Back to Front Page

ምልክቶቹን ጠንቅቀን እንያቸው!

ምልክቶቹን ጠንቅቀን እንያቸው!

 

በዑሱማን ሙሉአለም 2-28-19

ከሐራ-ገበያ

 

መፈንቅለ መንግስት አድራጊው መፈንቅለ መንግስት አወገዘ። በለፈው ዓመት በኦህዴድ ውስጥ ቲም ለማ በነሙክታርና አስቴር ላይ በኩዴታ ስልጣን ተቆጣጠረ። ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ ውግዘት እንዳያጋጥመው እነሙክታርን እነ በክርን ተማፅኖና አስፈራርቶ ወደንና ወደው ለውጡን ተቀብለን ነው አሰኝተው ሌሎች የኢህአዴግ ግምባር አባላት ለውጡን እንዲቀበሉት አደረጉ። ይህ ሲሳካ ለሁለተኛው እና ለወሳኙ ኩዴታ ዝግጅታቸውን መዘጋጀት ተያያዙት። የለማ ቲም በኦሮሚያ የለውጥ ሃዋርያ ነኝ ብሎ አዲስ የለውጥ ሃይል እንደሆነ ለማሳመን የሚከተሉትን ስልታዊ እንቅስቃሴ አደረገ።

 

የኢኮኖሚ አብዮት ብሎ ለወጣቱ ስራ ዕድል እንፈጥራለን በሚል በኦሮሚያ ኢንቨስት ያደረጉ ባለሃብቶችን የፌደራል ፍቃድ እያላቸው ከህግ ውጭ እያስፈራራ በሓይልም በዜዴም ለኦሮሞዎች ብቻ ስራ ቅጠሩ ትርፍ ማስፋፍያ የያዛቹሁት መሬት እንወስደዋለን ለወጣቱ እናድለዋለን ብለው የተስፋ ምግብ እየመገቡ ቄሮ ቡዱን ልብ ውስጥ እንዲገቡ አስቻላቸው።

 

በፍንፍኔ ልዩ ጥቅም ይከበር በሚል የአዲስ አበባ ሰፈሮች ስም የድሮ ኦሮምኛ ስማቸው ይመለስልን ከሚል ጥያቄ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ በጋራ እናስተዳድራት የሚል የአዋጅ ድራፍት በኦህዴድ ማ/ኮሚቴ አስወስኖ ወደ ኢ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ል፣ከእህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ መጣ። የለማ ቲም። በኢህአዴግን ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ወቅትም ሌሎች ውሳኔ የምያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ብሎ ደረደረ።

Videos From Around The World

 

