Back to Front Page


Share This Article!
Share
ትግራይ ክልል ውሰጥ የታሰሩ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች ይፈቱ ።

ግራይ ክልል ውሰጥ  የታሰሩ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች ይፈቱ

ልኡል ገብረመድህን (ከአሜሪካ )

ቀን   ጥር 26 /2011 ።

     በእኔ እይታና አሰተሳሰብ ትግራይ የስልጣኔ መሠረት እንደሆነ ይሰማኛል ትግራይ ሰልም የትግራይ ህዝብ ማለቴ ነው የትግራይ ህዝብ የአስተሳሰብ ደረጃ የሚመጥን የአስተዳደር ተቋም ያሰፈልጋል በሳይንስ ጥበብና ህዝብ አሰተዳደር መልካም ውጤት የነበረው ህዝብ ያን ሰብዕና የሚያስቀጥል በመርህ ላይ የቆመ አሰተዳደር ያለመኖሩ ከማሳዘንም ያለፈ ነው

Videos From Around The World

    የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት  ነው ። የኪነጥበብ  ፣ ሰነ ህንፃ ፣ ሰነ መንግስት ፣ ሰነ ህግ ፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ ማዕከል ሆኖ ዘመናት የተሻገረ ህዝብ ቁልቁል የሄደበት አንዱና ዋናው አስረጅ የአስተዳደር ተቋም ብልሹነት ወይም ተቋም ያለመኖር ብሎ መደምደም ይቻላል ። የአክሱም መንግሰታዊ ሰልጣኔ እንደ ራእይ ካልተጠቀምንበት ፣ ሲቀጥልም ካልተማርንበት ወድቀት መጋበዝ እንደሆነ ይሰማኛል ። ትግራይ የዲሞክራሲ ተቋም ተምሳሌት መሆን ነበረባት ። እድሉም ነበራት። ትግራይ ህዝብ ሳይሆን መሪ አጥታ ምጥ ላይ ቆይታለች = አሁንም ምጡ እንዳለ ነው ። የትግራይ ህዝብ የሚመጥን መሪ ወይም የፖለቲካ ተቋም የለም ። የተስተካከለና በጭብጥ የተማከለ ታሪክ ያለው ህዝብ በመንግሥት አሰተዳደር እጦት ሲቸገር ማየት ይከብዳል ።

   በትግራይ ክልል ውስጥ የአስተዳደር ሰልጣን ላይ ያለ የፖለቲካ ድርጅት ለትግራይ ህዝብ ፈፅሞ አይበጅም ። መነሻ ሆነ መድረሻ ምክንያት አንድና ያው አንድ ነው ። ይህውም  ትግራይ እያስተዳደረ ያለ የፖለቲካ ድርጀት በዝምድና ሐረግ የተተበተበ ከመሆኑም ባሻገር ድርጅታዊ ባህሪው ደግሞ ፀረ ዲሞክራሲ ነው ።  የመጀመሪያ ተግባሩም ነፃ ሃሳብን መቀንጠሰ ላይ ያተኮረ ሲሆን በሌላ ጎን ደግሞ የታርጋ ልጣፋ ሥራ ይሰራል ። በዚህ ሁኔታ በርካታ የትግራይ ሙህራን ሰለባ ሆነዋል ። በርካታ የፖለቲካ ሙህራን ተሸመድምደዋል። የትግራይ ሙህራን አገራዊ ሆነ ክልላዊ ሙህራዊ አሰተዋጽኦ ሳያደርጉ ቆይተዋል።

   የትግራይ ህዝብ የጥቃት ሰለባ የሆነው በራሱ ክልሉ በሚመራ ድርጅት ነው ። ህዝቡ የሐሳብ ነፃነት ተከልክለዋል ፣ ጥርናፈ በዝቶበታል ፣ በድህነት እንዲኖርም ተደርጓል ። There is  and has been sort of motif systemic political sickness within the political party that administers Tigrai Regional State . ለህግ ልዕልና ተገዢ ያልሆነ  ድርጅት አገራዊ ሆነ ክልላዊ የተረጋጋ ሰላምና የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጣ አይችልም ።  በትግራይ ውስጥ ድርጅታዊ አፈና በሰውር ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ይህ የማይቀር እውነታ ነው ። ጉዳዩ አንድ በሬ ሰቦ አንድ ድርጅት አሰቦ የሚመጣ ለውጥ ለእኔ ግልፅ አይደለም ። ከታርጋ ለጣፊ ድርጅት የሚገኘው አገልግሎት እርባና የለውም ።

