Back to Front Page

ሁለት ሌቦች የሰረቁትን ሲካፈሉ ይጣላሉ

ሁለት ሌቦች የሰረቁትን ሲካፈሉ ይጣላሉ

(ኦሮማራ የጥገኞች ቡድንም እንዲሁ)

*************

ሌባ ሌባ ነውና ፍትሀዊነት የሚባል ነገር አይገባውም፡፡ የፍትሀዊነት ሽታም ፈፅሞ የለውም፡፡ መስረቅ፡ መሸወድ፡ ማታለል ማሞኘት ዋና ዋና የህይወት መርሆቹ መለያ ባህሪዎቹ ናቸው፡፡ ማንኛውም ሌባ በማንኛውም እንቅስቃሴውና በሚያደርጋቸው ግንኘነቶች ሁሉ ከነዚህ መርሆዎች ውጭ አንዲት ስንዝር መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ በመሆኑም አንድ ሌባ ከሌላ ሌባ ስውር ስምምነት ሲያደርግም እርስ በርሱ እነደሚሸዋወድ ስለሚያውቅ በውስጡ ፕላን- ይዞ ነው የሚደራደረው ወይም የሚስማማው፡፡ የነዚህ ሁለት ሌቦች ፕላን- በጋራ አቅደውት በጋራ ሲፈፅሙት፤ ልክ ፕላን- እንደተፈፀመ በቀጥታ አንዱን ሌላዉን የሚሸውድበት የየራሳቸው ፕላን- በድብቅ በማዘጋጀት አንዱ ሌላውን በማታለል ከተቻለ በጋራ የሰረቁትን ሁሉንም አንዳች ሳያስቀር ለራሱ ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ኣብዛኛውን ለራሱ ለማድረግ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ፡፡ ለዚህ ነው ሌቦች ሁሌም አብረው የሰረቁት ሲካፈሉት ይጣላሉ የሚባለው፡፡

Videos From Around The World

በአሁኑ ወቅት የአገራችን ፖለቲካ ስናየው በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የተፈጠረው ከነዚህ የሁለት ሌቦች ስምምነት ውጭ አይደለም፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ እየገነገነ የመጣው የበሰበሰው ጥገኛው ሀይል ህዝባዊ ውግንናው ወደጎን በመተው፣ የድርጅቱ እሴቶች እና የውስጥ አሰራር በመጣስ ድብቅ ቡድን በማቋቋም ቡድኑ በውጭ ማን ጠቅላይ ሚኒስተር እንደሚሆን ማን ምክትል እንደሚሆን በፕላን-ኤ ጨርሰው በመግባት የኢህአዴግ የሊቀመንበርነት ቦታ በይስሙላ ዴሞክራሲያዊ ድምፅ ብልጫ ተቆጣጥረውታል፡፡

 

ይህ የበሰበሰው የጥገኞች ቡድን ባለፉት 10 ወራት፣ ህገመንግስታዊ ስርዓቱ በማፍረስ ስራ ላይ ተጠምዶ ነበር ያሳለፈው፡፡ በመሆኑም አገሪቱ ልክ ቆፎዎቻቸው እንደተሰባበረባቸው ንቦች ስርዓት አልበኝነት ነግሶ ህዝቡ ሲሰቃይ ማየት የተለመደ ሁኔታ ሆኖዋል፡፡ ቆፎዎቻቸው የተሰበሩባቸው ክልሎች /ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ወዘተ ሰላም ርቋቸው መፈናቀሎች እያስተናገዱ ይገኛሉ/፡፡ ይህ ጥገኛ የበሰበሰ ቡዱን የየራሱ ፕላን-ቢ መተግበር ሲጀምር እርስ-በራሱ ሲወነጃጀል ይታያል፡፡ ዋነኛው የውንጀላ እና የንትርክ ነጥብ የሆነው የስልጣን ይገባኛል ቢሆንም፣ ለዚህ ድብቅ መሰሪ ዓላማ ድጋፍ ማስገኛ ይሆናል ወይም በዙሪያችን ህዝብ የምናሰልፍበት አንዱ አጀንዳ የአዲስ አበባ አጀንዳ ነው በሚል ሁለቱም ፅንፈኛው የኦሮሞ ጥገኛ እና ፅንፈኛው የአማራ ጥገኛ አዲስ አበባ ላይ ለመፋለም እየተዘጋጁ ይገኛሉ፡፡

