Back to Front Page

በትግራይ ጀነራሎች የተፈፀመ ግድያ ከባህርዳር መፈንቅለ መንግስት ይያያዛል?

በትግራይ ጀነራሎች የተፈፀመ ግድያ ከባህርዳር መፈንቅለ መንግስት ይያያዛል?

ተፃፈ በወዲ መንገለ 6-27-19

ሰኔ 15, 2011 በጀነራል ሰዓረ መኮነን እና በመጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ በቤታቸው ውስጥ (በጀነራል ሰዓረ መኮነን መኖርያ ቤት ) በጠባቅያቸው በኩል አሰቃቂ የሆነ ግድያ ተፈፀመባችዋል። እነዚህ ጀነራሎች አኩሪ ታሪክ የሰሩ የትግራይ ምርጥ ልጆች ናቸው። በሉ ጀግኖቻችን ናቹ እና ዕረፉ ከሰማታትና ተፀንበሩ ክብሩ እናመሰግናለን ሰማታትና።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ከተማ ባህርዳር ላይ የተፈፀመ መፈንቅለ መንግስት (በእኔ እምነት መንግስት እንካን አልነበረም) ሙከራ በክልሉ ፀጥታ ኃላፊ በብርጋዴል ጀነራል አሳምነው ፅጌ የሚመራ መሆኑ ተገልፀዋል። ከሁሉም በፊት መግለጫ ለመስጠት የዳዳው ንጉሡ ጥላሁን የሚባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሰክሬታራያት ኃላፊ በEBC ነው። በመግለጫው መፈንቀለ መንግሰቱ በመከላከያ ሃይል እንደከሸፈም ጨምሮ ገልፀዋል። ከሌሊቱ ስድስት (6) ሰዓት አከባቢ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ቴቪ ብቅ ብሎ በአምራ ክልል በለስልጣናት ሞትና ጉዳት እንደደረሰ እንዲሁም መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ ከፍተኛ አመራር ሲሰጥ የነበረው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ዋና አዛዥ (ጀነራል ሰዓረ መሆኑ ነው )ጥቃት እንደተፈፀመበት አሳወቀ። ከጎሬቤት ሃገርዎች እገዛ ለመስጠት እንደጠየቁም ጨምሮ ገልፀዋል።

Videos From Around The World

በሁለቱም ጀነራሎች የተደረገው ግድያ ከባህርዳር በነበረው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተያያዘ መሆኑ መንግስት ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በእኔ እምነት በጀነራል ሰዓረ መኮነን የተገደለው ከባህርዳር ተፈፀመ የተባለው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተያያዘ አይደለም። ይሄ የምለው በምክንያት ነው። በባህርዳር ከተማ የተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እኔ እስከማቀው መፈንቅለ መንግስት አድራጊው እና የክልሉ መንግስት መሃከል ምንም አይነት ልዩነት አልነበረም። በተለይ በፌደራል መንግስት (አብይ አህመድ ) ሁለቱም አካላት የለውጡ ሃወርያት ተብለው የተሞካሹ ናቸው። አሳምነው ፀጌ ይሁን አምባቸው መኮነን (ዶ/ር) ለሚድያ የሚሰጡት መግለጫ እንዲሁም በተለይ በተለያዩ መድረኮች የሚያደርጉት ንግግር ተመሣሣይ እና መንም አይነት በመሃከላቸው ልዩነት የሌላቸው ናቸው። በተለይ በአማራ አክራሪነታቸው ፣ የትግራይ ህዝብ ጠልነታቸው ፣ ለሕግ መንግስቱ ክብር እንደሌላችቸው እና እንደማይቀበሉት ፣ በፍኮራቸው እና በሽለላ ችሎታቸው ሁሉም ያው ናቸው። ሁለቱም የአብይ አህመድ መደመር ፖለቲካ ደጋፊዎች እና አቀንቃዮች በተለያየ ጊዜ የገለፁ ሰዎች ናቸው። በተለይ አሳምነው ፅጌ በባህርዳር በተደረገው የአብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ንግግር አድርጎ ነበር። ለአብይ አህመድ የገለፀበትም መንገድ አስገራሚ ነበር፤ የኢትዮጵያ ሙሴ የሚል ይዘት ያለው መልክት አስተላልፎ ነበር። ለዚህም ነው በመደመር ፖሎቲካ መርህ መሰረት (በሬ እና ጅብ አብሮ እንደመኖር ማለት ነው ) ወንጀል ሰርቶ ተፈርዶበት እስርቤት የነበረ በኃላ በይቅርታ የተፈታው አሳምነው ፅጌ የክልሉ ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ኃላፊ ተደርጎ የተሾመው።

