Back to Front Page

አምስተኛው ሹክ በተመለከተ። ፈጣሪ በኦቦ ለማ መገርሳ አድሮ ሊታረቀን ነው እንዴ?ክፍል አንድ

አምስተኛው ሹክ በተመለከተ። ፈጣሪ በኦቦ ለማ መገርሳ አድሮ ሊታረቀን ነው እንዴ?

ክፍል አንድ

 

በሰንደቁ ያይላል

ነሃሴ 25/2011

 

የመጨረሻው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ (የመጨርሻው የሚለው በሁለቱም ትርጓሜ ይወሰድልኝ በቅደም ተከተልነት የመጨረሻው/የቅርቡ ፣ ከአሁን በኋላ የመካሄድ እድሉም ጠባብ ስለሆነ የማብቅያ ስብሰባ በሚል) ከአዋዛጋቢና ደም አፋሳሽ ክስተቶች ብኋላ ባልተለመድ መልኩ መካሄዱ ይታወሳል። ያልተለመዱት ክስተቶች አንድም ከስብሰባው አዳራሽ ይጀምራል። ከሁለት ቀን ሰብሰባ በኋላ ያለመግለጫ የተጠናቀቀ መሆኑም ጭምር የተለየ ያደርገዋል። በዋናነት ልዩ የሚያደርገው ነገር ግን መግለጫ ባይሰጥም የስብሰባው አንኳር አንኳር ነጥቦች ሹክ በሚል ርእስ በአንድ ፀሃፊ መውጣቱ ነው። እኛም አነበብነው። በተበጣጠሰ መልኩ ሲሰማ የነበረው መረጃ በስርአት ሰንዶ ያቀረበ ፁሁፍ ነው። ሙሉ ፅሁፉን ይህን ሊንክ በመጫን ማንበብ ይችላሉ። http://www.aigaforum.com/amharic-article-2019/reportage-latest-eprdf-executive-meeting-08-2019.htm

እንደ እኔ እይታ ፣ የኢህአዴግ የመጨረሻ ስብሰባ ዋናውና ቁልፉ እይታ የተከበሩ አቶ ለማ መገርሳ ያቀረቡት ሀሳብ ነው (አምስተኛው ሹክ ነው)። በእርግጥም የአቶ ለማ አስተያየት አዳራሹን ያናጋ ሊሆን እንደሚችል አያጠራጥርም። በተጨናነቀው አደራሽ ውስጥ ከፊት ረድፍ ተቀምጠው የነበሩት ተሳብሲብዎች እንደ አይናፋር ተማሪ ወደ መጨረሻው ረድፍ ተቀምጠው አስተያየት ሲሰጡ የነበሩትን አቶ ለማን በእርግጥ እሳቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወደ ኋላ ገልመጥ ገልመጥ ሳይሉ አይቀሩም።

Videos From Around The World

አቶ ለማ ምንድ ነው ያሉት፥-

ንግግራቸውን የጀመሩት በሊቀምበር ዶክተር አብይ የተዘጋጀው የመወያያ ፅሑፍ አርእስትን በመቃወም ነበር። ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት የሚለው አርእስት ተቀይሮ ሁኔታችን የሚገልፀው አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው ቢሆን ነው የሚሻል አሉ። ኢህአዴግ ፈርሷል። የለም። ከአሁኑ የፈራረሰው ኢህአዴግና አገር ከለውጡ በፊት የነበረው ኢህአዴግና አገር ከነችግሮቹ ይሻላል አሉ። ከለውጡ በኃላ እየታዩ ያሉ ችግሮች በአገራችን ታሪክ ተከስተውና ታይተው የማያውቁ ናቸው። አገር የሚያጠፉ ናቸው። ዋናው ችግራችን ኢህአዴግ ኣለመኖሩ ነው። ለውጡ ስለተጠለፈ (hijacked ስለ ተደረገ) ነው ችግር ላይ የወደቅ ነው። መዳን ከፈለግን ኢህአዴግ ወደ ነበረበት ቁመና እንመልሰው። ወይም በሰላማዊ መንገድ እንለያይ አሉ።

