደው የማስተካከያ እርምጃ የሚበረታታ በመሆኑ ህግን የማስፈን ተግባርም መጠናከር ይኖርበታል ። የዘር ጥላቻ ለመቀነስ የዘር ተኮር ፖለቲካዊ አወቃቀር በምርጫ ቦርድ መታገል ይኖርበታል ። የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያን ቁልቁል የሚንድ በሽታ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው ። ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል አንዱ ምክነያት ሁሉም ለራሱ በማድላቱ የተከሰተ ማህበራዊ ውስብስብና ምስቅልቅል በቀላሉ በአጭር ጊዜ እልባት የሚያገኝ ጉዳይ አይደለም ።

በላፉት የታሪክ ክስተቶች ላይ ተመርኩዞ ለቀጣይ አዲስ ለውጥ መሰለፍ እንጂ እንዲህ ነበረ እያሉ ጊዜ ማባከን ግብዝ ከመሆን ያለፈ አይደለም ። ወደፊት እንጂ ወደኋላ ማሰብ የሚያመጣው አገራዊ ለውጥ አይኖርም ። የትላንት በትላንት ሒሳብ መዝጋት ብልህነት ነው ። የኦሮሞ ህዝብ ሆነ የአማራ ለኢትዮጵያ ህልውና ቀጣይነት ከፍተኛ ሚና ማበርከት የሚችሉ ህዝቦች በመሆናቸው ከዘር ፖለቲካ መላቀቅ ይኖርባቸዋል ። ከዘር ፖለቲካ በፀዳ ለሚያከናውኑት አገራዊ ተሳትፎ እንዲበረታቱ ማጋዝ የሁሉም ዜጎች አገራዊ ሀላፊነት ነው ።

 

 

 

Back to Front Page