Back to Front Page

ህወሓት የምር ይወስን።

ህወሓት የምር ይወስን።

 

ተፈራ ሀይሉ

ጥቅምት 1፤ 2012

አዲስ አበባ

 

ህወሓት በጥልቀት ተሃድሶ ወቅት ከኢህአድግ አበላት ድርጅቶች ውስጥ ብቸኛ ራሱን በጥልቀት ያየ ድርጅት ነው።ይህ ግምገማ ህወሓት ራሱን ብቻው የገመገመዉ ሳይሆን የያኔው ብአዴን፣ኦህዴድ እና ደህዴን ምስክርነተቸው የሰጡበት ጉዳይ ነው። የአስራሰባቱ ቀን ግምገማ ማካሄዱ ህወሓትን ያስሞገሰ ነበር እንጂ ህወሓት አልገመገመም ያለ አካል ይሁን የተባለበት ስብሰባ አልነበረም። ለሌሎች የኢህአዴግ ፓርቲዎች ግን የተለያዩ አስተያቶች ተሰጥቶ ነበር፡፡ ደህዴን ሙከራው ጥሩ ነው ተብሎ ነበር።ኦህዴድና ብአዴን ግን ምንም ማየት አልጀመራቹህም ተባሉ።ራሳቹሁን ማየት ሲገባቹ ወደ ሌሎች መቀሰር ወይም ምክንያትና ሰበብ ነው እየፈለጋቹህ ያላቹህ ተብለው እንደገና ገምግሙ ተባሉ። ይህ ሪከርድ የተደረገ ነገር ነው።

 

ይሁን እንጂ የኢህአድግ ጥልቀት ተሃድሶ አልተቋጨም፡፡ የጥልቀት ተሓድሶው አመቺነት ተጠቅመው በኢህአዴግ ውስጥ በህገወጥ መንገድ የተደራጀው የለማ ቲምበውጭ ሃይሎች መሪነት በኢህአዴግ የጠቅላይ ሚኒስተር መተካት ጫወታ አካሄደ፡፡ እናቴ ከህፃንነቴ ጀምራ ንጉስ ትሆናለህ ብላኛለች የሚለው ሰው ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ ተሾመ።በምርጫው ህወሓትና ጥቂት የብአዴንና የደህዴን አመራሮች የአብይ መመረጥ አምርረው ተቃውመው ነበር።ኦሮሞነቱን ቢፈልጉም አብይን ግን አልፈለጉም ነበር።በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዓት የፈጀ ክርክር እንደተደረገ ይታወቃል።አብይ ከተመረጠ አገሪቱ ትጠፋለችተብሎ ሰፊ ክርክር ተደረገ፡፡ ነግር ግን ከስብሰባው ውጭ ሁሉ ነገር ጨርሰውና ተደራጅተው ከመጡ ሰዎች ጋር ከመነታረክ ውጭ ፋይዳ አልነበረውም።አብይ አህመድ ተመረጠ።

 

Videos From Around The World

ህወሓት ምርጫውን በመድረክ ቢቃወምም አንዴ ከተመረጠ በሃላ ውሳኔውን አክብሮ እንደሚቀጥል በራሱ ስብሰባ በፖሊትቢሮም በማእከላይ ኮሚቴም በሙሉ ድምፅ እነደወሰነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ጉዳይ አንድም አባል የተቃወመ ወይም ድምፀ ተአቅቦ ያደረገ አልነበረም።ሁሉም መደገፍ እንዳለብት ተስማምተውና ወስነው ነበር። ለዚህ ምንንያተቸው ግልፅ ነበር፡፡ አብይን መደገፍ ማለት አገራችን ኢትዮጵያ እንዳትወድቅ መደገፍ ነው በሚል መንፈስ ነብር።

 

በዚህ ውሳነ መሰረት የተጀመረው የጥልቀት ተሃድሶ መድረክ ይቀጥላል በሚል መንፈስ ህወሓት ተንቀሳቀሰ።አብይምወደ መጀመርያ አከባቢ ወጣ ያሉ ምልክቶች ቢታይበትም ጠቅልሎ ኢህአዴግን ይክዳል ብሎ የጠረጠረው ሰው አልነበርም።ያልጠረጠረ ተመነጠረ ነገር ሆነና አረፈው።በየክልሉ እየሄደ የወርቅ፣ የሞተር፣ የጀግና፣ የፍቅር ፣ የቅርስ እና . . . ወዘተ አገርየሚሉ ቅፅሎች ደረደረ፡፡ በጣም የወረደ የፖፑሊስት /ህዝበኛ/ ባህሪው ታየ።የህዝቦች ጥያቄ መመለስ ትቶ እወዳቹሃለሁ አለ። በዚህም ብዙውን ሰው ማታለል ቻለ።

