ብሄር ለጠፉብን
ስንወለድ ኢትዮጵያዊ
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ኢትዮጵያዊ
ብለውን እንዳልነበር
...
ትንፋሻቸን ሲያልቅ
... ተጠራን በብሄር
... ኢትዮጵያዊነታችን
ተፍቆ ተጣለ ...
ልንገባ ተዘጋጅተን
ተሰልፈን ሳለን
...ወደ ተማሰው ምድር
አሉን ... ኦሮሞ፣
አማራ ፣ ጉራጌ፣ ስልጤና
ሀድያ
ተደመርን ብለን
... ተቀነስን ዳግሚያ
በሰንጠረዥ ወጣ
... ብሄራችን ተብላላ
መች በዚህ አበቃ...
ሀይማኖታችንም
... በቁጥር ተሰላ
የገዳዮቻችን
ስም ...
ብሄርና ፣ ጾታ
ሀይማኖትም ሳይቀር
... ሆን ተብሎ ተረሳ
ምንም ዝርዝር
የለም ... የገዳይ አስገዳይ
ወላጅ፣ ዘመድ
አዝማድ ... በጣም ተቆጥቷል
... እርሶንም በወንጀል
... መክሰስ ይፈልጋል
የመኪናው ሾፌር
... እርሶ ኖት ብሎ ያምናል
በርሶ የሚነዳው
... መኪናው አልሰራም
ግድ የለም ይልቀቁ
...
ያቁሙ መዘወሩን
... ፍሬኑ የማስራውን
ላደጋ አጋላጭ
... ብልሹ መኪናውን
በሰላም ያስረክቡ
... መንጃ ፈቃዶትን
ያክብሩ ተሳፋሪውን
... ደሞዞን ሰፋሪውን
መሾፈር እምቢ
ላለው ... መሞት የፈራውን
ግድ የለም ይተዉት
...
አልነዳም ብሏል
... መኪናው አልሰራም ።
ኢዮብ ከ ጮማ እምኒ
11-4-19
Videos From Around The World
|