Back to Front Page

ኢትዮጵያ እንደ አገር ለምን ሰላም የራቃት ሆነች ?

ኢትዮጵያ እንደ አገር ለምን ሰላም የራቃት ሆነች ?

ሓጎስ ኣረጋይ (18/07/2019)

ኢትዮጵያ እንደ አገር ለምን ሰላም የራቃት አገር ሆነች ? ለሚለው ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ ሰዎች የተለያዬ እሳቤ ሊኖራቸው ይችላል ። ነገር ግን ችግሩ ባለማወቃችን ምክንያት ዛሬም ለመፍትሄው ብዙ ርቀት መጓዝ ያልቻልን ህዝቦች ይመስለኛል። ስለዚህ አሁን ኢትዮጵያ ብለን በምንጠራት አገር ውስጥ የተለያዩ ህዝቦች የተለያዬ ትውፊቶች እንዳሏቸው አሁንም ድረስ በግልፅ የሚታዩ ናቸው ። እነሱም

1.      ኢትዮጵያ ብለን በምንጠራት አገር ውስጥ አንድ አይነት የዘመን አቈጣጠር አልነበረንም። ለምሳሌ የሲዳማ ህዝብ የፍቸ ጨምበላላ የዘመን መለወጫ (calendar) አሁን እንደ አገር ከምንትጠቀምበት የዘመን አቆጣጠር በጣም የተለዬ ነው። በመሆኑም ሲዳማዎች ከመቶ አመት በላይ ጠብቀውት የነበረ በራሳቸው ከራሳቸው የፈለቀ የፍቸ ጨምበላል ሳይንሳዊ የዘመን ቀመር ትንተና መኖሩን በግልፅ ያሳያል።

Videos From Around The World

2.      ብዙውን ግዜ ዴሞክራሲ በኣመሪካን አገር የተጠነሰሰ ባህል ተደርጎ ይወሰዳል። ነገር ግን በኦሮሞ ማህበረ ሰብ ብቻ ለዘመናት ያክል የገዳ ስርዓት ይጠቀሙ ነበር። የገዳ ስርዓት የተጠነሰሰው እና የፈለቀው በኦሮሞ ማህበረ ሰብ ውስጥ ብቻ ነው። የዴሞክራሲ ባህል ከየተኛውም የአለም ክፍል በር ከፋች ተደርጎ መወሰድ ሲገባው ከአመሪካ ዴሞክራሲ ለማኝ ሁኖ/ሁነን ቆይተናል /ቆይተዋል ።

3.      ካደጉ አገሮች የስንዴ ለማኝ ድሃ ህዝቦች ነን ። ድሃ የሆነው ደግሞ በተፈጥሮቻን ድሃ በመሆናቸን አይደለም። ለምሳሌ የደቂቀ እስጢፋኖስ አስተሳሰብ እንውሰድ። ደቂቀ እስጢፋኖስ ከ 1406-1504 በትግራይ ክልል የተንፀባረቀ አስተሳሰብ ነው። የደቂቀ እስጢፋኖስ አስተሳሰብ ያመለጠን የአብርሆት ዘመን ነው ብለው የሚጠሩት ሰዎችም አሉ ። ለማነኛውም የደቂቀ ኢስጢፋኖስ ፥

በመርህ ደረጃ የሚገለፅ

         የሰው ልጅ ለሰው መስገድ የለበትም ይላል ። ከዴሞክራሲ አንጻር የተለያዬ ትንተና ሊሰጠው ይችላል።

         የሃይማኖት አባቶች ራሳቸው በራሳቸው መቻል አለባቸው ። ከገበሬ ማስገበር የለባቸውም ይሉ ነበር።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚገለፅ

         የአትክልት ማዳቀል ስራ የተመለከተን እንይ። ያኔ በጉንዳጉዶ ብርቱካን ለማዳቀል በቅተዋል። በዚያን ግዜ የተዳቀለው ብርቱካን አሁንም ድረስ ጣፋጭ ብርቱካን ከቦታው ይገኛል። እንግዲህ የማዳቀል ስራ ከአለም የቀዳሚነት ስፍራ ይይዛልማለት ነው።

