|
የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሃላፊ የብልጽግና ፓርቲ ጸረ ሕገ መንግስትና ጸረ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም መሆኑን አጋለጡ
12-15-19
ዓለም
እንደሚያውቀው ሕገ
መንግስት ምን ዓይነት
መንግስት መመስረት እንዳለበት፣
የመንግስት መዋቅር ምን
መሆን እንደሚገባውና እያንዳንዱ
መዋቅር የሚኖረው ስልጣንና
መዋቅሮቹ እርስ በርሳቸውና
ከህዝብ ጋር የሚኖራቸው
ዝምድና ምን መሆን እንዳለበት
የሚደነግግ ፣ የዜጎችን
መብት
የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች የደነገገ፣ ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ባህሎችና ታሪኮች ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያን አገር እንደሆነች በጉልህ የተቀበለና እነዚህ ህዝቦችን የሚያስተዳድር ሌላ ህዝብ ሳያስፈልግ ራሳቸው የስልጣናቸው ባለቤት እንደሆኑ ደንግጎ የህዝቦች ባህል ቋንቋና የህዝቦች አሰፋፈር መሰረት ያደረገ የክልሎች አደረጃጀትን ተቀብሎ ፌደራላዊ መንግስትን መስርቷል። እነዚህ ብሄር ብሄረሰቦች ወደ አንድነት የሚመጡት በሙሉ ፈቃዳቸው እንደሆነ እምነት ለማስጨበጥ ባልፈለጉበት ወቅትም የራስን እድል በራስ የመወሰን መብታቸውን ተጠቅመው ከህብረቱ መውጣት እንደሚችሉ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል በሚል መተማመኛ አንቀጾችን አስፍሯል። ይህ በመፈቃቀድ አንድ ማህበረ ኤኮናምያዊ ስርዓትን ለመመስረት አልሞ የጸደቀ ሕገ መንግስት የአንድ ብሄር የበላይነትን በፍጹም አይቀበልም። ይህ ህገ መንግስት እነዚህ ብሄር ብሄረሰቦች አንድነታቸውና ማንነታቸው ለዓለም የሚገልጹበት መለያ የሆነ ምልክት ከማሃሉ ያለው ባንዴራ በአንቀጽ 3 ደንግጓል። በተጨማሪ ደግሞ አዋጅ ቁጥር 48/1999 በዝርዝር ባንዴራው እስከነ ምስሉ አስፍሯል።
የብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተ በኋላ ብሄር ብሄረሰቦች ዶ/ር አብይ ከነዶክተር ብርሃኑ ነጋና መሳይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ከማይቀበሉ ጽንፈኞች ጋር ብድብቅ እያሴረ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝማችንን በትኖ አሃዱአዊነትን ሊያነግስ፣ ህልውናችን፣ ባህላችንና ቋንቋችንን ሊያከስም የተነሳ ሴራ ነው የሚል ከፍተኛ ተቃውሞዎችን በማስነሳታቸው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ጀምሮ የተለያዩ የፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናት የብልጽግና ፓርቲ ያለውን ሕገ መንግስት የሚቀበልና ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርአቱን የሚያስቀጥል ነው፣ የብሄር ብሄረሰቦች መብቶችን አይደፈጥጥም እያሉ ደጋግመው ምለው ተገዝቷል።
በተግባር
የሚታየው ግን ሌላ እየሆነ
ነው። ትንሽ ሳይቆዩ ትላንትና
ባህር ዳር የተደረገውን
ሀገ መንግስቱን የመጣስ
ተግባር የብልጽግና ፓርቲ
ከፍተኛ አመራሮች በሰሜን
አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች
እየተዘዋወሩ በግላጭ ሕገ
መንግስቱን የመጣስ ዘመቻ
እየደገሙት ነው። ብሄር
ብሄረሰቦች ያጸደቁትን
ባንዴራ በመተው የድሮ
ልሙጡን ባንዴራ በረዥሙ
ሰቅለው ተገኝቷል። ለአብነት
ይሆናችሁ ዘንድ ዘ ሃበሻ
ካሰራጨው ዜና ትመለከቱ
ዘንድ ሊንኩን የአማራ ክልል ባንዴራ ነው እንዳንለው የአማራ ክልል ባንዴራ ነው ተብሎ ብህግ የጸደቀው ባንዴራ ከስር ያለው ነው።
ታድያ በሕገ መንግስቱ ያልጸደቀውን ልሙጡን ባንዴራ በረዥሙ ሰቅሎ መገኘት ሕገ መንግስቱን መጣስ አይደለምን?ይህ ህገ መንግስቱን የመጣ ምልክት ቀላል ኣይደለም። የብልጽግና ፓርቲ ጉዞና ለሀገ መንግስቱ ታማኝ አለመሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። እነዚህ ሰዎች ዛሬ እንዲህ ካደረጉ ብሄርና ብሄረሰብ የሚል ቋንቋ እንደ እሬት ይመራቸዋልና ነገ በኢትዮጵያ ያለውን የክልሎች አከላለ አፍርሰው ኢትዮጵያን በአራት፣ ወይም እንደ ድሮ በጂኦግራፊ በክፍለ ሃገር እንደማይከልሉትና የብሄርና ብሄረሰብ ህልውናን እንደማያከስሙ ምን ዋስትና አለን? የብሄር ብሄረሰብ መብቶችንንና ህገ መንግስታቸውን አከብራለሁ ያለ ፓርቲ ባንዴራቸውን ካላከበረ ምን ሊያከብር ነው?ለህገ መንግስቱ ያለው ታማኝነትስ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?ሸፍጥ ብዙ ርቀት መጓዝ አይችልም። ሃቀኛ ገጽታ መደበቅ አይቻልም። የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሃላፊዎች የብልጽግና ፓርቲ ጸረ ሕገ መንግስትና ጸረ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም መሆኑን በህገ መንግስት የጸደቀውን ባንዴራ አስወግደው ልሙጡን ባንዴራ በማንበልበል ገሃዱን ለዓለም አጋልጧል።
|