ኦህዴድ በኦሮሞ ወጣት ተቀባይነት ለማግኘት የተነሳውን አመፅ ማብረድ የምንችለው ሊሰማን የሚችለው የአፋን ኦሮሞ የፈዴራል ቃንቃ ማድረግ ሲቻል ነው፣  በፌደራል ያሉ ቁልፍ ቦታዎች ኦሮሞ ሲሾሙ ነው ብለው አለቃቀሱ። ተሃድሶ እንዳደረጉና ህዝቡ ለመጀመርያ ጊዜ እነሱን መስማት እንደጀመረ ለፈለፉ።  ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ውጭጉዳይ ሚኒስቴር፣ መከላከያ፣ ድህንነት በተወሰነ ብሄር ሰዎች ተይዞ ኦሮሞ ስለማይታመን ብቃት የለውም ተብሎ ነው የተገለለው እያለ ነው ህዝቡ እኛም በተወሰነ እንጋራዋለን አሉ። ኦህዴድ ነፃ ህልውና አልነበረውም በህወሓት ጣልቃገብነት ይተዳደር ነበር ብለው እንደገመገሙም ገለፁ። የውስጣቸውን ችግር ሳያዩ ሁሉም ውጫዊ ችግሮች ዋነኞች አድርገው እየደጋገሙ ሰው ጆሮ ላይ እንዲገባ ባለመታከት በሁሉም መንገድ ተንቀሳቀሱ። የኦሮሚያ ሁኔታ እንዲባባስ ሆን ብለው በመንቀሳቀስ በአንድ ወቅት ከሶማሊ ክልል፣ ከደቡብ ክልል፣ ከቤንሻንጉል ክልልና በአዲስ አበባ ግጭቶች እንዲፈጠሩ አደረጉ። ግጭቶቹ ለመፈታት ሲሞከር መከላከያ፣ ፈዴራል ፖሊስና ድህንነትን አንፈልግም ወጣቱ የወያኔ ናቸው ስለሚል አትግቡብን እኛው ራሳችን እንወጣዋለን አሉ። ከሱማሊ ክልል ጦርነት ከፍተው በሁሉም ወሰን ውግያ ከፈቱ። ሙክታርና ወያኔ ሲያስመቱህ ከርመዋል እኛ ደረስንልህ አስባሉ። ኦቦ ለማ ኦቦ ዓብይ ጀግኖች አስባሉ። ለማና ዓብይ ፎቶግራፋቸው በክልሉ መኪናዎች መስትዋት ላይ አስለጠፉ። በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ ፋብሪካዎች እንዲዘረፉ እንዲወድሙ አስደረጉ። ወደ አዲስ አበባ የሚገባና የሚውጣ ትራንስፖርት እንዘጋለን ብለው ዘጉ። ህግ ይከበር ሲባሉ ቄሮን አትንኩት ይውጣለት ብለው ዝም አሉ። አሁንም ችግሩ የፈደራል መንግስትና የቆየው የኦህዴድ አመራር እንደሆነ እያማረሩ ገለፁ። እነሱ ግን ህዝቡ መሰማትና ማደመጥ ጀምረናልና ከውጭ ሁናቹህ ብቻ የጠየቅናቹህ ባጀት ስጡን አሉ። ሃይለማርያም ላይ ጫና በማድረግ የኦሮሚያ ችግር ከሌላው የተለየ አድርገው አቀረቡለት። ሶማሊንና አብዲን ብቻ እየተንከባከብ ነው ብለው ጨቀጨቁት። ሃይለማርያምን በትንሹ መሃል ሰፋሪ ማድረግ ከቻሉ በሃላ በነሱ ወገን እንዲሰለፍ ተንቀሳቀሱ። እየተሳካላቸውም መጣ።

 

ጎን ለጎን በወያኔ የተከፉ በሚል የከፋኝ ቡዱን መመስረት ጀመሩ። ህዝብ ለህዝብ በሚል ያልተጣላውን የኦሮሞና አማራ አገናኛን አስታረቅን በማለት የለየላቸው ትምክህተኞች የሚመሩት እንቅስቃሴ አቀጣጠሉ። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ብለው በአማራ ክልል ተቀባይነት ለማግኘት ቻሉ። የትግራይ የበላይነትና የህወሓት ወያኔ የበላይነት እናጠፋለን ብለው ኦሮማራ ብለው ተንቀሳቀሱ። በኢህአዴግም ከጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ስልጣኔን እለቃለሁ ማለት ተከትሎ በኦህዴድ እና በብአዴን ቁንጮ አመራር መካከል ከኢህአዴግ አሰራር ወጭ ሚስጥራዊ ግንባር በግንባር ውስጥ ሌላ ግንባር ፈጠሩ። ተልእኮው ግልፅ ነበር። ወያኔን መጣል። ስልጣን መንበሩን መቆጣጠር። ይህ ደግሞ ተጠናክሮ ከውጭ ሃይሎችም ድጋፍ እንዲያገኝ ተደረገ። ከለየላቸው የኢህአዴግ ጠላቶች ጋርም ሚስጥራዊ ግንኙነት መሰረቱ። በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ሳይቀር ግንኙነት ፈጠሩ። ህወሓት በቅንነት የራሱን ችግር ለማየት ሳላሳ አምስት ቀን መቐለ መሽጎ የውስጥ ትግል ሲያደርግ እነሱ የወያኔ ዘመን የሚሉትን ጥለው እንዴት ለውጥ እንደሚያመጡ ሲዘጋጁ ቆዩ።