ይህንን የአቶ ለማ መገርሳ ንግግር ደግሜ አነበብኩት ፣ ሰለስኩት ምንም ስሜት አልሰጥህ አለኝ። ደጋግሜ አነበብኩት። ኦቦ ለማ የጠናባቸው የጤና ችግር ውጭ አገር እያመላለሳቸው እንደሆነ ሲነገር ከርሞ ለወራት ከህዝብ እይታ ከተሰወሩ በኋላ የገረጣውና የወየበው ፊታቸው ትንሽ ወዝ አግኝቶ በተመለሱበት ማግስት ፥ እንዲህ አይነት አፈንጋጭ አስተያየት ምን የሚሉት ነው?። ምናልባት ወደማይቀረው መሄዴ ላይቀር ፣ ማተብ አስሬ ልጓዝ ብለው ይሆን?። እኔና አብይ ሞት ነው የሚለየን የሚለው መርህ የለሽ ድንፋታቸውስ የት ገባ?። ወይስ ፈጣሪ በኦቦ ለማ መገርሳ አድሮ ሊታረቀን ነው?

የተናገሩትን እስኪ አንድ በአንድ እንይ፥-

1ኛ - የዶክመንቱ ርእስ አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው በሚል ቢስተካከል ይላሉ!። በእርግጥም አገር አጥፍተን እኛም እየጠፋን ነው የሚለው የዶክመንት አርእስት ብቻ ሳይሆን የኢህአዴግ ተጨባጭ ሁኔታ ገላጭ ነው። አገር አጥፍተን እኛ እንኖራለን በሚል ስሌት የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ሀገር በልቶ መዋጥ እንደማይቻል ዘግይቶም ቢሆን ገብቷቸው ከሆነ አስየው ነው። የዘገየ ምህረት ከእርግማን ይሻላል ነው ነገሩ። ሓቁን ግን ደርሰውበታል ብዮ አስባሎህ። ባለፉት 18 ወራት በሀገር የደረሰው ጥፋት ውድመት ከሚል ቃል ውጭ ገላጭ የሆነ ቃል የሚገኝለት አይመስለኝም። በሁሉም ዘርፍ። ሀገር በተጠናና ባልተጠና መንገድ እየፈራረሰች ነው። መጠገን የማይቻልበት ደረጃ የደረሰ ይመስለኛል። ምናልባት ይህ የ አቶ ለማ ንግግርና መገለጥ ከጀርባው የሆነ ነገር አዝሎ ካልመጣ ፣ በኔ አረዳድ ምስጋና ለለውጥ ሀይሎች ኢትዮጽያ የሚባል ሀገር ታሪክ ከመሆን የሚታደገው አካል ያለ አልመሰለኝም። ይህን የሚታይና የሚጨበጥ ሂደት በሳይንሳዊ መንገድም ማረጋገጥ ይቻላል። Rule of law index, social progress index , indicators of a failed states ወዘተ የሚሉት የሀገርና መንግስት መለኪያዎች ተጠቅመው ኢትዮጽያን ቢፈልጓት የትም አያገኝዋትም። በሁሉም መለክያ አገር እየጠፋች ለመሆንዋ የምያከራክር አይደለም። እኛም እየጠፋን ነው የሚለውም ምንም ግራ ቀኝ የሚያሰኝ አይደለም። እንዴ!? ካጠገቡ የነበረ ሰው ብን ብሎ እየጠፋ እያየ አለን ደህና ነን ማለት ምን ማለት ነው?። ጓዶቻቸው እየጠፉ ከሆነ ኢህአዲግ እየጠፋ ነው። ኢህአዴግ የቀረው ነገር ሰዎቹ ነበሩ።. መስመሩማ ከጠፋ አመታት አስቆጠረ እኮ!። ኢህአዴግ አለ ሲባል የነበረው እኮ ቢያንስ የሰዎች ስብስቡ አለ ከሚል መነሻ ነው። ሰዎቹ በጠራራ ፀሃይ ሂወታቸው እየተነጠቀ እየጠፋን አይደለም ማለት ለመረዳት ያስቸግራል። እኔ እስካሎህ ድረስ የተፈጠረ ችግር የለም ከሚል አስተሳሰብ ካልሆነ ኢህአዴግ አለ የለም የሚለው ክርክር እኮ በኢትዮጽያ ኢሊቶች ዘንድ ፕሮግራም ተይዞለት የመወያያ አጀንዳ ከሆነ ቆይተዋል። ይህ አስተያየታቸው ወቅታዊውን የሀገሪቱና የድርጅቱ ሁኔታ በስሙ እንደመጥራት ነው።

