Back to Front Page

የትራምፕና ገዱ ውሎ

የትራምፕና ገዱ ውሎ

 

አልማዝ በዳኔ እንደተረከችዉ 5-15-19

 

አቶ ገዱ ዋሽንግተን ዲሲ መልእክት ይዘው ሂደው ነው።አቀባበል የተደረገላቸው ያኔ ወያኔን ጥለን መጣን ውሮ ወሸባዬ የተባሉለት ጊዜ አይነት አይደለም። እንደ ጊዜ ከዳተኛ የለም! አሉ ገዱ በሆዳቸው ዳላስ አየር ማረፍያ ሲደርሱ።ከዓለም ቁጥር አንድ መሪ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት በመብቃታቸው ትልቅ ኩራትና ደስታ እየተሰማቸው፣በሌላ በኩል ደግሞ ፍርሓትና ጭንቀት በስሱ ይሰማቸዋል።የፍርሃቱ መንስኤ ግን በውል አልተገነዘቡትም።ገና ከአዲስ አበባ ሲነሱ ጀምሮ ነበር በውስጥ ስሜታቸው ውስጥ አብሮ የተነሳው።ግን መቀነስ ሳይሆን እየጨመረ ነው የሄደዉ።

ገዱ ምን አስፈራኝ? አሉ ትራምፕ የቅማንት ጭፍጨፋ ያቅ ይሆን? ትግሬዎችን የሚገደሉት ተገድለው ሌሎቹ ተፈናቅለው ያለንብረታቻው የሚበላና የሚጠጣ በየመንገዱ አጥተው ወደ ትግራይ በሱዳን በኩል መሄዳቸውም ደርሶበት ይሆን? ገዱ ጠየቁ ራሳቸዉንቀጠሉና ታድያ እነሱ ኢራቅ፣አፍጋኒስታን፣የመን፣ሶርያ የጨፈጨፉት አንሶ ነው እኔን የሚጠይቀኝ።ስደተኛ አልቀበልም አጥር ላሳጥር እያለ አይደለም እንዴ ራሱ! ከሱ በላይዘረኛ ኑሮ ነዉ እኔን የሚጠይቀኝ?ለውጭ ጉዳይነት አዲስ ብሆንም እኮ በዓለም ላይ ማንምን እንዳደረገ በዝርዝር አውቃለሁ።ለዛ አይደለ ከክልል ወደ ውጭ ጉዳይ የተሸምኩት።ይህ የሚያስፈራኝ ነገር የለውም ብለው ራሳቸው ጋር እያወጉ ከቆዩ በኃላ የስቴት ዲፓርትመንት ፕሮቶኮል ሰውየ በአውሮፕላን ስር ጠብቆ ሰር ዌልካም ብሎ የትኛው መኪና ላይ እንደሚሳፈሩ ይመራቸውና ወደ ተዘጋጀላቸው መኪና ይገባሉ።ወድያው እንደገቡ ሰርዌልካም ሲለኝ ምን ማለት ነበረብኝ? የኔ ነገር በሃሳብ ሁኜ (እጅ መስጠት የለም) ምንም ሳልመልስለት ዘው ብዬ መኪና ውስጥ ገባሁ።የራሱ ጉዳይ እኩያዬ አይደለ ተራ አስተናጋጅ መልስ ሰጠሁኝ አልሰጠሁ ምን አስጨነቀኝ።ይሉኝታ የሚሉት አብሮ ትኬት ቆርጦ ይመጣል እንዴ? አሉ ይሉኝታ የሚያቁ ይመስል።

Videos From Around The World

 