በጊዜ ሂደት የሃሳብ ልዩነት ወይም የስልጣን ሽምያ አይፈጠርም ወይም አይኖርም አይባልም። ይሁን እንጂ በአጭር ጊዜ በተለይ ደግሞ የአማራ ጠላት (ትግራይ፣ አማራ ወይም ሌላ ፌደራሊስት ኃይል ) በዝተዋል ወይም አማራ ተከቧል በሚባልበት ጊዜ ይሄ ይከሰታል ተብሎ አይገመትም። ግን ሆነና አንዱን ሌላኛውን ለመብላት ወይም ስልጣን ለመንጠቅ ተሞከረ። የፌደራል መንግስት እንዳለው ህግና ስርዓት ለማስከበር በተለይ ለሚፈጠረው እልቂት ለመቀነስ ጣልቃ እንዲገባ ተደርጎ መፈንቅለ መግስት ሙከራው ከሸፈ። በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድራጊው ኃይል ስር ገብተው የነበሩ የመንግስት ቢሮዋች እና የፀጥታ መዋቅር ለማስመለስ እንደተቻለ ተገልፀዋል። እዚህ ላይ ትኩረት እንዲሰጠው የሚፈልገው አብይ አህመድ ስለ መፈንቅለ መንግስት ሙከራና ክሽፈት እንዲሁም ከመፈንቅለ መንግስት ሙኮራ ተያይዞ ተፈፀመ የተባለው ጥቃት የሰጠው መግለጫ ነው። አብይ አህመድ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረው እና በበላይ ሲመራ የነበረው ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጥቃት እንደተፍፀመበት ገልፀዋል። እዚህ ልብ ማለት ያለብን መፈንቅለ መንግስት የተደረገው ባህርዳር ነው ጀነራል ሰዓረ መኮነን የተገደለው ወይም ጥቃት የተፈፀመበት ግን አዲስ አበባ ነው። ከየት ወዴት ነው ነገሩ? ሌላ በአብይ አህመድ የሚዘውሩ እና ባለፈው አንድ ዓመት ድራማ ሲሰሩ የነበሩ ሚድያዎች እንድለመዱት በጀነራሎቹ ገዳይ ሌላ ድራማ ለመስራት መኩረዋል። ግን የአሁን ዳይሬክተሩ አልተሳካለትም። በሰባት (7) የዜና እወጃቸው ሙተዋል ተብሎ የታወጀውን ገዳይ በማታ አንድ ሰዓት ላይ ገዳዩ አልሞተም እየታከመ ነው ብሎው ሌላ ዜና አስነግረዋል። ወይ ኢትዮጵያ የስመኘው በቀለ ድራማ በሰዓረ ሊደገም?

እስቲ የእኔ ጥያቄ ላንሳ፡ ሰዓረ መኮነን በባህርዳር የተሞከረው መፍቅለ መንግስት ለማክሸፍ በሚደረገው ጥረት በከፍተኛ ኃላፊነት በመምራት እያለ በአጃቢው ተግደለ ወይም ለማክሸፍ ትዕዛዝ ስለ ሰጠ በውስጥ ቅጥርኞች ተገደለ የሚለው መርዶ እንዴት ልቀበለው ወይም ልመኖው? በዛች ቅፀበት አጃቢ ይቅር እና የመርጃ አነፍናፊ የሚባሉ ሰዎች(ጋዜጠኞች ) ጥርት ያለ መርጃ ስለመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ባላገኙበት ሁናቴ በባህርዳር መከላከያ ኃይል እንዲሰማራ እንዲሁም ሙከራው እንዲከሽፍ ሰዓረ መኮነን ስለ አደረገ ወይም ትእዛዝ ስለአስተላለፈ አጃቢው ይህንን ሰምቶ ገደለው የሚል መግለጫ ለእኔ እንደ ማፌዝ ነው። ሰዓረ መኮነን ጥብቅናው ለሕገ መንግስቱ ነው ፤ ለአምባቸው ወይም ለአሳምነው አይደለም። አንዱን ከአንዱ ለይቶ ሊደግፍ አይችልም። ምክንያቱ ሁለቱም የትግራይ ህዝብ ዘር መዘሩ ማጥፋት የሚፍልጉ ፣ ህገ መንግስቱ የማይቀበሉ ናቸው። ይሁን እንጂ አምባቸው መኮነን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተብሎ የተቀመጠ ሰው ስለሆነ በምንም መልኩ በሕገ ወጥ መንገድ ከሰልጣን ማውረድ አይቻልም ፤ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ነው። ግን ተደረገ የክልሉ ፕሬዚደንት ዶ/ር አምባቸው መኮነን ጨምሮ ሌሎች ሁለት የክልሉ ባለስልጣናት እንደተገደሉ ተገልፀዋል። እኔ በግሌ የተቃጣውን ግድያ በጣም አዝኛለው፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይሄ ድርጊት አወግዛለው።

