Back to Front Page

ሰላም፣ልማትና ዴሞክራሲ የሰፈነባትን ሃገር ለመገንባት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል - ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

ሰላም፣ልማትና ዴሞክራሲ የሰፈነባትን ሃገር ለመገንባት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

 

 

https://www.ena.et/wp-content/uploads/2019/08/detsi.jpg2_.jpgኢዜአ ነሃሴ 20/2011 ሰላም የሰፈነባት ፣ ህዝቦቿ እንደታሪካቸው በመከባበር የሚኖሩባትን ሀገር ለመገንባት ሁላችንም የድርሻችንን ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ ይህን የተናገሩት ህገ-መንግስትና ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓትን ማዳን ለዴሞክራሲያዊ ሀገራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቀሌ ከተማ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ ነው ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት አንዣብቦ በታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የዜጎች መብቶች በአደባባይ ሲጣሱ የታየበት ፣ ህዝቦች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት የማይችሉበት፣ ሃብት ለማፍራት የተቸገሩበት ፣ ለጥቃት የተጋለጡበትና የህግ የበላይነት አደጋ ላይ የወደቀበት መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህ አስከፊና አደገኛ ሁኔታ ለዜጎች ህይወት መጥፋት ፣ ጉስቁልናና የወደፊት ተስፋ መታጣት ምክንያት ሆኗል ያሉት ዶክተር ደብረፅዮን በዚህ ከቀጠለ በአገሪቱ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ላይ የከፋ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት መፍጠሩንም አስረድተዋል።

እየታየ ያለውን ከፍተኛ ስጋትም ሁላችንም ተባብረን በመታገል ህዝቦቻችን የሚፈልጉትን ሰላም ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈን ችግር የሚፈጥሩ አካላትን በብቃት መመከት አለብን ብለዋል ።

አሁን በአገሪቱ በስፋት እየተከሰቱ ያሉትን ቸግሮች ህገ-መንግስቱን ካለማክበርና የህግ የበላይነትን ካለማረጋገጥ የሚመነጩ ናቸው ብለዋል።

 

እየተፈጠሩ ላሉት ችግሮች ምክንያቱ የፌዴራል ስርዓቱ እንደሆነ ለመግለጽ የሚሞክሩ ሃይሎች መኖራቸውን ገልጸው የብሄር ግጭቶች፣ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች http://aigaforum.com/images/conference.jpgመበራከታቸው በፌዴራል ስርዓት በመመራታችን ሳይሆን ህግና ህገ-መንግስትን በአግባቡ ማስከበር ባለመቻሉ የመጣ እንደሆነም ተናግረዋል።

ብዝሃነትን መሰረት ያደረገው ፌዴራላዊ ስርዓት አሉታዊና አወንታዊ ገፅታዎች እንዳሉት የማይካድ ሀቅ ነው ያሉት ምክትል ርእሰ-መስተዳድሩ አወንታዊ ገፅታውን በማጠናከርና አሉታዊ ገፅታውን በማስተካከል ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራሊዝምን ማስቀጠል አማራጭ የለውም ብለዋል።

አሁን የገባንበት ፖለቲካዊ ሁኔታ በአግባቡ ተመርቶ በጥበብ ማለፍ ካልቻልን ከባድ ጉዳት ሊያጋጥመን ይችላል በማለት ለህገ-መንግስቱና ለፌዴራላዊ ስርዓቱ መጠናከር ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል ።

የውጭ ጠላቶቻችን የሀገራችን መዳከም ብቻ ሳይሆን መበታተን የግድ አስፈላጊ ነው ብለው እየተረባረቡ ይገኛሉም ብለዋል ።

በመድረኩ ላይ ህገ-መንግስትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት ዶክተር መንበረጸሐይ ታደሰ በበኩላቸው አራተኛ ህገ-መንግስት የሆነው የአሁኑ ህገ-መንግስት የተረቀቀው በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሰፊ ውይይት ተደርጎበት መሆኑን ተናግረዋል።

ህገ-መንግስቱ ከመጽደቁና ተግባራዊ ከመደረጉ በፊትም በ22 ሺህ ቀበሌዎች ውስጥ በህዘብ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ከመሆኑም ባለፈ፣በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት የህገ-መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን ተቋቁሞና በወቅቱ ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደነበርም አስታውሰዋል።

Videos From Around The World

ህገ-መንግስቱ በተለይ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውስጥ የነበሩ መሰረታዊ የማንነት፣የሰላም እጦትና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄዎችን የመለሰ መሆኑንም አስረድተዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሔደው መድረክ ላይ ህብረ-ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት በኢትዮጵያ፣የህግ የበላይነትና ሰላምና ደህንነት በኢትዮጵያ ና ምርጫ 2012 በኢትዮጵያ በሚሉ-ርእሰ ጉዳዮች ላይ በምሁራን ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ ክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።

 


Back to Front Page