ሹመት ማግኘታቸውን የሰሙት እዚሁ ዋሽንግቶን እያሉ ነው።ከተማዋን የሳቸው ዕድል ቀና እንዲሆን ያደረገች አድርገው ወሰደዋታል፡፡ ለዚህም ውድድ አድርገዋታል። ገዱ ያኔ ሲሾሙ ቤተሰብ ተሰባስቦ ቀጣይ ኑሯቸውን ምን መሆን እንዳለበት ለመወሰን ነበር እዚህ ከተማ ከቤተሰቦቻቸው የነበሩት። እንዳውም ቤት ለመግዛት ከሚሸጡ ቤቶች አንዳንዱን እያማረጡ ነበር።እሳቸው 30 ዓመት የታገልኩት ህዝቡን ያገለገልኩበት ዋጋ ነው፡፡ እንዲያውም ሲያንሰኝ ነው ባይ ናቸውብለው እንደሚያምኑ የዲሲ የወሬ ምንጮች ይናገራሉ። ይሁን እነጂ ማንም ስለ እውነትነቱ የሚያቅ የለም ከጊዜና ከፈጣሪ በስተቀር።

 

ይሁንና አሁን ገዱ በማያውቁት ፍርሓትና እንገዳ ሓሳብ እየተብሰከሰኩ የተያዘላቸው ሆቴል ደረሱ።ረዥም ሰዓት ነው::ጉዞውአድካሚ ነው:: ብሎ ፕሮቶኮሉ የተዘጋጀላቸውን ሰፊ ሳሎንና የመኝታ ክፍል መክፈቻ ቁልፍ/ካርዶቹን በመስጠት የሚፈልጉት ነገር ካለ ብሎ የራሱን አድራሻና የተመደቡላቸው ጥበቃ የያዙት ክፍል ቁጥር ነግሯቸው ሊሄድ ሲል ታንክዩ ቨሪማችአሉት አማርኛ አማርኛ በሚል ድምፀት።ፕሮቶኮሉ እንደሄደላቸው እንዳወቁ በረዥሙ ተነፈሱና አንድ ነገር ተሸክመው እንደነበር ነገር ቅልል አለላቸው።

 

ወዲያዉ የመጡበት ጉዳይ የሚያትተውን ፕሮግራሙን ለማንበብ ሞከሩ ግን ሃሳባቸውን መሰብሰብ አልቻሉም ወይም እንግሊዝኛው ጠጥሮባቸው ሐሳቡን ስላልተረዱት ወረቀቱን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጡት፡፡ ወደ ክፍሉ ስልክ አምርተው ወንበሩ ላይ በመቀመጥ ወደ ራሳቸው ፕሮቶኮል ለመደወል ሲሞክሩ በስህተት ወደ ሪሰፕሽን ደወሉ። ደስ በሚል የሴት ድምፅ ሪሰፕሽን መሆኑና ሚኒስተር አንዳርጋቸው ምን ልርዳዎት ትላቸዋለች እንዴ የአብየን ስም እንዴት አወቀችው በማለት እንደ መደንገጥም መገረምም ብለው ፕሮቶኮሌን አገናኝኝ! ይሏታል።የሳቸው ፕሮቶኮል አሜሪካዊ ሁሉም ማወቅ ግዴታ ያለበት ይመስል።ሪሰፕሽንዋ አልገባትም።እባክዎን ምን አሉኝ?ይድገሙልኝ ስትላቸው ትህትናዋን በማድነቅ ተይው ብለው ለመተው ከተግደረድሩ በሃላ የፕሮቶኮላቸውን ስም ተናግረው ፈልገውት እንደነበረ ሲገለፁ ልምድ ያላት ሪሰፕሽን ሰራተኛ ከመቅፅበት ስሙን ተጠቅማ ፕሮቶኮሉጋ ደውላ ታገናቸዋለች።ሚ/ር ገዱ ግን በሳቸው የኮሚንኬሽን ችሎታ ያገኙት ይመስል ፕሮቶኮላቸውን አምባሳደሩ ተቅብሎን በዛው ሄደ እንዴ?አሉ ቀብረር ብለዉ፡፡

 

ፕሮቶኮሉም ያዩት ይመስል ከተቀመጠበት ብድግ ብሎና ቆሞ አረ አምባሰደሩ እርሶን እየጠበቀ ነው።እዚህ ከኔ ጋር ነው። አለቸዉ

ቬሪ ጉድ ወደ ክላሴ ላከው አሁኑኑ!

