የብርቱካን
ሮቮሎሽን ለምን
በኢትዮጵያ ሊሰራ
አልቻለም? አስተያየት.
በመጀመሪያ
ለወንድሜ ጐርፉ ያለኝ
አስተያየት ከፍተኛ
ነው፡፡ ምክንያቴም
እሳቸው አስበውና
ተመራምረው
የአገራቸውን ጉዳይ የብርቱካን ሮቮሎሽን
ለምን በኢትዮጵያ
ሊሰራ አልቻለም ብለው
ላቀረቡት ሃሳባቸው
የኔን አስተያየት
በተጨማሪ እንዲህ
በማለት ለመናገር
እሞክራለሁ፡፡
1)
የኢትዮጵያ
ብርቱካን ሮቮሎሽን
ለምን ግቡን ላይመታ
አስቻው? ምንስ ነበር
ምክንያቱ? ባጭሩስ
ለምን ሊቀር ቻለ?
ኡክራይን ግን ያን
በምን ሁኔታ አልፋ
ወደግቦቿ ደረሰች፡፡
ኡክራይንም ከራሺያ
ጋር ከፍተኛ ፍጥጫና
ከሕዝቧም ቁጥሩ እጅግ
የበዛ ያለው በአገሪቱ
ምሥራቃዊ ክፍል ውስጥ
ባጠቃላይ
ራሺያዊያኖች
ናቸው፡፡ ጠቅላይ
ሚኒስቴር ወይም ፕሬዚዴን
ሁሉግዜም ቢሆን ከ2ቱ
አንዱን አያጡትም፡፡
የነኛ የራሺያኖቹ ፍላጐት
ከሞስኰ ጋር የሰመረ
ነው፡፡ የነኝህናዎቹ
ደግሞ ከጀርመኖች ጋራ
የተቆራኘ ነው፡፡
ልዩነቶቹ እዚያጋ
ናቸው፡፡
2)
እንጊህ
በኢትዮጵያስ ለመሆኑ
የኢትዮጵያ ህዝቦች
ተዛማች ቤተሰቦች የመሰሉ
የጐረቤት አገሮች
አሉን ወይ? ቢኖሩንስ
እነሱ ለኛ ጥያቄ ምን
ያህል አስተዋጾ
አላቸው ወይም
ያሳያሉ፡፡ በዚያም
ላይ በቅርብ ጂቡቲ
ኤርትራና ሶማሊያ
ኬኒያውና ሱዳኖች
ናቸው ዘመዶችም ይሁኑ
ወይም ሌላ ምክንያት
ቢገኝም፡፡ ታዲያ
እነኝህ ሰዎቭ
ራሳቸውን አልፈው ለኛ
ችግር ደራሽ ናቸው
ወይ? አይደሉም ነው
መልሱ፡፡
3)
ኢትዮጵያ ውስጥ
አንድ ነገር ሲታቀድ
በመጀመሪያ እድል
ሰጥቶ ሊታሰብ የሚገባው
በአገሪቱ የመኖር
የመቀጠል ሕልውናዎቿ
ላይ መሆን አለበት፡፡
ምክንያቱም ቀድሞም
ሆነ እስከዛሬ ድረስ
የመገንጠልን
ፍልስፍናዎች እንደነጻነት
አምጭ አድርገው
ቆጥረውት የሚጓዙ
በውስጣችን
ስለሚገኙ፡፡ የገዛ
አገራቸውን እንደውጭ
ሰዎች ሆነው ለቅኝ
ገዥዎችና ኃያላን አገሮች
የራሳቸውን ጉዳይ
በማጋለጥ በግርግር
የነሱን ሃሳብ ለማሟላት
እድሉ ይገጥማቸው
ይሆናል በሚል ብዙዎቹ
የብርቱካኑን ሮቮሎሽን
እስከዚህ ግድ
አልሰጣቸውም
ነበር፡፡ የነሱ
አስተውሎ ያለው በአገራቸው
ላይ ቆይቶ ሊደርስ
የሚችለው በማሰብ
ስለሆነም፡፡
4)
ማንም ሕዝብና
አገር ለውጥ
ይፈልጋል፡፡ ግን ይህ
ለውጥ ተግባብቶ በመስራትና
ብሎማ ከፓርላማው
ጀምሮ እስከ ህዝቡ
ድረስ የሚጠቅመውንና
የሚጎዳውን ነገሮች
አብሮ ተመካክረውበት
ነበረውይ? እንግዲህ
መሆን ያለበትን
ተረስቶ እዚያ አስመራ
ወይም የሻዕቢያ
ኤርትራጋ ምን
አስፈልጓቸው
እስከዚያ ተጉዘው ሄዱ
ጠቅላይ ሰፈራቸውንም
በዚያ በማድረግ በሆርን
አፍሪቅ ራዲዮና
ቴሌቪዥን ላይ
ሳምንቱን ሙሉ
ከመቀመጫቸውም
ሳይነሱ ምን ሲሰሩ
ነበር ወደ ኢትዮጵያ
ይተላለፍ የነበረው
ዜና ምን ዓይነት የመሰለች
አገርን ለመፍጠር
ነበር ዓላማቸው?
