ጥቅምት 13፣ 2000
በሳንድጎ ከተማ የተነሳው እሳት ብዙ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡
ሳንድያጎ፣
ካሊፎርንያ፡ እሁድ እለት ከ8 ቦታዎች በላይ የተነሳው የዱር ሰደድ እሳት በሳንድያጎ ላይ ከ 1ቢልዮን ዶላር በላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ ባለፈው እሁድ ውች ክሪክ
(Witch Creek) ከተባው ከስንድያጎ ከተማ ራቅ ብሎ ከሚገኝ ቦታ የተነሳው እሳት ሃይሉን በመጨመር ወደ ሳንድያጎ ከተማ በመጠጋት ብዙ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በዛሬው እለት ከሰላማዊ ውቅያኖስ ወደ የብስ የሚነፍሰው ቀዝቃዛ ንፋስ ለእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች እገዛ ያደረገ ሲሆነ፣ የተወሰኑ ከተሞች ተፈናቅለው የነበሩ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከ 580ሺ ህዝብ በላይ ቤት ንብረቱን ጥሎ ወደ መሃል ከተማው በተመደቡ የመጠላያ ጣቢያዎች ሲገኝ፣ የተወሰኑ ግለሰቦች ደግሞ ወደ ዘመድ አዝማድ እና ሆቴል ተከራይተው እሳቱ እስከሚቀንስ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ ነገር ግን በሳንድያጎ ከተማ ባሉ ሆቴሎች ለስብሰባ ቀደም ብለው ተይዘው ስለነበር፣ አንዳነድ ተፈናቃዮች አልጋ ማጣታቸው ተዘግቧል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሳንድያጎ ከተማ እና ሳነድያጎ ካውንቲ (አውራጃ) ሁለት የተለያዩ መጠሪያዎች ሲሆኑ፣ ሳነድያጎ ከተማ የሚገኘው በሳንድያጎ ካውንቲ ውስጥ ሲሆን እሳቱ በጣም ያጠቃው በሳንድያጎ ካውንቲ ውስጥ በደቡብ እና በምስራቅ በኩል ያሉትን ከተሞች ነው፡፡ የተወሰኑ ኢትዪጵያውያን ከሳንድያጎ ከተማ በስተ ሰሜን በኩል ካሉት ራንቾ በርንናዶ፣ ፓዌ፣ እና ራንቾ ፓናስኪቶስ በተባሉ ከተሞች ሲኖሩ፣ ከሳንድያጎ ከተማ በስተ ደቡብ በኩል ከሜክሲኮ አገር ድንበር ተጠግቶ ወዳሉት ከተሞች ማለትም ቹላ ቬስታ፣ ኢስት ሌክ ፣ ቦኒታ ከተባሉት ቦታዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን እንዲለቁ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ቤቱ የተቃጠበት ኢትዮጵያዊ አልሰማንም፡፡
ከ 90 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ የሚኖረው መሃል ሳንድያጎ ስለሆነ እስካሁን ድረስ የተጎዳ ኢትዩጵያዊ የለም፡፡ በዚህ አጋጣሚ የመጠለያ ጣቢያዎች ለመሃል ከተማ ቅርብ ስለሆኑ ግለሰቦችን ለመርዳት
ነዋሪዎች የሚያሳዩት መተባበር በጣም የሚያስደንቅና
የሚያስቀና ነው፡፡ በአንድ አጋጣሚ በሳንድያጎ ከተማ ያሉ ታክሲ ነጂዎች ገንዘብ
አዋጥተው ውሃና የተለያዩ ቁሳቁሶችን የረዱ ሲሆን ህዝቡ ለመርዳት በጣም ሰለበዛ እርዳታ አንቀበልም የተባሉ ግለሶች እንዳሉ ተረድተናል፡፡ በዛሬው አለት መሃል ሳንድያጎ እንደተለመደው ህዝቡ
በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ ግለሰቦች በመንገድ ላይ እና ቡና ቤቶች ይታያሉ፡፡ አንዳንድ ግለሰቦች አፋቸውን ሸፍነው የሚንሳቀሱ ሲሆን ያው እንደተለመደው ከተማው ጭስ ጭስ ነው የሚሸተው፡፡ በሳንድያጎ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን የከተማዎች መዘጋጃ ቤት እና የመንግስት መስሪያቤቶች ዝግ ናቸው፡፡ በሳንድያጎ ከተማ ያሉ የቴልቭዥን ጣቢያዎች ሃያ አራት ሰዓት ያለማቋጥ ዘገባ እያደረጉ ሲሆን፣ ሪፖርተሮች እጥረት ስላለባቸው ከተለያዮ ከተሞች ሪፖርተሮች መጥተው ዘገባ የሚያደርጉት