 

ትንሽ ቆየት ብሎ ደግሞለውጡ በቲም ለማ የመጣ ነው ብሎ ደሶኮረልን። የለየለት የአምባገነኖች ፍረጃም ጀመረ፡፡ ለውጥ የሚደግፉና ለውጥ ያልተቀበሉ የሚል ንግግር ጀመረ።መደመር ፍቅር አንድነት ሲል ይቆይና የተደመሩና ያልተደመሩ፣ ሪፎርም የሚቀበሉና የማይቀበሉ ብሎ ይከፋፍላል።ቆየት ብሎ ደግሞ የቀን ጅቦች፣ ጠጉረ ልውጦችና ትግርኛ ተናጋሪዎች ማለት ጀመረ። አገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ሰዎች ሰብአዊ መብት ጥሰትና ኮራፕሽን ፈፅመዋል በማለት ማሰር ጀመረ።በግልፅምአነድ ብሄር ላይ ያነጣተረ ጥቃት መፈፀም ጀመረ።የለውጡ ዋና ዓላማም ወያኔን ከቤተመንግስት ማውጣት ነበረ፣ተሳክቷልም ተባለ።ወያኔ ደስ አይበለው በሚል አባዜ ብዙ የማግለል ስራ በግልፅና በአደባባይ ተነገረ።ተሰራም፡፡ እነ ሰራዊት ፍቅሬ በወያኔ አርባኛ ዓመት ለምን ደደቢት ትግራይ ሄድክ ተብሎ በሚድያ ተቀርቅሮ በአደባባይ ቶርቸር ተደረገ።

 

ጆኖሳይድ በሁሉም ክልሎች በሚባል ደረጃ በለውጥ ስም ተፈፀመ። በሶማሊ፣ በኦሮሚያ፣በደቡብ በጌድዮ እና በአማራ ክልል በሚኖሩ የትግራይ፣ የቤንሻንጉል፣ የቅማንት እና የከምሴ ኦሮሞ ግለሰቦች ላይ ጆኖሳይድተፈፀመ።የሚያሳዝነው ግን ፀረ ለውጥ እንዳይባልና እንዳይፈረጅማንም ተቃውሞ የጮሀ የለም። ኢንጅነር ስመኘው በአገሪቱ አደባባይ በጠራራ ፀሃይ ተገደለ። የኢትዮጵያዊው ጀግና ገዳይ ወንጀለኛን ለማወቅ ግን ምርመራ ሳይደረግ ቀረ።የህዝብ ተመራጮች እነ አምባቸው በባህርዳር በፀጥታ አካላት ቢሯቸው ውስጥ ተረሸኑ።ጀነራል ሰዓረ ከወዳኛቸው ጋር በግል ጠባቂያቸው ተገደሉ።ምርመራ ይደረጋል ተባለ። እሰካሁን ምርመራ የሚባል ነገር የለም።አሁንም ዝም ተባለ። ነግር ግን በየበአሉ በቤተመንግስት ጭፈራና ግብዣ እንደቀለጠና እንደቀጠለ ነው።

 

በአሁኑ ወቅት የየክልሉ ተመራጭ ፕሬዝዳንቶች ከትግራይ በስተቀር በሁሉም ክልሎች ተቀይረዋል።የቀየራቸው የመረጣቸው ህዝብ አይደለም፡፡ የቀየራቸውከፈደራል መንግስትነት ወደ ማዕከላዊ መንግስትነት ራሱን ያሸጋገረ የአብይ መንግስት ነው።እሱን ያልተቀበለ ሁሉ ፀረ ለውጥና ያልተደመረ ተብሎ እርምጃዎች ይወሰዱበታል። ይህንን ለማስፈፀም በሚል በየክልሉየለውጥ ቡዱን በምስጥር ይደራጃል፡፡ ባጀት ይመደባል፡፡ ክፍፍል እንዲፈተር ያደርጋል፡፡ ክፍፍሉ ሲፈጠር የሚድያ ዘመቻ ከተደረገ በኃላ ስብሰባ ተጠርቶ የፓርቲ ውስጥ መፈንቅለ መንግስትይደረጋል። ለውጥ ተካሄደ ይባላል፡፡ አገራዊና ክልላዊ ህገ መንግስት በጠራራ ፀሓይ እየተጣሱ ዝም ይባላል።ከዛ መደመር የሚል መዝሙር ይዘመራል።

