Back to Front Page

ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉቡኝ

ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉቡኝ

(ክፍል 3)

ዘመድኩን ዘሪሁን

12-10-19

 

ሰሙነኛ የውህደት አጀንዳ በተደመሩ ሚድያዎች በኢሳት፤ ኢበሲ፤ ዋልታ፤ፋና፤ አስራት፤ አሃዱ ወዘተ ለኢትያጵያ ችግር እንደ ፍቱን መደሃኒት ተወሰዶ እየተዘመረለት ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉቡኝ በሚል ርዕሰ የሌ/ኮ አብይና ሌኮ መንግሰቱ መመሳሰል በሁለት ክፍል አቅርቤ ነበር ፡፡አሁን ደግሞ ከውህደት አጀንዳ ጋር ተያይዞ የንጉስ አብይና ንጉስ ኃይለስላሴ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ተመሳሰሉቡኝ፡፡

አሁን ንጉስ አብይ በብርኃን ፍጥነት እየሮጠበት ያለው የኢትዮጵያ ፈደራል ስርአት ወደ አኃዳዊ ስርአት የመቀየር ጉዞ ንጉስ ኃይለስላሴ የኤርትራ ፈደሬሽን ለማፍረስ የተጠቀሙበት ዘዴ አንድና አንድ ነበር፡፡ ለነገሩ ከአሀዳውያን የአስተሳሰብ አንድነት ካለህ ከሌ/ኮ መንግሰቱና ንጉስ ኃ/ስላሴ መመሳሰል የግድ ነው፡፡ ቤተመንግሰት ማሳደስም አሃዳውያን ማወደስም የሚመነጨው ከዚሁ አስተሳሰብ ነው፡፡

Videos From Around The World

ንጉስ ኃይለስላሴ የኤርትራ ፈደሬሽን ለማፍረስ የነበራቸው ጥድፍያና የውሳኔው ፍጥነት አስገራሚ ነበር ፡፡አስቀድመው ውስጥ ለውስጥ የፌዴሬሽን መንግሰት የሚያፈርሱ ከኤርትራ ም/ቤት አደራጁ በመቀጠል የፌድሬሽን አስተዳዳሪ ተድላ ባይሩ በቢተወደድ አስፍሀ ወ/ሚካኤል ተቀየሩ ፡፡ አዲሱ የፌድሬሽን አስተዳዳሪም የተሰጣቸው ቀዳሚ ተልዕኮ ፌዴሬሽን ማዳከምና ማፍረስ ነበር፡፡ በዚህ መሰረትም ከህግ ውጪ የተሸሙት አዲሶቹ መሪዎች የፌዴሬሽን ምልክት የሆነው ኤርትራ ባንዴራ በኤርትራ ምድር እንዳይሰቀል አደረጉ፤ቀጥሎ የኤርትራ ፌዴሬሽን አስተዳደር የሚለው ስም ወደ ኤርትራ ጠቅላይ ግዛት ቀየሩት ፤የኤርትራ የስራ ቋንቋ የነበሩት ትግርኛና አረብኛ አዳከሙት ፡፡

በመጨረሻም እ.አ.አ ህዳር 15 ቀን 1962 ኤርትራ ውህደት ተግባራዊ ለማድረግ የኤርትራ ፌድሬሽን ጥዋት አጭር ስብሰባ በወታደር ተከቦ አደረገ ተፌዴሬሽን ይፍረስ ብሎ ወሰነ ፡፡ ውህደቱም የተከናወነውም በንጉሱና ኤርትራ በነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ነበር፡፡ የንጉሱ የኤርትራ እንደራሴ ጉዳዩን አይቶት በዛው ዕለት ወደንጉሱ ተላከ፤ ንጉሱ በዕለቱ ወደ ህግ መወሰኛ ም/ቤት መርተውት ህግ መወሰኛ ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ረቂቅ አቅራቢዎች መርጦ ረቂቁ ተመልሶ ለህግ መወሰኛ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ቀርቦ በመጨረሻ በዕለቱ ንጉሱ ለኢትዮጵያ ህዘብ የደስታ መግለጫ አደረጉ ፡፡ በዚህ ሁኔታ በአንድ ቀን የኤርትራ ፌዴሬሽን 14ኛ የኢትያጵያ ጠቅላይ ግዛት አድርግ ጠቀለላት ፤ ዓረብኛና ትግርኛ ታገዱ በምትኩ በኤርትራ አማርኛ የስራ ቋንቋ ሆነ ፡፡ ይህ ውሳኔ ለኤርትራ ጉዳይ የመጀመርያም የመጨረሻም ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ድራማ ሲሰራ እንካን የኤርትራ ህዝብ ይቅርና የአስመራ ከተማ ነዋሪ እንካን ምን እየተደረገ እንዳለ አይውቅም ነበር፡፡

