Back to Front Page

የጃዎር ኪንግደም

የጃዎር ኪንግደም

ከማህፍቅ 8-12-19

አስታውሳለሁ በአገሪቱ ውስጥ በተለይም በኦሮሚያ አከባቢ የተነሳው ተቃውሞ ለማርገብ ኢህአደግ የተለያዩ ነገሮች ቢሰራም እንደፈለገው ሊሳካለት ባለመቻሉ ህወሓት ቀደም ብሎ ለውጥ መምጣት አለበት በማለት ረዘም ላሉ ቀናት በጥልቀት ተወያይቶ አመራር ለውጥ በማድረግ ወደ ኢህአደግ ተመለሰ፡፡ ሌላው ቀጠለና በዚሁ መንገድ ለውጥ በሚል ስም የአመራር ለውጥ በማድረግ ነባር ታጋዮች እና አመራሮች ከአመራርነት አስወገዱ፡፡

ኢህአደግ በወቅቱ የወሰደው የመፍትሄ ሀሳብ ኦሮሚያ በሚባለው ክልል የተነሳውን ችግር ለመቅረፍ የአመራር ለውጥ በማድረግ በተለይም ከኦሮሞ የወጣ መሪ በመምረጥ ፍቱን መዳኒት በማድረጉ ሁሉም ተስማምቶ ደ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መጣ፡፡

እንግዲህ የእውነት የሰውየው ወደ ስልጣን መምጣት ያስደሰተው የህብረተሰብ ክፍል ከፍተኛ ሲሆን ይህም አብይ ከንግግሩ በዘለለ የፊቱ ቅርፅ በቀላሉ በሰው ልብ ለመግባት አግዞታል፡፡

ደ/ር አብይ አህመድ የሁሉንም ልብ እያሸነፈ በመልካም መንገድ መሄድ ከጀመረ ቡዙም ሳይቆይ የልቦች ክፍፍል በተለያዩ ቦታ አከባቢ ማስከተል ጀምሯል፡፡

በወቅቱ የሆነውን ለማስታወስ ሁለት ክንፍ ነበሩ

Videos From Around The World

የመጀመሪያው ክንፍ የተቃዋሚ ረድፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን በአብዛህኛው ጥላት መሰረት አድርገው የተነሱ፣ ህወሓት ላይ ተንጠልጥሎ በአገኙት መንገድ እና መድረክ ህወሓትን ለመበቀል አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዱ የነበሩ ናቸው፡፡ ከእርምጃዎቹ መካከል መሳሪያ በማንሳት ጦር መግጠም፣ ታላላቅ መሰረተ ልማቶች እንዲወድሞ ማድረግ እንዲሁም በገንዘብ ረገድ ከፍተኛ ጫና ማሳደር ናቸው፡፡እውነት ለመናገር ድርጊታቸው ከፍተኛ የህብረተሰብ ችግር ያስከተለ መሆኑን እና አሁንም ላለው የጥላቻ መንፈስ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው እና እናዳለው ማንም እንደማይገነዘበው ተረጅቻለሁ፡፡

ምሳሌ እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በራሰችን ይህን ያህል ጥላቻ አልነበረንም፡፡ ቀጠለና ኢህአደግም ቢሆን በፈጠረው የክልል መዋቅር መሰረት ተደርጎ የነበረው የጥላቻ መንፈስ በጣም ዝቅተኛ ነበር፡፡እርግጥ ነው በቋንቋ ምክንያት ተግባብቶ መስራት ከባድ መሆኑን መረዳት ብንችልም፡፡የፀረ ህወሓት ሚድያዎች ፣ ነፍጥ ያነሱ ተቃዊሚዎች እንዲሁም መሰል ድርግቶች ዝም ብሎ የነበረው ሰው እርስ በእርሳችን እንድንጠላላ መሰረት መጣል ጀመሩ፡፡ የጥላቸው ነፋስ በስፋት ተሰራ፤ በዚህ መንገድ የመጣ የጥላቻ መንፈስ ካለው ክልላዊ መዋቅር ጋር በፍጥነት ለሜሄድ ምንም አላገደውም ነበር፡፡

ስለዚህ ደ/ር አብይ ሁሉንም በተቃውሞ ረድፍ የነበሩት ሰዎች ስነ ልቦና አሸነፈ፤ እንዴት ከተባለ እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በማድረግ፡፡ ለምሳሌ የነበረውን መንግስት ማቆልሸት፣ "ገበናውን" ማውጣት ወዘተ በማድረግ፡፡

 

 

