Back to Front Page

ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉበኝ

ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉበኝ

ከዘመድኩን ዘሪሁን (ከአዲስ አበባ) ፤

5-8-19

ታሪክ ወደ ሃላ መለስ ብለን የምናው ተመሳሳይ ስህተት ላለመድገም ነው፡፡

እነዚህ ሁለት ሰዎች በብዙ መንገድ ይመሳላሉ ፡፡ በአገራቸን የቅርብ ጊዚ ታሪክ ወደ ሃላ መለስ ብየ ለማየት የሚያስገድዱ ክስተቶች እየተፈጠሩ ናቸው፡፡ እኔም ያለፈው ታሪካችን ወደ ሃላ መቃኘት ጀመርኩና የሁለት ሰዎች ብዙ ነገር ተመሳሰለብኝ ፡፡ እነዚህ ሁለት ሰዎች ተራ ሰዎች አይደሉም በታሪክ አጋጣምሚ ወደ ኢትዮጵያ ስልጣን መንበር በድንገት ሳይጠበቁ ብቅ ያሉ ናችወ፡፡ እነሱም ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ሀ/ማርያም እና ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድ ናቸው ሌላው ቀርቶ በወታደራዊ ማዕርጋቸውም ይመሳሰላሉ ፡፡ ምን ከምን አገናኛቸው የሚል ሃሰብ አይጠፋም ፡፡ ለማንኛውም የሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ባህረርያት በወቅቱ አዋቂ የነበርን ሰዎች ወይም ከታሪክ በተለያየ መንገድ የተረዳን ብዙ ስለሆንን ታሪኩም የቅርብ ጊዜ ትዝታቸን ስለሆነ ጠንቅቀን የምናውቅ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ አንፃር የአሁኑ መሪ ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድ ባህርያትና አካሄድ ከሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ለኔ በጣም እየተመሳሰለብኝ ነው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ንግግራቸው፤ ቁጣቸው፤ ማሰፈራራታቸው፤ ፍረጃቸው፤ ጭብጫባና ሙጎሳ መውደዳቸው ፤ አኔ ማላታቸው ፤በንግግር ወራፊ መሆናቸው፤ ሁሉም አቃሎህ ባይነታቸው፤ አለባሰቸው ሳይቀር( ሲፈልጉ ወታደራዊ ስፈልጉ ሲቨል) ፡

ለመግብያ ይህን ከጠቃቀስኩ የሁለቱም ኮሎኔሎች ሁኔታዎቹና ባህሪያቶቹ አንድ በአንድ ለማቅረብ እሞክራሎሀ ሆኖም አንባቢ ሊረዳኝ የምፈልገው በቁም ነገሩ እንጂ መስትዋታዊ ወይም ካረቦን ቅጂ/ኮፒ/ በሆነ ሁኔታ አይደለም ንፅፅሩ ፡፡ በተጨማሪ እንደ ሰው /መሪ /ሌሎች የሚያለያያቸው እንዳተ ጠበቀ ነው፡፡ ለኔ ግን እየተመሳሰሉብኝ ስለሆነ ተመሳሳይነታቸው አቅሪቤ አሎህ ፍርዱ ለአንባቢ ትቻሎህ፡፡ የሚገባቸው ክብር እንደ ተጠበቀ ሆኖ ለመፃፍ እንዲመቸኝ ለሁለቱም አንተ የሚለው ቃል ተጠቅሜሎህ፡፡

Videos From Around The World

1.  ወደ ስልጣን አወጣጥ፡-ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ስልጣን የመጣው በድንገት ሆኖ በተደረጉ የደርግ ስብሰባዎች ወቅታዊና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር በማድረግ ጎልቶው የወጡ ናቸው ፡፡ ይህ እንደ መስፈንጠርያ ተጥቅመውና ውሰጥ ለውስጥ ቅሰቃሳ አድርገው ሁኔታዎችን በማመቻቸት በፊት ተሰልፈው የነበሩተ ብ/ጄ ተፈሪ ባንቲ አጥናፉ አባተ በብልጠት በማሰወገድ ወደ ስልጣን ተቆናጥተዋል ፡፡

ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድም ወደ ስልጣን አመጣጣቸው በድንገት ሆኖ በየመድረኩ በሚያደርጋቸወ ወቅጣዊ አና ስሜት ቀስቃሽ ቅስቀሳ ጎልቶ የመውጣት እደሉ አገኙ ይህ እንደ መስፈንጠርያ ተጥቅመው የኦህዴድ ም/ሊቀመንበር ፤የም/ቤት አባልና ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የነበሩት ዶ/ር ውርቅነህ ገበዮህ ሲጠበቁ ተራ ማዕከላይ ኮሚቴ የነበሩት ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድ በመድረክ ተናጋሪነታቸው ፤በብልጣ ብልጥ አካሄዳችውና ውስጥ ውሰጡ ዋና ለተባሉት ሰዎች የተሻለ የለውጥ አራማጅ መስለው በመታየተቸው ለዚህም ሆን ብለው በመስራታቸው ከማሃል ሜዳ ተንስተው እያታለሉ በአጥቂ መስመር የነበሩትና ለጠ/ሚስተር ስልጣን በቡዙ መመዘኛ ቅድምያ የነበራችው ዶ/ር ወርቅነህ አልፈው ሳይጠበቁ ግብ አስቆጦሩ፡፡ ከተራ ማዕከላዊነት ወደ የኦህዴድና ኢህአዴግ ሊ/መንበርነት ቀጥሎም ጠ/ሚኒስተር ስልጣን በአንዴ ተቆጣጠሩት፡፡

