Back to Front Page

ብሔርተኝነት የኢትዮጵያ ደህንነት ስጋት ሳይሆን አደጋ ነው።

ሔርተኝነት የኢትዮጵያ ደህንነት ስጋት ሳይሆን አደጋ ነው።

በልኡልገብረመድህን (ከአሜሪካ )

 4.9. 2019

ከተቻለ ለኢትዮጵያ ከጎሳዊ ብሔርተኝነት አገራዊ ብሔርተኝነት ቢዳብር መልካም ይሆናል ነበር።የአገር ፍቅርና አንድነት ሳይኖር በምንም መለኪያ አልያም መስፈርት የጎሳ አንድነት አይኖርም።በተመሳሳይ ጨቋኝ አንድነትም ከጎሳ ብሔርተኝነት በላይ የከፋ ነው።ማንነትን ፣ ባህልንና ቋንቋን የሚደፈጥጥ አንድነት ቅቡልነት የለውም ። ማንም የጎሳ ዘር ብሔርተኛ አይደለም ። በመተባበር ፣ በመረዳዳት ፣ በፍቅርና መከባበር መኖር የማይሻ የጎሳ ዘር የለም ። በኢትዮጵያ የአንድነት ቅኝት መሠረቱ ስህተት ነበረው ። ማንነት በመግታት አንድነት አይሳካም ። የአንድነት ማሳለጫ መንገዶች  በአግባቡ ተለይቶ በተግባር ካልተተገበሩ በቀር ስለአንድነት ብዙ ቢባል ተፈላጊ ውጤት ላይመጣ ይችላል ። ማንነት በህግ ሳይከበር ስለአንድ መናገር ሆነ ማሰብ ጨምር የሚቻል አይሆንም ። መፍትሔ ካልተበጀለት በቀር ለኢትዮጵያ አደጋ የሚሆነው የማንነት ጥያቄ ሳይሆን የብሔር ፖለቲካ ማራመድ ነው ። በብሔር ተደራጅቶ ህዝብና አገር ለመምራት ሰልጣን ያገኘ ብሔር ከራሱ ብሔር ውጭ ዘላቂነት ያለው ተቀባይነት አይኖረውም ።

Videos From Around The World

ሁሉም የኢትዮጵያ ግሳዎች (በዘመኑ አገላለጽ =ብሔሮች ) ለአንድነታቸው አቅም የሚሆነው ማንነታቸው ታውቆ ፣ ተከብሮ ፣ በህግ ልዕልና በአገራችን በነፃነት ሠርቶና አምርቶ መናገር ሲችሉ ሆኖ ከማንነት የፖለቲካ አደረጃጀት ውጭ ሲሆኑ በጋራ ለጋራ ጥቅምና አንድነት ይሰራሉ ፣ በእኩልነትና ነፃነት ይኖራሉ ፣ በጋራ ፈቅዶ በመረጡት መንግስት ለመተዳደር ይችላሉ ። በኢትዮጵያ በርካታ የጎሳ ቤተሰቦች ቢኖሩም ሁሉም ለአገራቸው በጋራ ለመሥራት የሚያሰቸግሩ ሁኔታዎች የሉም ። ጎረቤት ኬንያ የኢትዮጵያ ያህሉ ጎሳዎች ባይኖራትም ወደ ሰባ የሚጠጉ የግሳ ቤተሰቦች አላት ። ነገር ግን አንድም በግሳ የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት ኬንያ ውስጥ የለም ። በጎሳ ህዝብ ብዛት ትልቁ የኪሲ ጎሳእንካን የብሔር ድርጅት የለውም ። ኬንያ በምዕራቡ ቀመር 1963*  ከእንግሊዝ አገዛዝ ነፃ ከሆነች በኋላ ሁለት ጊዜ  የህገ መንግስት ማሻሻያ አድርጋለች ። በምዕራቡ ዘመን አቆጣጠር በ 1969* እንዲሁም 2010*. በርካታ ህገ መንግሰታዊ ማሻሸያ አድርጋለች ። የኬንያ ህገ መንግስት መግቢያ እንዲህ ይላል “ We, the People of Kenya , acknowledging the supremacy of the Almighty of God of all creation, honoring those who heroically struggled to bring freedom and justice to our land, proud of our ethnic , cultural and religious diversity and determined to live in peace and unity as one indivisible sovereign Nation .”  እሰቲ ደግመን ደጋግመን እናንብበው ። በግሌ ይህ የኬንያ ህገ መንግስት መግቢያ ሳነብ የሚሰማኝ እርካታ ቢደመር አያልቅም ።  የኬንያ ህገ መንግሥት መግቢያ እኛ የኬንያ ህዝቦች በማለት ይጀምርና በኬንያ ያሉ የተለያዩ ጎሳዎች የአገራችን ኩራት ናቸው በማለት የዜግነት ላዕለዋይ ክብር ያጎናፅፋቸዋል። እንደየ ባህላቸውና እምነታቸው በሰላምና አንድነት ለአንድ አገር ልአላዊነት እንደቆሙ የኬንያ ህገ መንግስት በማያሻማ አገላለጽ አስፍሮታል ።

