Back to Front Page

የትግራይ ህዝብ የወቅቱ ቀንደኛ ጠላት ፡ ኢሳት ክፍል አንድ

የትግራይ ህዝብ የወቅቱ ቀንደኛ ጠላት ፡ ኢሳት ክፍል አንድ

ሓጎስ ስዩም መቐለ 9-20-19

 

መቐለ ላይ ኢዘማ ባካሄደው መድረክ የኢዘማ ልሳን ከሆነው ኢሳት ጋር ተያይዘው ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ ለመሰጥት ተብሎ በቀን 6/1/2012 ዓ/ም በማክሰኞ የምሸት የዜና ትንታኔ ፕሮግራም (3:00-4:00 ሰዓት) ዝግጅት ነበረ፡፡ እንደ አጋጣሚ እኔ ኢሳት በሚያቀርበው የምሽት የዜና ትንታኔ አብዘኛው ግዜ እከታተላሎህ፡፡ ይህንን ፕሮግራም ስከታተል የዚህ ድርጅት አጠቃላይ ማንነት፣ የአጭረና የረጅም ግዜ አላማ ከሞላ-ጎደል ማወቅ የሚስችል መረጃ አግኝቼ አሎህ ብየ አሰባሎህ፡፡ ከዚህበመነሳት የሚከተሉትን የኢሳት ጥንካሬ እና ደካማ ጎን እንዱሁም ለግንዛቤ ያህል ይጠቀማሉ ብየ ያሰብኩዋቸውን የመደምደምያ ሃሰቦች ለማቅረብ እሞክራሎህ፡፡

በጥንካሬው ስጀምር ኢሳት በትግራይ ህዝብ እየተነሱ ላሉት ሃሳቦች ምንድናችው ብሎ በየቀኑ መከታተሉ እና መልስ ለመሰጠት መመኮሩ፣ በአንአንድ ጉዳዮች ዘጊይቶም ቢሆን ፣ምንም ይሁን ምን ምክንያት ይኑረው ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ መጠየቁ እንዲሁም ለወደፊት የትግራይ ህዝብ አሰተሳብ እና አመለካከት የሚወክል ሃሰብ እናሰተናግዳለን ብለው ማለተቸው ጥሩ ጎኑ ነው ብየ አስባሎህ፡፡

ደካማው ማነነታቸው

Videos From Around The World

ኢሳቶች ይቅርታ የሚጠይቁበት መንግድ ሲታይ በጣም ያሰገርማል፡፡ ሲጀመር የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በመነጠል ህዋሓትን ማዳከም ድርጅቱ የተቛቛመበት ዋና አላማ መሁኑ ራሳቸውም ደጋግመው የሚገልፁት ጉዳይ ነው፡፡ ሰለዚህ ወደ ትግራይ የሚውስዱ መንገዶች ይዘጉ፣ አምስት ለ ዘጠና አምስት፣ የኢትዮጵያ ሃብት ወደ ትግራይ እየተሰደ እና እየተዘረፈ ነው፣ ወዘተ ብለው ማሰተጋባታቸው ከዓላማቸው፣ ከውስጥ ስሜታቸው፣ከወደፊት ምኞታቸው የመነጨ ሆድ ያመቀው ብቅል ያወጠዋል እንጂ በምንም አይነት የግለስብ ግዝያዊ ስህተት ነው ብሎ ማለት ማንንም ማሳመን የሚችል መልስ መሆኑን አለመገንዘባቸቸው፣