መተናት ያለበት ያን
ጉዳይ ይመስለኛል፡፡
5)
የኡክራይን
ሕዝብ ሌላ አማራጭ አሁንም
ድረስ አለው፡፡
ያንንም አማራጭ ህዝቡ
ብቻ ሳይሆን ውሾቻቸው
ጭምር ይረዳቸዋል
በሚል እገምታለሁ፡፡
በዚያም ላይ
ኡክራይኖች ሲበዛ በዘመናዊ
እውቀቶችና በሳይንስ
የተራቀቁና ዓለም
እስከዛሬም
ያልሰራቸውን ዘመናዊ
ትላልቅ የሰውም ሆነ
የዕቃ ማጓጓዣ
አይሮፕላናቸውን
ለተመለከተው ብዙዎቹ
የሰለጠኑ አገሮች
ከነሱ ነው የሚከራዩት
አንዳንዴ ሲያስፈልጋቸው፡፡
በደንብ አድርገው
እኛን በእውቀት
ይበልጡናል ማለት ነው፡፡
በአላማና
በአስተሳሰብ ቢለያዩ
እንኳ በአገራቸው
ውስጥ አብረው ለመኖር
የሚመርጡ ካልሆነ
በስተቀር እንደ እኛጋ
የጽንፈኛ ስብስቦችና
የጠመንጃን ማምለክ
ፍላጐቶች
የሏቸውም፡፡ በነዚያ
ምክንያቶች ዘወትር ጥሩ
ይኖራሉ፡፡ የቶር
አይሮፕላኖችን
ሳይቀር ይሰራሉ
ታንክና ጠመንጃዎችንም
በመስራት ለዓለም
ገበያዎች
ያቀርባሉ፡፡
6)
እኛስ? ሌላው
የአሜሪካ የስለላው
ድረጅት ባለሶስት
ፊደሉ ከ78 ሚሊዮን ዶላር
የበለጠ ለዚያ ሳምንት
ለፈጀ ኦሬንጅ
ሮቮሎሺን ወጭ
አድርጐላቸው ሕዝቡ
በድንኳንም ሆነ
በምግብ አቅርቦትና
በሞቃት ነገሮች
ክረምት ስለነበረ
እንዲታጀቡ ከሙዚቃ
ጋር አድርጓል፡፡
የምዕራባዊያን የዜና
ምንጮች እነ ቢቢ እና
ሲኤነን 24 ሰዓት ሙሉ
ሌላ ሳያወሩ
ስለኡክራይን ጉዳይ
ኮመንቶችን
ሰንዝረዋል፡፡
እኛስጋ?