 

በመጋቢቱ የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ ብአዴንና ኦህዴድ ምክርቤት አባላት በከፊል ተደራጅተው መጡ። ከደህዴንም በደህዴን ማ/ኮሚቴ የተወቀሰው ሃይለማርያም ወያኔ አልደረሱልኝም ጨከኑብኝ ብሎ ከከፋኝ ቡዱኑ ጎን በመሰለፍ በደኢህዴን ውስጥ ክፍፍል በመፍጠርና በድለላ አደርጅተው ገብተው ድጋሚ መፈንቅለ መንግስት በኢህአዴግ ምክርቤት ውስጥ አካሄዱ። ንጉስ ጥላሁንና ዐቃቤ ህጉ ብርሃኑ አስመራጭ አድርገው በእርካብነት ተጠቅመው መንበሩን ተቆጣጠሩ። ኮ/ል ዓብይ ተመረጠ። የለውጥ መዝሙር ዳንኪራ ተመታ። ልክ እንደ ደርግ ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ብሎ አገሪትዋን ሲኦል እንደከተተው ፍቅር፣ አንድነት፣ መደመርና ኢትዮጵያዊነት ተሰበከ። ለውጥ ላይ ነን ተባለ። ህዝቡን በተስፋ መገቡት።

 

ይሀው ለውጥ በሚል በነውጥ ሁነን ለአንድ ዓመት ቆየን። የለውጡ ባህርይ ነው። በሽግግር ወቅት የሚያጋጥም ነው እየተባልን ስላም አጣን። መፈናቀል በሽ ሆነ። ኦሮሚያም እስካሁን እየታመሰ ነው። የኦሮሞ ወጣት ጥያቄ አንድም እንኳን አልተመለሰም። በኦሮሚያ ልማት ከጠፋ ቆይቷል። ወቅታዊ ጥያቄ ሰላም ሆኗል። መንግስት የሌለበት አገር ሆኗል። የስልጣን ጥም ያንገበገበው ቡድን ስልጣን እንደያዘ ስልጣኑን ለማደላደል እንጂ ለህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ሲያደርግ አይታይም። ህዝቡ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ፀረ ለውጥ የሆኑ ሃይሎች እያለ ያፍናል። ሲያምፅ ደግሞ ይጨፈጭፋል። ወለጋ፣ ቅማንት፣ ቤንሻንጉልና ጌድዮን ላይ የነበሩ ጭፍጨፋዎች ስልጣን የያዘው ሃይል ማንነት የሚያሳዩ ናቸው። በህጉ ጊዚያዊ አዋጅ አውጆ ህግ ማስከበር ሲችል ህጋዊ ያልሆነ ድብቅ ያልታወጀ ጊዚያዊ አዋጅ አድርጎ ኦሮሚያ፣ ሶማሊና አማራ ክልሎችን በኮማንድ ፖስት እያስተዳደረ ነው። ምርጫውን ለማራዘም አስቸካይ ጊዚያዊ አዋጅ ያውጃልና ከአሁኑኑ እንዳይቃጠልበት ነው በኮማንድ ፖስት ጊዜውን እያረዘመ ያለው ተብሎ የሚታማው የዓብይ መንግስት አሁን ደግሞ አንድ ክስተት ተፈጥሯል። ምንነቱ በማይታወቅ ክስትት አመራሮች እርስ በርሳቸው  እየተገዳደሉ ነው። ለምን? ማነው ተጠያቂው?