ከመሬት በላይ በኢትዮጵ የተሰሩ ሁሉም ዓይነት ጥፋቶች የህዋሓት ሰዎች ብቻ ናቸው የሚል ጫፍ የረገጠ አሰተሳሰባችው ነው፡፡ እዚህ ላይ መነሳት ያለበት እውነትም ቀድም ብየ እንዳሰቀመጥኩት ከቆሙለት ዓላማ አንፃር ስታይ ኢሳቶች እንዲህ ማለታቸው ትክክል ቢሆንም ሁሉም ህዝብ የሚያውቃቸው በፌደራልም በየክልሉም ህዝብና ሃብት ስያሰተዳድሩ የነበሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሌሎች አባል ድርጅቶች አልነበሩም ወይ የሚለው ነገር ምንም እንኳን አንዳንደቹ የጉንበት -7 አባለት በመሆን ያገለገሉ ሰለሆነ (ዶ/ር አብይ፣ ወዘተ) ታሳቢ ቢደረግም ሌሎች (ደመቀ መኮንን፣ ብርሃኑ ፀጋየ፣ ወዘተ) ለዘመናት የአመራሩ ቀንደኛ ተዋናይ እና አሰፈፃሚ አካለት የነበሩ አሁንም እንዳውም በተጠናከረ መንገድ አገር እያመሱ የሚገኙ አመራሮች ምንም ነገር አለማለታቸው በራሱ ትእዝብት ውስጥ እንዳሰገባቸው አለመገንዘባቸው፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ድግሞ ሁሉም የህዋሓት መሪዎች ከዚህ የኢትዮጵያ ምድር መጥፋት አለባቸው፣ መገልል፣ መታሰር፣ ወዘተ አለባቸው ብለው የሚሉት ጭምር ለትግራይ ህዝብ በጭራሸ የማይዋጥለት መሆኑ አለማወቃቸው፣

ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ መነሳት ያለበት ሁሉም የህወሓት መሪዎች ህግ-ጥሰዋል፣ መታሰር አለባቸው፣ ወዘተ ብለው ሲያበቁ በጣም ከሚገርመው ነገር ደግሞ የጠቅላይ ሚ/ር መለስ በተደጋጋሚ ስም የማጥፋትና የእሱ አሻራ ያለበት ነገር ሁሉ ከምደረ-ገፅ ኢትዩጵያ ለማሰውገድ የሚያደርጉት ጥረትና ፐሮፖጋንዳ ነው፡፡ እንዳውም ቅድም ብለውም በተደጋጋሚ አንስተውታል በዚህ በመቐለ መደረክ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሲሰጡም ያነሱት ጉዳይ መለስ ፓርክ ተብሎ አድስ አበባ የተሰየመው ፓርክ መወግድ አለበት ብለዋል፡፡ የቆጡን አውርድ ብላ የብብትዋን ጣለች እንደሚባለው የትግራይ ህዝብን አንነካም ብለው የተናገሩበት አንደበታቸው ለትግራይ ህዝብ ከማንም በላይ ለሆነው ጀግና አዲሰ አባባ ስሙ መታየት የለበትም ያሉበት መንገድ የበለጠ ግጭት ቀስቃሽ መሆኑ ግምት ውስጥ አለማሰገባታችው ነው፡ ፡ ምክንያቱም አድስ አበባ እንኳን የመለስ ይቅርና የእነ አፄ ምንሊክ እና ኀ/ሰላሴም ሃውልትም አለና ነው፡፡ ይፍረስ ከተባለ የማን መቅድም እንዳለበት ታሳቢ አላደረጉም፡፡

ሁሉም አሰታየት የሰጠ ህዝብ የኢዘማ እና የኢሳትን ዓለማዎች የሚደግፍ መሰሎ ካልታያቸው ሁሉም የህዋሓት ካድሬ ነው ብሎ የመፈረጅ አባዜ አለባቸው፣፡ በትግራይ ከተሞች፣ አዲሰ አባባ፣ በተለያዩ ዩኒቨረሰቲወችም ሆነ በሌሎች ቦታዎች በተለይም ህገ-መንገስት፣ ፌደራሊዝም (ቛንቛ መሰረት ያደረገ)፣ ቢሄር እና ቢሄረስብ ከተያያዙ ጉዳዮች አሰመልከተው እና ደግፎው ሃሳባቸው ለሚገልፁ የትግራይ ሊህቃኖችም ሆነ ተራ ህዝብ በእሳት ቤት ህወሓት ተብለው መፈረጃቸው፣

እውነተኛ የትግራይ ልጆች ብለው ለአብነት የሚያነሱዋቸው ሰዎች (እንደነ ገ/መድህን አርአያ፣ አረጋዊ ፣ግደይ፣ አብረሃ ወዘተ) በትግራይ ህዝብ ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት (0.00%?) ግምት ውስጥ ሳያሰገቡ የትግራይ ህዝብ አሰተሳሰብ እያንፀባረቅን ነው ብለው በድፈረት የሚናገሩበት መንገድ ምን ያህል ትክክል እንደሆኑ አለመገንዘባቸው ነው፡፡