ሁለተኛው ክንፍ ደግሞ የነበረው አመራር በተለይም ነባሩ ኢህአደግ ነው፡፡

ይህ ክንፍ ስነ ልቦናው ለመፍትሄ ብሎ የለቀቀውን ፖለቲካ መድረክ ተወቀሰበት፣ ተባረረበት ብሎም "ታሰረበት"፡፡ ስለዚህ ይሄኛው ክንፍ ምንም እንኳን ደ/ር አብይ ጥበበኛ ሰው የነበር ቢሆንም ነገር ግን የዚህን ክንፍ ስነ ልቦና ማሸነፍ አልቻለም፡፡

ሁለቱን ክንፍ ደግሞ ማስማማት ካልተቻለ አሁንም የነበረው ችግር ፊቱን አዙሮ እንደሚጣ ሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አልመጣም ማለት ነው፡፡

ህወሓት እዚህ ላይ እንደተሸወደ ማሰብ የሚከብድ ነገር አይደለም፡፡እኔ ማንም በቅንነት መሸወድ ይችላል ሁለተኛ ጊዜ ግን ተመሳሳይ ጥፋት ማጥፋት ግን በአጭሩ የዋህነት ነው፡፡ የዋህ ሰው ሁልጊዜ ልትሸውደው ትችላለህ ምክንያቱም ልቡ ቅን ስለሆነ በፖስቲቭ ይወስድላሃል፡፡ህወሓት ግን የዋህ ሆኖ አልጨረሰውም በሶስተኛ ብልጥ ሆኗል፡፡እንግዲህ ትክክል ነው አይደለም የሚለው ይቆይና ህወሓት በመጀመሪያ በቅንነት ስልጣኑን ለኦሆዴድ አስረከበ ፤ ቀጠለና የነበሩት ከፍተኛ የደህንነት ሰዎች ፣ የመከላከያ አመራሮች እንዲሁም ቁልፍ ሰዎች ሲባረሩ አሁንም በየዋህነት አለፈው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ እስከመቸ ብሎ የትግራይን ህበዝብ ለሁሉም ነገር እንዲዘጋጅ አደረገው፡፡

እርግጥ ነው ሶስተኛ ደረጃ ሳይደርስ በሁለተኛው የደ/ር አብይ ሪፎርም ላይ ህወሓት ተቀባይነቱን ማሳደግ ይችል ነበር፡፡ምክንያቱም ወሳኝ የሀገሪቱ ቦታዎች በስሩ ስለነር በቀላሉ በዙ ሳይለፋ ህብረሰተሰብ ላይ ሳይደረስ የፈለገውን ማድረግ የችል ነበር፡፡

ለማንኛውም የሆነ ሆነ እና የመጀመሪያው ክንፍ ላይ ከነበሩት ተቃዊሚዎች መካከል የጃዋር ድርሻ ከፍ ብሎ ነበር እና ወደ ፊት መምጣት ጀመረ፡፡ጃዋር ማንም ሊነካው የማይችል ፣ እነደ ፈለገው ዲሞክራሲን ከጥግ እስከ ጥግ መጠቀም የቻለ ብቸኛው ሰው መሆን ጀመረ.፡፡ ሄዶ ሄዶ እና እውነት ያሻውን ማድረግ የሚችል ፣ ሰው እንዲያምፅ ከፈለገ ማድረግ የሚችል በጋርዶች ታጅቦ ሜሄድ የሚችል ፤ የተናገረው የማይጠፋ ፣ ቃሉ የማይታጠፍ ፣ የማይነካ ብሎም የሚፈራ ብቻ ምን ልበላቸው ንጉሳዊ ሂይወቱን በኦሮሞ ጫንቃ ላይ መሰረት አድርጎ መኖር ጀመረ፤ ቀጠለ፡፡

የጃዋር ኪንግደም በሚገርም ሆኔታ ከአብይ መሪነት ጋር አንድ ላይ የነገሰ ሲሆን በዋነኝነት ቀደም ሲል ያራምዳቸው የነበሩትን መሰረታዊ አላማውን ማሳካት ቀጠለ፡፡