7)
አሁንም
ኡክራይኖች የምስራቁ
ክፍል በተለይ
ከራሺያጋራ
ተደባልቀው የመኖር
ፍላጐቶች እንዳሏቸው
ያስታውቃሉ፡፡ ያም
የሚሆነው ኡክራይን
የናቶ ቃልኪዳን ውስጥ
እገባለሁ ካለች፡፡
ከዚያም የአውሮጳው
ማሕበር ውስጥ አባል
ልሁን ካለች፡፡
እነኛዎቹ ያን ጊዜ
ወደ አገራቸውና
ዘራቸው ሕዝባቸው ወደ
ሩሲያዊያን ቤታቸው
ትተዋቸው ያመራሉ
ማለት ነው፡፡
አማራጫቸው ያን ይመስላል፡፡
8)
በኛስጋ በአገረ
ኢትዮጵያ? እኛው
በኛው ተቻችለን
በስልት ካልተንቀሳቀስን
በስተቀር አንዱም
ቢሆን ሊሳካልን አይችልም
ወደ አደገኛ ሁኔታዎች
ላይ ነው ሊወስደን
የሚችለው፡፡ ዛሬ አንዳንድ
ሰዎች
እንደሚመስላቸው
ሳይሆን አሁንም ነገም
ተቻችሎ ካልተሄደ እጅግ
አደገኛ ወደሆነ
አቅጣጫ አገራችን
እንዳታዘነብል
ነው፡፡ ያየነበረው
የአሰላለፍ ሁኔታ
የሚያስገርም ነው፡፡
ሁሉም በአንድ ቀንና
በአንድም ሳምንት
ውስጥ ይፈትጸም
የሚሉም ይገኙባቸው
ነበረ፡፡
9)
እንደአገራቸውን
ያሉ አገሮች ያን
የመሰለ ቅጽበታዊ
ውርጅብኝ ራሳቸውን
አስቷቸው ሰውነታቸው
ዞሮ ይወድቃሉ፡፡
ይንኰታኰታሉም፡፡ ለመሆኑ
የቅርብም ሆነ የሩቅ
ወዳጅ አሉን ወይ?
በበኩሌ ኢትዮጵያ
የአፍ ወዳጆች
እንዳሏት ቢረዳም
የልብ ወዳጅ
እንደሌላት አውቃለሁ
ብል አልተሳሳትሁም፡፡
ለምን ይቸኩሉ ነበር
የዚያን ጊዜ ሰልፉም
ሆነ ጥያቄ አንሽዎቹ?
እኔ አላውቅም
አልተረዳኝም፡፡
ምክንያቱም
አንደኛውን ስንጠቅም ሌለኛውን
እያራቅን እንደነበረ
አድርጌ ነው
የምረዳው፡፡
10) እንግዲህ ሥልጣን
ወይስ ለምን ነበር
ያሁሉ ችኮላ? ለምን
ወደ ፓርላማ ገብቶ
ከዚያ በኋላ ቀስ
በቀስ ተቀራርቦ
በመስራት ፍላጎትን
ለማንጸባረቅ ለምን
ሳይሞከር ቀረ? ያሁሉ
ታዲያ መልስ የሚፈልጉ
ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ከዚያስ
በሆላንድ አገር
የተደረገው የሰነድ
ፊርማዎችስ እነማንን
የሚጐዱ ማንንስ
የሚጠቅም ነበረ?
እንግዲህ የሲዳማ
አርነት ግንባር?
ወይስ የኦጋዴ
ተገንጣይ ክፍልን?
ካልሆነስ የኦነግ
በጠመንጃ በኃይል
ተመክቶ ኢትዮጵያን
ለመቆጣጠር ከዚያም
ወያኔ ኢሕአዴግን
ካባረርናቸው በኋላ
ከዚያ በመቀጠል
የምናደርጋቸው
ጉዳዮች ምንድናቸው
በሚል የሚያነሧቸው
ጥያቄዎቻቸው @ህዝብ
ይበል@ የሚለው
ነው፡፡ ያንንም ስንመለከተው
ልክ የሻዕቢያ የነበረ
ጥያቄን
ይመስለናል፡፡
11) ነጻሕነት ወይስ
ባርነት የትኛውን
ትመርጣለህ ነበር?
በህዝቡም ህሊናዊ
አስተሳሰብ ላይ
ከፍተኛ ተጽኖዎች
ነበሩበት ጠመንጃ
ከፊቱ እየተቀባበል
ሲመለከት ወደደውም
ጠላውም ያንኑ
ያቀረቡለት ከባርነት
ይልቅ ነጻሕነትን
ነበር የመረጠው፡፡
አሁንም የብርቱካኑ ሮቮሎሽን
ቢቀናው ኖሮ
በኢትዮጵያ ላይ
ሊደርስ ይችል
የነበሩት አደጋዎች
ከላይ በቀላል አማርኛ
ያነሳኋቸው ናቸው፡፡
12) በበኩሌ ለምን በምን
ዓይነት መሰራት
እንዳለበት ያገር
ጥያቄን የሚያውቁት
ስንቶቹ ነበሩ
ካልሆነስ በቂም በቀል
ዘመቻስ የተሰለፉት
ስንቶች ናቸው? እነኛን
ሲያመዛዝኗቸው
አቋሙን የሳተ ከፍተኛ
ወከባዎችና ብሎም
የስድቦች ጋጋታዎች
የበዙበት ያሁኔታ
አሁን አልፎ
ሲመለከቱት እንዲህ
ቀላል ነገር
ይመስላል፡፡
13) እንግዲህ
የኡክራይኑ የሚለው
ከኢትዮጵያ
የብርቱካን ለውጥ!