እሰቲ በምዕራቡ ዘመን አቆጣጠር ነሐሴ 21, 1995 የፀደቀው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ እንመልከት ፣

“ We, the Nation , Nationalities , and people of Ethiopia : strongly committed in full and free exercise of our right to self -determination , to building a political community founded on the rule of law and capable of ensuring a lasting peace , guaranteeing a democratic order, and advancing our economic and social development .” በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ ለብሔር እንጂ ለህዝብ ወይም ዜጋ መብት አልሰጠም ። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ መገንጠል እንጂ አንድነት የሚያበረታታ አይደለም ።  የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ደግመን ደጋግመን ውስጡ ስንመረምረው ህዝቦች የመተሳሰብና የአንድነት ቁመና አያጎናፅፋቸውም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ከ 1995 ( 1987 ዓ.ም ) ጀምሮ በግልፅ ተለያይተዋል ። በአሁኑ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም ። ያሉት አገር የሌላቸው ብሔሮች እና  ብሔረሰቦች ናቸው ። ለምሳሌ ፣ የኦሮሞ ተወላጅ አገር ቢጠየቅ የሚመልሰው መልስ ኦሮሚያ የሚል ይሆናል ። የአማራ ፣ የትግራይ ፣ የአፋር ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ፣ የደቡብ ፣ የጋምቤላ ፣ የቤኒሻንጉል ፣ ወዘተ በአሁኑ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሠረት ሁሉም ከየት አገር እንደሆኑ ቢጠየቁ የሚመልሱት መልስ የክልላቸው ስም ይሆናል ። ይህ የሚያሳዝን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በዜጎች ላይ የዜግነት በደል ተፈፅሟል ። ህዝቦች ሳይለያዩ ህገ  መንግሥቱ እንዲለያዩ አድርጓል ። እንዳየነው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሲጀምር ብሔር ብሎ ይጀመራል ፣ ቀጥሎም ብሔርሰቦች ይላል ፣ በመጨረሻም ህዝብ የሚል ቃል ያስቀምጣል ። በዚህ አገባብ መሠረት በኢትዮጵያ ብሔር የላቀ ቦታ ህገ መንግሰታዊ ድጋፍ ( legitimacy ) አለው ። በመሆኑም አናሳ ብሔር ይሁን አይሁን የመንግስት ሰልጣን በመያዝ ብዙሃኑን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው ። ይህ ከሆነ ደግሞ አምባገነን እንጂ በህግ ልዕልና የሚመራ መንግስት ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ። ምክንያቱም የዲሞክራሲ መርህ ጉድለቶች ስለሚኖሩት አንድ ብሔር የራሱ ብሔር አሰባስቦ እና በፖለቲካ አደራጅቶ ህዝብና አገር ለማስተዳደር የሚያስችል የመንግስትነት ባህሪ አይኖረውም ።Hence, Ethnic politics is against democracy, justice , and rule of law.

