Back to Front Page


Share This Article!
Share
ብቸኛው ሀገራዊ መፍትሔ

ብቸኛው ሀገራዊ መፍትሔ

ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ 1-10-19

 

"All we have to decide is what to do with the time that is given us."

The Lord of the Rings

በሕብረተሰብ የትላንት የዛሬና የነገ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚኖሩ ግንኙነቶች ግጭቶችና ሂደቶችን ማስተዋል እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ እንደሀገር የምንወያይና የምንገልጽም ከኾነ የሀገር ችግር አልያም የሕብረተሰባችን ችግር ከማለት በፊት ዕውን ችግር ምንድነው? ችግራችንስ ምንድነው? ብሎ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

የሕብረተሰብን ችግር ከራሱ ከሕብረተሰቡ የንቃተ ህሊናና ነባራዊ ኹኔታ አንጻር መመልከት ለመፍትሔ መነሻ ሊኾን ይችላል፡፡ (በራሱ ግን መፍትሔ አይደለም፡፡) ለዚህም ነው - የሕብረተሰብ ባለሙያዎች (sociologist): "Social problem: is a problem recognized as a problem by a group of people who feel strongly enough to take steps toward change."(PP 3: SARA TOWE HORSFALL: SOCIAL PROBLEMS 2012)ብለው የሚያስቀምጡት፡፡

Videos From Around The World

እንደ-የሳይኮሎጂ (psychology) ባለሙያዎች ትንተናም "ሕዝብን መረዳት እንዴት እንደሚያስብ ምን እንደሚል እና የሚያደርጉት ለምን ያደርጋሉ; በጥቅሉ ሰዎችን ምን ያነሣሣቸዋል; ምንድነው ጠቀሜታው ለኛ እና ለምንስ ሁላችን በአንድነት ውስጥ ግላዊ እንኾናለን፡፡" (PP 1 Nicky Hayes: UNDERSTAND PSYCHOLOGY: 1994)የሚሉ ጥያቄዎችን "ከአስተሳሰብ ከማህበራዊ ግንኙነት ከግላዊ መነሣሣትና ልዩነት ከአካላዊ ተጽዕኖ ከለውጥ ሂደትና ከንጽጽር" (PP 9 Nicky Hayes: UNDERSTAND PSYCHOLOGY: 1994) አንጻር መጠየቅ መረዳት መገንዘብና ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡

በሀገራችን እጅጉን ከተዘነጉና ትርጉም ባለው መንገድ ካልታዩት ጉዳዮች አንዱ የባሕል ጉዳይ ነው፡፡ ባሕል ራሱ የሕዝብ ማንነት በመኾኑ ስለሕዝብ በሚነሡ ማናቸውም ኹለንተናዊ ጉዳዮች መታየትና አጽንዖት ሊሰጠው የሚገባ ትልቅ ነገር ቢኾንም የተሰጠውና የሚሰጠው ትኩረት አናሳ ነው፡፡

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ኹሉ የላቀ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ ምክንያቱም ባሕል ሚኒስቴር የኹሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ኹሉ እናት ስለኾነች፡፡ ነገር ግን &የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እናት& የኾነችው ባሕል ሚኒስቴር ባለፉትም ኾነ ባኹኑ ሥርዓት ብሎም በሌሎቻችን ዘንድ ባሕል እንደዘርፍ ይታያል፡፡ ከuu አጠቃቀማችን ጀምሮ &የባሕል ዘርፍ& ነው የምንለው - ይህ ትልቅ መሠረታዊ ስህተት ነው፡፡ ሰው የሰውነት ክፍሎች ይኖሩታል እንጂ ክፍል ራሱ ሰው የለውም፡፡ በመኾኑም የሀገራችን ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ማለትም ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጉዳዮች ኹሉ ከባሕል መነሻነትና መዳረሻነት አንጻር መታየት አለበት፡፡ እውነተኛ ሕዝባዊነትም ይኸው ነው፡፡

"ባህል ለሰው የሰራው የተጠቀመበት የተማረው ያወቀውና ያመነበትን ኹሉ ነገር የሚያጠቃልል" (PP 55:John A. Perry & Erna K. Perry: Contemporary society: an introduction to social science: 2010) በመኾኑም የኢትዮጵያውያንን ባህል ለማወቅ ከኹሉ በፊት የባህል አካል (element) የኾኑትን ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ትላንትም ኾነ ዛሬ የሰሩትን የተጠቀሙበትን የተማሩትን የሚያውቁትና የሚያምኑበትን ትርጉም ባለው መልኩ መረዳት ብሎም ከነገ ፍላጎትና ምኞት አንጻር ደግሞ መስራት መጠቀም መማር ማወቅና ማመን የሚሹትን መገንዘብ አስፈላጊ ብቻ ሳይኾን የግድ የሚባል ሂደት ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

