Back to Front Page

የመደመር ቀለም አብዮትና መዘዙ፡ ክፍል አንድ

የመደመር ቀለም አብዮትና መዘዙ፡

በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ እንደገና አዲስ የቀለም አብዮት እየተሸረበ ነው!

 

ክፍል አንድ

ዑስማን ሙለዓለም ከሐራ ገበያ

መስከረም 2012 /

 

መግብያ

የአብይ መንግስት በመደመር የቀለም አብዮት ስትራተጂና የታክቲክ ጥበብ እንቅስቃሴ እውን ከሆነ ድፍን ዓመቱ አሳልፎ ሁለተኛ አዲስ ዓመት በቤተመንግስት አክብሯል። በመጀመርያ አከባቢ የቀለም አብዮቱ መሪዎች፣ ቁልፍ ተባባሪዎቻቸው እና ተከታዮቻቸው በውጤቱ ጮቤ ረግጠው ደስታቸውን በሁሉም መንገድ ገልፀው ነበር። ይሁን እንጂ እንደ ሁሉም በዓለማችን የተፈፀሙ የቀለም አብዮቶች የድል ተገኘ ፈንጠዝያው ረገብ እያለ ሲሄድ ሁኔታዎች ከመቅፅበት ወደ ሐዘን ወይም ወደ ያልታሰበ ፈጣን የውድቀት ጉዞ እንደተቀየሩት የአገራችንም ፈንጠዝያ ወደ ዋይታ የተቀየረው ወዲያውኑ ነበር።

 

የዩክሬን ብርቱካናማው ቀለም አብዮትና የአረብ የፀደይ አብዮት በቱኑዝያ፣ በሊብያ፣ በግብፅ፣ በየመንና በሶርያ ያስከተሉት ሁኔታ ይህንኑ ነው፡፡ በየአገራቱ በቀለም አብዮቱ የተነሱት የዲሞክራሲና የዳቦ ጥያቄዎች እንኳን ሊመለሱ የነበራቸው ሰላም ማስፈን አልቻሉም፡፡ የቡዙ ሰዎች መፈናቀል፣ ስደትና ሞት የበዛበት፣ የሃብትና የንብረት ውድመት ያስከተለበትና ሀገሮች እንደ አገር መቆም አቅታቸው ብዙዎቹ የመፈራረስ አደጋ አጋጥማቸዋል፡፡ እንደ ግብፅ ያሉት ደግሞ እንደ አገር ቢቀጥሉም ወደ ዴሞክራሲ ሳይሆን ከሙባረክ ወደ የኮ/ል አሻግሬ ጌታ አል ሲሲ አምባገነናዊ መንግስት ይሸጋገራሉ። መሸጋገር ከሆነ።

 

ስለ ቀለም አብዮት በአጭሩ

የቀለም አብዮት በጥሩ ቀለሞችና ስሞች አሸብርቆ ከውጭ ታቅዶ፣ ተሰርቶ፣ ወደ ዒላማ የተደረገ አገር የሚመጣ አብዮት (imported revolution) ወይም ለውጥ ወይም ሪፍርም ነው፡፡ በመሆኑ በዘለቄታው ስኬታማ ሊሆን አይችልም። ከውጭ መምጣቱ ብቻ ግን ለውድቀቱ ምክንያት አይደለም። የሚጠቀምባቸው ስትራተጂዎችና ታክቲኮችም ስርዓት ለማፍረስ እንጂ ስርዓት ለመገንባት የሚዉሉ ስላልሆኑ በተካሄዱባቸው አገሮች አገር ለመገንባትና ዲሞክራሲ ለማስፋፋት ውጤታማ ሲሆኑ አይታዩም።

 