  በኢትዮጵያ አገር ውስጥ ከደርግ ሰርአት ውድቀት በኋላ የብሔር መንግስት እንጂ የህዝብ መንግስት የለም ። በመሆኑም በኢትዮጵያ ህዝብ ለተፈፀሙት ዘርፈ ብዙ የመብት ሆኖ የስርቆት ወንጀሎች መንግስት ተጠያቂ አይሆንም ። መንግስት ተጠያቂነት ለብሔሩ እንጂ ለህዝብ አይደለም ። ለዚህም ነው  ወንጀል ፈፅሞ በየ ብሔራቸው ጉያ የተደበቁ ። ምክንያቱም የተጠያቂነት ጉዳይ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች ጉዳይ ሳይሆን የብሔር ጉዳይ ይሆናል ። አንድ ባለስልጣን ወንጀልና ሰርቆት ሲፈፅም ከርሞ ተጠያቂ ሲሆን ብሔሩ ጋር ይደበቃል ። በመሆኑም የዚህ ብሔር አካል በመሆኔ ጥቃት ደረሰብኝ ይላል ። ማለትም አለበት ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እንደዛ እንዲል ሙሉ መብትና ከለላ ይሰጠዋል ። የህዝብ መንግስት ባልነበረበት በወንጀል ጠያቂና ተጠያቂ ፣ አሳሪና ታሳሪ ፣ አጋጅና ታጋጅ ፣ አባራሪና ተባራሪ ማን ይሆናል ?። የቱ ብሔር ለየትኛው ብሔር መጠየቅና ማስገደድ ይችላል ?። በጣም የሚገርመው ደግሞ ወንጀል ሆነ ሰርቆት ሰፈፅም ከተደረሰብኝ እገነጠላለሁ (self -determination ) የሚል  አገላለጽ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መካተቱ የሚያስደምም ፣ የሚያስገርም ነው ።  ህዝብ የብሔሮች ሰብሰብ ነው በሚል ግብዝ አመለካከትና አሰተሳሰብ መነሻ ተደርጎ የፀደቀው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በግላጭ የብሔሮች ዋንኛ ጠላት ነው ። ማንም ብሔር የራሱ ያልሆነ ብሔር ከክልሉ የማስወጣት ህገ መንግሰታዊ መብት አለው ። ምክንያቱም በኢትዮጵያ የብሔር እንጂ የዜጎች (የዜጋ ) መብት በግልጽ የለም ። ህዝብ ወይም ዜጋ ህገመንግስታዊ መብት የለውም ። ትግራይ በትግራይ ክልል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች በሙሉ የማስወጣት ህገ መንግሰታዊ ሙሉ መብት አለው ። አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ደቡብ ፣ ምዕራቡ ፣ ምስራቁ እንዲሁ ተመሳሳይ መብት አላቸው ። ለዚህ ነው ዜጎች የሚያፈናቅሉ ሰዎች ወይም ቡድኖች ወይም የመንግስት ባለስልጣኖች ለፈፀሙት ዜጎች የማፈናቀል ተግባር በህግ አግባብ ተጠያቂ የማይሆኑ ።

   የኢትዮጵያ ችግር ከአናቱ ነው ። ህገ መንግሥቱ መሻሻል ይኖርበታል ። የደቡብ ክልል በመልክዓምድር የተቀሩት የኢትዮጵያ ጎሳዎች ደግሞ በብሔር እንዲሁም በቋንቋ በመከፋፈል ለዜጎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው የፌዴራል አወቃቀር በሚገባ መጠናት ይኖርበታል ። በኢትዮጵያ የጎሳ ግጭት አንዱ መነሻ ምክንያት የህገ መንግስት ችግር ነው ። አንድ ዜጋ በብሔሩ መጠን ልክ የሚያሳብና ለዛ የሚኖር በዛ የታጠረ ከሆነ የአገር አንድነትና ፍቅር በብሔር ልክ ለሚያሰብ ዜጋ ምኑም አይደለም ።ብሔርተኛ መሆን በራሱ ችግር አይደለም ። ሰው የተወለደበት ጎሳ (ዘር) ሁለንተናዊ ባህሪ የተላበሰ እንደሆነ እሙን ነው ።ሰለሆነም በተለያዩ የተግባር መስኮች ላይ ማህበረሰብ ተኮር አገልግሎቶች ሊያበረክት ይችላል ። ለአብነት  ፣ የግብረሰናይ አገልግሎት ፣ የአካባቢ ልማት ፣ የቴክኖሎጂ እውቀት ድጋፍ ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ብሔር ተኮር ድጋፍና አገልግሎት ማበርከት ይቻላል ። ለተወለዱበት የዘር ሐረግ መቆርቆር እና ዘር ላይ ያተኮረ የፖለቲካ አደረጃጀት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ። በጎሳ መጠናቸው ከኢትዮጵያ የበለጠ ብዛት ያላቸው የአለም አገራት የብሔር ፖለቲካ አደረጃጀት የላቸውም ።የብሔር ፖለቲካ አገራዊ ራእይ አይኖረውም ። ምክንያቱም የብሔር ፖለቲካ አወቃቀር ከአገር ግንባታ የሚቀድም በመሆኑ አገር ይኑር አይኑር ጉዳዩ አይደለም ። ለብሔር ፖለቲከኞች የአገር ግንባታ ሁለተኛ አልያም ሦሰተኛ አጀንዳቸው ነው ። በመሆኑም ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ የከተታት አንዱ ችግር የብሔር ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነት ነው ። መፍትሔውም እንደ ጎረቤት ኬንያ የዘር ፖለቲካ በህግ ማገድ ነው ።