 

የአዲስ አበባ ጉዳይ በህገመንግስቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆንም ሁለቱም ፅንፈኞች ህገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ የኔ ናት የኔ ናት በማለት ህዝቦችን በማፈናቀል እና በማጋጨት እኩይ ተግባር ተጠምዷል፡፡ ሌቦች ሲካፈሉ ነው የሚጣሉት የሚባለው ተረት አሁን የኦሮማራ ሌቦች በግላጭ በአዲስአበባ ሲጣሉ እያየናቸው ነው፡፡

 

ይህ ቡድን የሌባ ቡድን ለማንም አይወክልም፡፡ ገና ከጅምሩ በአንድ አገር ውስጥ ሆኖ ህዝቦችን ለያይቶ ለኦሮሞ እና ለአማራ የወገነ ቢመስልም ያው መጨረሻ እንደ ሌቦቹ አማራና ኦሮሞ ለማጣላት ሲወራጭ ይታያል፡፡ አንድን ህዝብ ማግለል የጀመረ ሀይል ሁሌም ጥገኛና የማንም ህዝብ ወገን ሊሆን አይችልም፡፡ ትናንት በኦሮማራ ሲምሉና ሲገዘቱ የነበሩ ሀይሎች ዛሬ አንዱን ህዝብ ሲያዋርዱት እና ሲያንቋሽሹት ማየት አዲስ ነገር ሳይሆን የጥገኞች ባህሪ ነው፡፡

 

ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ከአማራ ህዝብ ለማጣላት እየሞከሩ ያሉ የኦሮሞ ፅንፈኛ ሀይሎች ነገ ለራሱ ለኦሮሞ ህዝብ በዞን ከፋፍለው እንደሚያፋጁት ምንም ጥርጥር የለውም ምክንያቱ የጥገኞች ባህሪ እንደዚህ በመሆኑ፤

በሌላ በኩልም የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ለማጣላት ወይም ለማጋጨት እየሞከሩ ያሉት የበሰበሰው ፅንፈኛው የአማራ ሀይል ነገ ለራሱ የአማራ ህዝብ በዞን በመከፋፈል ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ወሎየ ሸዋ በሚል እንደሚያጋጩት ምንም ጥርጥር የለውም፣ ምክንያቱ የጥገኞች ባህሪ ህዝቦችን በማጋጨት ብቻ ነው በስልጣን መቆየት የሚችለው፡፡

 

ስለዚ እነዚህ ኢህአዴግን በማበላሸት ህዝቡ እንዲያማርር የሚያደርጉ የነበሩ የበሰበሱ ጥገኞች አሁንም ኢትዮጵያን ለማመስ መጀመሪያ ኦሮማራ አሁን ደግሞ ሌላ የጥፋት ድግስ እና ነጋሪት እያሰሙ ያሉ የነውጥ ሀይሎች በቃቹ ሊባሉ ይገባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከመከባበር፣ ከመቻቻል፣ ከእኩልነት እና ከፌደራላዊ ስርዓት ውጭ ወይም ደግሞ በሌላ አነጋገር ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውጭ እንደ አገር መቀጠል አትችልም፡፡ የመቀጠል እና ያለመቀጠል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰላም እና የጦርነት ጉዳይ ጭምር ነው፡፡ ይህ ጥገኛ ቡድን ከመጣ ወዲህ አገራችን በከፍተኛ ግጭት፣ ብሄር ተኮር ጥቃት፣ ሀብትና ንብረት ውድመት መፈናቀል እና ረሀብ አደጋዎች ከመቸውም ጊዜ እያመሱን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ጥገኛ ሀይሎች በቃቹ ካልተባሉ ይህ ችግር ተጧጥፎ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ መበሻሸቅ ትተን ስለ አገር እናስብ፣ ስለ ሰላም እና መረጋጋት ያጣው የኢትዮጵያ ህዝብ እናስብ፣ ስለ በረሀብ እያለቀ ያለው የተፈናቀለ ወገናችን እናስብ፡፡

 

ኦሮማራ የጥፋት፣ የውድመት፣ ሀይል ነው መወገዝ አለበት !!!

 

ህዳሴ ኢትዮጵያ

መጋቢት 92011 ..

አስተያየት ካለ በሚቀጥለው ሊንክ ማድረስ ይቻላል

https://www.facebook.com/hidaseethiopiaa/

 

Back to Front Page