ወደ ዋናው ጉዳይ ልመልሳቹ። በመጀመርያ ሰለ ጀነራል ሰዓረ መኮነን በዚህ በአንድ ዓመት ያሉኝ እውነታዎች ላካፍላቹ።

1. ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ሁኖ ከትሾመ ብዙ ሳይቆኝ ለትምርት ወደ ውጭ እንዲሄድ ብዙ ውትወታ እንደተደረገ፣ ይሁን እንጂ እንዲሄድ ፍቃደኛ እንዳልሆነና በስራው መቀጠል እንደፈለገ፤ 2. ጀነራል ሰዓረ መኮነን ትግራዋይ ስለ ሆነ ያለበት ቦታ ይዞ እንዲቅጥል አይፈለግም። በተለይ በለውጡ ኃይል ነኝ ባዩ ይሁን በትምክህት ኃይል (በደርግ ትርፍራፌዎች እና ርዝራዜዎች ) በትግራይ ላይ የሚቃታውን ማንኛው ትእዛዝ አያስተላልፍም ወይም ሲቃጣ ዝም ብሎ አያይም ተብሎ ስለሚታሰብ፤ 3. በቅርብ ጊዜ የጀነራሉ አጃቢዎች የብሄር ተዋፅኦ በሚል ፈሊጥ ተቀይረዋል ወይም ተበውዘዋል። በማን ለምን የሚለው ጥያቄ መንሳቱ ተገቢ ነው። መልሱም ግልፅ ነው። የለውጡ ሃወርያ (አላምንበትም) የሚባለው ለማ መገርሳ ለምን መከላኪያ ሚኒስቴር እንደተመደበም መዘጋት የለብንም። 4. ጀነራል ሰዓረ መኮነን ዋና ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ቢሆንም ባለፈው አንድ ዓመት ለተፈጠሩ ችግርዎች ለመፍታት (በጎንደር ፣ በቅማንት ፣ ጭልጋ ፣ ከምሴ ፣ በወለጋ ወዘተ) የተደረጉ ዘመቻዎች (Operations) በዋናነት የሚመራው እና መግለጫዎች ሲሰጥ የነበረው ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም እና የኦፕሬሽን ዋና መምርያ ኃላፊ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ነው። ታድያ ዛሬ ላይ ደርሶ ሰዓረ መኮነን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ በዋናነት ሲመራው ስለነበረ በአጃቢው ተገደለ ሲባል ትንሽ ግር አይልም ትላላቹ?

በእኔ እይታ የተመኮረው መፈንቅለ መንግስት መመኮሩ አይቀር የለውጡ ኃይል ነኝ ባዩ ይሄን አስታክኮ ሰዓረ መኮነን (ጀነራል ) በመግደል አራት ነገሮች ማሳካት እንደሚችል መገመት ከነበረው አንድ ዓመት ልምዱ ማየት ይቻላል።

1. የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አጀንዳ ለማስቀየስ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ትክረት ለመከፋፈል (የትግራይን ጨምሮ)

ይህ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለለውጥ ኃይል ነኝ ባዩ (Team Lema ) ሌላ የዓመቱ ከባድ ውርደት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም ለውጥ ሳይሆን የነውጥ ጊዜ ላይ እንዳለን ያረጋግጣል። ለውጥ የሚባለው ነገር ውሸት እንደሆነ የመጨረሻው መርዶ ይሆናል። ግን የህዝቡን ትኩረት እንዲከፋፈል ጀነራል ሰዓረ እንዲገደል ተደርጎ በተለይ የትግራይ ህዝብ በራሱ ልጅ (ልጅዎች ) ሃዘን ላይ እንዲጠመድ አድርገዋል።