 

ሌላው የአብይ መንግስት የተሰጠው ተልእኮ ኢኮኖሚውን መበጥበጥነው።የቻይና ፕሮጀክት ሊሳካ አይችልም የሚል መልእክት ለመላውየአፍሪካ አገራት ለማስተላለፍ ሁሉም ፕሮጀክቶች እንዳይሳኩ ሆነ ተብሎ የማዘግየትና የማቆም እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።ያልተጠኑና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የማይገባ በማለትና አቃቂር በማውጣት ተጀምረው የነበሩት የህዳሴ ግድብ፣ የባቡር ፕሮጀክቶች፣ የስካር ፕሮጀክቶች እና ኢንዱስትሪ ፓርክች /የሚመረቁት ላይ ኢሳያስ አፈወርቅን ቢጋብዙም/ ልማት ተንቀራፍፎ እንዲሞቱ ተፈርዶባቸዋል።የገበሬውና የገጠር ልማቶች ሆን ተብለው ተረስተዋል።

 

ዋናው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የእርሻ ኢኮኖሚ ተረስቷል።ቴሌኮሚኒኬሽን፣የኢትዮጵያ አየር መንገድና ሌሎች ትላልቅ ኩባንያዎች ያለምንም ጥናትና ውይይት በዓለም ባንክና በአይ. ኤም. ኤፍ. ቀጭን ትዕዛዝ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ የድለላ ኩባንያዎች የዋጋ ስሌት ለማውጣት እሴቶቻቸውን እያጠኑ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጅቶች ለመሸጥ ቅድመ ሁኔታዎቹ በሩጫ ሲፈፀም ምስጋና ይግባቸውና ፕሮፈሰር አለማየሁ፣አቶ ክቡር ገና እና አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ በስተቀርሁሉም ዝም ዝም ብሏል። እነዚህ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በዓለም ባንክና በመሰል ተቋማት የቀረበ የርዕየተ ዓለም ተፅዕኖ ውጤት ነው ብለው ስጋታቸውን በመግለፅ መንግስትን እየሞገቱ ናቸው። የኢህአዴግ ግንባር ፓርቲ አባላት ግን ዝም ዝም እንዳሉ ናቸው። ይህ ዝምታቸው ግርምታን ከመፍጠር በላይ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ህገ መንግስትና ፌደራላዊው ስርዓት ለመጣስ አብይ ከግንቦት ሰባት/አዜማ/ ሲያሴር፣ ምርጫ ይተላላፍ ሲል፣ የህዝብ ቆጠራ እንዳይደረግ ሲያደርጉ፣መደመር ብሎ ኢህአዴግን ሲያፈርስና ክልሎችን ያለ ፓርቲ ሲያስቀር ዝምታው እንደቀጠለ ነው፡፡። በቅርቡ ደግሞ ጭራሸ ህወሓት ካድሬዎቹን ለአብይ ሰብስቦመደመር የሚባል የሌለ ፍልስፍና ፍልስፍና ተብሎ እንዲወያይበት ወስኖ መድረክ አዘጋጀ።አምስት ቀን ይፈጃል ተብሎ የተዘጋጀ ቢሆንም ካድሬዎቹ በተቃውሞና በጥያቄ አስጨንቀው ሰለያዙና ካሜራ ይግባ አይግባ፣ ውይይቱ ለህዝብ ግልፅ ይሁን አይሁን በሚል ክርክር ግማሽ ቀን ተቃጥሎ ከሰዓት በኃላ ብቻ በተደረገው እንትን ነገር አለቀ። ካድሬዎችም የፅናት መዝሙራቸውን ዘመሩ፡፡

 