 

የአማራ ክልል በአማራ ክልል ውስጥ በቅማንት፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በኃላም በቤንሻንጉል ጆኖሳይድ ፈፅሟል። ተጠያቂው ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ በክልሉ ባለስልጣኖቹ መካከል ልዩነት ተፈጥራል። ኮ/ል ዓብይ ራሱ ሄዶ ችግሩን ከመፍታት እሱ የሱዳንን ችግር ሊፈታ ሲሄድ ደመቀ መኮነንና ጄነራል ሰዓረን ልኮ ስብሰባ ቢቀመጡም ችግሩን አልፈቱትም። መፍታት ይቅርና እንዲባባስ ነው የሆነው። እነ አሳምነው ፅጌን ብቻ ተጠያቂ አድርጎ ዋነኞቹን እነ ገዱ፣ ደመቀ፣ አምባቸውና ዮሐንስን ነፃ የሚያደርግ ውሳኔ ተወሰነ። ይህ ውሳኔ ንትርክ ውስጥ እንዲገቡ አድርጋቸው። ከዚህ ውሳኔ በኃላ በቡዱን ተከፋፍለው አንዱ ቡዱን በአንዱ ቡዱን ላይ ሲሸርብና ሃይል ሲያሰባስብ ቆይቶ ሰኔ አስራ አምስት ላይ ፈነዳ።

 

መፈንቅለ መንግስት የሚል ስም እንዲሰጠው ቀድመው የተጉት ኮ/ል ዓብይ ይህ ችግር ጎልቶ እንዳይወጣና የራሳቸው ጉድ እንዳይጋለጥ ነው። የአሳምነው ቡዱን ሁላችን አምነንበት የተደረገ ጭፍጨፋ ነው እኔን ብቻ የምታሳጡበት ምክንያት የለም ብሎ ማንም የሚጠይቀኝ የለም ብሎ ሲፎክር ነበር። ደጋፊዎቹም አሁንም ድረስ ግድያ ከፈፀመ በኃላም ማንም እንዳይነካው ብለው ኮ/ል ደመቀን እንዳዳኑት አሳምነውን ለማዳን ቢንቀሳቀሱም አልተሳካላቸውም። ሲያመልጥ ከተገደለ በኃላም ጀግናችን ተብሏል። እውነት የቅማንት ዘር ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋ፣ የኦሮሞ ልዩ ዞን በከምሴው ላይ የነበረ ጅምላዊ ጭፍጨፋና በቤንሻንጉል የተፈፀመው የጆኖሳይድ ጭፍጨፋ አሳምነው ፅጌ ብቻ ነው ተጠያቂው? ገዱ፣ ደመቀ፣ አምባቸው፣ ዮሓንስና ሌሎች አይጠየቁም? ኮ/ል ዓብይ አይጠየቁም? ቢያንስ ባለማውገዛቸው ብቻ ተጠያቂ አያደርጋቸውም? የገለምሶ፣ የአወዳይ፣ የወለጋና የጌድዮ ጆኖሳይድ ያልተጠየቀ የኮ/ል ዓብይ መንግስት አሳምነው ፅጌን ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ ያደረገው እንቅስቃሴ ከሽፎበት በነአምባቸውና ጀነራሎቹ ግድያ የተፈፀመው። ጄነራል ሰዓረ ኮ/ል ዓብይ መስራት የነበረበትን ስራ እንዲስራ ልኮት በማያውቀው ጉዳይ አሳምነው ፅጌን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ እንቅስቃሴ ወስጥ በማገባቱ ነው ለግድያ ታርጌት የተደረገው ብሎ ለጊዜው መገመት ይቻላል። ግን የጀነራሎቹ አሟማትም ብዙ ግልፅ ያልሆኑ የተሸፋፈኑ ነገሮች አሉት። የጥበቃ ሃይላቸው በቅርብ ለውጦች ተደርገዋል ይባላል። ለምን? ማን ነው ምደባውን የፈፀመው? ጄነራል ሰዓረና ኮ/ል ዓብይ መካከል በቅርቡ ያልተስማሙበት ጉዳይ ገጥሟቸው ነበር ይባላል። ገዳያቸውም አንዴ ተይዟል። አንዴ ደግሞ ራሱን ገድሏል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ይቅርታ በስህተትት ነው ሞቷል የተባለው ተባለ። ለምን ተምታታ? ምን ለመደበቅ? ይህ ደግሞ ኮ/ል ዓብይም እጃቸው ይኖርበታል የሚል በትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በአማራ ህዝብ ጭምር ጥርጣሬ ጭሯል። በሴራው ግብፅና ኢሳያስ አፈወርቂም ከጀርባ ይኖራሉ የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ።