2ኛው ፥ ከአሁኑ የፈራረሰው  ኢህአዴግና አገር ከለውጡ በፊት የነበረው ኢህአዴግና አገር ከነችግሮቹ ይሻላል ያሉት ነው። ይሄም በጣም ሚዛናዊ አስተያየት ነው። የድሮው ኢህአዴግ ችግሮች እንደነበሩት ገልፀዋል። ግን ከነችግሮቹ የያኔው ኢህአዴግ ይሻላል። ያኔ ቀን ተሌት እንደ ቆቅ ሀገርን የሚጠብቁ ተቋማት ነበርዋት። ያኔ ባለስልጣናትን ከህዝብ ሳይለይ የፀጥታና የደህንንት ስራ የሚሰሩ አካላት ነበርዋት። ያኔ ሀገርን የሚያጠፋ ችግር እንዳይፈጠር በጥንቃቄ የሚሰራ ኢህአዴግ ነበር። ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ ተግቶ በታታሪነት የሚሰራ ኢህአዴግ ነበር። በሰርጎገቦችና ከአፍንጫቸው በላይ ማየት በማይችሉ የእናት ጡት ነካሾች ውስጥ ለውስጥ ተቦርቡሮ ባዶውን እስኪ ቀር ድረስ። ይህ አስተያየት ሓቅና እውነት ብቻ ነው ሊባል የሚችለው።

3ኛው ፥ ከለውጡ በኋላ እየታዩ ያሉ ችግሮች በአገራችን ታሪክ ተከስተውና ታይተው የማያውቁ ናቸው ያሉት ነው። እዚህኛው አስተያየታቸው ላይ አንድ ማስታወሻ ብቻ ጠቅሼ ልለፍ። ምክንያቱም በሃቅነቱ ላይ ብዙ ተከራራሪ ያለ አይመስለኝም። የለውጡ ሂደት የፈጠረው ነው የሚል የድንዙዛን ማስተዛዘኛ ይሰጥበታል እንጂ በአዲስነቱና በልዩ ክስተትነቱ የሚማጎት ሰው የለም። ሰው በአደባባይ ቁልቁል የሚሰቀልበት ክስተት የለውጡ ቱሩፋት ነው። የክልል ፕሬዝደንት የሚረሸንበት ፣ ኤትማዦር ሹም የሚረሸንበት ክስተት የለውጡ ቱሩፋት ነው። አዲስ ክስተት ነው።

4ኛው ፥ ዋናው ችግራችን ኢህአዴግ ባለመኖሩ የተፈጠረ ነው የሚል ግምገማቸው ነው። ይህ አስተያየታቸውም እውነትና ሳይንሳዊ ነው። አንድ ድርጅት የራሱን ህልውና ሳያረጋግጥ የሀገርን ህልውና ማረጋገጥ አይችልም። በተለይ እንደ ኢህአዴግ ያለ ህልውናው ከሀገር ህልውና ጋር በተለየ መልኩ የተጣበቀ ድርጅት ብቃቱ ወርዶ ህልውናው አጠያያቂ ሲሆን ሀገር ያፈርሳል። በሚገርም ሁኔታ ፣ በሌላ አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ተቀናቃኝ ፓርቲን እንዳይፈርስ እዳይከስም በፆሎትም ጭምር የሚወተውቱት እኮ የኢህአዲግ አለመኖር መዘዙ ስለተረዱት ነው። የሁሉም ችግር ምንጭ ኢህአዴግ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተጓዘበት ያለው ፍጥነት መሆኑን ስለሚገነዘቡ ነው። እነ ዶ/ር መራራ ፣ አቶ ልደቱ አያሌው ፣ እና ሌሎችም በተደጋጋሚ ኢህአዴግ እንዲኖር ጫና እያደረጉ ያሉት ከኢህአዴግ ፍቅር ይዞቻው ሳይሆን የሀገሪቱ ዋና ችግር ኢህአዴግ አለመኖሩ መሆኑን ስለተገነዘቡ ነው። ኢህአዴግ በማንኛውም መለክያ በሂወት የለም ወይም ኮማ ውስጥ ነው። የሂወት አድን እርዳታ ተደርጎልት ይተርፍ እንደሆን የሚታይ ሆኖ በግምገማ ደረጃ አቶ ለማ መገርሳ የችግሩን ምንጭ በትክክል የተገነዘቡ ይመስላል።