በትግራይ ህዝብ ለዘመናት በአፄ ምንሊክ፣ ሃይለሰላሴ፣ ደርግ የደረሰበት መከራና ግፍ (ቛንቛው፣ ባህሉ፣ መሬቱ የተዘረፈበት መንገድ) በምንም መልኩ ግምት ውስጥ አለማሰግባታቸውና ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ምንም የሚያነሱት ነገር አለመነሩ ነው፡፡

ኢሳት የሚያነሱት ሃሳብ ሁሎም ህዝብ እውነት ነው ብሎ የሚቀበለው ይመሰላቸዋል፡፡ነገር ግን ኢሳቶች የሚሉትና በተግባር የሚሰሩት እጅግ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ሰው (የትግራይ እና ሌሎች) በተለይም ደግሞ ሃሳቡ እየዋለ-እያደረ ሃቁን እየተገነዘበ ሲሄድ የማይቀበለው ሰለሚሆን ነገርዮው ሲሰረቀኝ ያየሁት ቢጨምረኝ አለማነውም እየሁነ እንደሚሄድ እና አሁን ያለው ትውልድ ንቃተ-ሂሊና በሚገባ ያለመገንዘብ ችግር ይታይባችዋል፣፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ህዝብ ማለት በነሱ ቤት የተጠራቀመ ሲውርድ ሲዋረድ የመጣው የገዢ መደብ ሊሂቃን አሰተሳሰብ የሚያነሳ ማለታቸው መሆኑ ነው፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ሃሳብ የሚያነሳ ግለሰብም ይሁን ቡድን የህዝብ ጥያቄ ብለው የሚያቆላምጡት ሲሆን የነሱን ሃሳብ የሚቃወም ከሆነ ደግሞ ብሄረተኛ አክራሪ (የህዋሓት/ኦነግ ደጋፊ) ብሎው ለመፈረጅ ግዜ አይውስድባቸውም፡፡

የኢትዮጵያ አንድነት ማለት ምን ማለት መሆኑ የሚገልፁበት መንገደድ ምንም ግልፅ ያለመሆን ችግርም ይታይባችዋል፡፡ ለኔ እንደመሰለኝ ከሆነ እነሱ የሚልዋት አንዲት ኢትዮጵያ በጀኦግራፊ የተከፋፈለ ክልል ያለባት፣ በአማርኛ የሚነጋገር የክልል ህዝብ ያለት ኢትዮጵያ (ምክንያቱም አንድ ክልል የተለያዩ ቛንቛዎች የሚናገር ህዝብ ካሰባሰበ በአማርኛ መነጋገር የግድ ይላልና ነው ልክ እንደ ደቡብ ህዝቦች)፣ የድሮው የሚኒሊክ ባንዴራ ያላት ኢትዮጵያ፣ ብሄር ብሄረሰብ የሚባል ድምፅ የማይሰማባት ኢትዮጵያ፣ በአብዛኛው (majority) ብሄር የሚገዛ ህዝብ ያላት ፌደራል ኢትዮጵያ ወዘተ ነው፡፡ እሁን ይገነባል እያሉት ያለው እንድነት ከድሮዋ ኢትዮጵያ ያላቸው ልዩነት በወጉ መግለፅ የሚችል አሰተሳሰብ የላቸውም፡፡