 

ፍትህ ሲጎድል ነው ያለፍትህ እነአምባቸውም ጥፋት ካላቸው በህግ መጠየቅ ሲገባቸው በጉልበተኛ በግፍ የተገደሉት። ደመቀ መኮንንና ገዱ ውጭ የነበሩት በአጋጣሚ ነው? ዮሓንስ እንዴት ወሬው አልተሰማም? ሃያ ሶስት ፖሊሶች በግጭቱ ምሽት ብቻ  ሞተዋል። አርባ ስድስት ቆስለዋል። ባህርዳር ከተማ በሰኔ አስራ አምስት ምሽት በነበረ የተኩስ ልውውጥ። በአዲስ አበባም በጀነራል ሰዓረ ቤትና በጦር ሃይሎች ካምፕ የሞቱ ወታደሮች አሉ። በዚህ ምሽት በቅሊንቶ ማረሚያ ቤትም ሁለት የማረሚያ ቤት ፖሊሶች ተገድለዋል። በማን? ግልፅ አይደለም። ዜና ላይ አልተነገረም። እነዚህ የፀጥታ አካላት ፖሊሶችና ወታደሮች ለክብራቸው ባንዲራ ዝቅ ያልተደረገላቸው መሞታቸው ዋጋ ሲለሌለው ነው? ገዥዎች ምን ያህል ስስታሞች ለራሳቹህ ስልጣን ብቻ ስግብግብ እንደምትሉ በግልፅ ያሳያል።

 

በዩኒፍርም ሚድያ ላይ የወጡት ባለ ዩንፎርሙ ጠቅላይ ሚኒስተር የአማራ ቴሌቭዥን ሎጎ ያለው ማይክሮፎን ፊታቸው ላይ ደቅነው ከጀርባቸው ምንም ነገር የማይታይበት ልሙጥ ግድግዳ ያለው ክፍል ሁነው የፍርሓትና ድንጋጤ እንጂ ምንም የሐዘን ሁኔታ የሌለው ፊት ይዘው ቀረቡ። የት ሆነው ነው መግለጫውን የሰጡት? የት ከተማ? የት ህንፃ? ሌሎች ሚድያ ቢሆኑ ይገልፁ ነበር። ለምን ዩኒፎርም ለብሰው ብቅ አሉ? ለምን የአማራ ቴሌቭዥን ሎጎ ያለው ማይክሮፎን ብቻ ሆነ? ባህርዳር ሂደው ነበር እንዴ? ምን ሊሰሩ? ለምን ታድያ አልተገለፀም? ቃል አቀባያቸው ንጉስ ጥላሁን ቀድሟቸው ጠቅለል ያለ መግለጫ የሰጠው በኢቲቪ ነው። መፈንቅለ መንግስት በክልል መንግስት ተሞከረ ብሎ። ከዛ ኢንተርኔት ተዘጋ። ንጉስ ጥላሁን በኢቲቪ ኮ/ል ዓብይ ቆይተው በአማራ ቲቪ ለምን ቀረቡ?

 