    በትግራይ ክልል ያልተሸራረፈ የዲሞክራሲና የፍትህ ተቋም ሳይውል ሳያድር ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ ነው ። ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም ። እስከአሁን በመዘግየቱ በክልሉ ለተፈፀሙት መንግሰታዊ ጉድለቶች መሪ ድርጅቱ ከተጠያቂነት ነፃ አይሆንም ። ባልፈፀሙት ወንጀል ታረጋ ተለጥፎባቸው በትግራይ ክልል እስርቤቶች ታሰሮ ያሉ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው ። ትግራይ እያስተዳደረ ያለ መሪ  የፖለቲካ ድርጅት የፖለቲካ ድርጀት አባሎች ለማሰር ተቋማዊ ብቃት ፈፅሞ የለውም ። ማን አሳሪ ማን ታሳሪ ይሆናል ። መታሰርም ካለበት ራሱ መሪ ድርጀቱ መሆን አለበት ። የአረናም ሆኑ የሌላ ፖለቲካ ድርጅት እስረኞች ይፈቱ ! ። በትግራይ ዲሞክራሲና ፍትህ ይንገሥ ፣ አፈና ይወገድ ።

    ትግራይ የውጭ ሆነ የውስጥ ችግሮች ያሉባት ክልል ሆናለች ። ከኤርትራ ጋር ያለው ግኑኝነት ግልጽነት ይጎድለዋል ። የኤረትራ ህዝብ ከማንም በላይ ለትግራይ ህዝብ ይቀርባል ብቻ ሳይሆን ደማዊ ትስስር ያለው ህዝብ ነው ። ህዝቦች ላይ ችግር አልነበረም ፣ የለም ፣ አይኖርም ። የፖለቲካ ጎረምሶች እልህና መካረር የፈጠረው ችግር ለተራው ህዝብ ተረፈ ። በችኮላና ሰሜት የተፈፀመ ስህተት ቤተሰቦች አለያይተዋል ፣ አገር ጎድተዋል ፣ ሰላም ደፍርሷል ። የተፈፀመ ስህተት ለማስተካከል ጊዜ መውሰዱ አይቀርም ። ምክንያትም አሁንም እየተደራደሩ ያሉት ችግር ፈጣሪ  የነበሩ በመሆናቸው ሰላም በአጭር ጊዜ ተግባራዊ አይሆንም ። ችግር ፈጣሪዎች አንዳቸው ወይም ሁለቱም ማሰወገድ የግድ ይላል ። በትግራይና ኤርትራ ህዝብ ቀናኢ ሰላምና መልካም ግኑኝነት እንዲሰፍን የኤርትራ መሪ ሆነ ትግራይ የሚመራ የፖለቲካ ድርጅት መወገድ ጊዜ የማይሰጥ አንገብጋቢ ጉዳዩ ነው ። ሌላው አማራጭ ደግሞ ተቀራርቦ መነጋገርና ፍትሀዊ ይቅርታ መፈጸም ይሆናል ። ከዚህ ውጭ ተአምር የለም ።

     ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ ታሪክ የላትም ። በመሆኑም ትግራይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላት ተሰሚነት ክልሉ በሚመራ የፖለቲካ ድርጀት ምከንያት አሁን አሁን እምብዛም አይደለም ። ትግራይ በኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ክልል ከመሆኗም በላይ የአገር ዘብ ጠባቂ ክልል ነው ። በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙም ጊዜ ውጫዊ ሆኑ ውስጣዊ ችግሮች ከሰሜኑ ጫፍ የሚመነጩ በመሆናቸው ትግራይ የመጀመሪያ ተጠቃሚ የመሆን እድሉ ስፋትና ጥልቅ አለው ። በመሆኑም ያለ ትግራይ በኢትዮጵያ የተረጋጋ ሰላም ሊኖር የሚችል አይሆንም ። ውስጣዊ ሰላም ደግሞ የሁሉም መነሻ ምከንያት ነው ። አሁን በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት መልካም ግኑኝነት የለም ።ለህዝብ አይነገር እንጂ ችግሮች አሉ ። የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የማንነትና የአስተዳደር ጉዳዮች ኮምሽን አልተቀበለውም ። ይህ ለማድረግ ክልላዊ ሰልጣን እንዳለው የሚያሳይ የህግ ማዕቀፍ የተዛባ ነው ። የሆነ ሆኖ ይህ የክልል ምክር ቤት ውሳኔ ችግር መውለዱ አይቀርም ። በሌላ ሁኔታ ደግሞ የትግራይ ክልል በሂደት የፀጥታና የኢኮኖሚ ችግሮች ያጋጡሙታል። የክልል በጀት እጥረት / Regional Budget Constrain / ያጋጥመዋል ። ሰራ አጥነትና ወንጀል ይስፋፋል ። ችግሮች ለመፍታት የሚችል የበቃ አመራርና ድርጅት ባለመኖሩ የችግሮች ጥልቀት ከፍተኛ ይሆናል ።

