ዛሬ የተሰማው የኦጋዴን ተገንጣይ ቡድን በ… የሚረዱት አስፈላጊው እርምጃ ስለተወሰደባቸው

 

 

ለንዶን ተሆኖ http://www.voanews.com/english/2007-08-07-voa30.cfm የጽንፈኞቹ ቃል አቀባይ የሚሰጣቸውን አስተያየቱን ሄዳችሁ እንድትመለከቱት እጋብዛችኋለሁ፡፡ ያም የሚያሳየን የምዕራባዊያን እያለቀሱ ሳይሆን እየሳቁ መቅበር የሚመስል  ቴያትሮችን እንድናስባቸው ያደርገናል፡፡ የቀይ መስቀሎቹ ጫጫታዎች ባለፉት ሳምንታት ሲታሰቡ ምንኛ አገራችን በሌላት ኤኮኖሚ እነኛን ከይሲዎች ለማደንና ወደ ፍርድ ቤት ይዞ  በማቅረብ ለማስቀጣት የምታደረው ውጣውረዶችን ሳያስቡና ሳይመለከቱ ከኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣና ከዋሽንግተን ፖስት ጋር በቀጣይነትም ከአለም አቀፉ የቀይመስቀል  ድርጅት ግር ያች አገር ስትመላለስ ከርማለች፡፡

 

እረ ለመሆኑ የብርቲሽ መንግሥት ፀረ ቴሬሪስት ነኝ፡፡ የአሜሪካም መንግሥትና የምስተር ቡሽ አስተዳደር አሸባሪዎችን እንዋጋለን እያሉ ጠዋትና ማታ ሲነገር እንሰማለን? ነገር ግን እዚያው ከምስተር ጎርደን ብራውን አገርና መናገሻ ከተማ በምሥራቁ ከተማ ለንደን ኖአሪዎች ከሆኑት ውስጥ የአሸባሪውና ምንም ያላደረጉ ሲቪሎች ላይ ባለፈው ቀናት ቦንብ በመወርወር 1 ሰው ሲሞት 8 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ይታወቃል? እንግዲህ ኢትዮጵያ  ይህን ያደረጉትን ሰዎች እና በአጠቃላዩ በኦጋዴን ክልላዊ መንግሥት ውስጥ እየተዘዋወሩ ነውጥ እና ግድያዎች ድምሰሳዎችን እየፈጸሙ ያሉት ሰዎች  መሪዎቻቸው ዋናው ምሽጋቸው ለንደንና አሜሪካ ውስጥ እንደሆነ ግልጽ ሆኖ  ይስተዋላል፡፡

 

ታዲያ እነዚህ አገሮች ኢትዮጵያ ቴሬሪስቶችን ለመፋለም የቅርብ ረዳታችን ናት ብለው የሚያምኑ ንከሆነ በቅድሚያ እነኛን ሰዎች ሰብስበው አሳልፈው ለኢትዮጵያ እንዲሰጡ ይገባል? ምክንያቱም  የነኛ ነፍሰ ገዳአዮች ሶንኮፋቸው የሚገኘው እዚያና በተለይም  በአሜሪካ ማስሜዲያዎችና በተለይም በቢሲ ሃሳባቸውን ያለምንም ፍርኃት ሲሰጡ ስለሚሰሙ፡፡

 

የኒው ዮርክ  ታይምስ ጋዜጠኛ በቅድሚያ ቪዛ ጠይቆ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው ስለምን ነበር?ላሊበላን ጎንደርንና አክሱምን ሄዶ ለመጐብኘት ነበረ? ግን እሱ ያን ሳያደርግ ኦጋዴን ውስጥ ሄዶ  በቀጥታ ለኒውዮርክ ታይም ዜና ዘጋቢ ሆኖ ተቀምጦ  ነበር? አሳዛኝ ነገር ነበር፡፡ ከዚያም ሲለቀቅ በኬኒያ በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድምበሮች መሃል ሆኖ የበለጠ የጥላቻ ዘገባውን ሲያወርደው ከረመ? እንግዲህ ለመሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማለት እስከምን ድረስ ነው በዲፕሎማሲ መንገድም የበላይነት መኖር አለበት ወይ? የራሱን ጥቅም  ለማስጠብቅ የሚጥር አገርና መንግሥት እንዴት የሌላውን ደም አፍሳሾችና ዛቻና ጦርነት አካኃጆችን የነሱን ወኪል  አሳልፎ  ለጠያቂዋ አገር አይሰጥም? ሌላም  ብዙ መነሳት የሚገባቸው ጥያቄዎች ነበሩ ግን አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ ትቼዋለሁ፡፡