ልክ እንደ አሁኖች በክልል ያሉ ቢተወደዶች እጅግ በጣም አጭር ጊዜ ለሆነ ስልጣን ሲሉ/ፍርሃት ተላብሰው/ በህገ መንግሰት ራሰን በራሰ ማሰተዳደር ስልጣን ለብልግና ፓርቲ አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም ህዘቡ ያልተወያየውና ያልተቀበለው አጀንዳ በመጫን የሚመኙት ስልጣን በፍፁም ማቆየትም ማግኝትም አይችሉም፡፡ ምክንያቱም የንጉስ አብይ ድራማ ያልገባው ህብረተሰብ ክፍል የለም ፡፡

እዚህ ላይ በእጅጉ የሚገርመው ጉዳይ ንጉሱየኤርትራ ፌድሬሽን ለማፍረስ ከኤርትራ ህዘብ እወቅና ውጪ በአንድ ቀን ይህ ሁሉ ሩጫ ያስፈልግ ነበር ወይ ? ለኤርትራ ህዘቡስ ጉዳዩ ሚሰጥር መሆን ነበረበት ወይ ? የኤርትራ 30 አመት ጦርነትም የዚህ ወጤት ነው ፡፡ የንጉስ አብይ አካሄድም አንድ አይነት ነው፡፡ ምክንያቱም አስተሳሰቡና ድርጊቱ ከንጉሰ ኃ/ስላሴ ጋር አንድና አንድ ነው፡፡

በወቅቱ የጥድፍያ ውህደት ሲቃወሙ ከነበሩት የንጉሱ ቅርብ ሰዎች ውሰጥ የጤና ጥበቃ ሚ/ር አቶ አበበ ተፈራ የሚከተለው ተናግረው ነበር የኤርትራ ህዘብ በህግ ተሰጥቶት የቆየውን ፌዴሬሽን ሲፈርስበት የበለጠ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ብለው የሚያልሙ ሰዎች የማሰብና የማስተዋል ችግር የተሳናቸው ናቸው (አክሊሉ ባዮግራፊ፤ 2003፤157) በተመሳሳይ መልኩ አክሊሉ ኃበተ ወልድ የኤርትራ ውህደቱ ከጥንስሱ ጀምሮ ጊዜው ያልጠበቀና ብዙ መዘዝ የሚያመጣ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልፀዋል፡፡ ንጉሱ በ10 አመት የኤርትራ ፌዴሬሽን ቆይታ ፌዴሬሽን አደረጃጀቱና ቃሉ ጭምር ፈፅመው የማይፈልጉትና የተለያየ ስም እየሰጡ ሲያጣጥሉት ነበር ይህም ፌዴሬሽን መጤ ነው፤ ፀረ አንድነት ነው፤ መለያየት ያመጣል ወ.ዘ.ተ ነበር ፡፡ ሆኖም መለያየት ያመጣው ፌደሬሽን ሳይሆን ሁሉም በመጨፍለቅ አንድ ኢትዮጵያ የሚለው ንጉሳውያን፤ ደርጋወያንና የንጉስ አብይ(አሃዳዊ ) አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ አሁንም እየሆነ ያለው ከንጉሱ ድርጊት ተመሳሳይ ነው የፈደራል ስርአት በማፍረስ ሁሉም ብሄር በሄረሰብ ቀስ በቀስ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ እንዲሆን በማድረግ የበለጠ ኢትዮጵያዊ ይሆናል የሚል አሀዳውያን አስተሳሰብ ነው፡፡

