Back to Front Page

ለ12ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በአል አከባበርን አስመልክቶ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

 

ለ12ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በአል አከባበርን አስመልክቶ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ቀን - መስከረም 29/2012

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የአገራችን ሉዓላዊነትና የሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት መገለጫ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሰንደቅ ዓላማን የነፃነታቸውና የሉዓላዊነታቸው ምልክት አድርገው የመረዳት የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው፡፡ የሪፓብልኩ ስንደቅ ዓላማ  ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ለመላቀቅ ለታገሉ አፍሪካዊ ህዝቦችም የነጻነት ኩራት መሆኑ እሙን ነው፡፡

ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው ዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል፡፡ የስንደቅ ዓላማ አዋጁ የክብረ በዓሉን ዕለት ከመወሰኑም በላይ ለብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ሊሰጥ የሚገባውን ክብርና ትርጓሜ ያብራራ አዋጅ ነው፡፡ በመሆኑም የአዋጁን ዓላማ ለማሳካት የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በተለያየ መልኩ እየተከበረ እነሆ አስራ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሮ ከአገራዊ የለውጥ ምዕራፍም ደርሷል፡፡

ባለፋት ረዥም አመታት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እ ለሀገራችን ነፃነት የተደረጉ ትግሎች የሪፐብሊኩን ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነት መገለጫና ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ አንድነት ምልክት መሆኑ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ሥራ ተሠርቷል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ሲከበርም በሪፓብልኩ ስንደቅ ዓላማ ዙሪያ ጥናቶች እየቀረቡ ግልጽነት እንዲፈጠር  መንግስት አስተባብሯል፡፡ ሰንደቅ ዓላማው የሉዓላዊነት መገለጫና ለህዝቦች ዲሞክራሲያዊ አንድነት ምልክት መሆኑ ላይ የጎላ ልዩነት ባይኖርም በዓርማው ላይ ግን በሚፈለገው ደረጃ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር የተቻለ አለመሆኑን ይታወቃል፡፡ እንዲህ ዓይነት ልዩነቶች ሲኖሩ በህጋዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ከሕዝብ ጋር በሚኖር ውይይት የሚነሱት ጥያቄዎች እየተመለሱና መግባባት እየተፈጠረባቸው እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡

 

Videos From Around The World

ዘንድሮ የሪፐብሊኩን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ማክበር የሚነሱትን የተለያዩ ጥያቄዎች ለህዝብ በማቅረብ በለውጡ ሂደት ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ለመፍጠር ያግዛል፡፡ በህገመንግስታዊ ስርዓት በምትተዳደር ሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው የጋራ በሚያደርጉ ሀገራዊ እሴቶች ላይ  እንዲወያዩ እድል ይሰጣል፡፡ በሰንደቅ አላማ የምንወክላት የጋራና የምንወዳት ሀገር እንዳለችን በማረጋገጥ መወያየትና  የሃሳብ ልዩነቶችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስተናገድ እንዲቻል ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡ የአገራችን ዜጎች በልዩነት በሚያነሳቸው ጉዳዩች ላይ የተደራጀ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በህግ የጸደቀውን የሪፐብሊኩን ሰንደቅ ዓላማ በማክበር ላይ አቋም እንዲይዝ ማድረግም ያስችላል፡፡

በመሆኑም 12ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል “ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ስናከብር መንግስት የሚተገብራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች፣ ስለ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች፣ ስለ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ ስለህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት የጋራ መግባባት በሚፈጥር መልኩ እየተወያየን በሕገ-መንግሥቱም ሆነ በአዋጆች ዕውቅና ያገኘውን ሰንደቅ ዓላማ ማክበርና በጋራ ከፍ አድርጎ ማውለብለብ ተገቢ ይሆናል፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Back to Front Page