Back to Front Page

አዎ! የትግራይ ህዝብና ህ.ወ.ሓ.ት አንድ ናቸዉ!!! በሶሰት መሰረታዊ ምክንያቶች፡፡

አዎ! የትግራይ ህዝብና ህ.ወ.ሓ.ት አንድ ናቸዉ!!! በሶሰት መሰረታዊ ምክንያቶች፡፡

 

ኖህ ሙሴ ታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

 

የተለያዩ ሰዎች (በተለይም የአማራ ትምክህተኛ ሊህቃን) የትግራይ ህዝብ ከህ.ወ.ሓ.ት ጋር አንድ አይደለም ሲሉ በሌላ በኩል አብዛኞቹ የትግራይ ሊሂቃን ደግሞ የትግርይ ህዝብና ህ.ወ.ሓ.ት አንድና አንድ ናቸዉ ብለዉ አጥብቀዉ ይሞግታሉ፡፡ እኔም ይህንን ከሚሉት አንዱ ነኝ፡፡ ለዚህም በቂ ምክንያት አለኝ፡፡

ምክንያቶቼን ዘርዘር አድርጌ ላቅርብ፡-

1ኛ. ህ.ወ.ሃ.ቶች ትግርዉያን መሆናቸዉ ነዉ፡፡ ይህ ማለት የህ.ወ.ሓ.ት ሰዎች በትዉልድም በመንፈሰም በባህልም ተጋሩ ስለሆኑና ከዛዉ ህብረተሰብ አብራክ የወጡ የራሱ ልጆች በመሆናቸዉ፡፡

Videos From Around The World

2ኛ. የትግርይ ህዘብ ህ.ወ.ሃ.ት ስለሆነ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የትግርይ ህዝብ ህ.ወ.ሃ.ት የሚባለዉን ድርጅት ወልዶ ፤ ተንከባክቦና ጠብቆ እዚህ ያደረሰና የድርጅቱ ደጋፊ ኃይል ሳይሆን የድርጅቱ ባለቤትም ራሱ ስለሆነ፡፡ ስለሞተ ፤ ሰለቆሰለ ፤ ልጆቹንና ንብረቱን ሳይሳሳ ሰለገበረም ጭምር ነዉ፡፡

3ኛ. የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ህዝቡ ህ.ወሓ.ትን ከመሆን ዉጭ ሌላ አማራጭ እንዳይኖረዉ ስላደረጉት፡፡

ይህም ሲተነተን ደርግም ይሁን ኢ.ህ.አ.ፓ ይምርዋቸዉ ከነበሩ ሃይላት ጀምሮ እሰከአሁኑ ኢ.ዜ.ማና ብልፅግና ህ.ወ.ሓ.ትና ህዝቡ ያወና ያዉ ናቸዉ ሰለዚህም ህ.ወ.ሃ.ትን ለማጥፋት መጀመርያ ህዝቡን ከሌላዉ ህዘብ ነጥሎ መምታት ያስፈልጋል እያሉ (አሳን ለማጥፋት መጀምርያ ባህሩን ማንጠፍ) የሚል ፖሊሲ ስላራመዱና የ 5፤95 ትርክት በየሚድያዉ ስለሰበኩና በተግባርም ግድያና ማፈናቀል ስላደረሱበት ትንሸ ይጠራጠር የነበረ የህብርተሰብ ክፍል ቢኖር እንኳ ህ.ወ.ሓ.ትን ከመሆን ዉጭ የተሻለ የመኖር ዋስትና እንደሌለዉ አዉቆ ህ.ወ.ሓ.ት.ን በመቀላቀሉ ናቸዉ፡፡

በመሰረቱ ከዚህ ዉጭ የሀ.ወ.ሓ.ት የትግል ፕሮግራም ፡ የመሰመር ጥራት ፤ የዓላማና የዲሲፕሊን ፅናት መርጦ ህ.ወ.ሃ.ት መሆንን የመረጠ ህዘብም ሳይረሳ ማለት ነዉ፡፡

እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን የትግሬይ ህዝብና የህ.ወ.ሃ.ት አንድ መሆን ከማንም በላይ ከነዛ አንድ አይደለም እያሉ ሲያላዝኑ የሚዉሉ ትምክህተኛ ኃይሎች በላይ የሚያምን አለመኖሩ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ህ.ወ.ሓ.ት እንደሌላዉ ድርጅት በሊሂቃን ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን ረጂም ህዝባዊ መሰረት ያለዉ መሁኑ አሳምረዉ ሰለምያወቁ ያለአንዳች ልዩነት በህዝቡ ላይ እንዲዘመት ለአመታት ሲዶሰኩሩ ፤ሲፅፉና ሲያቀነቅኑ ስለነበሩና ሰላሉ፡፡

ለዚሁ ማሳይ የሚሆነን ወደ ትግራየይ የሚያሰኬዱ መንገዶችን ከመዝጋት ጀምሮ ከትግራይ ጋር ንኪኪ አላቸዉ የሚልዋቸዉን አዉቶብሶች ማቃጠል፤ እህልና ዘይት መዝረፍ ወዘተ በቂ ማሳያ ናቸዉ፡፡

ይህን እያደረጉ ነዉ ታድያ የትግረይ ህዝብና ህ.ወ.ሓ.ት ለየብቻ ናቸዉ እያሉ ጉሮራቸዉ እሲኪሰነጠቅ ህዝቡን ሲያደነቁሩ የሚዉሉት፡፡

በመሰረቱ የትግረይ ህዘብ በኢትዮጵያዉነቱ ሊታማ የሚችል ህዘብ አይደለም ምክንያቱም ልክ የህ.ወ.ሓ.ት ባለቤት እንደሆነዉ የኢትዮጵያም ባለቤት ሰለሆነ፡፡ ይህ አጉል ትምክህት አይደለም በቀላሉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ያሰኛትን ነገሮች መርምሮ ምንጪ ከየት እንደሆነ ማወቅ ብቻ የሚጠይቅ ቀላል የቤት ስራ ሰለሆነ፡፡

ይሁንና የትናንት ተላላኪ ነበርን ባዮችን የዛሬ የለዉጥ ኃይሎች አሁንም ከታሪክ ሳይማሩ ከህ.ወ.ሓ.ት ጋር አንድ አይደለም ያሉትን ህዘብ ለመቅጣት ብዙ ላይና ታች ሲሉ ማየት ምንኛ የከፋ ድንቁርና በእነሱ ላይ እንደነገሰ የሚያሳይ ከመሆን አልፎ ህዝቡ በዚሁ ተንብረክኮና ርዶ ይገዛልናል ብሎ ማሰብ የዉድቀት መጫረሻ ማሳያ ነዉ፡፡ ምናልባት ትንሽየ የሰዉ ባህሪ ካላቸዉ በግዜ አካሄዳቸዉ ቢያርሙት ይሻላል፡፡ ካልሆነ ግነ ዉጤቱ ራሱ ይነግራቸዋል፡፡

ህዘቡን እርሱ በእርሱ ለመከፋፈል የሚደረግ ሩጫም ፈፅሞ የማይሳካና ይብሱኑ ጥርስ ዉስጥ የሚስገባቸዉ መሆኑን ቢያዉቁት መልካም ነዉ፡፡

የትግራይ ህዝብና ህ.ወ.ሓ.ት ግን አንድ ናቸዉ ቢያነስ ከላይ በጠቀሰኩዋዉ ምክንያቶች ስለሆነም ህ.ወ.ሓ.ትን ለመምታት የሚደረግ ሩጫ በቀጥታ የትግራይን ህዘብ ከመምታት ተለይቶ መታየት የማይኖርበትም በዚሁ ምክንያት ነዉ፡፡

ቸር ይግጠመን

Back to Front Page