      በኢትዮጵያ የህገ መንግስት ማሻሻያ በፍጥነት ካልተፈፀመ ፣ የብሔር (ዘር ) ፖለቲካ አደረጃጀት ካልታገደ ኢትዮጵያ የሽብርተኞች መንደር መሆኗ የማይቀር ጉዳይ ነው ። ሰላምና መረጋጋት ማስፈን የማይታሰብ ነው ። የመልካም አሰተዳደር ችግር ለመቆጣጠር የሚያሰችል ህጋዊ መሠረት ያለው ተቋም አይኖርም ። በኢትዮጵያ እያደገ የመጣ የዘር (ጎሳ) ግጭት የብሔር ፖለቲካ የሚያራምደው መንግስት ሙሉ ሀላፊነት መውሰድ አልያም ሰልጣን መልቀቅ ይኖርበታል ። መንግስት ለዘር ግጭት ሌላው ምክንያት ነው ። የብሔር ፖለቲካ ድርጅቴ የተመሠረተበት ልደት በዐል የሚያከብር ህዝብና አገር የሚመራ መንግስት ባለበት አገር እንዴት ሰላምና መረጋጋት ይሰፍናል ። በብሔር ከተመሠረትኩ ይህ ያህል አመት አሳልፌያለሁ እያለ የዘር ፖለቲካ ልደት የሚያከብር መንግስት በምን መስፈርት አገርና ህዝብ ሊያሰተዳድር ይችላል ?።የብሔር ፖለቲካ ምሰረታ እንደ ልደት የሚቆጠርበት አገር እና መንግስት ተይዞ እንዴ የአገር አንደነት እንዲሁም የአገር ግንባታና መግባባት ሊኖር ይችላል ?።የዘር ፖለቲካ ምስረታ በአል የማክበር ባህሪ የአምባገነኖች ባህሪ ነው ። በመሆኑም የዘር ፖለቲካ ምስረታ ለዘር ግጭት ምክንያት ሆነዋል ። ሰለሆነም ይህ የአምባገነኖች የጭፈራ ጋጋታ መቆም ያለበት ይመስለኛል ። የዘር ፖለቲካ ምስረታ በአል ለማክበር የህዝብ ቅሰቀስሳ መቆም አለበት ።

      በኢትዮጵያ ከአድዋ ድል በአል በላይ የዘር ፖለቲካ ምስረታ ሲከበር ላስተዋለ ሰው ምን እንደሚሰማው መገመት የሚያስቸግር አይመስለኝም ። የዘር ፖለቲካ ምስረታ በአል ለማክበር የሚመደበው የበአል ወጪ ገንዘብ ምንጩ ከየተ ነው ?። የአገርና የህዝብ ገንዘብ ለዘር ፖለቲካ ምስረታ በአል ላይ ማዋል ግልፅ ስርቆት ነው ።ይህ አሰራር ሀላፊነት የጎደለው በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ ። ወገን በችግር እየኖረ በዘር ፖለቲካ ምስረታ ዳንኪራ መውረድ ከአንድ ሀላፊነት ከወሰደ ፖርቲና መንግስት የሚጠበቅ ተግባ አይደለም ። መንግስት የዘር ፖለቲካ እያረመደ ሌላውን ዘረኛ ማለት የሚያስችል አቅም አይኖረውም ። ላለፉት 30 አመታት የትግራይ ዘር የኢትዮጵያ ስልጣንና ሀብት ተቆጣጥረዋል በሚል ምክንያት የትግራይ ህዝብ ላይ የወቀሳ መከራ ሲወርድበት ነበር ። አሁን ደግሞ የወቀሳ ቁማር የኦሮሞ ህዝብ ላይ በድምቀት ተጀምሯል ። የኦሮሞ ህዝብ ዘረኛ ፣ አግላይ ፣ ህዝብ አፈናቃይ ፣ በሜንጫና ገጀራ ሰው ገዳይ ፣ በአጠና ሰው አሳዳጅ ፣ ያልሰለጠነ ህዝብ ፣ ቤት ቀማኛ ወዘተ የሚል ተለጣፊ ስሞች በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየተሰነዘሩ ነው ። ይህ አሳዛኝ ጉዳይ ነው ። በተወሰኑ ዘረኛ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የተነሳ የኦሮሞ ህዝብ የሚወቀስበት አንዳች ምክንያት መኖር አልነበረበትም ። አሁን የትግራይ የወቀሳ ፅዋ የኦሮሞ ህዝብ ተቀብሎታል ። በዘር ፖለቲካ የተነሳ ሲወቀስ ይኖራል ።

በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ እንደ አሸን በተስፋፋበት ሁኔታ ጠንካራና ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መፍጠር አሰቸጋሪ ይሆናል ። በመሆኑም የህገ መንግሥት ማሻሻያ ካልተደረገ የኢትዮጵያ መፃኢ ሁኔታ አሳሳቢ ብቻም ሳይሆን አደገኛ የዘር እልቂት የመነሳቱ ሁኔታ የማይቀር ነው ። በጉዳዩ ላይ ሀላፊነት የሚወሰዱ አካላት የኢህአዴግ መር መንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባለት ይሆናሉ ። የመኝታ አልጋ ከቤት ይዞ መምጣት ብቻ የቀራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት (Parliament ) አባላት የህግ ማሻሻያ ረቂቅ የመፃፍ መብት በአግባቡ የሚጠቀሙበት አይመስሉም ። በሚኒስትሮች ምክርቤት ፀድቆ የሚላኩ አዋጆች ብቻ አይቶ ማፅደቅ ሳይሆን የወከሉት ህዝብ አይንና ጀሮ መሆን አልቻሉም ። Parliament has full right to propose constitutional amendments because members of the Parliament are public representatives who represent the interests of their constituencies . However , members of the Ethiopia Parliament have not achieved satisfactory performance  as what they supposed to. Members of the Parliament are responsible and accountable for not to protect mass displacements and killing of innocent civilians by mob justice gangs all over the Nation .Members of Parliament are accountable and responsible to law of the land to be ruled out.

በኢትዮጵያ ለአገር ግንባታ ሆነ ለህዝቦች መቀራረብና መጠናከር የሚበጀው የዘር ፖለቲካ ማስቀረት ሲሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ሊያገልግል የሚችል ሀገ መንግስትና መንግስት ማዋቀር ይሆናል ። ለዚህም በዘር ፖለቲካ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች የአወቃቀር ለውጥ ማድረግ ይኖርባቸዋል ። በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካ ቀጣይነት አይኖረውም ። ምክነያት ህዝብ በዘር እየተናቆረ ለመኖር አይሻም ። በመሆኑም ህዝብ አማራጭ መንገድ ማፈላለጉ የማይቀር ጉዳይ ነው ። የኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ መንግስት አገርና ህዝብ በቅጡ ማስተዳደር አልቻለም ። የህግ በላይነት ማስከበር አልቻለም ። ራሱ የመንግስትነት ሰልጣን የያዘ አካል በዘር ፖለቲካ የቆመ በመሆኑ ዘረኝነትን ማስቆም አልቻለም። የዘር ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ከረሐብ ያልተናነሰ ችግር ሆኖባታል ። ይህ ችግር አፋጣኝ መፍትሔ ይፈልጋል ። በዘር የተሰባሰቡት ፖለቲከኞች እንዲሁም የዘር ፖለቲካ ድርጅቶች በፍጥነት የድርጅት አወቃቀር ለውጥ  ይጠበቅባቸዋል ። ምክንያቱም በህዝቦች መካከል እየተከሰቱ ላሉት ችግሮች የዘር ፖለቲከኞች አንዱ መነሻ ምክንያት ናቸው ።