ፕሮቶኮሉም አምባሳደሩን ወደ ሩም 2010 ይሂዱና ክቡር ሚኒስትሩን ያግኙ ብሎ ይነግራቸዋል።አምባሰደሩ የተባሉት ክፍል ሲደርሱ ደወል ይደውላሉ።ሚኒስትሩ ከፍተውላቸው እንደገቡ እንዴት ነህ? ሰፊ ክላስ ነው ያዘጋጁልኝ እነዚህ አገር? ከኛ ጋር መቀራረቡ ፈልገውታል።ቻይናን ከአባረርንላቸው እነሱም በደምብ እኛን መደገፍና አሁን ከገባንበት ቀውስ እንድንወጣ ማድረግ አለባቸው አሉት።

አምባሳደሩም እዚህ አገር ስታንዳርድ አላቸው ለሚኒስተር ለዋና መምርያ ዳሪክቶሬት አብሯቸው ለሚመጡ ኢክስፐርትስና ፕሮቶኮል ምን ዓይነት ሩም እንደሚሰጡ ይታወቃል ብሎ ሳይጨርስ እንዲህ ዓይነቱ ልምድ ትምህርት ወስደን መስራቤታችንን ሪፎርም ለማድረግ ይጠቅመኛል።እየፃፋችሁ ላኩልንአሉት።

አሁን የኛን መምጣት እንዴት እየጠበቁት ነው? ብለው ጥያቄ ያስከትላሉ። ከኛ ጋር በሽብርተኝነት በተለይም በሶማሊያና በሁለቱ ሱዳንም ፀጥታ ጉዳይ መነጋገር ይፈልጋሉ

ሌላስ?

ያው በኢኮኖሚ ፖሊሶዎቻችን ሪፎርም እንድናደርግ እየጠበቁ ነው።ዘግይታቹኃል እያሉን ነውእያጣደፉን ነው። አለ እየተቅለሰለሰ ይህማ አይቻልም። የወያኔን ነገር መልክ ሳናስይዝ የሚቻል አይደለም።ምን ይዘን ነው ቻይናዎቹን የምናሰናብታቸው? ቀላል ችግር አይደለም ያለንበት ሁኔታ፣ ሊገባቸው ይገባል። አሉ ጠበቅ አድርገው።

አምባሳደሩም ይህማ መምጣትዎ ካልቀረ ለሁሉም የሚያገኝዋቸው ባለስልጣን ጠበቅ አድርገው ይንገሩልን።ዋነኛዎቹን እኮ እኛ አናገኛቸውም። ይሏቸዋል።

ሚኒስትሩም ግድ የለህም ይህማ አስምሬ እነግራቸዋለሁ። ቀጠል አድርገው ፕሮግራማችን እንዴት እንዴት ነው?

ፕሮግራሙን የስቴት ዲፓርትመንቱ ፕሮቶኮል አልሰጠዎትም እንዴ?

ብሎ ጠየቃቸው።

ሰጥቶኛል ላንች ዲነር በዛበት ዋና ዋና ቁምነገሩን ብቻ እስቲ ግለፅልኝ አሉት

አምባሰደሩም ከእጅ ቦርሳቸው ከስቴት ዲፓርትመንት የተሰጣቸውን ወረቀት በማውጣት ነገ ቴን ኤኤም ከስቴት ዲፓርትመንት ሰክሬታርያት ጋር ቀጠሮ አሎት።

አቋረጡት ሚኒስትሩ የለም እንዴ? ከፀሓፊው ጋር የምንገናኛው?ክብራቸው የሚነካ ድርጊት እንደተፈፀመ ከንክኗቸዋል።

አምባሳደሩም ፈጠን ብሎ በፀሓፊዋ በኩል ሚኒስትሩን ነው የምናገኛቸው ብሎ ሳያሳጣቸው ይመልስላቸዋል።

ፕሬዝደንቱን መቼ ነው የማገኛቸው? ብለው ተጣድፈው ይጠይቃሉ። ቴንታቲቭሊ ነገ ፎር ካልሆነ ደግሞ ከነገ ወድያ አራውንድ ሚድ ደይ በለውናል ነገ ኮንፈርም እናደርግላቹሀለን ብለውናል።