2.  በመጀመርያ የስልጣን ወቅት፡- ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ተከታታይ በሆነ ሁኔታ ስሜት ቀስቃሽ ውይይቶች፤ ስብሰባዎች ለወዛደሩ፤ለገበሬ ማህበር፤ ሴቶች ማህበር ፤ወጣት ማህበር፤ ለመምህራን ማህበር ፤ ለከተማ ነዋሪች ማህበር ፤ ለካድሬው ፤ለውታደሩ ወዘተ በምክንያት መድረክ እየፈጠረ ማርከሲዘም ሌኒነዝምና የአብየቱ ፍሬዎች እያለ ሰበከ ራሱን የኢ/ያ ቆራጥ መሪ እና ከሁሉም የተለየ አዋቂ አድርጎ ለመሾም አድል አገኘ፡፡ አጫፋሪዎቹ ዘፈኑለት ህዝቡም አጨበጨበ መጨረሻ አይኔኬ ሁኖ ቁጭ አለ ህዝቡም በንንግሩ ብቻ ሰማይ ሰቀለው ቅፅል ስሙም ቆራጡ መሪያችን ሆነ ቀጥሎም ለህዘቡ ቆራርጦ ጣለው ፡፡

ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድ በመጀመርያ የሥልጣን ወቅት ልክ እንደ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ እጅግ ተከታታይ በሆነ ሁኔታ ሁሉም ክልሎች እየዞረ ስሜታቸውን የሚኮሮኩሩ ቅስቀሳዎች አደረገ ቀጥሎም የተለያዩ ህ/ሰብ ክፍሎች በተመሳሰይ መልኩ ስሜት መቀስቀስ ጀመረ ከፍተኛ ድጋፍም አገኘ ፡፡ ሁሉም ቀስቅሶ ሲጨርስም የፈለገው መልዕክት ለማሰተላለፍ በቻ እንዲመቸው ድንገት የሆነ አካል ይጠራና ራሱን ከፍ የሚያያደርግ

መልዕከት በቅስቀሳ መልክ ያስተላልፋል አንዳንዶቹ ከሙሴ እኩል አደረጉት አሱም በድፍረት ተቀበለው፡፡

መድረክ እንካን ቢጠፋ ባልተለመደ መልኩ የሃይመኖትና ባህላዊ በአላት የፆም መግብያ ሳይቀር የመደመርና ፍቅር ያሽንፋለ ዲስኩር/ስብከት ለማሰረፅ ተጠቀመበት፡፡ ቀስበቀስ ግን የሰበካ ቃለት በቁጣ፤ በማስፈራራት ፤በስደብ/ተረብ/ና በትርፍ ቃለት እየተተኩ ሄዱ ያው ተመሳሳይ እንደ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ፡፡

3.  የተመረጡ መፍክሮች ደጋግሞ ማሰተጋባት ፡-ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት ፤ ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም አቆርቃዥ ይውደም የሚል መፈከር ያስተጋባ ነበር ፡፡ ሆኖም በየቀኑ ሰወ አገር ጥሎ እየሄደ ፤ እየተገደለና እየተረሸነ አገር ሁሉ ደም በደም ሆኖ በእብሪት ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም የሚል መፈክር ያስተጋባል ፡፡ በወቅቱ ደም የማይፈስበት መንገድ ከመፍጠር ይልቅ አራምባና ቆቦ የሆነ ባዶ ጭሆት ይስተጋባ ነበር፡፡ ካደሬውም አጫፋሪውም እንደ ገደል ማሚቶ ይህን መፈከር እያስተጋባ አብዮት ልጅዋን ትበላለች እያሉ ሞትን አቀለሉት፡፡ ህ/ሰቡም ነገሩ ሁሉ ተገላብጦበት በአግራሞትና በስጋት ይከታተል ነበር፡፡ሊፈፀም የማይችሉ መፈክሮች በማሰተጋባት በአጭር ጊዜ አገሪተዋ ገነት አንደምተሆንና ጠላቶችዋ በሙሉ እንደሚወድሙ ሲሰብክ ነበር፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ኢ/ያ በህብርተሳባዊነት ተለመልማለች፤ማይመነት፤ደንቁርና ርሃብ ይውደም፤ ኢመፔርያሊዘም ይውደም ወዘተ. ያው ያኔ ሁሉም ነገር ይውደም ነው፡፡ አልፎ ተርፎም አድሃሪን በቻ ሳይሆኑ ተፈጥሮም በቁጥጥር ስራችን እናደርጋለን በማለትም ያስተጋቡ ነበር ፡፡ የሃላ ሃላ ግን በመፈክርና በስሜት የሚሆን ነገር የለምና ሶሻሊዝም ወድሞ አለም የኢመፔርያሊዝም ሆና ቁጭ አለች፡፡

