Back to Front Page

ዥንጉርጉር የሆነ ኢትዮጵያዊነት እና ውጤቱ (ክፍል አንድ)

ዥንጉርጉር የሆነ ኢትዮጵያዊነት እና ውጤቱ (ክፍል አንድ)

ሓጎስ ኣረጋይ 08/23/2019

መዳረሻው(የክልሉ ወሰን) ከየት እስከ የት መሆኑን በትክክል ባይታወቅም፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ረዥም ግዜ ማስቆጠሯን ይነገራል ። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት አገር ግን፣ በአፄ ሚኒሊክ የተሸበበች መሆንዋን አብዛኛው ሰው የሚግባባበት ይመስለኛል። በእርግጥ የአሁኑዋ ኢትዮጵያ ለመመስረት የተሄደበት ርቀትና አግባብ የሚያውግዙና የሚያሞግሱ በብዛት ይደመጣሉ።

Videos From Around The World

እንግዲህ ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ ያለውን ስንመለከት ኢትዮጵያውነት በአማራ ( ነገስታቱ) ባህል የተገነባ እንደ ነበር ይታወቃል። በመሆኑም ቀላል በማይባል ደረጃ ሰዎች በማንነታቸው አፍረው እና ተሸማቅቀው ይኖሩ እንደነበርም ለቀባሪ ማርዳትን ያኽል ይመስለኛል። በመሆኑም ለመምሰልና ለመኖር ሲባል ብቻ ለዓመታት ያህል በአማራ ባህልና እሴት የተገነባ ኢትዮጵያዊነት ተጨኖብን ነበር ማለት ይቻላል። እንዲሁም ጫናው በመልካም ጎኑ ከመቶ አመት በላይ ተዘምሮበታል ፣ ተዘምሮብናልም ። ነገር ግን በሃል የተገነባ ስርዓት በመኖሩ ብዙ ተቃውሞ ነበር ። ይነሱ ከነበሩ መካከል

         ኢትዮጵያዊ ማነው ወይም ማነው ኢትዮጵያዊ ? በግጥም መልክ ፣

         ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረ ሰቦች እስር ቤት ናት (ዋለልኝ)

         አልወለድም ( በአቤ ጎበኛ ወዘተ)፣ ማንሳት ይቻላል

ተቃውሞው ሃሳብን በመግለፅ የተወሰነ አልነበረም። ብዙ መስዋእትነትም ጭምር ጠይቀዋል። በተከፈለው መስዋእትነት ነገሮች ተቀያይሮ ፣ ከ1983/ም ጀምሮ ሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ብሄር ብሄረ ሰቦች እውቅና አግኝተው ራሳቸው በራሳቸው ማስተዳደር፣ በቋንቋቸው መማርና መዳኛት ወዘተ ከጀመሩ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል። ነገር ግን ከ2010 /ም ጀምሮ አንዳንድ አስተሳሰቦች ከወደቁበት ተነስተው ብቅ ማለት ጀምረዋል ። አሁን በኢትዮጵያ ያለው አስተሳሰብ በሁለት የዋልታ ጫፍ ልንገፀው እንችላለን። እንዲሁም እንደሁኔታው፣ በዋልታዎቹ መካከል ያለው ቀጥ ያለ መስመር ተከትለው ወደ ግራና ቀይ የሚዘሙ አስተሳሰቦች እንዳሉም መገንዘብ ያሻል ።

1.      ወንዝና ተራራ መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም (አሃዳዊ) የሚያቀነቅኑ ሃይሎች፣ የብሄር ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ አንድነት ጠንቅ ነው ብለው አጥብቀው ይሞግታሉ። እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝቦች ከልዩነታቸው ይልቅ አንድነታቸው ይበልጣል ብለው ይሞግታሉ። ጎሳ እንጂ ብሄር የለም ብለው ይከራከራሉ ። ብሄር የሚለው አስተሳሰብ ወያኔ የፈጠረው እንጂ በመሬት ላይ የለም ብለው ይሞግታሉ ። ስለዚህ አስተሳሰባቸው የሚያመለክተው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንደ ጀርመን፣ አመሪካ ፣ ጃፓን የመሳሰሉት አገራት አንድ አይነትና ተመሳሳይ አድርገው ይወስዳሉ ። በመሆኑም ከህዝቦች ይልቅ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር በጣም የሚያስጨነቃቸው ይመስላል። በብሄር ከተደራጀን እንደ ዩጎዝላብያ እንሆናለን ይላሉ።ስለዚህ ስለ ኢትዮጵያዊነት ደጋግሞ ማውራት፣ ስርዓት ትምህርቱ አንድ እንዲሆን ማድረግ ወዘተ ኢትዮጵያዊነት የሚገንባ ይመስላችዋል ።