አይ እኔ ፕሮግራሜን አረንጅ ማድረግ እፈልጋለሁ ተሎ ኮንፈርም ያድርጉልን።ሚኒስትሩ ራሳቸው ፈጥናችሁ ኮንፈርም አድርጉልን ብለዋል ብለህ ተጭነህ ኮንፈርም እንዲያደርጉልን አድርግ። አሉት እንደማዘዝ እያረጋቸው፡፡

እሞክራለሁ ክቡር ሚኒስትሩ።ረዥም ጉዞ ነው የተጋዛችሁትና አረፍ በሉ እኔ ኤምባሲ ደረስ ብዬ እመለሳለሁ። ብሎ አምባሳደር ተሰናብቶ ከክፍሉ ይወጣል።

 

በነገታው ስቴት ዲፓርትመንት በፕሮቶኮል ታጅበው ይደርሳሉ።የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ ውይይት ገቡ።መጀመርያ የስቴት ዲፓርትመንቱ ኃላፊ የእንኳን መጡ ንግግር አድርገው አሁን ኢትዮጵያ ያደረገችውን ለውጥ አድንቀው አሁንም ለውጡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዲሞክራሲና በኢኮኖሚ ሙሉ ለውጥ እንደሚጠብቁ አጽንኦት ሰጥተው ንግግራቸውን በምስጋና አጠቃለሉ።ሚኒስተር ገዱ ጎሮራቸውን ከጠራረጉ በኃላ ተፅፎ የተሰጣቸውን ረዥም ፅሑፍ አንባቡን አንዳንዴ እያወላገዱ አነበቡ።የለውጡን ታሪክ የሚያትተው የፅሑፉ አካል አብዛኛውን ስፍራ ይይዛል።የአሜሪካን ዲሞክራሲና የኢኮኖሚ ዘይቤ ያደንቃል ፅሑፋቸው።እናንተ እርዱን እንጂ እኛማ አብዮታዊ ዲሞክራሲን ለመቅበር ቆርጠን ተነስተናልአንድምታ ያለው ንግግር አነበቡ።ፈረንጆቹ ንግግራቸውን ያዳመጡት አይመስለም።መርዘሙ ሰልችቷቸዋል። ገዱም ደክሟቸዋል እየተንገዳገዱ ማንበቡ፡፡በስተመጨረሻ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ለፕሬዝደንት ትራምፕ ደብዳቤ ይዘው መምጣታቸው ገልፀው እስካሁን ለተደረገላቸው መስተንግዶ አመስግነው ማራቶን ንግግራቸውን ድምፃቸው ከፍ አድርገው ጨረሱ።የስቴት ዲፓርትመንቱ ሰክሬታርያት የዲፕሎማሲ ንግግሩን አድንቀው በተለይም በኢኮኖሚና በዲሞክራሲ ዙርያ የተናገሩትን የለውጥ አቅጣጫ ትክክለኛነት መስክረው ፈጥነው ወደ ተግባር እንዲገቡ አጽንኦት ሰጥተው አመስግነው ስብሰባው አለቀ።ሰክሬታርያቱ ሌላ ቦታ ከፕሬዝደንቱ ጋር ስለሚገኙ ራት እንዳይማይገኙና ረዳት ሴክሬታርያቱና ሌሎች እንደሚገኙ ተናግረዉ ተጣድፈው ተሰናብተው ሄዱ።እነ አቶ ገዱም ወደ ሆቴላቸው በመጡበት መንገድ ሄዱ።

 