የባህርዳር ሁኔታ እንደተሰማ የኮ/ል ዓብይ ቤተመንግስት ተጨማሪ ጥበቃና ወደ ቤተመንግስቱ የሚያመሩ ሁሉም መንገድ እንዲዘጉ ተደረገ። የት ሆነው መሆኑ ባይታወቅም ኮ/ል ዓብይ ሚድያ ቀድመው አጀንዳ ዘረጉ/ሴት ለማድረግ/ ተክነውታል። ይህ ብቻ በቂ ስላልመሰላቸው ሱዳን ላይ ኢንተርኔት ይከፈት ብለው ምክረሃሳብ የለገሱ ሰውዬ በሚመሩት አገር ኢንተርኔት ዘግተው በአንድ አቅጣጫ የሚፈስ ፕሮፖጋንዳ በመንፋት ፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ ያሉት መድረኩን ማጥበብ ሳይሆን በጣጠሱት። ህዝቡ ያለው ሁኔታ እንዳያውቅ የሚፈልጉትን ብቻ እንዲሰማ አደረጉት። የትግራይ አስተዳዳሪ ሳይቀሩ መፈንቅለ መንግስት ነበር ከሸፈ አሉ። ሁሉም ተነዳ። አብን መግለጫ አወጣ ተብሎ ውጭ አገር ይወራል። እዚህ ያለንው ግን አልሰማንም። በነበረከት ላይም ማረምያቤት እያሉ ግድያ ሊፈፀም ነበር ተብሎ ይወራል። እውነት ይሁን አይሁን የሚታወቅ የለም። አሳምነው ፅጌ ተገድሏልም እየተባለ ነው። በሚቆጣጠሩት ሚድያ መረጃውን አፍነውታል። እነ ተፈራ ማሞ፣ አለበል ከአሳምነው ጋራ ግንቦት ሰባት አባላት የነበሩ አወገዙ ተባሉ። ቴሌቭዥን ቀርበውም ምንም ስሜት የሌለው ፊት ይዘው ሲያወግዙ ታዩ። አሳምነውን አወገዙ የተባሉት ሰዎች ታስረዋል። ታስረው ነው አውግዙ ብሎ የክልሉ ፖሊስ በቴሌቭዥን ያቀረባቸው ተብሎ ይወራል። እንዲያውም ኮማንድ ፖስት የሚመራው መከላከያ የክልል ፖሊሱን እነ ተፈራ ማሞን አስረክቡን አናስረክብም ጭቅጭቅ እንደነበረና አስገድድው ይሁን ተደራድረው እንደተረከቧቸው ከወደ ባህርዳር ይወራል። አዲስ አበባም ሜጀር ጄነራል ሐሰን ኢብራሂምም በቁም እስር ይገኛል ይባላል። ተወራ ብላቹህ ደግሞ ስልኩን ዝጉት።

 

ኮ/ል ዓብይ አምባገንነት ፈልገውት ሳይሆን የስልጣን ጥምና መደባዊ ባህሪዎ የግድ ብሎ የተሸከሙት ክስተት ነው። ጋዳፊ ዙፋኑን ይዞ የሙጥኝ ሲል ቦይ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ። እንደዛ እንደሚሆን አቻዎ ኮ/ል ጋዳፊ መቼም ገምቶ እንደማያቅ እንደነበረ መገመት ይቻላል። ኮ/ል ዓብይ ግን መገመት አለበዎት። ከጋዳፊ አይተው ይማሩ። ወይም ከእንግሊዝዋ ትሬሳ መይ መማር ጥሩ ነው። ደሴ ጫፍ ጫፉን አንስተው እንዲህ ከሆነ ስልጣን ላይ አልቆይም ያሉት ስንት ወንጀል በሚፈፅምበት አገር ስልጣን ለመልቀቅ ምክንያት ባያማርጡ ይሻላል። መፈናቀሉን ጆኖሳይድ ጭፍጨፋን መቆጣጠር አልቻልኩም። ሰላም መረጋጋት ማምጣት አልቻልኩም። አገር በኔ ምክንያት ከምትበታተን እኔ ስልጣኔን ለቅቅያለሁ ይበሉ። ከነውጥ የርስዎ መለውጥ ይሻላል። እያደሱት ባለው የአፄ ሚኒሊክ ቤተመንግስት የጃንሆይ መቃብር እንደነበረው የእርስዎም መቃብር እንዳይሆን። በርስዎ ምክንያት ለምን አገራችን ኢትዮጵያ ትፍረስ? ስንኖር ኢትዮጵያውያን ስንሞት ኢትዮጵያውያን ያሉትን እስቲ በሰላም ሙተን የምንቀበርባት ኢትዮጵያ እንድትኖረን ስልጣኖን አልቻልኩም ብለው ይልቀቁ። የኢትዮጵያ ህዝቦች ለውጥ እንጂ ነውጥ አልነበረም ጥያቅያቸው።የርሶ በስልጣን መቆየት ህውከት እንጂ መረጋጋት አላመጣም። መንግስት የከሸፈ መንግስት አደረጉት። የጎበዝ አለቃ ድፍረት አግኝተው የክልል አስተዳዳሪ የሞት ፍርድ በይነው የሚፈፅሙበት አገር ፈጠሩ። ኤታማዦር ቤታቸው ውስጥ መገደል የሚችሉበት አገር ፈጠሩ። ሌላው ዜጋ ታድያ ምን ዋስትና አለው?