ስለኾነም አኹን በሥርዓት ላይ ያለውን ሥርዓት በአንድ ለሊት በዕውቀትና በምክንያት ላይ የተመሰረተ፤ አመራሮቹም በትርጉም ያለው ሀሳብ ላይ የተመሰረቱ፤ ለምንና እንዴት መኖር እንዳለባቸው የሚያውቁ፤ ከሣጥን ውጭ (out of box) ማሰብ የሚችሉ የግድ መኾን አለባቸው - ብንልና ሥርዓቱም ይህን ተቀብሎ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ቢያመራ - ሥርዓቱ በርግጠኝነት በነጋታው ይፈርሳል፡፡

ምክንያቱም ሥርዓቱ የተመሠረተው ይህን በሚሸከም መሰረተ ሀሳብና ዕሳቤ ላይ ባለመኾኑ ነው፡፡ በመኾኑም እንደሀገር ያለን አማራጭ ከተምኔታዊነት ባሻገር ቢያንስ ደረጃ በደረጃ መኾን ወደ ሚገባው ዕሳቤና መሰረተ ሀሳብ እንዲያመራ ማድረግ ነው፡፡

በሀገራችን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ በሕብረተሰብ ውስጥ ያልዳበረን በዕውቀትና በምክንያት ላይ የተመሠረተ ባህል ሳይኖር ወደ መንግሥታዊ አሰራር ማምጣት አስቸጋሪ መኾኑ አሌ የማይባል እውነት (Truth) ና እውነታ (Reality) ነው፡፡ ግን መንግሥት ከሕዝብ መቅደም እንዳለበት ሳይዘነጋ መኾኑ ከግንዛቤ ማስገባትን ደግሞ የግድ ይላል፡፡

"We know that if democracy is to work, it needs more than the establishment of a particular set of institutions. It has to be a lived practice, with at least two key elements.&(Grugel, democratization, pp. 238 -47)

- - - &The maintenance of democracy requires an effective state to regulate society, agree compromises and organize the distribution of public goods. It also requires a civil society of non-state actors that is organized, active and engaged and capable at a minimum of holding the state to account and at a broader level offers the seed bed for the development of democratic ideas and practice." (PP. 29 - Gerry stoker ፡ Why politics matters - making democracy work 2006) እዚህ ላይ ያሉትን ኹለት ዋነኛ ነጥቦች 'needs more than' እና 'has to be a lived practice' የሚሉትን በእጅጉ ማስተዋል የሚያስፈልግ ይኾናል፡፡

ያለዲሞክራት ዲሞክራሲ እንደማይኖር &there is no democracy without democrats, that is, without a specifically Democratic Man that desires and shapes democracy even as he is shaped by it.&(PP 135: Francis Fukuyama: THE END OF HISTORY AND THE LAST MAN: 1992) ኹሉ ያለ ነጻ ሰው ነጻነት፤ ያለ ፍትሃዊ ፍትሕ፤ ያለ ሕሊናዊ መብት፤ ያለ ባለ ራዕይ ራዕይ፤ ያለ ተስፈኛ ተስፋ ማድረግ፤ ያለ ምክንያታዊ ነጻ ሚድያ በተግባር ሊኖር አይችልም፡፡

በመሠረተ ሀሳብ ደረጃ የሀገራትን መንግሥታት አልያም ሥርዓታት እንቅስቃሴ ዕሳቤ ሂደትን - በሰው ልጅ ዕድገት መመሰል ይቻላል፡፡ ህጻን ልጅ ራበው ተብሎ አልያም ያስፈልገዋል ተብሎ አጥንት አይሰጥም፡፡ የሰው ልጅ ዕድገት ህጻን ታዳጊ ወጣት ጎልማሳና አዛውንት በሚል እንደሚከፈል ኹሉ መንግሥታትና ሥርዓታትም - እንዲህ ዓይነት የእንቅስቃሴ ዕድገትን ይመስላሉ፡፡

ህጻን ልጅ ያጠፋል፤ ማይገባ ተግባር ያደርጋል፤ ይሰብራል፤ ያለቅሳል፤ ይሰርቃል፤ ያሰርቃል፤ ይዋሻል፤ በጊዜያዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል፤ ያለሞግዚት መንቀሳቀስ ያዳግተዋል፤ ከተፈጥሯዊ አቅሙ በመነሣት አርቆ አያስብም - - - ጀማሪ የአስተዳደር ልምድ የሌላቸው ሥርዓታትም እንዲሁ ናቸው፡፡ በአስተዳደር ህጻን ይኾናሉ፡፡