         የመስኖ ስራ

         የነፋስ ሃይል መጠቀም ወዘተ ተጀምሮ ነበር።

እንግዲህ በደቂቀ እስጢፋኖስ የተጀመረው ስራ በኣፄ ዘርዓ ያቆብ እንዲቆም ተደረገ። ማቆም ብቻ ሳይሆን የደቂቀ እስጢፋኖስን አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎች በግፍ እንዲገደሉ ተደርገዋል። በእርግጥ የአኩሱምን ጉዳይ ካነሳን ደግሞ ህልም ሊሆንብን ስለሚችል እዚህ ላይ ላብቃ።

4.      በሃረር ፣ በጅማ ፣ በቤንሻንጉል፣ በአማራ ፣ በትግራይ ፣ በወላይታ ወዘተ የቀደምት ቤተ መንግስታት እንደ ነበሩ ያሳያል/ይነገራል ። አሁን በኢትዮጵያ ማቀፍ ውስጥ የገቡ ህዝቦች ቀደም ሲል የተለያዬ የስነ መንግስት መግለጫ እንደ ነበራቸው በግልፅ ያሳያል።

ከላይ ለመገለፅ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ ህዝቦች በስነ ልቦና ፣ በሃይማኖት ፣ በታሪክ ፣በስነ መንግስት ወዘተ የተለያዩ ህዝቦች መሆናቸውን በግልፅ ያሳያል። አፄ ሚኒሊክ ለመውቀስ ሳይሆን የሆነውን ግን መገለፅ አለበት። በመሆኑም አፄ ሚኒሊክ የተለያዬ ታሪክና አመጣጥ ያላቸው ህዝቦች ጨፍልቀው የፈጠሩዋት አገር መሆንዋን ግን መገንዘብ ያስፈልጋል ። ስለዚህ ከላይ የተገለፀው አስተሳሰብ ጥሞና ሰጥቶ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ፣ አሁንም

         ታሪካዊ አመጣጣችን ወደ ጎን በመተው ፣ በመቶ አመት የታሪክ አስተሳሰብ ቅኝት እኛነታችን ጨፍልቀው በጎሳ ፣ በዘር ፣ በጎጥ በመከፋፈላችን ነው ችግሩ የተፈጠረው ብለው ይሳለቁብናል።

         አሁን ያለው የአገራችን ችግር ዴሞክራሲ ለቀቅ ስለተደረገ ነው ብለው ራሳቸው ያሞኛሉ ። ነግር ግን በቀድሞ ኢህዴግ በትግራይና በአፋር የተለዬ ዴሞክራሲ አልነበረም። ነግር ግን በነዚህ ክልሎች አሁንም ድረስ ሰላም አለ። ማንም ሰው በማንነቱ አይፈናቀልም፣ አይሞትምም።

         ከምንም በፊት ሰው ነን የሚሉ አሉ። በመሆናችን ሰው በመሆናችን የኋላ ታሪካችን ጨፍልቀን እንጓዝ የሚሉም አሉ። ነገር ግን አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ይህንን የሚፈቅድ አይደለም ። ለምን ቢባል በተግባር ስንመለከተው በማንነቱ ብቻ ያለፍርድ ሰው እየተፈናቀለ ፣ እየሞተ ፣ ንብረቱ እየተዘረፈ ነው ወዘተ። ስለዚህ የበለጠ መጠራጠር ያነገስ ሁነዋል።

መፍትሄ፥

ማንም ከማንም የበለጠ ጥገኛ የምንሆንበት አገር/ክልል አይደለም ያለነው ። እንዲሁም መበታተን፣ መጠፋፋት ለሁላችን ጉዳት ነው። ስለዚህ ሁሉም ክልሎች እውቅና ማግኘት አለባቸው። እውቅናው የየራሳቸው ፖሊሲ ማውጣት ፣ ማስፈፀም፣ የመከላክል አቅም ማሳደግ የሚችሉበት ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል እላሎህ ። እንደ አገር ደግሞ በጋራ የምንሰራባቸው ሊኖሩ ይገባል። ስለዚህ በኮንፌዴሬሽን መጣመር አለብን እላሎህ።

ይህ ማድረግ ባልይቻለና የተንሻፈፈ ምክንያት ሰጥተን የምንጓዝ ከሆነ ግን ወጮ ቢገለብጡት ወጮ ነው የሚሆነው።

 

 


Back to Front Page