ሌ/ኮሎኔል አብይ አህመድ ልክ እንደ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ለወቅቱ ይሆናሉ ያላቸወን ባዶ ቃላቶች/መፈክሮች በመምረጥ ያለ ማቀረጥ ቀሰቀሰ ፡፡ ቃላቶቹም እስኪ ሰለቹን የሰመናቸው መደመር እና ፍቅር ያሸንፋል የሚሉ ናችወ፡፡ ይህም በተመሳሳይ መልኩ ወደ ስልጣን እንደ ወጣ መጀመርያ ወር ጀመሮ መደመር ሳይሆን ሞት ፤ መቁሰል፤ መንገላታትና መፈናቃል በብርሁን ፍጥነት ሊባል በሚችል መልኩ በየቀኑ የስው ሂዎት እየተቀነሰ የመደመር እና ፍቅር ጉዞ እያለ ይደሶኩራል፡፡ ይህ በስወ ቁስል እንጨት ስደድበት የሆነ አካሄድ አሁንም ድረስ እየቀጠለ ነው ፡፡ ካደሬዎቹም፤ አጫፋሪዎቹም የራሱ ሚዲያዎች ጨምሮ ከዚች አለም እየተቀነሱ ያሉ ዜጎች ከማውራት ይልቅ አንድ ቃል በተናገሩ ቁጥር ሃሰቡ ቢገናኝም ባይገናኝም የማይጨበጥና የማይዳሰስ መደመር እና ፍቅር ያሸንፋል እያሉ ሰው ያደነቁራሉ ፡፡ አልፎ ተርፎም የዜጎች ሞትና መፈናቃል የለውጡ አንድ አካል ነው ይሉናል፡፡ ልብ ብሎ ለተመለከተው ልክ አብዮት ልጅዋን ትበላለች የሚለው የአብዮቱ ዘመን አባባል መሆኑ ነው ፡፡ ህ/ሰቡም ነገሩ ሁሉ ተገላብጦበት በአግራሞትና በስጋት እየተከታተለ ይገኛል ፡፡ በአግራሞት የምንሰማወ የሶርያ ዜና ሰተት ብሎ አገራቸን ገባ ሌ/ኮሎኔል አብይም ያለው ችግር መርምሮ ከመፍታት ይልቅ በተመሳሳይ የማይጨበጡ ተስፋዎች በመደርደር ጊዜ መግዛት ይታያል ፡፡

4.  ፍረጃ አብዩቱ ያለደገፈ ፀረ አብዮት ነው፡፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ በማንኛውም ንግግሩ የማትጠፋው ፀረ አብዮት የሚለው ነው ፡፡ ይህም የአብዮቱ ጉዞ ፤ አቅጣጫ፤ መነሻና መደረሻ ግልፅ ያልሆነላችወ ብዙ ዜጎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የሚያነሱት ሃሰብና ጥያቄ ፀረ አብዮት ብሎ በመፈረጅ ፡፡ በአስተዳደሩ ያጋጥሙ የነበሩ ችገሮች በሙሉ የፀረ አብዮቶኞች ሴራ በማለት ሲፈረጅ ኖራል በመጨረሻም የሆነው አይተናል፡፡

ሌ/ ኮሎኔል አብይ አህመድ ም ልክ እንደ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ መንገዱ ፤ አቅጣጫው፤ መነሻናውና መደረሻ ግልፅ ያልሆነ መደመርና የፍቅር ጉዞ የሚባል ተረት ተርት ፤ ምን ማለት ነው? ፤ ምን ማለትስ አይደለም ብሎ የጠየቀ ሁሉ የለወጥ አደናቃፊ ፤ ያልተደመረ ፤ አሻጥርኛ ፤ ጥቅሙ የተነካበት ወዘተ ማለት ይታያል፡፡ ጠ/ሚ በመጀመርያ ንግግራቸው ውሰጥ ጅምላ ፍራጃ ይቁም እንዳላሉ አሁን ቁጥር አንድ በጀምላ ፈራጅ ሆነዋል ፡፡ በየአከባቢው እተከሰቱ ያሉ ግጭቶችም በዘላቂነት መፈትሄ ከማበጀት ይልቅ ቀላሉና ስራ የማይጠይቀው የለውጥ አደናቃፊዎች፤የታጠቁ ሃይሎች የፈጠሩት ነው ብሎ መፈረጅ የአመራሩ መለያ ባህሪ ሆናል ፡፡ ኢህአዲግ የተለያዩ ስሞች እየለጠፈ ጠላት እንዳበዛ ይህም ተመሳሳይ ጠላት ከማብዘት ወጪ የሚያመጣወ ለውጥ የለም፡፡