 

አሁንም ይህ በአንድ ሉዓላዊት  አገርና ነጻነት ላይ የተነጣጠረ አጥፍቶ መጥፋት እርምጃን አሜሪካንም ሆነች እንግሊዝ ከግምት ውስጥ አስገብተው በመመልከት ለኢትዮጵያ ድጋፋቸውን ሊገልጹላት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከወዲያ የሶማሊያ ጋንጊስተሮች ጋራ የምታደርገው ጦርነቶች ያም በየቀኑ ሰዓቱ በማይታወቅበት ጊዜያቶች ሁሉ መሆኑንም መገንዘብ አለባቸው፡፡

 

ከወዲህ በገዛ አገርዋ  ውስጥ በሰሜን ለጊዜው የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ  የሚታየው ከሻኢቢያ ጋራ ሆነው ከኦጋዴን ትስንፈኞች እስከ ኦነግ ተገንጣዮች ከሶማሊያ አክራሪ አሸባሪዎች እስከ ትጥቀኞቹንም በማስታጠቅ በማስተማርና የበለጠም  ወታደራዊ ስልቶችን በማለማመድ ያንን የመሰለም ጭካኔ የተመላበት ተግባራት ለመፈጸም ማሰባቸው ማድረጋቸውና ያንንም ለምን አደረጋችሁ ተብለው ሲጠየቁ ያውም እየፎከሩ ገና ብዙ ይቀረናል ጠንካራዎች ነን ማለታቸው ሲታሰብ ይህ ጉዳይ ወደ ብዙ ችግር አገራችንን ከመክተቱ በፊት እንደዚያ የሚያደርጉና እየፈጸሙ ያሉን በጥባጮች ኢትዮጵያ ኪሳራ በኪሳራ በማድረግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ ልታቀርባቸው ይገባል? ከዚያም ያየኦጋዴን አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ለራሳቸውን ለመከላከል ብሎም  ለጥቅምና ለሠላማቸው ሲሉ ከክልላዊና ከፌዴራል  መንግሥት ኃይላት ጋር አብረው በመቆም ጥቅማቸውን አግኝተው እንዳይጠቀሙበት የሚከለክሏቸውን አጋሚዶዎችን በመቃወም  አንድ ውሳኔ ላይ ሊደርሱ ይገባል?፡፡

 

የኢትዮጵያን ክብሮአንና ልዕናዋን ለመናድ የሚሞክር እና ብሎም ሲበጠብጥ ሲያስበጠብጥ ስራዬ ብሎ የሚኖሩ ካሉ ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ጠበቆች ቀጥራ በዴ ሃጉ የዓለም ፍርድ ቤት ከሳ ከየ አድራሻቸውም ተጠርተው እንዲመጡ እና ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ እንዲሰጡ የማድረግ የማስደረግ ችሎታ አላት ያን መብቷንም አስታውሳ ልትጠቀምበት ይገባል?፡፡

 

በመቀጠልም የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛን ሰው እዚያው ኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው የአሜሪካ ፍርድ ቤት በመክሰስ ይህ ሰው በአንድ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱንም በማስመስከር ልታስቀጣው ወይም ኢትዮጵያን ይቅርታ እንዲጠይቋት ይገባል?፡፡

 

የሻኢቢያ መንግሥት ይህን የመሰለ   ለሌላው በሚያስደንቅ ሁኔታ ንቀትን ተላብሶ በኢትዮጵያ ላይ ይህን ያህል  ጥፋትና ጥቃት የማድረስና እያደረሰም ስለሚገኝ እነሱንም  በዴሃጉ የአለም ፍርድ ቤት በቅድሚያ ኢትዮጵያ ከሳ አስፈላጊውን ወቀሳም ሆነ ቅጣትና ካሳ ለኢትዮጵያ እንዲከፍሉና ከዚያም የመሰለ ጥፋታቸውና ጥቃታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቆጠቡ እንዲደረግ ይገባል፡፡

 