ንጉስ አብይና የህብረ ብሄራዊ ፈዴራሊዝም ስርአት

         ንጉስ አብይ ወደ ስልጣን እንደ ወጣ ቅድምያ ስጥቶ ሲሰራው የነበረ የቤት ስራ የፈደራል ስርአት፤ ብህር ብሄርሰብ፤ ህበረ ብህራዊ ፈደራሊዝም ማጠልሸት፤ የብሄር /የዘር/ፖለቲካ ይታገድ እያለ ቃላቸወን እንካን በተደመሩ የአሀዳዊ ሚድያ እንዳይነሳ አድረገዋል፡፡ ንጉሱ የኤርትራ ፈደራሽን ለማፈረሰ የተጠቀሙት መንገድ ተመሳሳይ ነበር ፡፡

         ንጉስ አብይ ህብሪ ብሄር ፈደራሊዝም የማጣጣል ዘመቻ ቀጥሎ ያደረገው ነገር ቢኖር በህገ መንግስት የተደራጁት የክልል መንግሰታት ለማፈረስ ፈደሬሽን አደረጃጀት ለመቀየር የማንነትና የወሰን ኮሚሽን አዋጅ አወጣ ፡፡ በዚህ መሰረትም በአዋጁ የአ/ር ክልል ልክ እንደ አሃዳዊ ወደ የአ/ር ወሰን ብሎ ቀየረው ፤ የክልል ፕረዚዳንቶች ኦቦ ለማን ጨምሮ ከትግራይ በስተቀር ሁሉም በቀጭን ትዕዛዝ ከስልጣን አንስተዋል ልክ እንደ ንጉስ ኃ/ስላሴ የኤርትራ ፌዴሬሽን አመራሮች ጠራርጎ በማወረድ በስልጣን በመደለል አዳዲስ ሰዎች የተኩት፡፡ ንጉስ ኃ/ስላሴም ፌደሬሽን ላይ የማጥላላት ዘመቻ ካከናወኑ በኃላ ያደረጉት ነገር ቢኖር የኤርትራ ፈዴሬሽን አጠራር ወደ ጠቅላይ ግዘት መቀየር ነበር ፡፡

         ንጉስ አብይ ህብረ ብሄር ፈደራሊዝም ለማዳከም ከወሰዳቻው እርምጃዎች ውሰጥ በትምህርት ፍኖተ ካርታ ስም ልክ እንደ አሃዳዊ ስርአት ሁሉም ክልል ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ በአማርኛ እንዲማሩ ወሰነ፤ የፈደራል ስርአቱን የሚቃወሙ አካለት ካሉበት እየተፈለጉ በመንግስት ሚደያ ፀረ ፈዴራል ስርአት ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ ፤በአዲሱ ብልፅግና ፓርቲ ደንብ ደግሞ ሁሉም ክልል አማርኛ ሁለተኛየስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰነ(አማርኛ ብለው ባይፅፉቱም ትርጉሙ አማርኛ ነው መሸዋወድ አያስፈልግም )፡፡ ንጉስ ኃ/ስላሴ የተጠቀሙበት አካሄድ የኤርትራ ፈዴሬሽን አመራሮች ስልጣን በመሰጠትና በማሰፈራራት ፤ የፈደራል ስርአት መገለጫ ሆኑትን ራሰን በራስ የማስተዳደር ና በቋንቋን መጠቀም ቀስበቀስ እየሸረሸሩ መጨረሻ የፈደራል ስርአቱ ያፈረሱት አሁን ንጉስ አብይ እያደረገ ያለውም ከንጉስ ኃ/ስላሴ ቀጥታ ቅጂ (copy paste) ነው::

 