5ኛ ፡ ለውጡ ስለተጠለፈ (hijacked ስለ ተደረገ) ነው ችግር ላይ የወደቅነው የሚለው ነው። እንግዲህ ከአቶ ለማ በላይ የለውጥ ሀዋርያ የት ሊገኝ ነው!። ከቄሱ በላይ እንዲሉ ለውጡ መስመር መሳት ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ከነአካቴው በጠላፊዎች እጅ ወድቆ አቶ ለማን ጨምሮ ሌሎች ኢህአዴጋውያን የለውጥ ሀይሎች የታገሉለት ለውጥ አድራሻውም የለም። አቶ ለማ ያቀጣጠሉት ለውጥ በጠራራ ፀሀይ የለውጡ ምልከቶች የሆኑት እነ ዶ/ር አምባቸዉን የሚበላ ስርአት አልበኝነት ያነግሳል ብለው እንዳልሆነ ማንም ጤነኛ አአምሮ ያለው ሰው መገመት ይችላል። አቶ ለማ የፈለገው አይነት ግንኙነት ይኑራቸው ግለሰብን ለማንገስ በማሰብ ለውጡን አቀጣጥለዋል ለማለት አይቻልም። አቶ ለማ ለለውጡ ካላቸው ቀናኢነት የተነሳ ብክንድ ርቀት የነበረውን ሰልጣን አሳልፈው ሰጥተዋል። ምናልባትም ከዚህ የተነሳ የተጠያቂነት ስሜት ሳይሰማቸው አይቀርም። አቶ ለማ የመጡበትን ክልል የተሻለ ለማድረግ እንጂ የፈረሰና የጦርነት ሜዳ ለማድረግ ቲም መርተው ለለውጥ አልታገሉም። ምናልባትም መፅሃፍ ኣዟሪዎች እንዳይዙት የተከለከለውና በአንድ ሚልዮን ብር ወጪ ተሰብስቦ እንዲቃጠል ተደርጓል እየተባለ ያለው የተጠለፈው ትግል የሚል መፅሃፍ የኣቶ ለማ መገርሳ ፅሁፍ ነው የሚባለው ጭምጭምታ እውነት ሳይሆን አይቀርም።

በመጨረሻም እንዲህ በማለት የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባሉ፥- መዳን ከፈለግን ኢህአዴግ ወደ ነበረበት ቁመና እንመልሰው። ወይም በሰላማዊ መንገድ እንለያይ አሉ። ይህ ማለት ኢህአዴግ ወደሚታወቅበት ዴሞክራስያዊ ማእከላዊነት የአመራር ዘይቤ ይመለስ ማለት ነው። ይህ ማለት መርህ አልባ ግኑኝነት አቁመን ሁላቸንም በግል ቁመን እንታጋል እንተጋገል ማለት ነው። መተጋገሉን የጀመሩት ይመስላል። ይህ ሃሳብ ከአንዳንድ እግር ያልተከሉ የስራ አስፈፃሚ ኣባላት ተቃውሞ እንደሚገጥመው የሚጠበቅ ቢሆንም ፣ ሀገሪቱንና ድርጅቱን ለማዳን ብቸኛው መንገድ ነው።

