Back to Front Page

የሑመራ ኡምሃጀር መንገድ መዘጋትና የለማና ገዱ ሹመትበአጋጣሚ ወይስ በዕቅድ?

የሑመራ ኡምሃጀር መንገድ መዘጋትና የለማና ገዱ ሹመት በአጋጣሚ ወይስ በዕቅድ?

 

ኡስማን ሙሉዓለም፣ ከሓራ ገበያ 4-19-19

 

የኤርትራና የኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ከተደረገ ወዲህ በሁለቱ ህዝቦች በኩል ብዙ ርቀት የሄደ መልካም ግንኙነት ተፈጥሯል።ቡሬ፣ዛላንበሳ፣ሑመራ-ኡምሃጀር መስመሮች በመከፈታቸው ህዝቡ ደስተኛ ነበር። በባድመ አቅጣጫ ግን የሁለቱም አገር ህዝቦች በግፊት ለመገናኘት ያደረጉት ሙከራ አልተሳክም፡፡ የሁለቱ አገር መሪዎች ቡሬ፣ዛላንበሳ፣ሑመራ-ኡምሃጀር ሂደው ቡራኬ አድርገው እንደከፈቱት እዚህም መጥተው ይከፍቱት ይሆናል ብለው ሁለቱ ህዝቦች ቢጥብቁ ምንም ለውጥ ሳይደረግ ቆይቷል።በኢሳያስ ወታደራዊ አዛዥች ከባድ ማስጠንቀቅያናሌላ ጊዜም ድርሽ እንዳትሉ!በሚል ማስፈራርያ እስካሁን አልተከፈተም።

 

የኤርትራና የኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ከተደረገ በኃላ ሁለቱ ህዝቦች ፍፁም ልባዊና ወንድማዊ በሆነ መንፈስ እየተገናኙ የደራ ገበያ ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ ነበር።ግን በተደጋጋሚ የሚታይ ችግር ይከሰታል።ይህም ስምምነት ተደረገ ከተባለ ጀምሮ የልጆች ጫወታ ይመስል ኢሳያስ ሲያሰኘው ህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ባልታሰበ ጊዜና መስመር በድንገት ዘግቸዋለሁኝ ሲል ቆይቷል። ለወደፊቱ እንዴት እንደሚቀጥል ደግሞ የምናየው ይሆናል፡፡ ከዚህ ጉዳይ በተያያዘ ሁኔታ ሰሙኑን ደግሞ ሁለት ክስተቶች ተፈፅመዋል።

Videos From Around The World

 

አንደኛው የኤርትራው መሪ ኢሳያስ ሑመራ-ኡምሃጀር መስመር እንዲዘጋ አዘዘ።ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያው መሪ አብይም ውጭጉዳይና መከላከያ ሚኒስተር መስርያቤትን ይመራሉ ብሎ ገዱና ለማን ሹሟል።ይህ ክስተት አጋጣሚ ወይስ ታቅዶ ታስቦበት የተደረገ ነው?በሁለቱ ክስተቶች መካከል ግንኙነት ይኖረው ይሆን?

 

ገዱና ለማ ሲያስተዳድሩዋቸው የነበሩት ክልሎች ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ሳያሳፍኑና የህዝቡን በርካታ ጥያቄዎች መልሰው እውነተኛ የለውጥ ሃዋርያነታቸውን ሳያስመስክሩ መነሳታቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡ ምስክር መጥራትም አይጠይቅም፡፡ ክልሎቹ አሁን ያሉበት ሁኔታ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል።ይሁንእንጂ ግጭትና ሞት መፈናቀል ስደት የሚታይባቸው ክልሎች ትተው አሁን ድግሞ ትላልቅ ሚኒስተር መስርያቤቶች ሊመሩ ተሹመዋል።ለምን? ለሚል አገሪትዋስ ያው የነሱ ብጤ አይደለም እየመራት ያለው ካልተባለ በስተቀር የሹመቱ ምስጥር ሌላ መሆን አለበት።

 

ሁለቱምሰዎቹ የክልል መሪዎች ሆነው በዳር ድንበር ከማያገናቸው አገር አስመራ ሂደዋል ከኢሳያስምጋር በተደጋጋሚ ተገናኝተዋል።ምን እንደተነጋገሩ ማንም አያቅም።መገመት ግን ይቻላል።ነገር ግን ግምት ግምት ስለሆነ ግምቱን ትተን ሌላ ሃቅ ብናይ ይሻላል።ሁለቱ ሚኒስቴር መስርያቤቶች ከኤርትራ ጉዳይ በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸው ግን የተረጋገጠ ሃቅ ነው።

 