5.  ጋዶኛች ወደ ስልጣን ማምጣት/ሲንየሮቸን ማሰወገድ ፡ ፡፡ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ስልጣን እንደ መጡ መጀመርያ ያደሩገት ነገር ቅርብ ጋደኞቻውና ወዳጆቻቸው ወደ ቁልፍ ስልጣን ማምጣት ነበር፡፡ ሌ/ጄ አማን ዓንዶም ፤ሃምሳለቃ ለገሰ ጨምሮ ሌሎች ከመስራቅ እዝ የመጡ፤ የሆለታ ገነት ምሩቃን ፤ ኮረስ ሜታችወና ሌሎች ወደሳቸው መስመር ቶሎ የተደመሩ አቅማቸው የፈለገ ይሁን እጅግ በርካታ ስው ሾሙ ያልተደመሩት በምክንያት በእስርም በግድያም ቀነሳቸው፡፡ ከነዚህ የቅርብ ወዳጁ የነበሩት ሌ/ጄ አማን አንዱ ናቸው ፡፡ በተጨማሪም ቀስ በቀስ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ በደርግ የነበሩት ከሌ/ኮሎኔል ማዕረግ በላይ በተለያየ ታክቲክና በግደያ በማሰወገድ ከ108 የደርግ አባል የመጀመርያው ሴንየር ሻለቃ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ ከ60 በላይ የሚሆኑት የደርግ አባላት ከም/መ/አ (መኮንን) በታች ነበሩ ለዚህም ነው ሌ/ጄ አማን አስር አለቃና አምሳ አለቃ ተይዞ አገር አይመራም ያሉት ፡፡ የተቀሩትም ውሰን ሻላቆችና ጂንየር መስመራዊ መኮንን (መ/አ እና ሻመበል) ነበሩ፡፡ በዚህ ሁኔታም የደርግ ም/ቤት፤ የሚኒስተሮች ም/ቤትና ስራ አስፈፃማው ሁሉም ከሌ/ኮሎኔል መንጉስቱ በታች ሆኑ በመቀጠል አገሪተዋ አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቁጭ አለ ፡፡

 

ሌ/ኮሎኔል አብይ ወደ ስልጣን እንደ መጡ መጀመርያ ያደሩገት ነገር ቅርብ ጋደኞቻውና ወዳጆቻቸው እያፈላለጉ ሽመት ሰጥተዋል ፡፡ ይህም ኢንሳ የነበሩት ጋዶኖቹ አቅማቸው ምን ይሁን ምን ስለተደመሩ ብቻ ወደ ከፍተኛ ሃላፊነት መጥተዋል ለምሳሌ ሻለቃ ተመስገን መጀመርያ የኢንሳ ሃላፊ አሁን የጠ/ሚ የደህንነት አማካሪ፤ ብ/ጄ አህመድ ሃምዛ የሜቴክ ዋና ዳሬክተር፤ ኮ/ል ዛጊር ሚኒስተር ዴኤታ፤ ሌ/ኮ አብርሃም (ዶ/ር) የኢ/ያ መብራት ሃይል ዋና ዳሬክተር ሌሎቸም ከኢንሳ የተሾሙት በርካታ ናቸው፡፡ ሌ/ኮሎኔል አብይ ወደ ስልጣን እንደ ወጡ የመጀምርያ እስር የጀመሩትም ባለመደመሩ ብቻ ለቀጣይ አደገኛ ነው ብለው ሰበብ ፈልገው በኢንሳ እያሉ የቅርብ ወዳጃቸውና ጋደኛቸው የሆነውን ሌ/ኮ ቢንያም ነወ ፡፡ በተጨማሪም ከአዲስ አባበ ዩኒቨርሰቲ ሲማሩ ያፈርዋቸው በርካተ ጋዶኞቻው በሚ/ር ዴኤታና፤ዋና ዳሬክተር ናፕረስ ስከሬታሬያት ቦታ ሾመዋል ፡፡

በመቀጠል ሌላ ከሌ/ኮሎኔል መንግስቱ የሚያመሳስላቸው ጉዳይ ያደራጁት ካቤኔ ነው፡፡ ሁሉም ሊባል በሚችል ሁኔታ ነባርና ልምድ ያላቸው ሚኒስተሮች የሴቶችን ተሳትፎ 50 ፐርሰንት ለማድረግ በሚል ሽፋን የተውሰኑ ካልሆነ በቀር የፖለቲካም የአስተዳደርም ልምድ የሌላቸው ሴቶች ሞሉት ይህም ብዙ ተዘመረለት፡፡ በተጨማሪም ወንድ ሚኒስተሮችም በተመሳሳይ አዳዲስ ናችው፡፡ በድመሩ ሲታይ የአገሪቱ ከፍተኛ ጉዳየች የሚወሰንበት ም/ቤቱ ሙሉ በሙሉ ከሌ/ኮሎኔል አብይ የፖለቲካ ጉልበትና ተሰሚነት ፤ ልምድና እወቀት ከኔ በታች ናቸው ብሎ ያሰባቸው ካቢኔ አደራጀ ፡፡ አሁን በቅርቡ ሁለት የፖለቲካ ብትር ያለቸው ሰዎች ፈደራል መንግሰት ለማገዝ በሚል ገብተዋል ለቀጣይም የፖለቲካ ተሰሚነት ያላቸው አካላት አየተተካ እንደሚሄድ የታወቀ ነው፡፡ ምክንያቱም አካሄዱ ስራ ሳይሆን ስራ የሚመስል ነገር እየፈጠሩ መሄድ ነው ፡፡ ቢሆኑም ተቃማዊ አሰራር ካልተበጀለት በስተቀር ብዙ ለውጥ አይመጣም ፡፡

