ሳንድያጎ፣ ጥቅምት 14፣ 2000
ላለፉተ አራት ቀናት ሳነድድያጎን እና አካባቢዋን ሲለበላባት የነበረው እሳት ዛሬ ትንሽ ቀነስ ባሏል፡፡ ትናንት ማታ የሳንድያጎ ቴሌቭዥኖች እና ሬድዎዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ማታ የመደበኛ ፕሮግራማቸውን በከፊል ያስተላለፉ ሲሆን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩ የተወሰኑ አካባቢዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ ይህ በይዘቱ እና ባይነቱ በአሜሪካ ታሪክ ተወዳዳሪ አይገኝለትም ተብሎ የሚገመተው እሳት ባሁኑ ወቅት ጉልበቱ እየቀነሰ እየመጣ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፓስፖርት እና ቪዛ የማይጠይቀው እሳት ማንንም ሳያስፈቅድ ወደ ሚክሲኮ ድንበር ቴካቴ በተባለው የድንበር ከታማ ገብቶ ነገር ግን በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል፡፡
በዛሬው እለት ሂወት ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት ለመመለስ እየቃጣው ሲሆን በመሃል ከተማ የንግድ ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች መደበኛ ስራቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ እሳቱ በተጠቃበት አካባቢ የፕስታ ስርጭት እና ሌሎች አገልግሎቶች ተቋርጠዋል፡፡
እንዲሁም ቤት ንብረቱን ዘግቶ የሄደውን ህዝብ ጭር ያለ ከተማ በመግባት የስርቆት ተግባር ሲፈፅሙ የተወኑ ግለሰቦች በህዝቡ ተሳትፎ በቁጥርር ላይ የዋሉ ሲሆን፣ መንግስት በብዙሃን መገናኛ የዚህን አይነት አስነቀዋሪ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ በከባድ ወንጅል እስከ 3 አመት የሚያስቀጣ እስራት እደሚቀጡ እስተውቋል፡፡
ይህን ሪፖረት እየተፃፈ እያለ ፕሩዜዳንት ቡሽ ከካሊፎርንያ አስተዳዳሪ ሸዋዚነገር ጋር ጋዚጣዊ መግለጫ እያደረጉ ሲሆን፣ እንደ እስተዳዳሪው ገለፃ ከ1400 ቤቶች እና ከ 500ሺ ኄክታር በላይ በቃጠሎው የተጎዳ ሲሆን ፕሬዜዳንቱ በቃጠሎው የተጉትን ቦታወች እንደሚጎበኙ ሲያስረዱ በዚህ ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው ገበሬዎች እና የአነስተኛ ንግድ ባለቶች ከ7ሚሊዮኝ ዶላር በላይ የአነስትኛ ወለድ ብድር እንደተፈቀደ እስረድተዋል፡፡
በሳስንድያጎ በደረሰው አደጋ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የቁሳቁስ እና የገንዘብ እርዳታ እያደረጉ ሲሆን ለአብነት ያክል በአለም ትልቁ ሱቅ ወልማርት 1ሚልዮን ዶላር፣ የህፃናት ታላቁ መዝናኛ ቦታ ባለቤት ዲዝኒ ላንድ 1ሚልዮን ዶላር፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ 1ሚሊዮን ዶላር፣ ወልስ ፋርጎ ባንክ 250ሺ ዶላር እና ከ250ሺ በላይ ቁሳቁስ የረዱ ሲሆን፣ ኳልኮም በተባለው ስዳዲዮም ለተፈናቃዮች ከመጣው እቃ ላይ በመኪና ጭነው ሰርቀው ሲወስዱ የታዮ ሶስት ግለሰቦች በስርቆት ተይዘው የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በህገወጥ የሚኖሩ ሆኖ በመገኘቱ ኢሚግሬሽን ተጠርቶ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የሳንድያጎ ሕዝብ ለተፈናቃዮች የሚያሳየው የመርዳት ርብርብ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ እንዳንድ የመጠለያ ጣቢያዎች በፍቃደኝነት ለመርዳት ሰልፍ መጠበቅ ያለ ሲሆን፣ ተፈናዋዮችን ለማዝናናት የሰርከስ፣ ማሳጅ (መታሸት)፣ የካውስሊንግ፣ የሙዚቃ፣ የሕፃናት የስእል ውድድር፣ እና የተለያዩ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦ ያሉ ሲሆን፣ ረጂ ለሌላቸው አርጋውያን ዶክተሮች እና ነርሶች ከፍተኛ እርዳታ እያደረጉ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድ ነፍሰ ጡር ደንቦል የሆነ ወድን ልጅ ከመጠላያ ጣቢያው እያለች በሰላም ተግላግላለች፡፡ በአጋጣሚ በግርግር ከቤተሰቦቿ ጋር ተጠፋፍተው ስለነበር በቴለቭዥን ሪፖርተር አመካኝነት ሆስፒታል ውስጥ ተገናኝተዋል፡፡
ለዚህ ያልታሰበ የሳት ጉዳት ለሚወጣው ወጪ የፌድራል እና የስቴት መንግስታት የተወሰነውን ወጪ እንደሚሸፍኑ ታውቋል፡፡
ይህን ዜና ከስብሰባው ያጠናከርነው የየቦ ኮሚኒኬሽን ኔት ወርክ ባልደረቦች ነን፡፡
ከሳንድያጎ
© 2007 Yebbo.com