Back to Front Page

ላልሰማው ጉድ ነው ዘንድሮ

ላልሰማው ጉድ ነው ዘንድሮ

ሓጎስ አረጋይ 8/05/2019

የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በላይ ነው። የትግራይ ህዝብ ህወሓትን ፈጠረ እንጂ ህወሓት የትግራይን ህዝብ አልፈጠረም ። ነገር ግን ህወሓትን በመጥላት ወይም ለመበቀል ሲባል፣

       95 ሚልዮን በ5 ሚልዮን (በትግራይ ህዝብ ላይ) ጦርነት ያወጀ ተቋም (ኢሳት ሚድያ)

       ከመቶ ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች ንብረታቸውን ዘርፎ/አስዘርፎ ያፈናቀለ ወይም እንዲፈናቀል ያደረገ ፓርቲ (ተቋም)

       በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በማንነታቸው ብቻ እንዲገደሉ እንዲሁም በጠራራ ፀሃይ በፖሊስና በሰው ፊት እንደ እባብ ተቀጥቅጠው እንዲገደሉ ያደረገ/ ያስገደለ ፓርቲ(ቡዱን)

       ራያ ፣ ቆቦ፣ ወልቃይት ፣ አኩሱም፣ እንድርታ ወዘተ ከህገ መንግስት እና ከአከባቢው ነዋሪዎች ፍላጎት እና ይሁንታ ውጭ በሃይል እና በጦርነት ለማስመለስና ለመግዛት የሚተጋ ፓርቲ (ተቋም)

       ወደ ትግራይ እህል እንዳይገባ መንገድ የሚዘጋ እና የተጫነውም የሚዘርፍ ፓርቲ (ቡዱን ወይም ተቋም)

       የትግራይ ነዋሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይጓዙ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ እንዳይመጡ መንገድ የሚዘጋ ወይም የሚያስዘጋ ቡዱን (ፓርቲ)

Videos From Around The World

ከህወሓት በላይ

  ለትግራይ ህዝብ የሚያስብ፣ የትግራይን ህዝብ ወንድም አድርጎ የሚያይ መሆኑን ፣ ጥሩ ነገር ይሰራል ወዘተ ብሎ የሚቀባጥር ቡዱን (ፓርቲ) እንዲሁም

  በምስጢር የተያዘውን ለሆዳችን እንተወውና በግልፅ አዋጅ የትግራይን ህዝብ ለማዳከም እና ለማንኳሰስ የተሄደውን ርቀት የሚክድ ቡዱን ( ከላይ የተገለፀው ማንበብ)

ለሆድ አደር የሚተጋ ከመሆን ይልቅ ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም። ምናልባት ከሆነ ደግሞ ለህዝብ ሳይሆን በህወሓት ያለው የግል ጥላቻ አግዝፎ የህዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ቂሙን ለመወጣት የሚሰራ ቡዱን ነው ከማለት ውጭ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።

ስለዚህ ስለ ህዝብ እና ህዝብ የምናስብ ከሆነ ነውጥ ሳይሆን ሰላማዊ ምርጫ ማካሄድ ይጠይቃል። በመሆኑም ህወሓት ባለፈው ምርጫ በትግራይ ህዝብ ከሞላ ጎደል የተመረጠ ፓርቲ መሆኑን መገንዘብ ያሻል። ይህንን መካድ ደግሞ ዲያብሎስ ከምሆን የዘለለ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም። በመሆኑም ትግራይ ላይ መስራት ያለበት ምርጫና ምርጫ መሆን ይገበዋል። ትግራይን በባላንጣ ከሚፈርጁ ሃይሎች ጋር በመቆራኘት በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ማሰብ ለትግራይ ህዝብ አይበጅም አይጠቅምም።

የነውጥና የአቋራጭ ስልጣን ምን ግዜም ውድመት ነው ። በትግራይ ዴሞክራሲ የለም ለሚባለው ነገር ፣ ስለ ትግራይ ከማውራትዎ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ከተስፋፋው ገደብ የለሽ የኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አስተዳደርን ራስን ማውጣት ይጠይቃል።

ልንገነዘበው የሚገባ ፣ ከትግራይና ከአፋር ውጭ አገሪቱ በገሃድ ያልታወጀ ወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቃለች። በወታደራዊ አገዛዙ ስርዓት ላይ የግዜ ገደብም የለውም። በወታደራዊ አገዛዝ ስርዓት የወደቀ አገር ላይ ደግሞ ስለ ዴሞክራሲ መመጻደቅ አይቻልም። እንዲሁ በደፈናው ዴሞክራሲ የለም ማለት ይሻላል። ምክንያቱ በወታደራዊ አገዛዝ የወደቀ አገር በዴሞክራሲያዊነቱ የተጠራ የለም። ስለዚህ በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢ ወጥቶ ለመግባት ስጋት ላይ የወደቀ ህዝብ ባለበት ሰዓት ዴሞክራሲ አለ ብሎ መከራከር ድርቅ ያለ ክርክር ነው እላሎህ ።

ስለዚህ በትግራይ ላይ መሰራት ያለበት ጉዳይ እንነጋገር። የተሻለ የሚሆነው የተሻለ ሃሳብ አለኝ የሚል ፓርቲ በርቀት መቆዘም ሳይሆን ወደ ትግራይ በመምጣት ያላቸው ፕሮግራም ማስረፅና በቀጣይ ምርጫ ህወሓትን ለማሻነፍ ወይም ስልጣንን ለመጋራት መሞከር የተሻለ ያደርገዋል። መሰመር ያለበት ህወሓትን ከስልጣን ማውረድም ሆነ ቀጣይ የትግራይ መሪ የመሆን እድሉ ምርጫን መሰረት ያደረገ እና የትግራይ ህዝብ ሉአላዊ ስልጣን እንዲሆን ሁላችንም መስራት ይጠበቅብናል። አሁንም በትግራይ ያለው አየር ይህንን ያረጋግጣል ብዬ አስባሎህ።

Back to Front Page