የቀለም አብዮት ባለቤቶች አክራሪ የኒዮ ሌበራሊዝም ሐይሎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሐይሎች የራሳቸው ጥቅም መሰረት አድርገው ተፅእኖ ለመፍጠር እንጂ ከልብ የሌሎች አገሮች ህዝብ ችግር አስጨንቃቸው ወይም ርህራሄ ስላላቸው የሚያቅዱት አብዮት ወይም ለውጥ አይደለም። የቀለም አብዮት የድሮው ቅኝ ግዛት ፍልስፍና ተቀጥያ የሆነና ዘመናዊ ቅኝ ግዛት መፍጠርያና ማስፋፍያ ዘዴ ነው። የራስህ ተላላኪ አሻንጉሊት መንግስት በመፍጠር የተፅዕኖህ አድማስ በዓለም ደረጃ ማስፋፋት ዓላማ ያለው ነው። የቀለም አብዮት የልዕለ ሐያላን አክራሪ ኒዮ ሌበራሎች ገበያቸውን ለማስፋት በሚያደርጉት ውድድር አሸንፎ ለመውጣት የባህል፣ የአይዶሎጂና የፖሊሲ ወረራ ማስፈፀሚያ መሳርያ ነው። ከራሻና ከቻይና ጋር ሆኑ/ ወገኑ ወይም ፖሊሲያቸው ለኛ አይመችም ብለው ከሚፈርጅዋቸው አገሮች ላይ ፈርደው የቀለም አብዮት ያፋፍማሉ። ለውጥ ብለው አገር የሚያፈርስ ነውጥ ይፈጥራሉ።

 

የቀለም አብዮት ቀያሽና ጠንሳሽ ሐይሎች የሚጠቀምቧቸው ሰዎችና ቁልፍ ተባባሪዎቻቸው የራሳቸው ጥቅም ብቻ አፍቃሪ ናቸው፡፡ እንኳን የህዝብ ፍቅር ሊኖሯቸው ተራ የአገር ፍቅርም የሌላቸው ምላስ አደሮች ናቸው፡፡ የማይታመኑ፣ በውሸትና በቅጥፈት የሚታወቁና በዶላር የተሸመቱ ስለሆኑ ቁርጠኝነታቸው ከግል ስግብግብ ዓላማ መፈፀም ያለፉ ስላልሆኑ ለማህበረሰብ መሰረታዊ ለውጥና ለዴሞክራሲ ግንባታ ከጉንጭ ማልፋት ያለፈ አይጨነቁም። እነዚህ ከላይ ከላይ የለውጥ ቀለም ከመቀባትና ከማንፀባረቅ አልፈው የሰፊውን ህዝብ ኑሮ መብት ጥያቄ አይቀይሩም። አይመልሱም።

 

የነሱ አቅም የሚያስጎመጁና የሚያማልሉ የቀለሞ አይነቶች ወይም ወቅቶችን ስያሜዎችን ማውጣት ነው፡፡ ለምሳሌ ብርቱካናማው አብዮት፣ የፀደይ አብዮት፣ የቀስተደመና አብዮት እና የመደመር አብዮት ብለው የህዝቡን ቀልብ ሰርቀው ስልጣን መወጣጫ ይጠቀሙበታል፡፡ ይሁን እንጂ እንደስሙ ለውጡ/አብዮቱ የቀለም መልክ እንጂ የቁምነገርና የይዘት ለውጥ የለውም። የነበረው የህዝብ መብትና ሀብት ያጠፉታል እንጂ ምንም አዲስ ጠብ የሚል የኢኮኖሚን የዲሞክራሲ ለውጥ አያስመዝግቡም። በለውጡ ስም ሁሉንም ነገሮች ባልተጠናና በውጭ ሐይሎች ትዕዛዝ ስለሚነካካ ያልታሰቡ ችግሮች እየተፈጠሩ ለውጥ መሆኑ እየቀረ ነውጥና የማያቋርጥ ቀውስ ውስጥ ይከታል።

 

ሚልዮኖች ዶላር ከውጭ በማፍሰስ ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣትና ዲሞክራሲ መትከል አይቻልም። ለውጥ ከውስጥ ካልሆነ ስኬታማ ሊሆን አይችልም። ቀላል ምሳሌ እንይ። ደሮ እንቁላሎች ታቅፋ ሙቀት ከራስዋ ወደ እንቁላለቹ በማስተላለፍ በቂ ሙቀት እንዲያገኙ ካደረገች በኃላ የተፈጥሮ ጊዜውን ጠብቆ ጫጩቶች ይፈለፈላሉ። ነገር ግን በእንቁላል ፋንታ የእንቁላል ቅርፅና መጠን ያላቸው ድንጋዮች በተመሳሳይ ሁኔታ ብናሳቅፋት የደሮዋን ሙቀት እያገኙ በመቆየታቸው ብቻ ድንጋዮቹ ጫጩቶች አይሆኑም። ምክንያቱም የደሮዋ ማቀፍና ሙቀት ወሳኝ ስላልሆነና ውጫዊም በመሆኑ ነው፡፡ ዋናው የእንቁላሉ ውስጣዊ ህይወት ወሳኝነትና የአካባቢ መመቻቸት ሚና ተደምሮ ነው ለውጡ የሚከሰተው።