የጃዋር ኪንግደም መሰረታዊ ምሶሶች እና ተግባራት፡

ሲነሳ ሀይማኖት መሰረት አድርጎ የመጣው ጃዋር ቀጥሎ ኦሮሞ የሚባል ማህበረስብ አቅፎ ፤ ቆሮን እግረኛ ሰራዊቱ አድርጎ ወደ ንግስናው ሲመጣ በመሰረቱ ለህዝብ የማይታዩ ስራዎች በማቀድ እና በማስፈፀም ለውጡን እየነዳው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ስራዎቹ ዋንኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.   የኦሮሞ ሰው ወደ ፊት እንዲመጡ ማድረግ ፡ ይህ ዕቅዱ በቀላሉ ለማስፈፀም ምንም የከበደው ነገር አልነበረም፡፡ ምክንያቱም አብይ ደብዳቤ ይፅፋል በአንድ ብጣሽ ወረቀት ጀነራሎቹ ይባረራሉ፣ ይሸሻሉ፣ በምትኩ የኦሮሞ ተወላጅ ይይዛቸዎል፡፡እኔ የሚገርመኝ የለቀቁ ሰዎች ለመንግስት ምን ያክል ታምኝ መሆናቸው የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ ጦርነት ቦታ ሁለት ጠላቶች ሊጋደሉ ቁመው አንዱ ቦንብ ይዞ አንዱ እስክሪቢቶ ይዞ እስክርቢቶ የያዘው ሰው ቦንብ ለያዘው ሰው በደብዳቤ ቦንብህን ጣል ብሎ ፃፈለት እሱም እሺ ብሎ ተማረከለት አለቀ፡፡እንዲህ እንደማለት ነው የሆነው፡፡

2.   የኦሮሞ ህብረተሰብ በሚገባ ማደራጀት፡ የኦሮሞ ተወላጅ በስራም ቅድሚያ እንዲያገኝ በማድረግ ህብረተሰቡም አዲስ አበባ ላይ በስፋት በማስፈር ዲሞግራፊ ለውጥ በፍጥነት እንዲመጣ ማስቻል ነው፡፡እንዲህ ሲባል ውሸት ይመስላል ግን እውነት ግን ከልብ እየተሰራበት ነው፡፡

3.   የኦሮሞ ቋንቋ የዲሞግራፊ ለውጡን ዋንኛ መሳሪያ ማድረግ ነው፡ ቋንቋ መሰረታዊ የዲሞግራፊ ለውጥ መሳሪያ እንደሆነ መገንዘብ ቀላል ነው፡፡ ሰው አፉን በፈታበት ቋንቋ ዘሩ የፈለገ ቢሆንም በሂደት የተናገረው ቋንቋ ባለቤት ይሆናል፡፡ይህን ለመረዳት ሴሜቲክ የተባለው ኢትዮጵያ ክፍል በዋነኝነት የቋንቋ መነሻቸው እንኳን በጥልቀት ማየት ባይቻልም በቅርቡ ጊዜ ሂደት መሰረት ግን ከግዕዝ ነው፡፡ ትግርኛ ፣ አማርኛ እንዲሁም ጉራገኛ ምንጫቸው ግዕዝ ነው ማለት ነው፡፡ በሂደት እነዚህ ቋንቋ ባይፈጠሩ ንሮ የነበረው ህብረተሰብ በአንድ ቋንቋ መግባባቱ ይቀጥል ነበር፡፡ የዘረኝነቱ ሆኔታ በተነፃፃሪ ይቀንስ ነበር፡፡ነግር ግን በቋንቋ ተከፋፈሉ አሁን ምን ያክል ጥላቻ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል፡፡ስለዚህ አዲስ አበባ በአብዛህኛው አማርኛ ተናጋሪ ነው፡፡ ከትውልድ በፊት ምናልባች ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ግን አማርኛ ልጆች አፍመፍቻቸው አድርገው ስለተነሱ ይህንን ቋንቋ በስፋት እባዙት ቀደም ብሎ የነበሩ በመዋለድ የመጡ ቋንቋዎች እየጠፉ ሂደዋል ወይ ይሄዳሉ ማለት ነው፡፡ስለዚህ የሀገሪቱ እምብርት የሆነችው አዲስ አበባ የእኛ ናት በማለት ለውጥ አይመጣም፡፡ ፊንፊኔ ከኛ እያልክ የሚመጣ ለውጥ የለም፡፡ነገር ግን እውነት ለውጥ ለማምጣት ትውሉዱን መቀየር ዋንኛ ስትራቴጂ ነው፡፡ ይህም ትምህርት በኦሮመኛ እንዲማር ዕድሉን በማመቻቸት፣ ህብረተሰቡን በመለወጥ እንዲሁም የስራ ቋንቋ በመለወጥ ደሞግራፊን መለወጥ ይቻላል፡፤ ደሞግራፊው ከተለወጠ ደግሞ አዲስ አበባ ኬኛ የአውነት ይቻላል፡፡ የአሁኑ የኦሮሞ ልጆች ከጥንት የኦሮሞ መስፋፋት ጋር የሚለዩት ሲስተማቲክ ( ታክቲክ እና ስትራቴጂ ይለዋል ጃዋር) መጠቀማቸው ነው፡፡ አብይ ኢትዮጵያን ቀርቶ ሌሎች አፍሪካ አገራት ወደ እርቅ እንደሚጡ ማድረግ የቻለ ሰው ኢ/ያን ማረጋጋት ከበደው ብሎ መደምደም ዘበት ነው፡፡ በሌላው አጄንዳ ይሄኛው አጄንዳ መፈፀም መቻሉ ነው፡፡