ምክንያቱም ከዛ በፊት ሂደቱን ስላላፉበት፡፡ የአኹኑ ሥርዓትንም ብንመለከተው ከትምህርት አuርጠው በረሃ የገቡ - ኃላ በትግል ገዥ የነበረውን ሥርዓት አስወግደው - በሥልጣን የተቀመጡ በመኾናቸው - ኹሉ ነገር በአንድ ጊዜ መኾን ወደ ሚገባው ደረጃ መድረስ ነበረበት ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡

የአስተዳደር ዕድገት እንደሰው ልጅ ዕድገት ኹሉ እያደገና እየጎለበተ እንደሚሄድ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ነገር ግን በዕድገቱ ፍጥነትና ጥራት ላይ መወያየት መከራከር መገማገም መጠያየቅ - - - ወዘተ በእጅጉ ይጠይቃል፡፡ የተሻለ የነበረ ወደ ኃላ ሲመለስ - በምንም ተአምር የዝቅጠት እንጂ የዕድገት ሂደት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡

አንድ ሰው ከህጻን ወደ ታዳጊነት ከተሻገረ በኃላ ወደ ወጣትነት እንዲሻገር እየተጠበቀ ወደ ህጻንነት በእምነት፣ በእውቀት ብሎም በድርጊት ደረጃ ከተመለሰ - ይህ ሰው - በሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ሂደት አዘቅጥ ውስጥ እንዳለ - የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ - ታዳጊን በአዛውንት ደረጃ ካለ ጋር ማነጻጸርና እንደሱ እንዲኾን መጠበቅ ትልቅ ስህተትና አለማስተዋል ነው፡፡ ለመንግሥታትና ለሥርዓታትም እንዲሁ ነው፡፡

"Some ideas are transformative, but for the most part societal change and change in beliefs occurs slowly. - - - Change often occurs less rapidly than it seems that it should, and the slow evolution of ideas is one of the reasons that societies sometimes change slowly."(PP 150: JOSEPH E. STIEGLITZ; THE PRICE OF INEQUALITY: 2012)በመኾኑም ይህን በመረዳት ሥርዓታት በእኛነታችን ላይ የተመሠረቱ መኾን እንዳለባቸው፤ እኛን የሚመስል ሥርዓት እንደሚያስፈልገን፤ አለበለዛ ሥር ነቀል ለውጥ እንደናፈቀን ዘመናትን እንደምናስቆጥር አያጠያይቅም፡፡

ሥርዓታት በእኛነታችን - ስለኛነታችን - በኛነታችን ላይ መመስረት አለባቸው ሲባል በባሕሪያቶቻችን በጠባያቶቻችን በእምነቶቻችን በዕሴቶቻችን በዕሳቤያችን በሥርዓታችን በባህላችን በወጋችን በልማዳችን በሞራላችን በታሪካዊ አሻራችን - - - ማለት ነው፡፡

በዚህም ኹለንተናዊ ማለትም ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ብሎም ፖለቲካዊ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ስልቶች - እኛን ሳይመስሉ ሌሎችን ለመምሰል መትጋት ያለፉት ሩጫዎቻችን የትም አላደረሱንም የሚለው ነጥብ ዐቢይ ማሳያ ነው፡፡ በእኛነታችን ለመመራት በአንጻሩ በእኛነታችን ማመን እኛነታችንን ማወቅ ብሎም በእኛነታችን ላይ የተመሠረተ ኹለንተናዊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

ኾኖም ግን የአንድ ሀገር ሕዝብ ዘወትር በውስጡም ኾነ ከውጭ ጋር በሚኖረው ኹለንተናዊ ግንኙነት"societies, and various kinds of groups that exist within them, are not static entities. They are in constant flux, undergoing change and modification."(PP. 90 John a. Perry and Erna k. Perry, Contemporary society: an introduction to social science: 2009)መኾኑን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡

ስለኾነም ይህን ከትላንት ያለፈ ዛሬ ከሚኖር እና ነገ ከሚፈለግና ሊፈለጉ ከሚችሉ ነገሮች ጋር አስተሳስሮ መመልከት መረዳትና ማስተዋል ደግሞ እጅጉን አስፈላጊ ወሳኝ የመፍትሔ አቅጣጫ ነው፡፡ (ከሸክም የበዛበት ትውልድ 2009 ዓ.ም፡ ገጽ 230 236 የተወሰደ) ፈጣሪ ሀገራችን ነጻ ፍቃድን የኹሉ ነገር ማዕከል ወደ ሚያደርግ የዕሳቤ ሂደት ትገባ ዘንድ ይርዳን!

ቸር እንሰንብት!

 

 

 

 

 

 

 

Back to Front Page