         በመጨረሻ ንጉስ አብይ ፈደራል ስርአቱ ሲያጣጥል ከርሞ የማፍረስ ጊዜው ሲደርስ ኢህአዴግ በማፈረስ ስም ቁጥር ሁለት ኢዜማ ብልግና ፓርቲ ያደራጀው ፡፡ ኢህአዴግ የማፍረስ /ማዋሀድ/ሂደት ልክ እንደ ንጉስ ኃ/ስላሴ ኤርትራ ፌዴሬሽን የማፈረስ ሂደት በጥድፍያ በአንድ ቀን ጨረሰው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የብልግና ፓርቲ ፕሮገራምና ደንብ እንካን ሳይዘጋጅና ውይይት ሳያደረግ ልክ እንደ ንጉሱ ለማዋኃድ ና አኃዳዊ ስርአት ለማወጅ በአንድ ጀምበር አለቀ፡፡የአሁኑ በየበታው እየታዩ ያሉት የብልግና አሃዳዊ/ፓርቲ/ ስብሰባዎች ከፈረሱ ጋረው ቀደመ አይነት ነው ፡፡

         ንጉስ አብይ የቅርብ ሰዎቹን የነ ኦቦ ለማ ምክር መስማት ትቶ የሁሉም ነገር መለክያ ስልጣንና ስልጣን ብቻ በመሆኑ ከመረጠው የኦሮሞ /ኢትዮጵያ ህዘብ ጥቅም አፈንግጦ አየር ላይ ቀርተዋል አገሪትዋም በኮማንድ ፖስት ስር አድርጋታል ፡፡ ንጉስ ኃ/ስላሴ በተመሳሳይ ቀኝ እጃቸው የነበረው አክሊሉ ኃብተወልድ ምክር መስማት ትተው ፌዴሬሽን ስርአት ለመለኮታዊ ለስልጣኔ አደጋ ላይ ይጥላል ብለው አገሪትዋም ራሰቸውም አደጋ ላይ ወደቁ፡፡

         አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ በህገ መንግሰት የተሰጠውን ፌዴሬሽን ስርአት በውህድ ስም ሲቆረሰበት የበለጠ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ብለው የሚያልሙ ሰዎች የማሰብና የማስተዋል ችግር የተሳናቸው ናቸው፡፡ንጉስ አብይ ህብረ ብሄር ጨፍልቆ አዲስ ኢትዩጵዊነትና የበለጠ ኢትዮጵያዊነት እያለ የሚሰብከው ተረት ተረት ውስጡ ልክ እንደ ንጉስ ኃ/ስላሴ አሃዳዊና ጨፍላቂ ነው፡፡

         ንጉስ አብይ 21 ወራት ብሄር ብሄረሰብ ፤ ህበረብሄራዊ ፈዳራሊዝምና የኢፊደሪ ህገመንግሰት ራሱ ሲያጣጥል ከርማል፡፡ የተደመሩ ሚድያዎችም ሁሉም ልክ እንደ ኢሳት በነዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አወንታዊ ነገር እንዳይነሳና የማጥላላት ዘመቻ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፎ ሲያበቃ አሁን አሃዳዊ መሆኑ በግላጭ ከነገረን በኃላ በብሄር ብሄረሰብ ቀን ማክበሩ ለብሄር ብሄረሰብ ንቀት ነው ደግነቱ አሁን የሱ ማስመሰል የሚሰማ ሰው የለም፡፡

         ንጉስ አብይ አሃዳዊ አገዛዝ/አሃዳዊነት የጀመረው አሁን በበልግና ፓርቲ አይደለም ወደ ስልጣን በወጣ ማግሰት ነው ፡፡ የፈደራል መንግስት የመሰረቱት ክልሎች መሆናቸው ቀርቶ ንጉስ አብይ በይፋ አመራሮችን ከስልጣን ውረድ እያለ ፤ እያሰረ ፤ እያስፈራራ፤ በኦሮሚያ ደግም በተንኮል ፖለቲካ ኦቦ ለማ ወደ ፈደራል በማግለል የኦሮሚያ መዋቅር አሃዳዊ ሀይል እንዲቆጣጠረው አደረገ፡፡ ስለሆነም የአሃደዊ ስርአት /ውህድ ፓርቲ/ እንቅስቃሴና ውሰጥ ለውስጥ ማሰፈራራት የተጀመረው ኦቦ ለማ ከኦሮሚያ ክልል በተነሱ በማግሰቱ ነው፡፡