በመንገድ ላይ እያሉ ራት አልገኝም ረዳቴ ይገኛል የሚለው የባለስልጣኑ ንግግር አልጣማቸውም ምን ያህል ቢንቁን ነው? አሉ የኢትዮጵያዊነት ሱሳቸው ተቀስቅሶባቸው።አምባሳደሩ ነቅቶ ፊታቸው ሲኮሳተር አይቷቸው ስለነበረ ሆቴሉ እንደደረሱ ያው ዛሬ ራትጋ የሚገኙት ምክትል ሚኒስትሩ ናቸውሲላቸው ለውጥ አደረጉ አስከፋናቸው ብለው ነውአሉ።አምባሳደሩ ወርቅነህ ገበየሁ ተሎ መሰልጠን ጀምሮ ነበር በማለት በሆዱ እያማ፣ እዚህ አገር ዝም ብለው ምክትል ማለት ሲቀናቸው ረዳት ነው የሚሉት ብሎ ነገራቸው እሳቸውም በተራቸው ለለማስነቃት አጀንዳውን ለማስቀየር ዶናልድ ኮንፎርም አደረጉ? ብለው ይጠቃሉ። ክቡር ሚኒስትሩ ገና አላሳወቁንም።የእርስዎ ጥያቄ መሆኑንም ነግረናቸዋል።እንደምንም አፋጥነን እናሳውቃቹኃለን ብለዋል አለቸው እሺ ደክሞኛል ክላሴ ገብቼ ትንሽ ልረፍ ይሉታል አምባሳደሩን።አምባሳደሩም እኔም በፕሮቶኮሉ ሩም እጠብቃለሁኝ ብሏቸው ይለያያሉ።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ክላስና ሩም ምን ልዩነት ኖሮት ነው ሩም ሩም ሚኒስቴር ማለት እየቻሉ ሰክሬታርያት ረዳት ምን ግራ የተጋቡ አገር ናቸው አሉ በሀሳባቸው ክፍላቸው ውስጥ ገብተው ለመተኛት እየተዘጋቹ።ተኙ።ዲፕሎማሲ ያደክማል።

 

ትንሽ እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረጋቸው ዋይት ሀውስ ሲገቡ ዶናልድ በኦቫል ቢሯቸው በክብር ሲቀበላቸው ትራምፕ ጥያቄ ላይ ጥያቄ ሲያነባብሯላቸው የተፃፈ ማንበብ እንጂ በቃል ያልተዘጋጁበት ፈተና ገጥሟቸው የሀገር ጉዳይ ሆኖባቸው እንደምንም ብለው ያለ የሌለ አቅማቸውን በመጠቀም ጥያቄያቸውን መልሰው ሲያበቁም እሳቸውም የሶርያ ጉዳይ ሁሌ እንደሚያሳስባቸው ትራምፕን ቀርቅረው ሲጠይቃቸው፣ትራምፕ ይህ ያንተ ጥያቄ አይደለም የራሽያኖች ነውሲሏቸው አቶ ገዱም አረ! የራሴ ነው። ወያኔዎች ለውጡን በመቃዎም ኢትዮጵያን እንደ ሶርያ ልትበትኗት ነው እያሉ ስለሚያቸግሩን ሶርያን መልክ ብታስይዙልንና ወያኔን ምሳሌ ብታሳጡልን ብዬ ነው።ብለው በማስከተልም ምን በወጣኝ ነው የራሽያ ተላላኪ የምሆነው? በማለት ይመልሳሉ።ትራምፕም ለመሆኑ ወያኔ ምንድነው ሁለቴ ወያኔ አልከኝ ብለው ሲጠይቃቸው፣ አቶ ገዱ በመገረም ወያኔ አታቁም! ብለው በድንጋጤ ከህልማቸው ይባንናሉ።ላብ በላብ ሆነዋል።እኔም ከህልሜ ባነንኩኝ።ጠቅላዩ አቶ ገዱን ውጭ ጉዳያቸው አድርገው ሾሙ ሰምቼ ስተኛ የቃዥሁት ነው።በፌስ ቡክ ግን አቶ ገዱ ሹመቱን ሰምተው የኢትዮጵያ አገሬ የአውትሳይደር ሚኒስቴር መሆኔ በደስታ እቀበለዋለሁ ማለታቸውን ከእንቅልፌ ስነቃ አንዱ ጎርጋሪ አወጋኝ።

 

አልማዝ በዳኔ

ተንታ ሚካኤል

 


Back to Front Page