6.  ሚዲያ እንደ ፕሮፓጋንዳ መሳርያ ፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ በስልጣን ቆይታው በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ግጭቶች፤ ርሃብ፤ ተቃውሞዎችና ቅሬታዎች እያሉ ወደ ሚደያ ምንም አይቀርብም፡፡ሚድያው ስለ ጋድ መንግስቱ ታላቅነት፤ አብዮታዊነትና ቆራጥነት ይሰበካል ፡፡ ይህ የአምባገነን መሪዎች ባህሪ መገለጫ ነው ምክንያቱም ሚድያዎች ዋና ስራችወ የህዝቡን ድምፅ ሳይሆኑ የግለሰብ ዝና መካብ ስለሆነ ነው ፡፡

ሌ/ ኮሎኔል አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በየቀኑ ሊባል በሚችል ሁኔታ በርካታ ሰው በግጭት እየሞተና እየተፈናቀለ ምንም ሚድያ ሽፋን የለም፤ እርደታም በወቅቱ የሚሰጥ የለም ፤ ጠያቂ የመንግስት አካልም የለም ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ሚዲያዎቹ የ100 ቀን ለውጥ ፤ የ120 ቀን ለውጥ ፤ የ100 ቀን የሚነስተሮች ሪፖርት ወዘተ ምክንያት እየፈጠሩ ስለ ሌ/ ኮሎኔል አብይ ታላቅነት ብቻ ይሰብካሉ፡፡

ይባስ ብሎ ደግሞ ከመጋቢት አስከ መጋቢት የለውጥ ጉዞ ብሎ የራሱ ፎቶ አውደ ራዒ ሲጎበኝና ሲያስጎበኝ መዋሉ ለትዘበት ጥሎታል ፡፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱም አምባገነንነትና እኔነት የጀመረው እንዲህ ብሎ ነው ሚድያው የህዝብ ድምፅ ሳይሆኑ ምክንያት እየፈለጉ ስለ አሱ በቻ እንዲሰብክ ማደረጉ ነው ፡፡ አሁንም ተወደደም ተጠላም በወቅቱ ካልተስተካከለ በቀር እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ነው ፡፡

7.  ወታደራዊ ትርዒትና ማስፈራራት፡ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ስልጣን እንደ መጡ ትልቁ መመክያቸውና ማሰፈራርያቸው ጦር ስራዊቱ ነብር፡፡ ይህም ወታደራዊ ትርዒት በማዘጋጀት ተቃዋሚ ማሰፈራት/deter/ በማድረግ ተቃዋሚዎች ለውይይት ከመጋበዝ ከጅምሩ ጀምሮ በጉልበት ለማሰፈራት ከአፍሪካ አለ የተባለ ሰራዊት ገንብተናል እያንዳንደሽ ወይ የለሽ አይነት ዛቻ ነበር ይህም እፍኝ የማይሞላ ወንበዴ፤እዚህ ግባ የማይባል የኢህአፓ ርዥራዥ ወዘተ ተጠቃሽ ናችወ ፡፡ የመግደል ሙኮራ ተደርጎባቸው ትንሽ ቆስለው ነበር፡፡ ኮሎኔሉም ከመጀመርያ ህከምና በሃላ ቴሌቨዝን ቀርበው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ቀጥሎም ከዛ በፊት ለፀረ አብዮት ጀምረውት የነበረ ማስፈራራትና ዛቻ አጠናክረው ቀጠሉበት መጨረሻም በምን እንደተጠናቀቀ ሁላችን የምናቀው ነው ፡፡

 

ሌ/ ኮሎኔል አብይ ወደ ስልጣን እንደ መጡ በሰኔ ወር በመስቀል አደባባይ የፈነዳ ቦምብ ከሳቸው በሩቅ ርቀት ቢፈነዳም መጥፎ አጋጣሚ ነበር፡፡ ቀጥታ ቴሌቨዝን ቀርበውም ገና ማጣራት ሳይደረግ እርምጃ እንድንወሰድ እያስገዳዳቹሁን ነው በማለት ዛቻና ማስፈራራት ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ቀን በሃላ ኮሽ ባለ ቁጥር ማስፈራራቱ በራሳቸውና በተከታየቻቸው ቀጠለ፡፡ በተደጋጋሚ ሰዎች ነን እርምጃ ለመውሰድ እንገዳደለን ፤ ኦነግ አዲስ አበባ እንደ ገባ ገና ከመንግሰት ሰጣገባ ሳይገባ ሆን ብለው ከወጭ የመጡ ታጣቂዎቸን ለማሰፈራራት መንግሰት ከነ ሙሉ የስራዊት አቅሙ ነው ያለው ፡፡ ሁላቸሁም ተደመራቹህ ስራዊታቸሀ 10 ሺህ አይሞላም በማለት የማሰፈራራት መልእክት ነው ያስተላለፉት፤ የቤተ መንግሰት ጥበቃ ፕረዚደንሻል ጋረድ ብሎ በመሰየም በቤት መንግሰት የኢላማ ተኩስና ሌሎች ትርዕት ተደርገዋል ሌ/ ኮሎኔል አብይ እንደ ሌ/ኮ መንግሰቱ ዩኒፎረማቸው ለበስው ትረዕቱ ተመልክተውታል ፡፡ የፕረዚደንሻል ጋረድ አዛዥ ብ/ጄ ብርሃኑም የትርዒቱ አላማ ሲገልፁ ምናልባት ተንኮል የሚያስብ ካለ ለማስንጠቀቅ ነው ብለዋል የተለመደው የማፈራራት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ ተከትሎም ም/ጠ/ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ የአለቃቸው ንግግር ጎላ ባለ መልኩ ለኦነግ ለማስፈራራት እንካን አሁን በመቶ የሚቆጠሩ ሰራዊት ይዞ በሽግግር ወቅት እንካን 30 ሺህ ጦር ይዞም ምንም አላመጣም ሲሉ በሚዲያ ተደምጠዋል፡፡ የዘነጉት ነገር ግን ይህ ችግር በድርደር ካልተፈታ በመቶ የሚቆጠሩ ብሎ የኦነግ ሰራዊት ማሳነስ በሃላ እዳ ያስከፍላል እያስከፈለም ይገኛል ፡፡ ይህ ከጅመሩ ሁሉም በወታደራዊ ሃይል የመፈታትና የመጨፍለቅ ፍላጎት እንዳለ ያሳያል፡፡ ከዚህ ማስፈራራቶች በሃላም በወለጋ የነበሩ አወዘጋቢ ውግያች የዚህ ማሰያ ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መንግስት ቢያስተባብልም ተዋጊ ሄሊካፕተር ተጥቅመዋል የሚል ክስ ሲቀርብ ነበር ፡፡