ህወሓት ዝምታው መሰበር አለበት፡፡ ህወሓት መንፏቀቁን ያቁም።ልምምጡን ያቁም።የእስካሁኑ ያሳየው ትዕግስት ውጤት የለውም ብዬ አይደለም።ነበረው።ግን ሁሉም ነገር ገደብ አለው።አብይ በመቐለ የተደረገውን የአገር እናድንና ህገመንግስቱን እና ፌደራሊዝም እናድን ስብሰባን በስልጣኑና በህልውናው የመጣ አድርጎ አይቶ በመደመር ስም ኢህአዴግን ቀድሞ አፍርሶ ህወሓትን ለማግለልና ክልሎችን ቀድሞ ለማሰለፍ እየተሯራጠ ነው።ህወሓት ይህን ተግባር ዝም ብሎ የሚያይበት ጉዳይ አይደለም።የህዝቦች ትግል ወደ ኃሏ የሚጎትት የአብይን ስርዓት ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችና ድርጅቶችን በማበር የከሸፈውን ጥልቅ ተሃድሶ መልሶ መቀጠል እንዲችል መታገል አለበት። እንዴት? ለሚለው የሚከተሉትን ነጥቦች እንያቸው፡፡

 

1.   ህወሓትየኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ ጠርቶ አብይ አህመድ አገር ለመምራት ብቁ አይደለህም ብሎ ምርጫ እንዲካሄድ ምክርቤቱን መጠየቅናመታገልአለበት።

2.   ህወሓት በየአካባቢው እየተፈፀሙ ያሉ የብሄር ጥቃቶች /የጆኖሳይድ ወንጀሎች/ በስማቸው ጠርቶ ማውገዝ አለበት፡፡ ይህንን ህዝባዊ አላማውም ያስገድደዋልና።

3.   ህወሓት በትግራይ ህዝብና በመሪ ድርጅቱ ላይ እየተፈፀመ ያለው የማያቋርጥና ተከታታይ የማጥቆርና የማግለል እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲቆም ተቃውሞውን በተከታታይ ማሰማት ይኖርበታል።

4.   ህወሓትየፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ዘንድ በግልፅና በድፍረት መጠየቅ አለበት። ውድ አገራቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የድህንነት፣ የፌደራል ፖሊስ፣የመከላከያ አባላትና እነበረከትና ታደሰ ጥንቅሹ በቂም በቀል ታስረዋል።በኦሮሚያ ጥያቄ ስላቀረቡ ብቻ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሶዎች ኦነግ- ሸኖ ትደግፋላቹ በሚል ተስረዋል።የአብንና የባላንደራስ አባላት ያለ ምንም ማስረጃ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርጉ ነበር ተብለው ታስረዋል።ከመድረክጀርባ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ዘንድመጠየቅናመለማመጥ መፍትሔ አላስገኘም።ሰለዚህ በአደባባይ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ይጠይቅ።ይታገል።

5.   ህወሓትበባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙ ግድያዎች ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እየተካሄደ ያለው ገለልተኛ ያልሆነ ምርመራ ተቋርጦ ነፃና ገለለተኛ ምርመራ እንዲካሄድና የሚጠረጠሩ ባለስልጣኖችም እንዲጠየቁ መወሰንና ድምፁን ማሰማት ይኖርበታል።

6.   ህወሓትበዚህ ባልተረጋጋና የአገሪቱን ሉዓላውነት በማይጠብቅ መንግስት ተብዬ እየተወሰዱ የሚገኙ ማናቸውም ስምምነቶች በአስቸካይ እንዲቆሙና ከዚህ በፊት ተወስነዋል የሚባሉትንም ተግባራዊ እንዳይሆኑ ጥሪውን ለአትዮጵያ ህዝቦች ማሰማት ይኖርበታል።ከዝምታና ከማጉረምረም ወጥቶ ፊት ለፊት መጋፈጥ አለበት።ጉዳዩ የአገር ሉዓላዊነትናህላዌ ነውና።

7.   በመጨረሻ ህወሓትከሁሉም የድርጅቱ አባላት፣ ከትግራይ ገበሬ፣የከተማ ህዝብ፣ወጣቶች፣ሙሁራንና ባለሃብቶች እና በትግራይ ከሚገኙ ህጋዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ተወያይቶ ውሳኔውን ለወንድሞቹ የኢትዮጵያ ህዝቦች ይግለፅ።ህገ መንግስትና አገር ለማዳን የአገር ወዳድ ሃይሎች ግንባር ይመስረት ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፍ።

8.   ይበቃል።

 

ቸር ሰንብቱ።

 

 

Back to Front Page