እንደው ስለ ቋንቋ ካነሳን አይቀር ገቢዎች በተለይ አየር መንገድ ካርጎ ላይ የሚሰሩ ፣ የከተማዋ ፖሊስ አባላት እንዲሁም አብዛህኛው የፌደራል ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች እንዲሁም መከላከያ ሚኒስተር ብሎም መሪዎቹ በሙሉ የስራ ቋንቋቸው በኦሮምኛ ሆናል፡፡

ይህ በአጋጣሚ የመጣ ከመሰሎት የዋህነት ነው፡፡

4.   እስልምናን ወደ ፊት ማምጣት ነው፡ ለጊዜው ከጃዋር ኪንግደም ዕቅዶች የገባኝ እና የደረስኩባቸው ከላይ ካሉት በተጨማሪ እስልምናን ሃይማኖት ወደ ፊት ማምጣት ነው፡፡ የአ/ያ ታሪክ በክርስትና የተመሰረተ በመሆኑ ይህን መፋቅ እና መለወጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የእስልምና ተከታይ የሆኑ አመራሮች ወደ ፊት በስፋት ማምጣት፣ እስልምናን የሚወክሎ ነገሮች በስፋት መፍቀድ ምሳሌ መስግድ ማስፋፋት፣ እስልምና ባንክ መክፈት እንዲሁም ልዩ እውቅና መስጠት የመሳሰሉትናቸው፡፡
በነገራችን ላይ እስልምና ባንክ መፈቀዱ እውነት በጣም የተሳሳተ ውሳኔ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደ ፊት ሁሉም ሀይማኖቶች የራሳቸውን ባንክ ካልከፈትን የማይሉበት ጊዜ ሳይመጣ ውሳኔው መታጠፍ አለበት፡፡ ምክንያቱም የንግድ ባንኮች ለእስልምና ሃይማኖት የሚሆን ሆኔታ ካመቻቹ ለምንድነው ሰው ከብሄር አልፎ በሀይማኖት እንዲከፋፈል የሚደረገው፡፡ አይ ጃዎር ለካ አንተ ለጊዜው የሚሳንህ ነገር ለካ የለም፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የተቀመጡ ስትራቴጂዎች በሂደት እየተሳኩ የማይመለሱበት ቦታ ሲደርሱ ሌላው ኢትዮጵያ ክፍል በሃይ ሆነ በግድ ሰላሙ ይረጋጋል፡፡ እስከዛው ግን ይህ ይቀጥላል፡፡
ለዚህ ሁሉ መሆን ግን ህወሓት ምክንያት እንደሆነው ማለትም በቅንነት ሰላም እንዲመጣ አስቦ ስልጣኑ ሁሉ ኦሮሞ ሲቆጣጠረው ዝም በማለቱ የመጣ በመሆኑ ነው፡፡

ለማንኛውም ህወሓት የሌለበትን ፀባይ ጥገኛ መሆን የለባትም ድሮውም የትግራይ ህዝብ ለማንም ተገዝቶ አያቅም ፤ አሁንም መሆን የለበት ካስፈለገ እርምጃ መውሰድ ነው ፣ ካልሆነ ዝም ብሎ የሞሆነውን መቀበል ነው፡፡

አማራ ዲሞክራሲ ፓርቲ አዴፓ ግን አሁንም ተለጥፋል( አይ ደመቀ )፡፡

እውነት አማራ እና የትግራይ ዘሩም አንድ ነው እናም የእውነት ለአገር ሰላም እና መቀጠል ሲባል አንድ መሆናቸው በድጋሚ ሊያስተውሉት ይገባል፡፡የጃዋር ኪንግደም በሀይማኖቱም ቢሆን ቡዙም የማይቆይ በመሆኑ ወደ ማስተዋል ይገባ ነው የመጨረሻው ምክሬ፡፡

Back to Front Page