ነው፡፡
ታዋቂው የፖፕሊክ ሪዲዮና
ቴሌቭዥን
(Public radio and TV) ማለተም NPR ና PBS ጣቦያ
KPBS የስርጭት አንቴናው ስለተቃጠለ ሪዲዮም ሆነ ቴልቪዥን ስርጭት አቁሟል፡፡ የሳንድጎ አየር ጠባይ እና አቀማመጥ ከኢትዮጵያ ጋር የሚመሳስል ሲሆን አሁን ጉዳት የደረሰበታ ቦታ ልክ እንጦጦን የሚመስል ማራኪ ቦታ ነው፡፡ እንዲሁም በአለም ላይ ታዋቂ የሆኑት እንደ ሶኒ
(Sony) ፣ ኳልኮም
(Qualcomm)፣ ኪዮሳራ
(Kyocera), ሞቶሮላ(Motorola) UCSD, USD, SDSU, Dervy,
National University , University Of Phoenix, San Diego City Collage, Mesa
Collage, SDSM, እና ሌሎችም ታዋቂ ኩባንያዎች የተዘጉ ሲሆን የትናንትናው እሳት በጣም ታዋቂውን የወታደር ማስልጠኛ የመሪን ካምፕ
(Camp Pendleton) አጥቅቷል፡፡ በሳንድያጎ ደቡብ በኩል የሚገኙ ሁለት የስቴት እና የካውንቲ እስር ቤቶች ከሳቱ በጣም ተጠግተው የነበረ ሲሆን የእስር ቤቱ ባለስልጣኖች እስረኞችን ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ነበሩ፡፡ በሳንድያጎ ሰሜን በኩል በጣም ጉዳት የደረሰበት ቦታ ራንቾ ሳንታፊ
(Rancho Santa Fe ) የተባለው ቦታ በአሜሪካ ውስጥ ውድ የሚባሉ ከ 2 ሚሊዪን ዶላር በላይ የሚያወጡ ቤቶች ያሉበት፣ ፕሬዜዳንቶች እና አክተሮች የሙያርፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህንን አጋጣሚ በማድረግ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ በእግር አቋርጠው ለመግባት ሲሞክሩ በእሳት መካከል ከ አምስት በላይ ሜክሲካኖች በድንበር ጠባቂዎች ነፍሳቸው ድኗል፡፡
ይህ በይዘቱና በአይነቱ ተወዳዳሪ የሌላው እሳት በአንድ ግለሰብ ላይ የሞት አደጋ ሲያደርስ፣ይህ የ 50 ዓመት ግለስብ የሞት አደጋው የደረሰበት የ15ዓመት ልጁን ለማዳን ሲሞክር ሲሆን የግለሰቡን ሂዎት ለማዳን ሲሞክሩ አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ይህ ሪፖርት እስከሚፃፍ ድረስ ከዚህ በታች ያሉት ጎዳቶች ደርሰዋል፡፡ ይህንን አሃዝ ተጨማሪ ሪፖርቶች ካገኘን እናስተካከላለን፡፡ በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ከ ሳንድያጎ ወደ ሎስ አንጀለስ የሚወስደው አውራ ጎዳና አይ-5 ተከፍቷል፡፡ ነገ በሳነድድያጎ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማየት ፕሬዜዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡
በዚህ
አጋጣሚ በኢትዩጵያና
በተለያዩ አገሮች
የሙኖሪ አመድ
ወዳጆችን እንዳያስቡ
ንገሯቻው. ለውሰጥ
ካለ በወብ ሳታችን
እናስታውዋልን
የሂዎት መጥፋት አደጋ 1
የአካል መጎዳት 17
የተቃጠሉ ቤቶች
Witch Creek and Harris fires= 700
The Rice Canyon fire=400
structures
የተቃጠለው ቦታ የቆዳ ስፋት
Witch Creek and Harris fires=270,000 acres
The Rice Canyon
fire=7,500 acres
© 2007 www.yebbo.com