Back to Front Page


Share This Article!
Share
እንደገና ይድረስ ለዶ/ር አቢይ አህመድየኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራቲክ መንግስት ጠ/ ሚኒስቴር

 

እንደገና ይድረስ ለዶ/ር አቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ፈደራላዊ ዲሞክራቲክ መንግስት ጠ/ ሚኒስቴር

 

ሰላም የሚመጣው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ሲፈልግ ብቻ ነው

ጦሩን (ወታደሩን የማንቀሳቀስ አብሶሉት ፖወር የፈደራል መንግስቱ ብቻ ነው፡

ጠ/ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ. January 5,2019

 

 

በቀለ ብርሃኑ 1-7-19

 

 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ፤

 

አሁንም ሰላምና ጤና እየተመኘሁ ለያዙት ኢትዮጵያን የመምራት ሃላፊነት ያለኝን አክብሮት በመግልጽ ልጀምር። ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ሁለት መልክቶችን ለክቡርነትዎ ልኬ ነበር። እነሆ ይሄኛው ሶስተኛ መሆኑ ነው።

Videos From Around The World

አዲሱ የጽ/ቤት ሃላፊዎ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አይንዎና ጆሮዎ የሆናሉ በሚል እምነት መልክቴ እነሆ።

 

በትላንትናው እለት ላስተማሪዎች የሰጡትን ማብራርያ በከፊልም ቢሆን አዳምጫለሁ። ባሁኑ ጊዜ የመንግስት ሚድያዎች (የዜና አውታሮች ) ከ ፌስቡክ የተሻለ ይዘት ስለሌላቸው ብዙም አይስቡኝም።

 

ከላይ የጠቀስኳቸው አባባሎች በደንብ፤ በጥሞና መታዮት ያለባቸው ነገሮች ናቸው። በኔ ግምት ላይላዩን እውነት ቢመስሉም መሰረታዊ ስህተት ያለባቸው ናቸው። የዚህ ችግር ዋና ምንጭም የግልጽነት መጓደል ይመስለኛል።

 

እንድሚያውቁት ሰላም የሁሉም ህዝብ ፍላጎትና ምኞት ነው። ጦርነት ቀስቃሾች ህዝብን እንወክላለን የሚሉት መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያና - በተለየ ሁኔታ ደግሞ ጎረቤቶቹ የትግራይና የአፋር ህዝብ- የኤርትራ ህዝብ ጦርንትን ፈልገው አያውቁም። እናም ቀስቃሾቹ መንግስታቱ ናቸው። ደንታ-ቢስ መንግስቶች ዘራፍ ካሉ ህዝብ ቢማጸንም አይመልሳቸዉም።

 

በትግራይ ክልል ያሉት ጎረቤት ወረዳዎች- ክቡር ጠ/ሚኒስቴር- የሚያነሱት ያለመረጋጋት ስሜትና ሰራዊታቸው ነገሮች እስኪረጋጉ ድረስ ባሉበት ይቆዩልን የሚለው መረዳት እንዴት ይሳነዎታል? እንዚህ ህዝቦች እኮ ባለፈው 20 አመት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተዋል። ይህን አለመረዳት መንግስት ማድረግ የሚገባዉን ህዝብን የመጠበቅ ሃላፊነት እንደመዘንጋት ዪቆጠራል።

 

ሕዝብ የሰላሙ ጠባቂና ጦርነት አስወጋጅ የሚሆነው አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የዲሞክራሲ እርከን ስትደርስ ብቻ ነው። ያም በከፊል እውነትነት ይኖረው እንደሆን እንጂ ጎዶሎ አባባል ነው። የበለጸጉት ም እራባውያን ያለማቋረጥ በጦርነት አውድማ ውስጥ የሚዘፈቁት ህዝባቸው ፈቅዶላቸው አይደለም። እንኳን ያቶ ኢሳያስ ኤርትራ የኛዋ ኢትዮጵያም ዲሞክራሲ የሩቅ ህልማችን ነው። ስለዚህም ህዝብ ሰላምን እስከፈለጋት ሁሉ ቢያንስ አንደኛው መንግስት ነገር አይጭርም ማለት ቢያንስ ቢያንስ አካባቢዉን በደንብ ካለመቃኘት የሚመጣ ስህተት ዪሆናል የሚል መላ-ምት አለኝ።

 

እናም ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፤ ህዝቡን ምንም አትሆኑም፤ በኔ ዪሁንባችሁ ብሎ የህዝብን ጥያቄ ማጣጣል ተገቢ አዪሆንም።

ህዝቡ መከላከያ ሰራዊቴ ጠብቀኝ፤ ጥለህኝ አትሂድ ባለ እንደ ቡራዩ ወጣት እንዳይጨፈለቅ ማሰበዎ አንድ ጥሩ ነገር ሆኖ ሁለቱን ሁነቶች ማወዳደር ግን እንደ -አራምባና-ቆቦ የተራራቁ መሆናቸውን ግን ሳልጠቅስ ማለፍ ከበደኝ።

 

ክቡር ጠ/ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ፤

 