 

ኮ/ል ዓብይ የፈለገው ሃሳብ ይዘው ወደ ስልጣን ይምጡ እንጂ ምንም የሞራል ብቃት የሎትም መፈንቅለ መንግስት አከሸፍኩኝ የሚሉበት። በመፈንቅለ መንግስት የመጣ መሪ ሌላን ተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስት ኮኑኑ ማለት አይችልም። እርስዎ የሙክታርና የአስቴርን ስም ገድለው ስልጣን ተቆጣጠሩ። ግን ዓለማው ወደ ፌደራል እንጂ ክልል ውስጥ ሊወሸቁ አልነበረም። አሳምነው ዶክተር አምባቸውን ገድሎ ስልጣን ሊይዝ ፈልጎ ነበር እያሉ ነው? እስቲ ገድሎ ቴሌቭዝን ጣብያ ተቆጣጥሮ የአማራ አገር መሰረትኩኝ ሊለን ነበር ማለት ነው? ያስረዱን። ለዛ ነበር ቴሌቭዥን ተዘግቶ የቆየው? ከዋሹ አይቀር እቅዱን አግኝተናል ይበሉን። እየተጣራ ነው ይበሉን። አሁን የሁሉም ጥያቄ መሆን ያለበት ገዳዮቹ አነሱን በስተጀርባ የመሩ ተጣርቶ ይፋ ይሁን ለፍርድ ቀርበው ይቀጡ አይደለም። የህወሓት መግለጫ ተሳስቷል። ጥያቄው ለምን አገራችን በችግር ላይ ችግር ተከታተሉባት? መንግስት ለምን መምራት አቃተው? መንግስቱን እየመራ ያለው መሪ ኮ/ል ዓብይ ብቃት የለውም ውረድ ብሎ እንዲወርድ ማድረግ ብቻ ነው መፍትሔው። ይጣራ ተብሎ እያድበሰበሱ አገራችን በህይወት አለች እያልን ከእጃችን ታመልጣለች። ህዝቦች አይበቃም? አንድ ዓመት ዕድል የተሰጣቸው ሰውዬ ከቀውስ ወደ ቀውስ እያሸጋገሩን ነገሮችን በተናጠል እያየንና እየቆጠርን ዝም ማለት ተጠያቂ የሌለው አገር ሁነን እንፈርሳለን። ነቃ ማለቱ አይበጅም? በተናጠል ክስተቶችን እያየን እየረሳን ሌላ ክስተት ሲፈጠር ደግሞ እየደነግጥን ለየብቻው ምልክቶቹን እያየን አያዛልቀንም። የተያያዙና የተሳሰሩ ከእንድ ምንጭም የሚፈልቁ ናቸው። ምልክቶቹን ጠንቅቀን ማየቱ ብቻ ነው የሚበጀን። ለተፈጠሩ ችግሮች በተናጠል መግለጫ የሐዘን ቀረርቶ እያሰማንና ሻማ እያበራን ስንት ጊዜ እንቆያለን? አገር ፈራርሳ ህዝቦቿ ሲበታተኑና ሲተላለቁ ማን ቀረርቶና ሻማ ያሰማልናል ያበራልናል?

 

አገራችን ፈጥነን በመታደግ የህዝቦችዋን ድህንነት እንጠብቅ!

 

ብህብረት ፈጥነን ድምፃችን እናሰማ!   


Back to Front Page