በኢትዮጵያ ላይ ደንቃራ የሚያደርጉ ሁሉ በነሱም ላይ ኢትዮጵያ ደንቃፋ ነገሮችን መሰንዘር እንደምትችል ለመጀመሪያ ጊዜ አገራችን ችሎታዎቿን ማሳየት እንድትችል ሙከራዎች ማድረግ ይጠበቅባታል? እንግዲህ ዓለም ዓቀፍ ሕግ የማይገዛውና ሥራዓት ዓልባ የሆነን ነገር አገራችን በኃይሏ ተጠቅማ ከትከሻዋላይ ማስወገድ ይጠበቅባታል፡፡

 

ሠላም ነጻነትና ስምምነት እንዲኖራት ኢትዮጵያ የምትወድ መሆኗንም እስከዛሬ አሳይታለች አስመስክራለችም፡፡ ያን አልፎ በህዝቦቿና በሰላሟ በልማትና በብልጽግናዋ ላይ ሻጥሮችን እሰራለሁ አወድማታለሁ እናወድማታለን ብለው የሚያስቡ እንዳሉ ቢታወቅም ኢትዮጵያ ግን እነኛን ቀድማ እነሱን ለመፋረድ ክንዶቿን ማጠንከር ልጆቿንም ጥሩ ልምምድና ብሎም እይታቸው በጠላቶቻቸው ላይ በይበልጥ እንዲያቶኩር ማድረግ ይኖርባታል?፡፡

 

እነኛን የመሳሰሉ ሁኔታዎች ሲዘጋጁና ብሎም የጠላቱን አቅጣጫና ማንነቱን ያለበትን ቦታ ጥሩ አድርጐ የሚያውቅ ሊረዳም የሚችል በተለይም ልምዱና አካባቢውን ጥሩ አድርገው የሚያውቁ የዚያው አካባቢ ሰዎችን ወጣቶችን በጥሩ ትምህርት አንጾ ከአገሪቱ ሠራዊቶች ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረግ በማዕረግንም ሆነ ለኑሮውድነት እንዳይጋለጡ ለቤተሰቦቻቸው ጥሩ እርዳታዎችን መስጠት አገሪቱን ዳር ድንበሯንና የሚወጣውን የሚገባውን ማንኛውንም ዓይነት የንግድና የኰንትሮባንድ ዘመቻዎችን ማስቆም፡፡

 

የኢትዮጵያን ብሮች በዘመናዊ ኮምፒዩተሮች እያሳተሙም እንደሆኑ መረዳት ህዝቡ እጅም እነኛ ብሮች እንዳይገቡ ይህን ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ የአገሪቱ የደኅንነት ሠራተኞች ሌት ተቀን በመስራት እነናን እንዲቆጣጠሯቸው፡፡ ይህ የሚሆነው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተማዎች ብቻ ሳይሆን በድንበር ዘለል አካባቢዎች ጭምርም መሆኑን መረዳት በጄኒሬተሮች ማተሚያዎቹ እንደሚንቀሳቀሱና ኰምፒዩተሩም ቢሆን እንደዚያ እንደሚሰራ መረዳት ይኖርባቸዋል» ከ3 እስከ 4 ሄሊኮፕተሮች ሳይታሰብ በኢትዮጵያ የጠረፎች መተላለፉያ ላይ እየተዘዋወሩ ትምህቱና ችሎታውን የቀሰሙ ወታደሮቿ በቁጭት ጭምር ያን የመሰለ ሕገ ወጥ ተግባራትን ሊለዩ ሊይዙም እንዲይዙም ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው? የኢትዮጵያ በሮች መሿለኪያዎች ብቻ ናቸው በዓለም ለማንም መተላለፊያ እየሆኑ የሚገኙት፡፡ያንን ለመቆጣጠር የሚያስችል ሁኔታዎችን ተመራምሮ  አገራቸው ከክስረት እንድትወገድ መርዳት የሁሉም ህዝብ ግዴታ እንደሆነ አውቀው ለዚያ መረዳዳት አብረው ሲሰለፉ ነው፡፡ የምንቸገረኝ ነገር ለአገራችን ጉዳት እንጂ አንድም  ልማቷን ሊሰጠን አያስችለውምና፡፡

 

