|
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው ማረክን አንዳይሉ ሰው የለም በጃቸው ምንአሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው ለወሬ አይመቹም ተንኰለኛ ናቸው
ስለ አፄ ቴድሮስ ድሮ ታሪክ ስማር ያነበብኩት ግጥም የላየኛው ነበር ይህ ሁሉ ግርግር ይህ ሁሉ ፉከራ ራሱን ገደለ እንጂ ታሪክ መቸ ሰራ መሞቱ ላልቀረ ከአፈር መቀበሩ አንድ ሁለት እንግሊዝ ቢቀዝፍ ባጭሩ ያኔነበር ጀግና ጐበዝ የሚባለው እንደ አርበኛ ሳይሆን በፍርሃት ለሞተው ጀግና በጠፋበት ፈሪውም ጀግና ነው ቆራጥ ላልሆነ ሰው ወኔ ላልነበረው ፎቶና ባንዲራ በላዪ ማዞር ነው
እምየ ምኒሊክ የክህደቱ ጀግና ሁሉም ላይ አሻጥሮ ተባለ ገናና ብዙ ታሪክ አለ ገና መች ወጣና
የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ተመልከት ልብ አርገህ ኢትዮጵያኮ ላነተ አንደኛ እናትህ ናት ሁለተኛም ክብርህ ሶስተኛም ሚስትህ ናት አራተኛም ልጅህ ሲልም ደግሞ ዘውድህ ስትሞት መቃብርህ ብሎ ለሞተላት ጠላቷን ሳያሳድድ መንደር ሳይወሸቅ ወይ ሳያጐበድድ ያነው ጀግና ማለት የሃገር አርአያ ለሚመጣ ትውልድ ጀግንነት ማሳያ ታዲያ ምንያረጋል ህልም እንደፈቺው ነው ጀግና በጠፋበት ፈሪውም ጀግና ነው ታሪክ መበራረዝ ሲያሰኝም መደለዝ ሆነና ነገሩ ጀግንነት ባይኖርም ይነሳ በፀጉሩ የሰረቁት ልጁም ይመለስ አገሩ
3-22-19
|