የኡክራይኑ
በምዕራባዊያን
በቀጥታ የደገፈ
ነበር፡፡ ከአሜሪካ
እስከጀርመኒና ኢንግላንድ
ድረስ የቤተሰብ ጉዳይ
አድርገው ነበረ
የሚወያዩበት
በኢትዮጵያስ? አንድም
ተወያይ አላየሁም፡፡
የሚሆነውን
የመጨረሻውን
ከመመልከት በስተቀር
አንድም የውጭ መንግስት
ግድና መንፈሳቸውንም
አልሳበውም፡፡
14) በመጀመሪያ
አገራችን ትንሽ
እፎይታ ያስፈልጋት
ነበር፡፡ ያንን የዴሞክራሲ
መጀመሪያ ይዞ
በመንቀሳቀስ ለ2011
ለሚኖረው ብሔራዊ
ምርጫ በቀጥታ ከህዝቡውስጥና
ከአለውም ሲስተም ጋር
ተዋህዶ በመጓዝ
በሚመጣው ምርጫ ያለምንም
ሌላ አማራጭ ከህዝቡ
ጋራ ጠዋት ማታ
አብረው በኃሳብ
እየተገናኙ ቢጓዙ ነበር
በሚቀጥለው ሕጋዊ
ምርጫ ጊዜ ምናልባት
የአጠቃላይ ምክር
ቤቱን ወንበር
ባይቆጣጠሩት እንኳብ
ለማሸነፍ
የሚያበቁትን
ወንበሮች በማግኘት መንግሥት
ይመሰርቱ ነበር፡፡
15) ያለፈው
አልፎአል፡፡
ከእንግዲህ ምን
መደረግ አለበት?
ይሄን ያው የብርቱካኑ
ሮቮሎሺን ሰዎቹ
መሪዎቹ ተፈተዋል
የሚያዋጣቸውን እነሱ
ራሳቸው ማወቅ
አለባቸው ነው፡፡ ይህም
ሁኔታውን በማቀዝቀዝ
ጥሩ ሃሳቦችንም
በማመንጨት በአገርም
ሆነ በውጭ የሚገኙትን
ደጋፊና
ከአባሎቻእውም ጋራ
ቀስ ብሎ መጓዝ ምን
እንደሆነና ብሎም
ከአነጋገሮችና ብሎም
አስተያየት ሰጭዎች
ሳይቀሩ ሕዝብና መንግሥትን
በመለየት ትክክለኛና
ተገቢ ጥያቀአቸውን
ካሁኑ ለማድረግ መንቀሳቀስ
ይገባቸዋል ነው፡፡
16) በገዢው ፓርቲና
መንግሥቱ ማድረግ
የሚገባቸው ቢኖር
በነሱ ጊዜ ለኢትዮጵያ
የተመኙላትን
የመበልጸግ
እቅዶቻእውን በስራ
በመግለጽ አሁንም ለ2011
ድጋሜ የምርጫው
አሸናፊ ለመሆን መጣር
ይኖርባቸዋል፡፡
ነገር ግን እንዴት
ዓይነት ነገሮች ናቸው
ብልጽግናን
ሊያጐናጽፉን
የሚቻላቸው? ማንም
በየመንደሩ
ከሚኖርባቸው አካባቢዎች
ጀምሮ አዳዲስ የስራ
ፈጠራዎችን በማሰብ
ፈጥሮ ያም ፈጠራ ለራሱ
ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃ
አህጉሩና ብሎም
ለዓለም ገበያ ድረስ
አቅራቢና መታወቅ
ካተረፈ
የሚያመጣለትን
ብልጽግናዎች ስራውን
ሲጀምረው ያንንም
ተስፋ አድርጐ
መንቀሳቀስ ሲችል
ነው፡፡
17) ምን አይነት የስራ
አፈጣጠሮች? በዚህ
ጊዜ አንድ ሰው
ከመንደሩ ጋራ ተባብሮ
ጥያቄና የሚዋጣውን
ሥራ ለመስራት
ለወረዳው ምክር ቤት
ከዚያም ለአውራጃው
ቀጥሎም ለክልሉ