ወደ ኤርትራ ስንዞር ደግሞ ሌሎች ሃቆችን መዳሰስ ይቻላል።የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የነበረውን ችግር ፈታሁ፣ ሰላም ወረደባለበት ወቅት ኢሳያስ ግን በሌላ መንገድ እየነጎደ ነው፡፡ በግድ ወጣቱን እያፈሰ ሳዋ /ወታደራዊ አገልግሎት/ ስልጠና መስጠቱን አጠናክሯል፣ ክፍለጦሮቹም ስልጠና አላቃረጡም፣ለኤርትራ ህዝብና ለሰራዊቱ የተጠናከረና ተከታታይ ስብሰባዎች ሲያካሂድም ሰነባብቷል።በየስብሰባው በኢትዮጵያ የተያዘብን መሬት በማንኛውም መንገድ ማስመለስ አለብን ተብሏል።ህዝቡ ደግሞ በማንኛውም መንገድ የምትለውን የኢሳያስ መንገድ ተቃውሞ በሰላምና በሰላም ብቻ ብሏቸዋል።ይሁንእንጂ ኢሳያስ የህዝቡ የሰላም ጥያቄ ወደጎን ትቶ የሰራዊቱ ዝግጅት ላይ አጠናክሮ ቀጥሎበታል።አሰብ ግንባር ከነበረው ሰራዊት አብዛኛውን ወደ ባርካ (ምዕራብ) አንቀሳቅሶታል።ይህንንም ሱዳን ላይ እየተካሄደ ካለዉ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማስመሰል /deception/ሙከራ እያደረገ ነው።በምዕራብ በኩል ወታደራዊ ሓይሉን ሁለት እጥፍ አሳድጎታል።ሃቁ ይህ ነው!በፈለገበት ሰዓት ወረራ ፈፅሞ በህግ የተወሰነልኝን መሬት አስመለስኩኝ ቢል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር- አብይ!፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር- ገዱ! የመከላከያው ሚኒስተር- ለማ! ምን ግብረመልስ ይኖራቸዋል?በኢትዮጰያን በኩል ዐንጃ

 

በሌላ አቅጣጫ የኢሳያስ መንግስት በኤርትራ ህዝብ ለምን በተጀመረው ሰላማዊ መንገድ አያልቅም? ተብሎ ሲጠየቅ ወያኔ እምቢ ስላለን ምንም አማራጭ የለንም! ብላል።ህዝቡም ታድያ በጦርነት ምን ያህል ነው በእርግጠኝነት መሬታችንን ማስመለስ የምንችለው? የኢትዮጵያ ሰራዊት ዝም ብሎ ያየናል ልንል እንዴት እንችላለን?ብሎ ደግሞ ሲጠይቃቸው ደህና!የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትይደግፈናልበማለት የሚገርም መልስ ሰጥል።

 

 

ይህ መልስ ከየት የመነጫል?ከሁለቱ መሪዎች ስምምነት ይሆን?ይህ በሁለቱ መሪዎች በአስመራ በኃላም በሳውዲአረብያና በኤሜሬት የተደረገ ስምምነት ከሁለቱ ሰዎች በስተቀር ሌላ አውቃለሁ የሚል የለም፡፡ የሁለቱ አገሮች ካቢኔዎች፣ ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮችና የህዝብ ተወካዮች አያውቁትም፡፡ ስምምነቱ ለሁሉም ይፋ ባልሆነበትና የሁለቱም አገር ህዝብ በጦርነቱ ልጆቹን የገበረበትና የተሳተፈበት ይሁንእንጂ ሰላሙ እንዴት ዘላቂ እንደሚሆን በመወሰኑ ላይ ድርሻው ተነፈጎታል፡፡ የስምምነቱ ሰነድ ላይ ዕውቀትም፣ ተሳትፎም፣ አስተያየትም አልሰጠበትም።ታድያ ማንም በይፋ ባላወቀበት ሁኔታ እንዴት ወያኔ ተቃወመው ይባላል!ሊቃወመውም ሊደግፈውም በቅድሚያ ሲያቀው አይደለም እንዴ?

 

የዚህ ሁሉ ችግር ኢህአዴግ ባስቀመጠው የሰላም ሰነድ ግልፅነት ላይ ተመስርቶ ስምምነቱ ባለመሄዱ ነው።ጉዳዩ አብይ የግሉ ተነሳሽነት ስላስመሰለውና የተቀመጠለት አቅጣጫ ትቶ ሌሎች የውጭ ሃይሎችን በሚያስደስት ብቻ ስለተቃኘ የተፈጠረ ችግር ነው።በኢሳያስ በኩልም ሆን ብሎ ወያኔን ለማግለል ስምምነቱ አቅዶ ፈፅሞት እያለ አሁን ስምምነታቹህ ግልፅ አይደለም ተብሎ በህዝቡ ሲጠየቅና ጫና ሲገጥመው game over (ወያኔ አለቀለት) እንዳላለ አሁን ወያኔን ተጠያቂ ማድረግ አይችልም።

 

ስለዚህየሚሻለው ኢሳያስ ሆይ! ከአብይ ጋር ምን ምን እንደተባባለችሁና ምን እንደተስማማችሁ ለሁለቱ አገሮች ህዝብ በግልፅ መጀመርያ ራሳችሁ ቀርባችሁ አስረዱ።ሰነዱንም ይፋ አድርጉ እንጂ ሌላ ላይ አታሳብቁ።

 

ለማጠቃለል እነዚህ ሰሙኑን የተከሰቱ ሁለቱ ነገሮች ከአጋጣሚነታቸው በላይ ዕቅድነታቸው ሚዛን ይደፋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ከነቤተሰባቸው ባልታወቀ ቦታ መሽገው ያሉት ገዱ አብይ ቲምሜቴ ጉድ አደረገኝ! ሳልሰማ! ሳላስበው! surprise! አደረገኝ ይሉን ይሆናል።ቀልዱበት ይህን ምስኪን ህዝብ።

 

 

ኡስማን ሙሉዓለም፣ ከሓራ ገበያ

ሚያዚያ 2011ዓ.ም.

Back to Front Page