በሌላ መልኩም ከኦነግ ትጥቅ መፍታት ጋር ተያይዞ ከመንግሰት ጋር አለ መግባባት ሲጀመር በወቅቱ መንግሰት ኮሚኒኬሽን አከባቢ የነበሩ ባለስልጣን ለውይይትና ለመግባባት ሳይሆን ቅድሚያ የሰጡት ተመሳሳይ ማስፈራራት በሚድያ ሰጥተዋል ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአፍሪካ አገሮች ሰራዊት ጠንካራና ቀዳሚ ከሚባሉት አገሮች ተርታ የሚሰለፍ ነው ስለሆነም አርፋቹ ተቀመጡ አይነት መልዕክትአስተላለፉ ፡፡ የአ/ ያ መከላከያ ሰራዊተስ ከአፍሪካ ማወዳደር ምን አመጣው ? ገና ከጥዋቱ የሌ/ኮሎኔል መንግስቱ አካሄድና እብሪትሰ መከተልስ/መደገመስ ለምን አስፈለገ ? ስለሆነም የስልጣኑ መተማመኛ ዴሞከራሲ ማስፋት ፤ ተደጋጋሚ ወይይትና ድርድር ፤መቀራራብ መፈጠር ሳይሆን ከአፍሪካ ቀዳሚ ጦር የሆነ የመከላከያ ሰራዊት ነወ ያለው አርፈህ ተቀመጥ ሆነ፡፡ ሰራዊት እንደ ብትር ማሳየት ወዴት እንደሚያመራን ታረካችን መለስ ብሎ ማየት ነው እንግዲህ ፡፡ ሰራዊቱስ ከኢትዮ- ኤርትራ ስምምነት በሃላ ሰላም መጣ ብሎ እፎይ ሲል ባልጠበቀው የእርስ በርስ ግጭትና ወግያ መክተቱ ሰራዊቱ የውግያ አቅም ከማዳከም አልፎ በሰራዊቱ መሰልቸት ያመጣልና እንደ መጀመርያ አማራጭና ማስፈራርያ መጠቀም መቆም አለበት፡፡ አሁን ጠንካራ የሚባለው ሰራዊት በአገር ውስጥ ሁሉም ቦታ ስታጣጋጭት እየጠነከረ የሚሄድ መስላቹህ ከሆነ ስህተት ነው በውስጥ ለውስጥ ግጭት በሰፋት የተሳተፈ/ጣልቃ የገባ ሰራዊት ተንኮታኩቶ ሲወድቅ/ሲዳከም እንጂ ሲጠነክር አልታየም ፡፡ ይሀ ደግሞ በታሪክም በወታደራዊ ሳይንሱም የተረጋገጠ ነው ፡፡

8.   ለራስህ ጥፋት ህዘብን ተጠያቂ ማድረግ ፡፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ በስልጣን ቆይታቸው ለረጅም ስአት በመናገር የሚታወቁ ሲሆን ከአብዮታዊና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር በተጨማሪ ህዝብን እንደ ህዘብ የወረፉበት ጊዜም ነበር፡፡ ይህም ቀስ በቀስ መንግስታችወ እየተዳከመ ሲሄድ የስርዓቱ ችግር ገምግሞ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ወርቅ ብታነጥፍለት ፋንድያ ነው የሚል ህዘብ ነው ብለዋል፡፡ በህበረተሰብ የነበሩ ቅሬታዎች ከማደማጥ ይለቅ ሁሉም ተሳደቢ ፤ ሁሉም አዋቂ ነኝ ባይና ሁሉም ተቺ የሆነበት አገር በማለት ለህዝብ የነበረው ንቀት አሳይተዋል፡፡ ያውም ህዘቡ ሃሰቡ የሚገልፅበት መድረክም ሚድያም ሳይኖር እኔ ያልኩተን ለምን እንደወረደ አልተተገበረም ብሎ የራሱ የቤት ስራ መስራት ሳይችል ሲቀር ህዘቡን ወረፈው፡፡