 

የዚህ መሰረታዊ አስተሳሰብ ስንመለከት የዘመን ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ከሚኒልካዊ አስተሳሰብ በምንም መልኩ የሚለይ አይደለም። ቢሳካም ባይሳካም ፣ ወደ ስልጣን ቢቆናጠጡ ደግሞ፣ የድሮን ስርዓት የመመለስ አባዜ አይኖርም ብሎ መከራከር አይቻልም ። የመርህ ጉዳያቸው ስንመለከት ደግሞ እኛ ነን ኢትዮጵያን የፈጠርናት። በመሆኑም በፈጠርናት መልክ መጓዝ አለባት ብለውም ይሞጉታሉ። አንዳንዴም የሰው ልክ ለአንድ ብሄር ብቻ የሚሰጡ አሉ ። እንዲሁም ፈጣሪ ሰውን ፈጥሮ እንደተመሰገነ ሁሉ የአሁኑዋ ኢትዮጵያም የፈጠረ ሊመሰገን ይገበዋል ብለው የሚሞግቱም አሉ። እንድግዲህ ኢትዮጵያ የተመሰረተችበት አገባብና እንዲሁም ትርፋቱ ለኢትዮጵያውያን ነበር የጠቀመው ወይስ ለገዢዎች? ኢትዮጵያስ በአኩሱምና በዛጉዌ ስርወ መንግስት በነበረችበት ወቅት ጠብቃ ነው የተራመደችው ወይስ የቁልቁለት ጉዞ ? መልሰን መላልሰን ማዬት ያለብን ይመስለኛል። ጥናት ተካሂዶበት ለህዝብ መሆን የሚገባው ይመስለኛል።

 

2.      ብሄርን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም የሚያቀነቅኑ ሃይሎች፣ አገርን በህዝብ እንጂ በወንዝና በተራራ አይገልፁም። በኢትዮጵያ ህዝቦች ያለው አንድነት እንዳለ ሁኖ በመካከላቸው ያለው ልዩነት አሳንሰው አይመለከቱም። እስከ አሁን በኢትዮጵያ የተከሰተ ችግር ልዩነትን በአግባቡ ባለመገንዘባችንና ባለማስተናገዳችን መሆኑን ይገነዘባሉ ። ኢትዮጵያ ራሷን የምትመስል አገር እንጂ ልክ ኢትዮጵያን ሊወክል/ሊመስል የሚችል አገር የለም ይላሉ ። በመሆኑም የውስጥ ችግራችን መርምረን ከለየን በኋላ የአለም ተሞክሮ ማየት እንችላለን። ነገር ግን ኢትዮጵያ በአለምቀፍ ተሞክሮ /ጃኬት/ ብቻ ውሽቆ መራመድ ውድቀት ነው ይላሉ። በመሆኑም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ፣ ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማስቀጠል የሚቻለው፣

 

         የግልና የቡዱን መብቶች (እንደዬ ሁኔታው) በጣምራና በተናጠል ያለ መሸራረፍ ሊከበሩ ይገባል ይላሉ ፣

         ብሄሮች ራሳቸው በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ፣ እንዲዳኙ ፣ አካባብያቸው እንዲያለሙ ወዘተ የማይጣስ መብት መሆኑ መገንዘብ እና መተግበር ይሻሉ፣

         የራስን እድል በራስን የመወሰን መብት ለመከበርና ለማስከበር መቀበልና ማመን ያስፈልጋል ይልላሉ፣

         በመከባበርና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ለመከበርና ለማስከበር መቀበልና ማመን ያስፈልጋል ይልላሉ

ከዚህ አንጻር ሲታይ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ሊወሰን የሚገባው/ የሚችለው በመፈቃቀድ እንጂ ማንም በሌላኛው ኢትዮጵያዊነትን መጫን የኪሳራ መንገድ መሆኑን ለመገንዝብ ይቻላል። በመሆኑም በወንዝና በተራራ መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም (አሃዳዊ) ስርዓት፣ በምንም መልኩ በኢትዮጵያ ሊተገበር አይችልም ። ቢሆንም ኢትዮጵያን ወደ ችግር አዙሪት እንጂ ወደፊት ሊያሻግራት አይችልም ብለው ያስባሉ።

በሁለቱ የዘውግ ፖለቲካ ምክንያት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ ናቸው። የልየነቱ ማእከል ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት መምጣት ያለበት አስተሳሰብ ነው። እሱም

በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የኢትዮጵያዊ አንድነት እና በአንድ አይነትነት የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት አግዝፎ ማዬት ናቸው።

የዚህ ውጥረት ወዴት ይወስደን ይሆን ። በቀጣይ . . . .


Back to Front Page