አዲሱ ፖለቲካ
እኔን ለማጥፋት
ቀረ እኮ መልፋት
ትፈበርኩና ውሽት
ተባብራችሁ በህብረት
ሹክ ብላችሁ ኮዷን
ሌብነት ምትባለዋን
አቀነባብራችሁ ውሸት
በአላማ በዘረኝንት
አስፈንቅላችሁ ከስራዬ
ተሾማችሁ በፋንታዬ
ተወልጄ ባደኩበት
ቤተሰብ ባፈራሁበት
አይኔን ባየሁበት
አንቱ በተባልኩበት
አላማችሁ ሰምሮ
በጥቂቶች ተቀነባብሮ
በአብዛኛው ተደግፎ
ተሾክሽኮ ተለፍፎ
ገፍታችሁ ገፋፍታችሁ
ከተማዋን አጽድታችሁ
ከኔ አይነቱ አናሳ
ከተባለ ነቀርሳ
ሳልወድ በግዴ...
ንብረት ቤቴን ቸብችቤ
ከነመላው ቤተሰቤ
ጥዬላቸሁ ገባሁ
በኮድ ስሙ በምትታወቀው
ዋሻ ከምትባለው
ኢዮብ ከጮማ እምኒ
1-27-19