ሌ/ኮሎኔል አብይ ፡- መጀመርያ ወደ ስልጣን እንደወጣ ሰባኪ ንግግሩ ብዙ አድናቆትና ጭብጨባ አግኝታል፡፡ ቀስ በቀስ ግን ጭብጨባ ሳይሆን ከተለያዩ አካለት ጥያቄ መቅረብ ጀመሩ የሚመልስ ግን የለም ፤ አመራሩ አገር ወስጥና ውጭ አገር በጫጉላ ሽርሽር በመጠመዱ በየአከባቢው የሚከሰቱ ግጥቶችና ጥያቄዎች በአገር ደረጃ ይሁን በክልል ደረጃ መልስ የሚሰጥና ችግር የሚፈታ መሪ ጠፋ ፡፡ ከዚህ በመነሳት በማዕከላዊነት የሚመራወ መሪ ሲጠፋ ክፍተቱ እየሰፋ የአከባቢ ጎበዝ አለቃ መሪነቱ ተቀበለው ፡፡ ሌ/ኮሎኔል አብይ እነዚህ ግጭቶችና ጥያቄዎች በወቅቱ የመንግሰት ስራ ጀምሮ ሌሎችም እንዲጀምሩ ባለማድረጉ የተፈጠሩ ናችው ፡፡ ይህንን ራሰቸው የፈጠሩት ከፈተት ከማሰተካከል ይልቅ ለኢትዮጵያ ህዘብ እንደ ህዘብ ነፃነት መሸከም ያቃተው ፤ ዲሞከራሲ የማይመቸው፤ ባርነት የለመደ፤ ለስው መፈናቀልና ሞት መፍተሄ ከመሰጠት ይልቅ የታፈነ ቤት ሲከፈት ሽታ አለው በማለት ቸግሩ ወደ ህዘቡ በማደረግ ሞትና መፈናቀል ቀለል አድርጎት ያልፋል ፤ ህዝቡ የመደመርና ፍቅር ፍልስፍና ጥልቅ በመሆኑ ገና አልገበውም እያለ ያሾፉበታል ፡፡ የመንግስት ሚድያዎቸንም መንግሰትን ይሁን ጠ/ሚኒስተሩ ማሰተካከል የሚገባቸው ጉድለቶች ከመግለፅና ከመጦቆም ይልቅ ችገሩ ከህ/ሰቡ ንቃተ ህልና ማነስ የሚመነጭ ነው እያሉ ስለ ጠ/ሚኒስተሩ ትልቅነት ብቻ ይሰብካሉ ፡፡ የሚፈጠሩ ሞትና መፈናቀልም ሃላፊነት የሚወስድ የመንግስት አከል የለም ፡፡ ማን መሆናቸው የማይታወቁ ሁሌ የለውጥ አደናቃፊ ና የታጠቁ ሃይሎች ተጠያቂ ማደረግ ነወ ፡፡ ልክ እንደ ሌ/ኮሎኔል መንጉስቱ ለሁሉም ችግር ተጠያቂ ፀረ አብዮቶኞች እንደሚሉት ማለት ነው፡፡

9.  ራሱን እንደ ልዩ ሰው ያሰረፀ ፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ስልጣን እንደ ወጣ ያደረገው ነገር ቢኖር በየአከባቢው እየተዛዛረ ወቅታዊና ስሜታዊ ንግሮች በማድረግ ከፍተኛ ቀውጢ የሆነ ጭብጨባና ድጋፍ ተደገፎ የራሱ ሃሰብ ብቻ አስርፆ ትዕዛዝ ሰጥቶና ራሱን አዋቂ አድርጎ ኖሮዋል፡፡ በእጀጉ በትመህርትና በልምድ፤ በአዘዥነትና ከፍተኛ ጦርነትን በመምራት የሚልቁትን ለሚኒስተሮችና ጄንራሎች ሰብሰቦ ስለ ጦርነት ዕቅድ፤ ስልትና አፈፃፀም ሲተርክ ትኝሽ ሀፍረት አልነበረውም ፡፡ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ በወታደራዊ በተለይ በኦፕረሽናል እወቀት ብዙ አልነበረም ፡፡ ከአመጣጡ ጋር ተያይዞ የመሰርያ ግመጃ ቤት (ድጋፍ ሰጪ) በመሆኑ ሆን ብሎ አወቃሎህ ለማለት አስተማሪዎቹን ቁጭ አድርጎ ሲያስተምር ነበር፡፡ በተጨማሪም ለካድሬዎች፤ ለሙሀራን ፤ለወዛደሮች፤ ለሰራዊቱ ወዘተ የማርክሲዝምና ሶሻሊዝም ርዕቶ አለም በድፍርት ሲያሰተምር ነበር ፡፡ ካድሬዎችም ጋድ መንጉስቱ ሀይለማርያም ጋር ወደፈት አያሉ ፎቶው አገሪቱ በሙሉ እሰከ ቀበሌ ተሰቀለ፡፡ ጋድ መንጉስቱም ከልክ በላይ ተካበ እንዲህ ያደረጉትም ሽሞት በሽሞት ሆኑ ፡፡ ሰውም በሙሉ የስብሰባ መዝግያና መክፈቻ ከጋድ መንጉሰቱ ሃ/ማርያም ጋር ወደፊት እያለ ቀጠለ ትርጉሙ ግን የሚዘመርለትም ዘማሪውም አያወቅም ነበር ምክንያቱመ በተጨበጭ ሁሉም ነገር ወደ ሃላ እየሄደ በጭፍን ወደ ፊት ይባል ነበር ፡፡ ይህም እንደ አሁኑ ፍቅር ጠፍቶ በየቀኑ እተቀነስንና ሌ/ኮ አብይ አጫፋሪዎች የመደመርና የፍቅር ጉዞ እያሉ ያደነቁሩናለ ታሪክ ራሱን ሲደግም ማለት እንዲህ ነው፡፡