ምክርቤትና መንግሥት
ድረስ የተቀጣጠሉ
ሰንሰለቶችን
በማሳመን አልፎ
ጥያቄዎቹ ከጸደቁለት
ያለምንም ችግር
ገንዘብ በቀላል ወለድ
ከአገሪቱ ብሔራዊም
ሆነ ንግድ ባንክ
ገንዘብ መበደርና
ሥራውን መስራት
ይችላል
ይመስለኛል፡፡
18) ያንን አድርገው
ለምሳሌ በአገራችን
ዛሬ ሳይሆን በኛ
የልጅነት ዘመን የምች
መድሃኒት የድንገተኛ
መድሃኒት የቁርጠት
መድሃኒቶች የሚገኙት
ከሰፈሩ አዋቂዎች
ነበር፡፡ ያን
የመሰለውን ሁኔታ ልክ
እንደቻይናዎች እኛም
በአገራችን
የመድሃኒት አጠቃቀም
ብንጠቀም የቱን ያህል
ከዚህ ኬሚካል
ሳይንሳዊ ግኝቶችም
ለመገላገል
ይቻለናል፡፡ ነገር
ግን ይህን ስል ዘመናዊውን
ግኝቶችን አቅልዬ
ለማየት ሳይሆን
በተለይ በገጠሪቱ
ኢትዮጵያ የሚኖሩት ያደጉበትንና
የኖሩበትን ሁኔታ ጥሩ
አድርገው ስለሚረዱ
እነሱ በመሰላቸው
ስልጠን ባለመልኩ
ተዘጋጅቶ
ቢቀርብላቸው ሁሉም
ሊጠቀሙበት ያስችላቸዋል
ማለት ነው፡፡
19) በጓሮ አትክል
የጐመን አቅርቦት
ለአዲስ አበባ
ሆቴሎችች የፍየል እና
የበግ ሥጋ አቅሮት
ቨማርባቱና
መንከባከቡ ላይ
የተመሰረተ ዘመናዊ
ንቃት ባለው ሁኔታ
ሲሰራ፡፡ ቀጥሎም የወተት
አቅርቦት፡፡ ከዚያም
በሰፈሮች እና በአዲሱ
ትውልድ አጋዥነት ከትምህርት
ቤትም መልስ የኪስ
ገንዘቦችንም
ለማግኘት አንዳንዴ
ለዚያ ለቤተሰብ ከ2
እስከ 3 ሰዓት በማገዝ
በሳምንት ብዙ ገንዘብ
ማግኘት ይቻላል፡፡
ክፍያው በሰዓት ታስቦ
መከፈል አለበት፡፡
ከዚያ ያስራም
የቦሌኬቶች ሥራ
ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያዊያን
በየትም ሥፍራ ያሉት
የሚኖሩት የአገራቸውን
ደንና ጥሻዎች
ተንከባክበው መያዝ
ይጠበቅባቸዋል፡፡ለሚቀጥሉት
100 ዓመት ለሚመጡት
ትውልድ መልካም
አገርን ከመልካምም
ፍሬዎችና ጥላነቷ ጋራ
ለማስረከብ ከተፈለገ
ለእንጨት ሲባል፡፡
ቤትንም ኬንጨት ተቆርጦ
ጣራና ግድግዳ ማገርና
ምሶሶ በማድረግ
አገሪቱ ቀድሞ 40%
የነበራት የጫካ
አገልግሎት ዛሬ 2% ብቻ
መገኘቱ ከእንግዲህ
ከ25 ዓመት በኋላ አገራችን
የሰሃራ በረሃ መሆኗ
አይደለም ወይ? በነኛ
ምክንያቶች የተነሳ
በአገሪቱ ማሽኖች
የተግባረ ዕድ
ተማሪዎች ለመመረቂያቸው
ሲሰሩ በመጀመሪያ
መስራት ያለባቸው
እንዴት በአንድ
ቤተሰብ አማላኝነት
ቦሎኬቶችን ማምረት
ይችላሉ
በየአካባቢያቸው
ብለው በማሰብ በርካሽ
ዋጋ ሊጠቀሙበት