         አሁን ደግሞ የውህደቱ ዋና መሀንዲስ አዴፓ/አብን መሆናቸው ራሰቸው እየገለፁ ነው፡፡ እነዚህ አካለት ደግሞ ከልውጡ ማግሰት ጀምሮ ሲከናውኑት ከነበሩት ተግባራት ውሰጥ ህገመንግሰት ይቀደድ፤ ፈደራል ስርአት በጂኦግራፊ ይሁን፤ የብሄር ፖለቲካ ይታገድ ፤ ኢ-ህ ገ መንግሰታዊ የወሰንና ማንነት ኮሚሽን አዋጅ ማወጅ ፤ የሁሉ ችግር ህገ መንግሰት ብሎ መስበክ ፤ በክልሉ ውስጥ ና በአጋራባች ያሉ ብሄረሰቦች በጉልበት መጨፍለቅ፤ ማፈናቀል፤ በጅምላ መግደል ወዘተ፡፡ እነዚህ ጨፍላቂና አሃዳውያን ቡዱን ያደራጁት አሃዳዊ ፓርቲ እንዴት ህብረ ብሄር ፈደራሊዚም ያራምዳሉ ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ታድያ ንጉስ አብይ እንዴት የዚህ አሀዳዊ ና ብዝህነትን የማይቀበል ጨፍላቂ ፓርቲ ግንባር ቀደም መሪ ለሆኑ ቻለ የሚል ጥያቄ ያለው ሰው ካለ የንጉስ አብይ የ21 ወራት እንቅስቃሴው ምን ይመስል ነበር ህብረ ብሄር ፈደራሊዝም ወይሰ አሀዳዊ/ጨፍላቂ መለስ ብሎ ማየት ነው፡፡

አሁን ንጉስ አብይ የጥድፍያ አካሄድ የኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ነው ወይስ አዲሰ ፓርቲ? የኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ለመባል የሚያስችል ይዘትም ቁመናም በፍፁም የለውም፡፡ አልፎ ተርፎም የብልግና ፓርቲ አመራሮች መሾም ጀምሮል ስለሆነም አሁን ስልጣን ላይ ያለው የብልግና ቡዱን አገር መምራት አይችልም፡፡ የምርጫ ቦርድ በበላይነት በኢዘማ ስለሚመራ ብልግና ፓርቲ ቢመዘገብም በንጉስ አብይና ፓርቲው ቁቡልነት ምንም ለውጥ አይመጣም ፡፡

ሲጠቃለል ቀጣይ የንጉስ አብይ ዕጣ ፈንታ እየሆነ ያለው ከህዘብ ተነጥሎ እንደ ባሎን አየር ላይ መንሳፈፍ ነው ፡፡ የተቀሩትም እስርና ዕንግልት ፈርተው፤ ስልጣን ዘላቂ መስላቸው ነው እንጂ የልጆች ጨዋታ መሆኑ ያውቁታል፡፡ ሆኖም ፖለቲከኛ ማለት ለሆድ ማደር አይደለም ያለመንበት ጉዳይ የሚቃወም፤ ለለውጡ ምክንያት የሆኑት የህዘቦች ጥያቄ ለመመለስ አስፈላጊው መስዋእትነት የሚከፍል እንጂ ሳይገባው የሚደመር፤የሚወሃድ፤የሚደግፍ፤የሚያስተጋባናሳይወያይ የሚቀበል ማለት አይደለም፡፡አሁንእየመጣ ያለው ቡደን የፖለቲኮኞች ስብስብ ሳይሆን የአሳማዎች ስብስብ ለመሆኑ የሚጠራጠር ሰው ያለ አይመስለኝም ፡፡

 

Back to Front Page