ሌ/ኮሎኔል አብይ ወደ ስልጣን እንደመጡ በደጋፊዎቻችው በታቀደና በተደራጀ ሊባል በሚችል ሁኔታ ብዙ ተሰበከ ከሙሴ ጋር እኩል በማድረግ ዘመሩለት፤ ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታም ተባለለት ሚድያዎችም ሆን ብለው ይህንን ብቻ አራገቡ እሱም ራሱ ከሰዎች በላይ ከፍ አደረገ፡፡ ጠ/ሚኒስተሩን እየተከተሉ ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባቸው የመደመርና ፍቅር ጉዞ ብለው ሲለፍፉና ሲያስተጋቡ የነበሩም ለውለታቸው የሚኒስተርነትና ቁልፍ የሚባሉ አገሮች አመባሰደረነት ተሾሙ ስም መጥቀስ ብዙ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የሙሴነት ክብር ተቀብሎ 7ኛ ንጉስ እንደሚሆን ያውቅ እንደ ነበረ ለማሰመንም ባገኛው ዕድል ሁሉ ብዙ ተናገሮል ::

 

በመቀጠልም የወታደራዊ ጠቢብና አዋቂ መሆኑ ለህዘብ ለማሰየትም ሁሉም ጄነራሎች ሰብሰቦ ስለ ጦርነት እቅሞችና አይኖቶች አስተማራቸው በሚደያም ተደጋጋሚ ተላለፈ አገር ጉድ አለ ገሚሱ አዋቂ/ወንድ ነው ቁጭ አደርጎ አስተማራቸው ምድረ ጄንራል አለ እሱም የሚፈልገው ይሀንን ነው ፡፡ ሁኔታው ስህተት መሆኑ የገባቸው ከመቼ ነው የጄነራሎች ስልጠና በሚደያ የሚተላለፈው ብለው ጥያቄ አነሱ ፡፡ የተሰጠው ስልጠናስ ከዚህ በፊት አያውቁትም ማለት ነው? በሌሎች አገሮችስ ግምት ውስጥ አንገባም ዋነኛ የድህንነት ተቃማችን አይደለም የሚል ጥያቄ ጭረዋል፡፡ ለግል ዝና ሲባልሰ ጀነራለቹ የጦርነት ሀ ሁ የሆነው የጦረነት ትምህረት በሚደያ ማሰተማር ለመከላከያ እንደ ተቃምና ለጄነራሎቹ እንደ አንድ የአገሪቱ የጦር መኮንን ክብርስ አይሰጥም ፡፡ ተቃዋሚ/ኦነግ ማስፈራረት ሲፈለግ ከአፍሪካ ቀዳሚ ጠንካራ ሰራዊተ ያላት ሀገር ይባላል ታዲያ ጄንራሎችዋ የጦርነት ሀ ሁ ሳያወቁ ነው አገሪተዋ ጠንካራ ሰራዊት የገነባችው ?

የሚገርመው ግን ልክ እንደ ሌ/ኮ መንግስቱ የወታደራዊ አቅሙ ድጋፍ ሰጪ(ኦፕሬተር) ነው፡፡ ለዚህም ነው የማያውቀው ጉዳይ እንደሚያወቀው አድርጎ በማቅረብ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበብት መስሎ ለህ/ሰቡ ለመቅረብ ነው ቢሆንም ከአንድ ሰሙን ወሬ አላለፈም ፡፡ አላማው ሁሉን አውቃሎህ የሚል የሌ/ኮሎኔል መንግስቱ አበዜ ለራስህ ሰማይ መቆለልና የሰው መነጋገርያ ለመሆን ነው፡፡ ለሚኒስተሮች የተሰጠው የአመራር ስልጠናም ተደጋጋሚ በሚድያ ተላልፈዋል መልአክቱ ተመሳሳይ ነው የግል እውቅና ጣራ ለመስቀል ያልሆንከውና የሌለህን ሆኖ መገኝት ነው፡፡ ጠ/ሚኒስተሩ ለአርቲስቶቹም ስልጣና ሰጡ ተብሎ በሚድያ ተላልፈዋል ይህም ጠ/ሚ የሁሉ እወቀት ባለቤት አድራጊ ፈጣሪ መሆናቸው ለማሰየት ነወ ፡፡ ሌሎች በርካታ አብነት መውስድ ይቻላል ለማሳያ ግን በቂ ነው፡፡

 

Back to Front Page