የሚያስችል ማሽኖችን
ሰርተው ማቅረብ
ሲችሉ፡፡
20) ቀጥሎም ይህን
ፕሮጄክት ለመስራት
የሚነሱ ገበሬዎችም
ሆኑ ኗሪዎች በተጨማሪ
ለመስራትና
ኑሯቸውንም ለመደገፍ
ለማሳደግ መሆኑን
ተገንዝበው ብሎም
አገራቸውን
ለመንከባከብ መሆኑን
ካወቁ ሁሉም የጀመሩት
ሥራ
ይቀናቸዋል፡፡ሳይታሰብም
እነሱ ይከብራሉ፡፡
ምክንያቱም ያገራቸው
ሕዝብ እነሱ
የሚያመርቷቸውን
ምርቶቻቸውን ህዝቡ
በፍላጎትና በቶሎ
ስለሚገዛቸው፡፡
ያገሪቱም መሬቶች
ያርፋሉ ውስጣቸውም
አፈሩ እንዲሰባ
ይሆናል ማለት ነው
ምክንያቱም ገበሬው
ሌላ ገቢ ካገኘ
ዘወትር በእርሻ ላይ
ብቻ መተመድ
አይኖርበትም፡፡
በምትኩ ግን ስለ
መሬቱ ስለጎርፍ
መሸርሸርን
በመመልከት መሬቱ
እንዳይፈር
በመገንባትና
በሽቦዎች በመወጠር
አፈሩ እንዳይሄድ
ይከላከላሉ ማለት
ነው፡፡ ያም ስራ
ስለሆነ እገዛ
ከወጣቶች
ይፈልጋሉ፡፡
ለወጣቱም ትውልድ
ካገሩ መሬት ጋራ
ሲዳረቅ ሲያመሽ ጥሩ
ስሜት በውስጡ
ሳያስበው ያገኛል፡፡
21) በኢትዮጵያ ግዛቶች
ውስጥ ግን ያለ
ልዩነቶች ሁሉም የጡብ
ሥራዎችን ብዙ
ገንዘቦች ሊያመጡለት
እንደሚቻላቸው
በማወቅ ለአገሪቱ
ግንባታና ለወደፊቱም
የኢትዮጵያ ቤቶች
በእቅዶችና ፕላን
ባለው መንገድ
ተስተካክለው ከተሰሩ
ህዝቡ በቀላሉ
ሳይታሰብ ወደ 21ኛው
ዘመን መኖሪያ ቤቶች
ውስጥ ሊኖር ገባ
ማለት ነው፡፡ ይህም
ሲሆን በየጋራው ላይ
ሆኖ በኩራዝ መብራት
በማትረባ ቅሊሶ ቤቶች
ከመኖር ይልቅ ከጋራው
በመውረድ ተጠጋግቶ
በመኖር ዘመናዊና
በዕቅድ የተመጸረተች
ሰፈር ውስጥ አብሮ
ተቀራርቦ መኖር
ይገባል፡፡ ቀጥሎም
የባንክ፡፡
የስልክ፡፡
የትምህርት ቤት፡፡
የፖስጣ፡፡ የውሃ፡፡
የስፖርት ቦታዎች
በህብረት፡፡ የሰፈር
ገበያ በቤት ውስጥ
ሆኖ ህዝብ በፈለገው
ጊዜ ሁሉንም ማግኘት
የሚችልባቸው
ማርኬቶች በህዝቡ
የአክሲዮን ገንዘብ
ሁሉም ሰፈር በማቋቋም
በባንኩ አማካኝነት ቁጥጥሩ
ዘወትር እየተደረገ
ብልጽግናውም በዚያ
በኩል ሊመጣ ይችላል፡፡
የህክምና ጣቢያ፡፡
ክሊኒክና መድሃኒት
ቤቶች፡፡ ከተቻለም
ሆፒታልና ማዋለጃ
ሃኪሞች የበዙበትም
ማድረግ ይቻላል፡፡
ይሄን ሁሉ ማድረግ ያለባቸው
ተቃዋሚውም ሆነ
የመንግሥት
ይሁኝታዎች
ሲታከሉበት ህዝቡ ራሱን
በራሱ ከያዘው ችግርና
ዘለአለምም ካለበት
ድሕነት ለመውጣት ብዙ
ዓመታት
አይወስዱበትም፡፡
ከማመስገን
ጋር
መከተ
ሰው
Aug
04, 2007