2. የፕለቲካ (የመደመር ፖሎቲካ ) ክስረት ለመቀነስ

በነበረው የአንድ ዓመት የውሸት ለውጥ ፀረ-ለውጥ ተብሎ የተፈረጀው ህወሃት (TPLF) እና የትግራይ ህዝብ አሁን ባህርዳር ላይ እየተፈፀመ ያለው ነገር ቀድም በተለያየ ጊዜ ግልፆታል። በተለይ ከጎንደር ኢና ሌሎች የአማራ ከልል አከባቢዎች ከ80,000በ በላይ የትግራይ ተወላጆች በግፍ ሲፈናቀሉ እና ንብረታቸው ሲዘረፍ የትግራይ ህዝብና መሪው ድርጅት ህወሓት በትግስት በመያዝ በተለያየ ጊዜ ምክራቸው ሲለግሱ ነበር። በተለይ ይህ ያበደ የትምክህት ሃይል በጊዜው ካልቆመ ለማአራ ህዝብ አልፎ ለኢትዮጵያ ህዝብ አደጋ እንደሚሆን በተለያዩ መድረኮች ምክር ስጥተዋል። ግምት ሆኖ አልቀረም ተከሰተ። ይህ ግምት አርቆ አስተዋይነት እና የፖለቲካ ነብይ የምያስብል ስለ ሆነ ይህ ክስተት አስታክከ የመደመር ፖሎቲካ ክስረት ለመቀነስ አንድ ነገር መደረግ ነበረበት። አብይ አህመድ ሁለቱም ጀነራሎች በመግደል የትግራይ ህዝብ በጀግኞቹ ሐዘን ብቻ እንዲጠመድ አድርገዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ የምያስቦው የፖሎቲካው ብልሽት ወይም የእብድዎች ፖለቲካ (የትምክህት ኃይል ፖሎቲካ ) ስለማስታገስ ወይም መሳከም ሳይሆን በከባድ ሐዘን እና የድህንነቱ ሁኔታ ብቻ ተውስኖ እንድያስብ አደርገዋል።

3. የጀነራል ሰዓረ መገደል ከሁኔታው ማያያዝ ወይም ማላከክ

ሰዓረ መኮነን እና ገዛኢ አበራ ብዙ ነገር ያዩ እና ያሳለፉ ጀግኖች ናቸው። በተለይ ሰዓረ መኮነን የነበረበትን የሃላፍነት ቦታ ብዙውቹ እዛ እዲንቆይ አይፈለጉም። ምክንያቱ ደግሞ የለውጡ ኃይል ንኝ ባዩ ታማኝነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለውጭ ኃይላት ነው። ከኤርትራ እስከ አረብ አገራት ፣ ከኤርትራ እስከ ግብፅ ፣ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ እንዲሁም በጎረቤቶቻችን ያሉት አክራሪዎች ዘንድም ጀነራል ሰዓረ መኮነን እዚህ ቦታ ላይ መቀመጥ የለውጡ ኃይሉ ውሳኔ አልተወደደለትም።

ጀነራል ሰዓረ መኮነን ብጥብቅ ክትትል የነበረ ሰው ነው። በማይመጥነው ፖሎቲካ እየተመራ እየታዘዘ ችሎ እስካአሁን ቆይተዋል። ይህ ጉዳይ ሰዓረም ያውቀዋል የለውጡ ኃይሉም ያቃል። ግን ሰዓረ ካለበት ገሽሽ እንዲደረግ ይፈለግ ነበር እና በለውጡ ኃይሉ አሁን አሪፍ ጊዜ ተገኘ እና ተፈፀመ። እዚህ ላይ ማያያዝ የምፈልገው ግድያው ከተፈፀመ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጠው መግለጫ የጎረቤት ሃገራት(ስም ባይጠቀስም ) እገዛ ለማድረግ እንደጠየቁ ጠቁሞ ነበር። በእኔ ግምት ካለው የጎረብቶቻችን ፖለቲካ ሁኔታ እርድታ ለመስጠት የጠየቀች ሃገር በኢሳያስ አፈወርቂ የምትመራው ኤርትራ ነች። በሁለት ነገርዎች እንደዜጋ እፍረት ተሰምቶኛል። ኢትዮጵያ አቶ ኢሳያስ የሚመራትን ሃገረ ኤርትራ ወደ አለችበት ደረጃ ተምዘግዝገን ወርደን የኛ አቅም አውቆ ኢሳያስ እርዳታ እንዲሰጠን መጠየቁ አንደኛው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሂወቴ ኢሳያስ ኢትዮጵያን የመበጥበጥ ስትራቴጂው እውን ሁኖ በማየቱ በጣም አዝኛለው። ጀነራል ሰዓረ መኮነን ከህወሐት (TPLF) ታጋዮች እንዲታሰሩ ወይም እንዲወገዱ በኢሳያስ አፈውርቂከሚፈለጉ ግንባር ቀደም ታጋይ ነው። ምክንያቱ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ይሁን የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ በነበረበት ጊዜ የአቶ ኢሳያስ አፈውርቂ ቶንኮል እና የኢትዮጵያ የመተራመስ ስትራቴጂ ከጥቅም ውጪ ካደረጉት ጀግኖች አንዱ ነው ጀነራል ሰዓረ መኮነን። ለዚህም ነው የደስታ ብዛት በሚመስል መንኩ ፍጥኖ እገዛ ለመስጠት የጠየቀው የሚመስለኝ።