በኢትዮጵያ ዘር መሠረት ያደረገ የመንግስት ሰልጣን ዘላቂነት የለውም ። ሁሉም ሰልጣን ፈላጊ በመሆኑ በዘር ፖለቲካ ተመስርቶ የህዝቦች ሁለንተናዊ ለውጥ ማሳካት ዘበት ነው ። አይታሰብም ፣ አይመከርም ። የአስተሳሰብና አመለካከት ለውጥ እድገት በሌለው ህዝብ ላይ የዘር ፖለቲካ ሲታከልበት የችግሩ መጠን መገመት አይከብድም ። ጉዳዩ በደንባራ ፈረሰ ቃጭል ተጨምሮበት ከሚለው ብሒል ጋር ይስማማል ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ምክረ ሀሳብ (public opinions ) መነሻ ያደረገ በሳል የፖለቲካ አመራር ሰራ ከመስራት ይልቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማይመጥን የዘር ፖለቲካ ውሐ ሲጠመቁ ማየቱ አሳዛኝ ነው ። መንግስት የሚፎካከሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አገራዊ አደረጃጀት ቅርፅ ከመያዝ ይልቅ ልቅ የሆነ የዘር ፖለቲካ መከተላቸው በኢትዮጵያ ለሚከሰቱት የዘር ግጭቶች ከተጠያቂነት አይድኑም ። ሁሉም የዘር ፖለቲካ ድርጅቶች የዘር ራእይ አያስፈልጋቸውም ። የዘር ፖለቲካ እያራመዱ አገራዊ ራእይ አይኖራቸውም ። በመሆኑም  የጥፋት መንገዶች ሁሉ እንዲዘጉ ከዘር የፀዳ የፖለቲካ አደረጃጀት ያስፈልጋቸዋል ።

አሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ በመሰራት ላይ ያሉ ዶክተር አብይ አህመድ በአፍ የአንድነት አቀንቃኝ ቢሆኑም በተግባር ዘረኛ ይመሰላሉ ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ፍላጎት የኦሮሞ የስልጣን የበላይነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ምንም የሚያጠራጥር አይሆንም ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግልፅነት ችግር ድሪቶ የለበሱ መሆናቸው የሚመሩት የዘር ፖለቲካ ድርጅት (ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ) በዘረኝነት ማስቀመጥ ከመጠን በላይ ፍላጎት አላቸው ። ይህ የዶክተር አብይ አህመድ ኦሮሞን በሰልጣን የማቆየት አባዜ መስበር አለበት ። በኢትዮጵያ ዘረኛ ኦሮሞ ሆነ ትግራይ ሆነ አማራ ሆነ ሐድያ ሆነ ጋምቤላ ሆነ ቤንሻንጉል አሰፈላጊ አይደለም ብቻ ሳይሆን በሽታም ጭምር በመሆኑ የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያ ማብቃት ይኖርበታል ። የዘር መንግስት ለኢትዮጵያ አይበጅም ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዘር ተኮር ፖለቲካ መለወጥ መቻል ይጠበቅባቸዋል ። የኢህአዴግ ዘር ተኮር ሰርአት ከዘር ፖለቲካዊ ቅርፅ ወጥቶ አገራዊ አወቃቀርና አካታች የፖለቲካ ድርጅት እንዲሆን ጊዜ መውሰድ አሰፈላጊ መሰሎ አይታየኝም ።

     የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጣዩ አገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ለስልጣን በሚያደርጉት ሰላማዊ ውድድር ብሔርን መሰረት አድርጎ ለሰልጣን የሚፎካከሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በካርዱ የማያዳግም ቅጣት መቅጣት ይኖርበታል ። የዘር ፖለቲካ ህልውና እንዲያከትም ህዝብ ሀላፊነቱ በተገቢ ሁኔታ መወጣት ይኖርበታል ። የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፖለቲካ የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች በስልጣኑ ማፍረስ ካልቻለ ኢትዮጵያ እንደ አገር የምትኖር አይመስለኝም ። በአገር ላይ የተቃጣ አደጋ የማዳን የዘረኛ መንግስት ስራ ሳይሆን የህዝብ ሙሉ ሀላፊነት ይሆናል ።  ለኢትዮጵያ ህዝብ የአመለካከትና አሰተሳሰብ ችግር ፣ የምጣኔ ሐብት ማሽቆልቆል (ድህነት ) ፣ እንዲሁም የዘር ፖለቲካ ቀጣይ የህልውና ፈተናዎች ይሆናሉ ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በራሱ ከመጠቃቃት ተቆጥቦ በሰከነ ሁኔታ ችግሮች ለመቅረፍ በአንድነት መንፈስ መነሳትና ለችግሮቹ መፍትሔ መሻት ይጠበቅበታል ።

Back to Front Page