 

የቀለም አብዮት ውድቀትም የሚጠነሰሰው ከውልደቱ ነው። ሲጀመር ሊብያዊ፣ ግብፃዊ፣ የመናዊ ወይም ኢትዮጵያዊ አይደለም። ከውጭ መጥቶ ውስጥን ማመስ ይችላል እንጂ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም። እሳካሁንም ውጤት ሲያመጣም አልታየም። በዓለማችን በዚህ አብዮት/ለውጥ አንድም የተሳካ ለውጥ ያመጣ አገር ሊጠቀስ የሚችል የለም። እንዲያውም የቀለም አብዮት በተካሄደባቸው አገሮች በቀላሉ የማይድንና ረዥም ዘመን የሚቆይ ጠባሳ ቁስል ትቶ የሚሄድ አደገኛ ክስተት መሆኑ በተጨባጭ የተረጋገጠ ነው፡፡ ለዚህ ደሞ በተካሄደባቸው አገሮች ከድህረ ቀለም አብዮት በኃላ ያለውን ሁኔታ ማጤን በቂ ነው።

 

የቀለም አብዮት ባህርያት

የቀለም አብዮት አምስት አጠቃላይ ባህርያት የሚከተሉት ናቸው።

1.      የአንድ አገር ውስጣዊ ተጋላጭነት የሚጠቀም ነው።

2.      የሰብአዊና ዴሞክራሲ መብቶች ጥብቅና የቆመ መስሎ እና ሽፋን ተጠቅሞ ተፅእኖ መፍጠርና ጥቃት መፈፀም የሚችል ነው።

3.      በአገር ውስጥና በውጭ የተቀናጀ ዝግጅት ያደርጋል።

4.      አጋጣሚዎች በመጠቀም ወይም አጋጣሚዎችን ሆን ብሎ በመፍጠር አለማውን ለመፈፀም የሚተጋ ነው።

5.      ሆነ ተብለው በሚፈበረኩ ውሸቶችና ልብወለድ ትርክቶች ዜናዎች፣ ዘገባዎች፣ ጥናታዊ የሚመስሉ ሃተታዎች በመሰራትና በመንዛት ህውከትና ሽብር መፈጠር ነው።

 

የቀለም አብዮት ስልቶች

የቀለም አብዮት አንቀሳቃሽ ሐይሎች የተለያዩ ስልቶች እንደየአገሩ ሁኔታ የሚጠቀሙ ቢሆንም በአጠቃላይ ግን የሚከተሉት ስልቶችን እንደሚጠቀሙ መገንዘብ ይቻላል።

Videos From Around The World

         1) የቀለም አብዮቱ በየምዕራፋ ተከፋፍሎ ብቃት ባለው ዝግጅትና ክትትል ይፈፅማሉ።

         2) ዒላማ በተደረገው አገር የተቃውሞና የዓመፅ ሁኔታ/ድባብ እንዲነግስ ያደርጋሉ።

         3) ከፍተኛ የሚድያ ዘመቻ በመክፈት ብጥብጥ ይጭራሉ።

         4) በውስጥም አነጣጥሮ ተኳሾችና ቅጥረኞች ይጠቀማሉ። ይህ በቂ አይደለም ካሉም ሰብኣዊ ቀውስ ተፈጥሯል በሚል ሰብብ የልዕለ ሐያላኑ የራሳቸው ሐይል ወይም የጎረቤት አገር ሐይል ተጠቅመው ወረራም ይፈፅማሉ። በሂደትም በሰበብ አስባቡ አገሩን ያፈራርሳሉ።

         5) የመንግስት ደጋፊ የሆኑ የአገር ውስጥ ይሁን የውጭ አካል ከህዝብ ለመነጠል ይሰራሉ።

         6) ቅጥረኛና ተላላኪ መንግስት በመፍጠር ለማረጋገትን ለሟቋቋም በሚል ስም አገር ይዘርፋሉ።

 

እነዚህ ከላይ ያየናቸው ባህሪያትና ስልቶች የቀለም አብዮት በተካደባቸው አገሮች እንዴት ተግባር ላይ እንደዋሉና እንደተፈፀሙ በምሳሌነት ማየት ይቻላል።

 

 

ከፍል 2 ይቀጥላል

 

 


Back to Front Page