4. በትግራይ እና ባአምራ ህዝቦች ያለው መቆራቆስ ዘላቂ ማድረግ ፣ የኩሽ መግስት ምስረታ ማፋጠን

በጀነራልዎቹ የተደረገው እኩይ ተግባር ከተፈፀመ በኃላ በባህርዳር ከተደረገው መፈንቅለ መንግስት አያይዞ የተገለፀበት ሁኔታ ከባድ መልክት ያለው ነው። የድርጊቱ ፈፃሚ ከየትኛው ብሔር እንደሆነ ለመገመት አይዳግትም። በተለይ አሁን እየታሰበ ያለው የኩሽ መንግስት ሀገር ምስረታ የሚል ቅጀት እውን ለማድረግ የሚያግዝ ፕሮጀክት ሰለ ሆነ የተውሰደ እርምጃ ነው። ይህ በትግራይ እና በአማራ ህዝቦች መሃከል ያለው ሁኔታ ለማባባስ የተሸረበ ቶንኮል ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ግኑኘነቱ በመገዳደል የታጀበ ከሆነ ሁለቱም ህዝቦች አይዋደዱም እንዲሁም አይተባበሩም አለፍ ሲሉም በጦርነት እርስ ብርሳቸው ይጨራረሳሉ የሚል የዱኩማን አስተሳሰብ ምኞት እውን ለማድረግ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ ታስቦ የተሰራ ድራማ ነው።

ከላይ 1-4 የተጠቀሱ ነጥቦች ሰዓረ እና ገዛኢ በመግደል የሚገኙ ትርፎች ናቸው ተብሎ በለውጡ ኃይል ንኝ ባዩ ይታሰባል። ይህ የምልበት ምክንያት የአንድ ዓመት ጉዞ በመታዘብ እና በመተንተን ነው። ለምሳሌ የኢንጅነር ስሞኘው በቀለ አገዳደል ማድበስበስ ፣ የውሸት ዶክመንተሪዎች በመፈብረክ ሕዝቡን ማደናገር እንዲሁም በመንጋ እንዲጋዝ ማድረግ ፣ አንድ ወገን የሚያጥላላ የፖለቲካ እና ፕሮፓጋንዳ መንዛት መንግስት 100 ሚሊዮን አስተዳድራለው የሚል መንግስት የዕለት ተዕለት ስራው ሁኖ ቆይተዋል። ሌላ የብአዴን/ አዴፓ ጨምሮ ሌሎች የአማራ ክልል ፖለቲከኞች እብደት ከጀመረበት ጀምሮ ብዙ የትግራይ ተውላጆች ከአማራ ክልል ከቀያቸው በግፍ ተባረዋል ፣ ተገድለዋል እንዲሁም ያፈሩትን ንብረት ተዘርፈዋል አዘርፈዋል። ብዙ ሕፃናት፣ እናቶች እና አባቶች የትግራይ ሰው በመሆናቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ እና እንደእባብ ተቀጥቅጠው ተገድለዋል። ኃላፍነታቸው አልተወጡም ብቻ ሳይሆን በድርጊቱ ተሳታፊ በመሆን በፖሊስ በታጀበ መልኩ የትግራይ ሰው የሆነውን ንብረት ዘርፈው ሲያከፋፍሉ ነበር። ይሄም ብቻ አይደለም የተፈናቀለውን የትግራይ ተወላጅ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ በማድረግ ወደ ሱዳን ሃገር እንዲሰደዱ አድርገዋል። ታድያ የአብይ አህመድ መንግስት ይህ የትምክህተኞት የፖለቲካ ዕበት ከማሳቀም እና ከማስታገስ ይልቅ ማስታመም ነው የመረጠው።