   በትግራይ ክልል በሒደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ለመፍታት የህዝብ የአስተሳሰብና እይታ ለውጥ / Paradigm shift / በእጅጉ አሰፈላጊ ነው ። ህዝብ በርጋታ ቀጣይ ጥቅሙንና ጉዳቱን መገንዘብ ይኖርበታል ። የክልሉ ፖለቲካ ድርጅት የተሳሳተ አካሔድ ማስቆምና እንዲስተካከል የማድረግ የፖለቲካ ድርጀቱ ሳይሆን የህዝብ ሐላፊነት ነው ። በተለይ የትግራይ ወጣቶች ሙሁራን የተዛቡ የክልሉ ማህበረ አኮኖሚ የመግራት ሀላፊነት አለባቸው ። ድርጅታዊ አፈና እንዲቆም መታገል አለባቸው ። የመናገርና የመደራጀት ነፃነት ያለምንም የክልሉ ፖለቲካዊ ድርጅት ተፅዕኖና አፈና መንቀሳቀስ መቻል ይኖርባቸዋል ። ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግና የትግራይ ህዝብ ከውጭ ሆነ ውስጥ ጥቃት መከላከል የትግራይ ወጣቶች ግዴታ ነው ።

   በትግራይ ክልል ለሚደረጉ የነፃነት አፈናዎች መሪ የፖለቲካ ድርጅቱ ተጠያቂ ይሆናል ። በትግራይ ክልል አንድም ሰው ቢሆን በፖለቲካ አመለከቱና እይታው መታሰርና መቀጣት ይቁም ። የበሰለ የፖለቲካ ወይይት / Political dialogue / መጠናከር ነበረበት ። አሁንም መፈጸም አለበት ። በጠላትነት መተያየት ይቁም ። በውይይትና ደርድረው እንመን። ዛሬ የሚወሰዱ የአፈና እርምጃዎች ለነገ አይበጅም ። ይቅር መባባልና መደማመጥ ማደግ አለበት ። መጠቃቃትና መጠፋፋት ይቁም ።  ለዚህም ያለወንጀላቸው የታሰሩ የትግራይ ፖለቲከኞች ያለምንም ሁኔታ ከእሰር ይፈቱ።

  በትግራይ የፍትህ ሰርአት ይስተካከል ። ያለ ሞያዊ ብቃት የፍትህ ተቋማት ማስተዳደር ፈፅሞ አይታሰብም ። የፍርድ ጉዳይ በፖለቲካ ታማኝነት አይለካም ። የፖለቲካ ሰው ህዝብ ማስተባበር እንጂ የፍትህ ተቋም ማስተዳደር ፖለቲካዊ ካልሆነ በቀር ሞያዊ ሊሆን ፈፅሞ አይችልም ። የትግራይ ህዝብ ከፖለቲካ የፀዳ ገለልተኛ የፍትህ ተቋም ያስፈልገዋል ። በትግራይ ክልል የፍትህ መዛባት ከሌሎች ክልሎች የከፋ ነው ።  የፍትህ ስርአቱ በዝምድናና ትውውቅ አልያም በፖለቲካ ጥገኝነት የሚፈፀም በመሆኑ በክልሉ ፍትህ አለ ለማለት አያስደፍርም ። የሥራ እድልም ቢሆን የፖለቲካ ጥገኝነት ያላቸው ሰዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ያገኛሉ ። ያውም ሥራ ከተገኘ ። ይህ አግባብነት የለውም ። ብዙ የተማሩ የትግራይ ወጣቶች ሥራ አጦች ሆነዋል ። አንዱ ምክንያት ደግሞ የክልሉ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከአምስት በመቶ (5 %) አይበልጥም ። ክልሉ ሰባ ከመቶ (70 % ) በፌደራል በጀት የሚተዳደር ክልል ነው ።

   ትግራይ በኢንዱስትሪ የበለፀገች ክልል ማድረግ ጊዜ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም ። ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የሰው ክህሎትና የገንዘብ አቅም ይጠይቃል ። በእኔ እይታ የሰው ክህሎት አለ። የሌለው የገንዘብ አቅም ብቻ ነው ። ክልሉ የሚያስተዳድር የፖለቲካ ድርጅት የናጠጠ እምቅ የገንዘብ አቅም አለው ። ትግራይ ለማበልፀግ የድርጅቱ ገንዘብ ከሚፈለገው በላይ ነው ። የሚያስፈልገው ቀና አመለካከትና እሳቤ ብቻ ነው ። የትግራይ ክልል መሪ ድርጅት ያለው መዋዕለ ንዋይ ትግራይ ለማበልፀግ ከበቂ በላይ ነው ። ይህ ሳያደርግ ቢቀር ግን ድርጅቱ በሒደት አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ጉዳይ ነው ።

    

Back to Front Page