በውጭው ዓለም ማንም የዩኒቨርስቲ እና የከፍተኛ ትምህር ተማሪዎች ብሎም  የሁለተኛና ከመለስተኛ ሁለተ ደረጃ ተማሪዎች ጭምር ለአገራቸው ጉዳት ከመንግሥታቸው ጋር አብረው ይሰለፋሉ? ጥቅምናጉዳታቸውንም  አብረው ያያሉ? ታዲያ የአገራችን ተማሪዎች ምርምሮች የሚያካሂዱት በምን ላይ ይሆን? ምክንያቱም አገራችን ከፍተኛ የተወሳሰቡ ችግሮች እንዳሉባት እንኳን ስንቶቻችን ነን የምናውቅላት ለዚያም መፍትሄ ይሆናል ብለን የምናስባቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ ታዲያ ያን ጉዳይ በምርምር መልክ በትምህርቱም ላይ ክፍል ውስጥ ለምን እንዲወያዩበት ትልቁም ወጣቱም ልጆቹም ስለ አገራቸው ጥናቶች እንዲያካሂዱ አይደረግም?

 

የኢትዮጵያ የብሮች ኖታዎች መቀየር ወይም  በተለያዩ የኤትሮኒክ አጠቃቀም ልክ እንደ ይሮ ገንዘቦች ባለብዙ ሚስጢራዊ ምልክቶች ተያይዞ ወጭ ተደርጎ ስሙ ሊጠቀስ በማይቻለው አገር ውስጥ ሊቀረጹ ይገባል፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያ ንግድ ባንኰችም ሆኑ ግለሰብ ነጋዴዎች ጭምር የገንዘቡን መቆጣጠሪያ በመብራት የሚሰራ ማሽኖች በብዛት ወይ አገር ውስጥ እንዲሰሩ ካለዚያም  ከውጭ ተገዝተው እንዲገቡ በርካሽም ዋጋ ተጠቃሚዎቹ ክፍሎች እንዲገዟቸው እንዲደረግ ሆኖ ዝግጅቱ ሊቀጥል ቢችል ያገራችን ኤኮኖሚ ከመዳሸቅ ይድናል በሚል አስባለሁ፡፡

 

አንድ አገርን ማጥቃት በዚህ ባለንበት ጊዜ ከጦር ሜዳው የበለጠ የሚያጎብጣት በኤኮኖሚዋ ላይ ሻጥሮች መስራት እንደሆነ ሊገለጽልን ይገባል፡፡ አገራችን አዳጊ አገር እንጂ እንደተትረፈረፋቸው አገሮች ለመድረስ ገና ብዙ አመታት ይወሥድባታል፡፡ እውነታው ግን እያንዳንዱ ዜጋ ስለ አገሩ እና ስለ ኤኮኖሚዋም ጭምር ሊያስብ ይገባዋል? የኢትዮጵያ መንግሥትም በአገሪቱ ኤኰኖሚ አውታሮች ላይ እየታሰበ ከሚደርሱ ጥቃቶችም ያገሩን ፍላጎት ለማስከበር መጣር ይኖርበታል?፡፡

 

አንድ አገር የውጭ ባለሃብቶች ወደ አገሯ ገብተው ገንዘባቸውንም አውጥተው ሥራ እንዲፈጥሩ የሚያደርጋት የሚያስችላትም? በመጀመሪያ በዙሪያዋ በአገሯ ሰላም ሲፈጠር ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደምናየው ሁሉ ባለፉት 3 ወራት አካባቢ ነዳጅ አሳሽ የሆነ የቻይና ኩባንያና ቻይናዊ ዜጐችና ብሎም ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞቹ እንደ ተዓምር በሚመስል ሁኔታ ተፈጅተዋል? ያጥያቄና ሁኔታውን ላገናዘበው እንዲህ ዝም ተብሎ  የሚታለፍ ቀላል ነገር አይደለም የሁሉንም ዜጐች መንፈሳቸውን የሚኰረኩር ጉዳይ ነው? ያን አይቶ ተቃውሞውንና ብሎም ስለ አገሪቱ ሰላም ለማግኘት ያልቆመ ዜጋ እሱ የሞተ ብቻ እንጂ በህይወቱ የሚኖር አያስመስለውም፡፡

 

  ለማንኛውም ነገር ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቃት ለልጆቿም ብርታቱን ይስጣቸው፡፡

መከተ ሰው, 08/07/07