Back to Front Page

የሊቨር ፑል Game Over በምስራቅ አፍሪካ!

የሊቨር ፑል Game Over በምስራቅ አፍሪካ!

 

ኡስማን ሙሉዓለም፣ ከሓራ ገበያ

ግንቦት 2011..

ደርጎቹ ግንቦትና ወያኔን አይወዱም። ኢሳያስም ሰኔና ወያኔን አይወድም። ደርጎች የሚመሩት የለማ ቲም ለውጥ ለኢትዮጵያ በተለይም ለለውጡ በግንባር ቀደምትነት የተጋው የኦሮሞ ወጣት ቅንጣት ያህል ለውጥ አላስገኘለትም። ጥያቄው አልተመለሰም ብቻ ሳይሆን አንዱን እንካን ለመመለስ አልተሞከረም። ስቃዩ አልበረደለትም። ሌላውም ህዝብም ምንም የተረጋጋ ኑሮ መኖር አልቻለም። መፈናቀል ከአንድ ወደ ሁለት ከሁለት ወደ ሦስት ከሦስት ወደ ሽቅብ ሚልዮን ቁጥር እየወጣ ነው። የሚሞተው ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ዓይነቱም ከጅምላነት ወደ ጆኖሳይድነት እየተቀየረ ነው። የተፈጥሮ ልዩነት እንደ ንቅሳት ለማጥፍት የምትታትር አዲስ ከተሜ ለማጥፋት ሲሞክሩ ልዩነት እያሰፉ ነው።

Videos From Around The World

 

አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የጉዞ አቅጣጫው ወደ ማይታወቅ መዳረሻ በፍጥነት እየነጎዶች ነው። አርማጌድዮን በቅርብ ርቀት እየሸተተ ነው። የሊብያ፣ የየመንና የሶሪያ መዳረሻ መናኻርያ በቅርብ ርቀት እንዳለ አሻግረን እያየን ነው። ተባብሮ አገራችንን ማዳን እየተቻለ እኔ ከሞትኩኝ ብለው ገዥዎቻችን በስመ ለውጥ ሁኔታው ከመጥፎ ወደ ባሰ ውስብስብ ሁኔታ እየነዱት ነው።

በኤርትራና ኢትዮጵያ ደንበር በኢሳያስ ለሰኔ እየተሸረበ ያለውን ወረራ ለማመቻቸት ደግሞ በኛዎቹ የለውጥ ሃዋርያት በወርሃ ግንቦት ትግራይን ለማዳከም የህዝቡን አንድነት ለማፍረስና የመሪ ድርጅቱን ህወሓት ተቀባይነት ለማሳጣት የተለያዩ ተንኮሎች ሸርበው እየተንቀሳቀሱ ናቸው። የማለስለሻ ተኩስ መሆኑ ነው።

 

1983 ኦፕረሽን ቡሊስማ ብሎ ህወሓት ከኦፒዲኦና ከአንጋፋው ኦነግ ጋር በመሆን በአምቦና በወለጋ ከፋሽሽቱ ደርግ ነፃ ለማውጣት በዚቹ ወር ግንቦት ሲዋደቅ ነበር። ትላንትና! ዛሬ ደግሞ የደርግ ርዝራዦች ኦፒዲኦን ለማጥፋት ከውስጡ ከበቀሉ አረሞች ጋር በመሆን በግንቦት 20 ድባቅ የመታቸውን የኢትዮጵያ ህዝቦችን ያስተባበረው ኢህአዴግና ህወሓትን በያዝነው ወር ብድር ለመመለስ በውስጥም በውጭም አሲረው እየተንቀሳቀሱ ነው። የትግራይን መንግስት በጀት ከመቁረጥ ጀምሮ ትግራይ ላይ ወረራ በማድረግ ኮር አባላቱን ጠራርጎ ለመያዝ እየተንቀሳቀሱ ነው። የሚድያ ስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ኢኮኖሚያዊ አሻጥርና ከፍተኛ የማግለል ስራ ሲሰሩ ቆይተው በቅርቡ ደግሞ ወታደራዊ ኦፕረሽን በማድረግ ትግራይ ውስጥ መሽገው ያሉ ሲሉዋቸው የነበሩትና የፖለቲካ አመራሮች፣ ጀነራሎች፣ የጦር አዛዦችና የፌደራል ፖሊስ አመራሮችና ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸዉ፣ በተለይ ደግሞ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ቀን ተለሊት ሲሰሩና በህዝቡ ተወዳጅነትና አድናቆት ሲቸራቸው የነበረውን የድህንነትና መረጃ ሰራተኞችና ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸዉ ላይ ወረራ ለመፈፀም ተዘጋጅተናል እያሉ ነው። የግንቦት 20ን ታሪክ እንቀይራታለን እያሉ ነው።

 

ይህ ኦፕረሽን ይሳካ አይሳካ የትግራይ ህዝብና መንግስት ግን በዚህ አጀንዳ ወጥሮ መያዝ እንዳለበት ሆኖ ኢሳያስ ደግሞ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት የድንበሩ ጉዳይ በሰላም፣ በውይይትና በአደባባይ ሁለቱ ህዝቦች በግልፅ አውቀውትና ተሳትፈውበት ማለቅ ሲገባው Game Over! ያለው ህወሓት እንደ ሊቨር ፑል በሻምፕዮን ሊግ እንደገና ህይወት ዘርቶ ተጠናክሮ ስለወጣ በሰላም በውይይት አሻፈረኝ ሙቼ እገኛለሁ ብሎ በጦርነት ድንገተኝነት ተጠቅሞ የሚገባኝን ወስጃለሁ ሊለን ወስኖ ተዘጋጅቷል። ሰኔ የመረጠበት ደግሞ ክረምቱ ተሎ ደርሶ ሊገላገል ነው። ያለፉት ሰኔዎች ስላልቀኑት በዘንድሮው ሰኔ ታሪክ ለማደስ ነው። በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉንስ?

 

ግንቦት 20 የህዝቦች በዓል

ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች!

በስመ ለውጥ አገር እያፈረሱ ያሉ ይሸነፋሉ!

 

 

 

Back to Front Page