እንግዲህ የመፍትሄዎች መጀመርያ በሽታን ማዋቅ ነዉና እቶ ለማ የተሟላ ምርመራ አድርገው በድፍረት አስተያየታቸውን አቅርበው ከሆነ ኢትዮጽያ የመዳን ተስፋዋ የሚያለመልም ይሆናል። ኣቶ ለማ ወደፊት ከመጡበት ግዜ ጀምረው ስከታተላቸው ህዝባቸውንና ሀገራቸውን የሚወዱ ፣ ስብእናቸው የተስተካከለ ፣ ታታሪና እርጋታ የሚታይባቸው ይመስሉኛል። በበኩሌ ሀገር የመምራት ብቃትና ዝግጁነት የነበራቸው ይመስለኛል። በዚህ ደረጃ አስተያየታቸውን ለመስጠት ድፍረቱን ካላቸውም ሃገርን ለማዳን ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። ይሁንና አስፈላጊውን ጥንቃቄ መውሰድ እንዳለባቸው ግን መዘንጋት የለባቸውም። ንጉስ በስልጣኑ ቀናኢ ነው።

ከአቶ ለማ ንግግር በኃላ የአዴፓ፣ ደህዴን፣ እና የኦዲፒ ተናጋሪዎች ለማ ያለው ትክክል ነው ብለው ይጀምሩና ግን ኢህአዴግ አልፈረሰም። በጠና ታሟል ነው ማለት የምንችለው አሉ።

እዚህ ጋ የመጀመርያው የመጣልኝ ነገር አቶ ለማ መገርሳን በቀጥታ የተቃወመ ሰው አለመኖሩ ነው። የሶስቱ ድርጅት ተወካዮች በሊቀመንበሩ ተመልምለው ወደ ስራ አስፈፃሚነት ያደጉና በአብዛኛው በራስ መተማመናቸው የላላና ተለጣፊዎች በመሆናቸው እንዴት የአለቃቸውን ትኩረት ለማግኘት አቶ ለማን ቤተክርስትያን የገባች ውሻ አላደረጓቸውም?። ለማ ያለው ልክ ነው ግን. . . ለምን አስፈለገ?። ግን ስልጣናችን ነው? ግን በመሃላችሁ አያገባንም ነው?። አቶ ለማ ከላይ ያስቀመጥዋቸውን ሓቆች ትክክል ነው ብለህ ስታበቀ ግን ምን አመጣው?። ወይስ ይህ ስብስብ የጌታውን ፊት እያየ ቅምሻ መሳይ ነገር ለማግኘት እንደሚቅለሰለሰው ውሻ ሆነዋል!። ለምን ደፍረው ድጋፋቸውን አላጠናከሩም?። ምናልባትም ህወሓት ስለ ደገፋቸው ወይም ግምገማቸው ከህወሓት ግምገማ ስለሚመሳሰል ይሆን?። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው? የሀገርን ጉዳይ እየወሰኑ መሆኑን እንዴት ይዘነጉታል?። በካፈርኩ አይመልሰኝ ሀገር ለመምራት መሞከር መጨረሻው እነሱንም ለሀፍረትና ለውርደት ይዳርጋቸዋል። ይልቁንስ ትክክል የሚሉትን ሀሳብ ያለማወላወልና ያለይሉኝታ በቁርጠኝነት በመደገፍ የተንገራገጨው የለውጥ ሂደትን መስመር ማስያዝ ከአንድ ከፍተኛ አመራር የሚጠበቅ ነው።

የህወሓት ተናጋሪዎች አቶ ለማን በመደገፍ ከአስር ወር በፊት ኢህአዴግ ፈርሷል ስንል ሰሚ አጣን። ያኔ ፈርሷል ስንል ዝርዝር ምክንያትና መገለጫዎቹም ገልፀናል አሉ።

በስብሰባው ላይ ሌሎች ክስተቶችም ታይተዋል። ምርጫን በተመለከተ ፣ ርእዮተ አለምን በተመለከት ፣ ህወሓትን ማድነቅን በተመለከተ ፣ surprise በሚባል መልኩ ተነስተዋል።

በክፍል ሁለት እንገናኝ።

 

Back to Front Page