በትምክህት እና በመንጋ የተዋጠው የብአዴን/ አዴፓ የፖለቲካ ድንቁርናው ጫፍ የሚለካው ይህ ያበደ ስብስብ ሂዶ ሂዶ ወደ ፖለቲካ ስልጣን መዝረፍ እንደሚሸጋገር አላወቀም ፤ ሲመከርም መስምያ ጀሮ የለዉም። መስሚያ ቢኖሮው ኑሮ የበረከት ስምኦን ምክር youtube ላይ ከፍተው ማዳመጥ በቂ ነበር። በአምራ ክልል የነበረው እብደት አድማሱ አስፍቶ ለአገሪቱ እንደሚተርፍ እና የአገሪቱ ከፍተኛ ስጋት (major tyrant ) እንደሚሆን በማያሻማ ቛንቛ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቁ በረከት ስምኦን ተናግሮ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው የብአዴን/አዴፓ እብደት ወሰን የለውም እና በረከትና ታደሰ ጥንቅሹ የተባሉ ነባር ተጋዮዎች እና የአላማ ሰዎች በመንጋ ውሳኔ አሰራቸው።

ሌላው ያበደው የአማራ ክልል ፖለቲካ የትግራይ ሕዝብ ጨፍልቆ ትግራይ ለመጨበጥ የነበረው ፍላጎት በቀጥታ ማሳካት ስላልቻላ (አፀፋው ከባድ እንደሚሆን ስለማያውቅ ) ፌደራል መንግስት እንድያስፈፅምለት በመደመር ፖለቲካ ስም ሰገደ። ይሁን እንጂ የፌደራል መንግስት ይህ የአምራ ከልል ፖለቲቀኞች እብደት አላስቆመም ይባስ ብሎ ያበደውን ለማስታመም ብዙ ርቀት ለመጎዝ መኩሮ ነበር። ፌደራል መንግስት በተቀናጀ መልኩ እብደዎችን ለማስደሰት ህገ መንግስት የሚጥስ አዋጅ አውጥተዋል ፣ ወደ ትግራይ የምያስኬዱ መንገዶች (በፌደራል መንግስት የሚተዳደሩ ) በእብዶች እንዲዘጉ ፈቅደዋል ፣ ከማህል ሃገር ወደ ትግራይ የሚጋጋዝ ማንኛው ነገር( በግ ፣ ጥራጥሬ ፣ ዘይት ወዘተ ) በወሮ በሎች በፖሊስ በታገዘ በየ ቦታው ሲዘረፉ አይቶ እንዳላየ ዝም ብለዋል፣ በአጠቃላይ በትግራይ ህዝብ ላይ ክህደት ሲፈፅም ቆይተዋል።

በመጨረሻ የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ባበዱ ፖለቲከኞች እየተመራ እዚህ ላይ ደርሰሃል። የምን ጊዜም ወዳች ጎረቤትህ በሁሉ መልኩ ከአንተ በባህል ይሁን በሃይማኖት የተቀራረበ የትግራይ ሕዝብ አስቀይመሃል ታዝቦበሃል። ግን ያንተ መለያ እንዳልሆነ ግን ያምናል። በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማትፈልግ እንዲሁም በተለይ ደግሞ አሁን በክልልህ እየተደረገ ያለውን አንተን የሚገልፅ አይደለም ብሎ ያምናል። የእብዶች አስታማሚ የነበረው የለውጥ ኃይል ነኝ ባዩ በዕብድዎች ማሃከል በተፈጠረው ንትርክ አስታክኮ ጀግነዎቻችን በመግደል ከሁኔታው በማያያዝ ከትግራይ እና በአማራ ግኑኝነት በደም ለመቀባት ሞክረዋል። ይሄን ተገንዝበ እነዚህ እብዶዎች አሸቀንጥረ ጥለ ራስህን መስለህ ከወንድምህ ከሆነው ከትግራይ ህዝብ ዳግም ግኑኘነትህ ማደስ ትችላለህ። አሁን የገጠመህ መጥፎ ጊዜ ተረድቶ የትግራይ ህዝብ ቂም አይዝልህም።

ክብር ለሰማቶቻችን!!!

 

 

 

 

-           


Back to Front Page