ከዚህ በላይ እጀግ ያስደመመኝና ያሳዘነኝ ህዝቡ ጉዳት እንዳይደርስበት ብለን ነው እንጂ ሰራዊቱን ማንቀሳቀስ አላቃተንም የሚለው አባባለዎ ነው። ህዝቡን ለማስፈራራት የተሰነዘረ ሽርብ (thinly veiled threat) ይሉታል እንግሊዞች።

 

በተለያዩ ቦታዎችና በዚህ ቀን ንግግረዎ ስለህዝብ የበላይነት ሲናገሩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታድያ የነዚህ ወረዳዎች ሰዎች የህዝቡ አካል አይደሉም እንዴ? ስልጣኑን የያዙት በህዝብ ስም አይደለም እንዴ? ህዝቡ ስጋት አለኝ ሲል የለህም የምንል እኛ ምን ሆነን ነው። የህዝብ አገልጋይ ለመሆን የያዙትን ስልጣን በዚህ መልክ ባይተረጉሙት ደግ ነው እላለሁ።

ልክ አይደለም። ከፈለግኩኝ ወታደሩን ባሰኘኝ በትናለሁ ማለት በምንም መለክያ ልክነት የለዉም።

 

ፍጹማዊ ሃይል (አብሶሉት ፖወር) የማአከልዊ መንግስት አይደለም። ያ ሃይል - በንምልበት ዲሞክራሲ ካመንን- የህዝብ ነው።

እዚህ ላይ ማንም ትንሽ የመንግስት አወቃቀር ለምያውቅ ሰው የተለያዩ የመንግስት እርከኖች እንዳሉ፤ ያንዱ ስልጣን ከሌላው እንደሚበልጥ፤ ባንዱ ስልጣን ላይ ደግሞ ሌላኛው ጣልቃ እንደማይገባ የታወቀ ነው።

 

ሖኖም እዚህ ያለው ጥያቄ የክልል መንግስት ወይም የወረዳ መንግስት ሳይሆን የወረዳዎ ህዝብ ነው። እናም መታየት ያለበት በዚያ አይን መሆን ዪኖርበታል። አይይ ህዝቡ ፈቅዷል፤ የምያንገረግረው የወረዳው ውይም የክልሉ መንግስት ነው የሚል ከሆነ አነጋገረዎ ያንን በግልጽ የማስረዳት ሃላፊነት ከርሰዎ እንጠብቃለን። እንድያም ከሆነ ነገሩ በት እግስትና በመላ መያዝ ብልህነት ነው።

 

 

ከበጎ እሳቤ ተነስተው ይህንን መግለጫ እንደሰጡ ጥርጥር የለኝም። ሆኖም ግን ከሁሉም ነገር በላይ የህዝብን ፍላጎት ማዳመጥ ግድ ይላል። እንዳሉት ሰራዊታችን ስልጠናም፤ እረፍትም ያስፈልገዋል። ተገቢና ትክክልም ነው። ያ ማለት ግን ህዝቡ ስጋት አለኝ የሚልባቸውን ቦታዎች ክፍት ትቶ መሄድ ማለት አይደለም። ሁሉም ሰራዊት አባል ባንድ ጊዜ ባንድ ቦታ ስልጠና ይወስዳል ብሎ መገመት በጣም አስቸጋሪ ዪሆናል።

 

የወሰን ጉዳይን በተመለከተ የተናገሩት አረፍተ-ነገር ቀልቤን ሳበው። የ ተቋቋመው ኮሚሺን ስራው ጥናት አካሄዶ ወደ ፈደረሽን ም/ቤት ማቅረብ እንደሆነ ጠቁመዋል። አማካሪ አካል መሆኑ ነው። ይህ አካሄድ ብዙም አይከፋኝም። ግን እንድያ ከሆነ ለምን ተጠሪነቱ ለፈደረሽን ም/ቤት አልሆነም?

 

ይህን በሚመለክት አንድን ነገር ረገጥ አድርገው ተናግረዋል። ይህውም ጥናቱ ተጠናቆ እስኪቀርብ ድረስ ምንም አይነት የወሰን ጥያቄ ወደ ፈደረሽን አይቀርብም የሚለው መደምደምያዎ ነው። በአክብሮት የምጠይቀዎ ነገር ቢኖር በህገ-መንግስቱ ለፈደረሽን ምክር ቤት የተሰጠ ስልጣን ጠ/ሚኒስትሩ መሻር ዪችላል ማለት ነው? ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነገር ሆነብኝ።

 

የኤርትራ መንግስት የአፋሩን ድንበር ከፍቶ የትግራዩን መዝጋት ያጋጣሚ ጉዳይ እንዳልሆነ አጎራባች ህዝቦቹ አሳምረው ይገነዘባሉ። እናም የህዝቡን ትርታ ማዳመጥ ከሁሉም በላይ የበለጠ ብልህነት ነው።

 

 

እንደወትሮው ለርሰዎ ስኬትን ለ ኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ሰላምንና ብልጽግናን እመኛለሁ።

 

ከአክብሮት ጋር

 

በቀለ ብርሃኑ

Back to Front Page