ማጠቃለያ

የነዚህ ሰዎች እና ድርጅታቸው ዋናው ችግር ያለው ህዋሓት እና የትግራይ ህዝብ ያላቸው ቁርኝት በሚገባ ካለመገንዘብ የተነሳ ይመሰለኛል፡፡ እርግጥ ነው በስነ-ሃሳብ ደረጃ አንድ ፓርቲ እና ህዝብ አንድ እና ያው ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ነገርግን የህዋሓት እና የትግራይ ህዝብ ግንኝነት ግን ከዚህ ስነሃሳብ የተለየ ነው፡፡ የመጀመርያው ነገር ህዋሓት ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለሌላው ጭቁን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘለአለማዊ ድህነት፣ ኀላቀርነት፣ አፈና፣ ወዘተ ያላቀቀ ድርጅት ነው፡፡ በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ለዘመናት ተሸክሞት ከነበረው የጨለማ ጉዞ ከጫንቃው አላቆ ወደ ሰላም፣ እድገት ጎደና፣ በቛንቛው እንዲማር (እንዲያስብበትም ጭምር) ፣ በቛንቛው እንዲዳኝ፣ በቛንቛው እንዲገኝ፣ባህሉ እንድያሳድግ፣ የአከባቢው ሃብት በሚገባ እንዲጠቀም፣ ወዘተ መንገድ ያሳየ ድርጅት ነው፡፡ ሁለተኛ ይህ ድርጅት በዚህ የ 17 ዓመት ትግል ጉዞው ከያንዳንዱዋ የትግራይ ቤትና ቤተሰብ የተሳተፈበት ትግል (የተሰዋ፣ የቆሰለ፣ የደከመ፣ የለፋ፣ ወዘተ) ከመሆኑ የተነሳ ህዋሓት የሚለው ስም በየአንዳንዱ ቤትና ቤተሰብ (ከ80% በላይ) ውስጥ አለ፡፡ ሰለዚህ ይህ ስም በአብዛኛው ህዝብ የሚታየው እንደ ቅርስ (እንደ አክሱም፣ ትላላቅ ባዓላት፣ ወዘተ) እንጂ እንደ ተራ የድርጅት ስም ተደርጎ እንዳልሆነ ግንዛቤ መወሰድ አለበት፡፡ለዚህ ነው ህዋሓት በተነሳ ቁጥር የትግራይ ህዝብ የሆነ አካሉ እንደተነካ ያህል እንቅልፍ አጥቶ የሚያድረው፡፡ ይህ ሲባል ግን የህዋሓት መሪዎች አይሳሳቱም፣ አይቀየሩም፣ የድርጅቱ ፕሮግራም በየውቅቱ አይታደስም ማለት አደለም፡፡ ይህ ነግር ሁነዋልም ለወደፊቱም እንደ አሰፈላጊነቱ ድርጅቱ፡ አባላቱና ህዝቡ ባመነበት መንገድ ማሻሻያዎች ይደረግበታል ብየ አምናሎህ፡፡

ምክረ-ሃሰብ

እነደዚህ አይነት የሚድያ መኖር ለአገር ጥሩ አማራጭ ቢሁንም ጉንበት - 7 እና ኢሳት ካለውቸው አላማ አንድ ህዝብና ድርጅት ለማጥፋትና ለማሸማቀቅ ማእከል አድረጎ የተመሰረተ ከመሆኑ አንፃር አላማውንም በግልፅ ኦፊሰላዊ በሆነ መንገድ እሰከ አልቀየረ ድረስ የህዋሓትና የትግራይ ህዝበ ጠላት ሁኖ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ይህ የማይቀርብን እዳ መሆኑ ሰለማይቀር እንደ ትግራይ ህዝብ ለንደእነዚህ ዓይነቱ የመጥፎ ፐለቲካ አረማጅ ድርጅቶች እንዴት መከላከል እንችላለን ብለን ነገሮችን ሳንንቅ ሁሉ ግዜ ማሰብና መከታተል ይገባናል ብየ አስባሎህ፡፡ ሰለዚህ የትግራይ መንግስት፣ ህዋሓት፣ ሊህቃንና ሌሎች እወነተኛ የትግራይ ድርጅቶችም ጭምር ለሚከተሉት ሃሳቦችም እና ሌሎች አማራጮች መውስድ ይገባችዋል ብየ አስባሎህ፡፡

ኢሳት ካላቸው አላማ እንፃር እና እስከአሁን ከረጩት ፖለቲካ ሲታይ ሁሉግዜም ቢሆን የትግራይ ህዝብ ጠላቶች መሆናቸውን በሚገባ ማወቅ፣

ኢሳት በየቀኑ በትግራይ ህዝብ ላይ ለሚያሰተላላፉት መርዝ ቀዋሚ የሆነ በሚገባ የተደራጀ እና የተተነተነ የሚድያ መልስ መስጠት የሚችል ፕሮግራም መኖር ይገባል፣

ሁሉም በየአቅሙ ፕሮጋራማችው መከታተልና በሚችለው ደረጃ መልስ መሰጠት ይቻላል

ነገርየው እየባሰ ከሄደ የጥፋት ሴራቸውም ከቀጠሉበት ተገቢ እርምጃ መውስድ የሚቻልበት መንገድ መታሰብ ይኖርበታል፡፡


Back to Front Page